ወሳኝ፣ አዲስ የሰበር ውሳኔ—ሰ/መ/ቁ. 292349 (የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም)
By Hailu Hasena
"የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1)—አካለ መጠን ባልደረሰች ልጅ ላይ የግብረ ሥጋ በደል የመፈጸም ወንጀል—ምንም እንኳን ከ15-25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ቢሆንም ድንጋጌው ዋስትናን አይከለክልም::
ስለሆነም ተከሳሽ የዋስትና ግዴታውን እንደማይፈጽም የሚያረጋግጥ በቂ ምክንያት ስለመኖሩ በአመላካች ማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የተበዳይ ዕድሜን አነስተኛነት፣ ወንጀሉ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያቀጣ መሆኑን፣ እና "ወንጀሉ በማ/ሰቡ ዘንድ የተወገዘ ስለሆነ ተከሳሽን ከወዲሁ በዋስ መልቀቅ አስተማሪ አይደለም"
የሚሉ ድምዳሜዎች ላይ በመድረስ ዋስትናን መንፈግ የዋስትና መብትን ሕገ መንግሥታዊ መርህነትን ሸርሽሮ ወደ ልዩ ሁኔታነት የሚቀይር እና የተከሳሽንም ከፍርድ በፊት ጥፋተኛ ሆኖ ያለመቆጠር መብትን የሚጥስ በመሆኑ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ነው::
ሰ/መ/ቁ. 292349 (የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም)
Behig Amlak -በሕግ አምላክ
legal consulting and representation
የአራጣ ወንጀል በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ
መግቢያ
አራጣ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ የህሊናን ወይም የሰውን ችግር መሰረት በማድረግ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ስር የሚካትት ወንጀል ሲሆን አስቀጪነቱም በሕጉ ተደንግጓል። ይህ ድርጊት በማኅበረሰብ ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ በሕግም ሆነ በሞራል ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው። በዚህ ጽሑፍ የአራጣን ምንነት፣ በሕግ የተፈቀደን የወለድ መጠን፣ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች እና የአራጣ ወንጀልን የሕግ ተጠያቂነት በአጭሩ እንዳስሳለን።
የአራጣ ምንነት
የሕግ መዝገበ ቃላት የሆነው ብላክስ ሎው መዝገበ ቃላት 8ኛው እትም እንደሚሰጠው ትርጉም ”USURY is an illegal contract for a loan or forbearance of money, goods, or things in action, by which illegal interest is reserved, or agreed to be reserved or taken.” ይህን ወደ አማርኛ በግርድፉ ስንመልሰው አራጣ ማለት ሕገ-ወጥ በሆነ የብድር ውል ወይም ገንዘብን፣ እቃዎችን ወይም በድርጊት ላይ ያሉ ነገሮችን መስጠት ሆኖ ሕጋዊ ያልሆነ ወለድ ለመጠበቅ ወይም ለመስጠት የሚደረግ ስምምነት ነው። በሌላ በኩል ማሪያም ዌብስተር የተሰኘው መዝገበ ቃላት አራጣን በተጋነነ የወለድ መጠን ገንዘብ ማበደር በማለት ይተረጉመዋል። በመሆኑም ከተለያዩ ትርጉሞች መረዳት እንደሚቻለው አራጣ ያልተገባ የወለድ ስሌት ተበዳሪዎችን በማስከፈል የሚፈፀም ድርጊት ነው፡፡ ተመጣጣኝ የወለድ መጠን ፋይናንስ ገበያው ወይም ብሔራዊ ባንኮች በሚወስኑት መሰረት ማሰብ ተገቢ ቢሆነም በሕግ ከተወሰነው የወለድ ምጣኔ በላይ ገንዘብ ማበደር በብዙ አገሮች ዘንድ ወንጀል ተደርጎ ተደንግጓል፡፡ ወንጀሉም አራጣ በመባል ይታወቃል፡፡
በሀገራችን በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ለአራጣ ቀጥተኛ ትርጉም ባይሰጥም በአንቀጽ 712 በአራጣ ወንጀል የሚያስጠይቁ ተግባራትን ያስቀምጣል። ይኸውም ማንም ሰው የተበዳዩን ችግረኝነት፣ የበታችነቱን፣ ወይም የገንዘብ ችግሩን፣ ወይም መንፈሰ ደካማነቱን፣ ወይም ልምድ ወይም ችሎታ የሌለው መሆኑን መሰረት በማድረግ፡-
በሕግ ከተፈቀደው ወለድ በላይ ገንዘብ ያበደረው እንደሆነ ወይም
ካበደረው ገንዘብ ጋራ በግልፅ ተመጣጣኝነት የሌለው ንብረት በምትኩ እንዲሰጠው ያደረገው ወይም ቃል ያስገባው እንደሆነ የአራጣ ወንጀል በመፈፀም የሕግ ተጠያቂነት ይኖርበታል።
በመሆኑም በአጠቃላይ አራጣ ማለት በሕግ ከተፈቀደው በላይ የተጋነነ የወለድ መጠን በማስከፈል እና ከገንዘቡ ጋር ተመጣጣኝነት የሌለው መያዣ በመቀበል የሚደረግ የብድር ስምምነት ሲሆን ይህም የተበዳሪውን ሁኔታ ማለትም ችግረኝነቱን፣ የበታችነቱን፣ የገንዘብ ችግሩን፣ መንፈሰ ደካማነቱን... መሠረት በማድረግ የሚፈፀም ብዝበዛ" (Exploitation of distress) ነው፡፡
በሕግ የተፈቀደ የወለድ መጠን ስንት ነው?
በኢትዮጵያ በሕግ የተፈቀደውን የወለድ መጠን ስንመለከት የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 1751 ሕጋዊ ወለድ (Legal Rate of Interest) ማለት በውል ያልተወሰነ ወለድ (ጥቅም) ከፋይ የሆነ ሰው በዓመት በመቶ ዘጠኝ (9%) ሂሳብ ይከፍላል ይላል። በተጨማሪም የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2479(1) የብድር ውል ተዋዋይ ወገኖች ተበዳሪው ሊከፍለው የሚገባው የወለድ መጠን በወር ወይም በቀን ሳይሆን በዓመት ከአስራ ሁለት በመቶ (12%) በላይ ሊበልጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም ሕጉ የፈቀደው የብድር ውል ወለድ መጠን በዓመት 12% ድረስ ብቻ እንደሆነ እንገነዘባለን።
ይሁንና ይህ የወለድ መጠን በባንኮች እና በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ላይ ተፈፃሚነት የለውም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ብድር አቅርቦት በተፈለገው መጠን መገኘትን፣ እንዲሁም የወለድ ተመንና ሌሎች ክፍያዎችን የመወሰንና የመቆጣጠር ሥልጣን የተሰጠው ሲሆን ብሔራዊ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 591/2000 ዓ.ም አንቀፅ 5(4) እና በመመሪያ ቁጥር 12/2010 መሠረት የብድር ውል ለደንበኞቻቸው በሚሰጡበት ወቅት ላበደሩት ብድር የወለዱን ምጣኔ በራሳቸው እንዲወስኑ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የወለድ ተመን መመሪያ ቁጥር 295/2020 መሰረት በብድር እና በቅድመ ክፍያ ላይ የብድር መጠን በተመለከተ በእያንዳንዱ ባንክ በነፃነት የሚወሰን እንደሆነ ያስቀምጣል። በመሆኑም ባንኮች በሚሰጡት ብድር ላይ የሚታሰበው የወለድ ምጣኔ ከላይ በፍትሐብሔር ሕጉ እንደተመለከተው የወለድ ጣራው በዓመት እስከ 12% ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ ማድረግ ይችላሉ። በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ጭማሪ ያደረገ ሲሆን በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፣ የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣ የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣ የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣ የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ጭማሪ ተደርጎባቸዋል። ስለዚህ አራጣ ማለት ሕጉ ከፈቀደው የብድር ወለድ መጠን በላይ ተዋውሎ ማበደር ማለት ነው፡፡
የአራጣ ወንጀል የሚያስከትላቸው ጉዳቶች
አራጣ በተበዳሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ተበዳሪዎች ለተበደሩት ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት የወለድ መጠኑ በጣም የተጋነነ ስለሆነ ብድሩን መልሰው ሳይጨርሱ ጥሪታቸው ወይም በብድሩ ገንዘብ ሰርተው ያገኙትን ትርፍ አበዳሪው ስለሚወስድባቸው ለኪሳራ እና ለከፋ ድህነት ይዳረጋሉ፡፡ ተበዳሪዎች ጊዜያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ብለው በተበደሩት ገንዘብ ድህነትን ሸምተዉ ድሀ ሆነው ሲቀሩ፤ አበዳሪዎችም ምንም እሴት በኢኮኖሚ ውስጥ ሳይጨምሩ ሀብት የሚሰበስቡበት ሁኔታ ይፈጥራል፡፡
የአራጣ ወንጀል በግለሰቦች ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባለፈ የድርጊቱ መበራከት ሀገራዊ ጉዳት በማስከተል የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅዕኖ ቀላል የሚባል አይሆንም። በአራጣ የሚዘዋወረው ገንዘብ ላይ መንግሥት እውቅና ስለማይኖረው ከትርፉ ላይ ግብር ስለማይከፈል መንግሥት ገቢ ሳይሰበስብ ይቀራል፡፡
ሌላው ጉዳት ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ገንዘባቸውን ባንክ እንዳያስቀምጡ ከማድረጉ ጋር የተያያዘ ሲሆን ይህም የሚሆነው ጥቂትም ቢሆን ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ገንዘባቸውን ባንክ ከማስቀመጥ ይልቅ አራጣ በማበደር እንዲሰማሩ በማድረጉ ነው፡፡ ገንዘቡ በባንክ ተቀመምጦ ለኢኮኖሚው ሊያበረክተው የሚችለውን አስተዋጽኦ የሚያስቀረው ሲሆን ወደ ባንኮች የሚገባው ተቀማጭ እየቀነሰ መሄዱ በመጨራሻም ባንኮች አቅም እያጠራቸው እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡ ባንኮች ለብድር የሚውል ተቀማጭ ገንዘብ ሲያጥራቸው በተዘዋዋሪ አራጣ አበዳሪዎች የብድር አማራጭ ይሆናሉ፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ በተመጣጣኝ ወለድ መጠን ገንዘብ ተበድረው ሥራ ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎች ብድር ሳያገኙ እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል።
የአራጣ ወንጀል የሕግ ተጠያቂነት
የአራጣ ወንጀል በወንጀል ሕጉ በአንቀፅ 712 ስር ሽፋን አግኝቷል። ከላይ እንደተገለፀው በድንጋጌው ላይ የዘረዘሩትን ተግባራት የፈፀመ ሰው በቀላል እስራት ወይም እንደነገሩ ሁኔታ ከ5 (አምስት አመት) በማይበልጥ ፅኑ እስራት እና በመቀጮ ይቀጣል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛውም ሰው ከላይ በተጠቀሰው ሀሳብ መነሻነት በአራጣ ላይ የተመሰረተ መብት የተቀበለ፣ በመከላከያነት የተጠቀመበት ወይም ለሌላ ሰው ያስተላለፈ እንደሆነ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጣል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የአራጣ ወንጀል በማኅበረሰብ እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ቀላል የሚባል ስላልሆነ ማኅበረሰቡ ብድርን በተመለከተ ሕጋዊ መንገድን መከተል እና ወንጀሉ ተፈፅሞ ሲገኘም ወንጀል ፈፃሚዎች እንዲቀጡ የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል።
በንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
05/12/2025
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ይችል ዘንድ የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያዎችን ሲያደርግ ቆይቷል። የዚህ ማሻሻያ አንዱ አካል ከሆኑት መካከል የፍትሕ ሚኒስቴር ተገልጋዮች የተሻለ ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ምቹ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የደንበኞች/ተገልጋዮች አገልግሎት የሥራ ክፍል ማደራጀት ይገኝበታል። በዚህ የሥራ ክፍል ተመድበው ለመስራት ፍላጎቱ እና ተነሳሽነቱ ያላቸው እና ከዚህ በታች የተመላከቱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሕግ ባለሙያዎችን በዐቃቤ ሕግነት ለመቅጠር ይህ ማስታወቂያ ወጥቷል። በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 26/03/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ በተወዳዳሪነት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች
· ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና በኢትዮጵያ የሚኖር የምትኖር፤ ለሕገ መንግስቱ እና ለሕግ የበላይነት ተገዢ የሆነ/የሆነች፤ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች፤ በታታሪነቱ/ቷ፣ በታማኝነቱ/ቷ፣ በሥነ-ምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈ/ች መሆኑን/ኗን ይ/ት/ሰራበት ወይም ከሚኖሩበት የመንግስት ተቋም ማቅረብ የሚችል /የምትችል፤ የወንጀል ቅጣት ሪከርድ የሌለበት/ባት፤ የፌዴራል መንግስቱን የሥራ ቋንቋ የሚችል/የምትችል፤ እንደ አስፈላጊነቱ የሚሰጠውን የጽሁፍም ይሁን የቃል ወይም ሁለቱንም ፈተና ማለፍ የሚችል /የምትችል
1. የደንበኞች/ ተገልጋዮች አገልግሎት ዐቃቤ ሕግ
የዐቃቤ ሕግ ደረጃ - ዐቃቤ ሕግ ደረጃ ሦሥት
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ
· ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ በ2016 ወይም በ2017ዓ.ም የተመረቀ /የተመረቀች፤ የመመረቂያ ነጥብ (Cumulative GPA) 3.25 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት፣ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት 85 ፐርሰንታል እና ከዛ በላይ በማምጣት ፈተናውን ያለፈ/ያለፈች፤ ሴት እና አካል ጉዳተኛ ተወዳዳሪዎችን እናበረታታለን፤
የሥራ ልምድ - 0 አመት
ብዛት - 20
የስራ ድርሻ/የስራ መዘርዝር፡-
· ለተቋሙ በጥሪ ማዕከሉ በኩል ከተገልጋዮች በስልክ ወይም በኢሜል ወይም በሌላ ማንኛውም የግንኙነት መንገድ የሚቀርቡ የአግልገሎት ጥያቄዎችን ተቀብሎ አክብሮትን የተላበሰ ፈጣን፣ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት፣ መርዳት፣ ጉዳዩ ወደሚመለከተው አካል መምራት፤
· በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የደንበኞች አገልግሎት ዴስክ በአካል የሚመጡ ተገልጋዮችን ተቀብሎ አክብሮትን የተላበሰ ፈጣን፣ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት፣ መርዳት፣ ጉዳዩ ወደሚመለከተው አካል መምራት፣ ተገልጋዮች ትክክለኛ መረጃ ማግኘታቸውን፣ ጊዜውን የጠበቀ አገልግሎት ማግኘታቸውን እንዲሁም ያገኙትን ፍትሕን የተመለከተ አገልግሎት አስመልክቶ አዎንታዊ እይታ ወይም እርካታ የተሰማቸው መሆኑን ማረጋገጥ
· ተቋሙን የሚመለከቱ ልዩ ልዩ መረጃዎች በአግባቡ ማደራጀት፤ መተንተንና መቀመር፣ የአዝማሚያ ትንተንና መስራት፣ ለህትመት የሚሆኑ ፅሁፎችን ማዘጋጀት እና የአርትኦት ሥራዎችን መስራት፣ ለማህበራዊ ሚዲያ፣ ለጋዜጣዊ ጉባኤ፤ ለጋዜጣዊ መግለጫና ለቃለ-ምልልስ የሚሆኑ ፅሁፎች የሚረዱ መረጃዎችን ማደራጃት፣ መቀመር፣ የአርትኦት ሥራ መስራት፣ የሁነት ዝግጅቶችን ማቀድና ማስተባበር፣ ዜና ማዘጋጀት፤ ወቅታዊ መልዕክት መቅረፅ፤ የሚዲያ ዳስሳ ማካሄድ፣ በሚኒስቴር መሥራያ ቤቱ የሚከናወኑትን የተግባቦት እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ማከናወን እና ማስተዳደር፣
· ሌሎች በአስተባባሪው የሚሰጠው/የሚሰጣት ተግባራት
ተጠሪነት - ለደንበኞች/ተገልጋዮች አገልግሎት አስተባባሪ / ለህዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
2. የደንበኞች/ተገልጋዮች አገልግሎት ዐቃቤ ሕግ አስተባባሪ
የዐቃቤ ሕግ ደረጃ - ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ ደረጃ ሦሥት
የትምህርት ዝግጅት እና የሥራ ልምድ - እውቅና ካለው የመንግስት ዩንቨርሲቲ በመደበኛው የትምህርት ሂደት በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ፤ በሕግ 2ኛ ዲግሪ ወይም በሕግ 3ኛ ዲግሪ ያለው/ያላት እና እንደ ቅደም ተከተላቸው 7 ዓመት፣ 5 ዓመት ወይም 3 ዓመት በሕግ የስራ ልምድ ያለው/ያላት ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ የመመረቂያ ነጥብ (Cumulative GPA) 3.25 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት ፣ ሴት እና አካል ጉዳተኛ ተወዳዳሪዎችን እናበረታታለን።
ብዛት - 1
የስራ ድርሻ/የስራ መዘርዝር፡-
· የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የደንበኞች አገልግሎት ዴስክ፣ ዲጂታል አገልግሎቶች እና የጥሪ ማዕከል አገልግሎቶችን መከታተል እና ማስተባበር
· የተገልጋዮች የመረጃ ጥያቄዎችን፣ ቅሬታዎችን እና የአገልግሎት ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ እና በውጤታማነት መስተናገዳቸውን ማረጋገጥ እና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማረጋገጥ
· ፈጻሚዎች በማስተባበር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃዎችን በመከታተል፣ ዲጂታል ሥርዓቶችን በመጠቀም እንዲሁም ቀጣይነት ያላቸው ማሻሻያዎችን በመለየት ተቋማዊ አገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ
· ሌሎች በኃላፊው የሚሰጠው/የሚሰጣት ተግባራት
ተጠሪነት - ለደንበኞች/ተገልጋዮች አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ
የምዝገባ ሁኔታ፡- http://www.justice.gov.et በሚለው የተቋሙ ዌብሳይት ክፍት የሥራ ቦታ በሚለው ሥራ ባለው ማስፈንጠሪያ https://forms.gle/zbjpMSUtvxNPaSou6 በመጠቀም የሚጠይቀውን መረጃ በመሙላት እና ማስረጃዎችን በማያያዝ ወይም [email protected] ወይም [email protected] ወይም በስልክ ቁጥር 0913154067 Telegram/ WhatsApp መረጃዎችን በመላክ መመዝገብ ይቻላል።
የምዝገባ ቀን፡- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ፤
ማስታወሻ፡- ተወዳዳሪዎች ሲመዘገቡ ሊያሟሏቸው የሚገባቸው ሰነዶች፡-
1. ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚገልጽ መታወቂያ/ፓስፖርት እና ብሔራዊ መታወቂያ በpdf scan የተደረገ፤
2. ለተራ ቁጥር 2 ላይ ለሚወዳደር ተወዳዳሪዎች ይሰሩበት ከነበረው መስሪያ ቤት የተጻፈ የሥነ-ምግባር ማስረጃ በpdf scan የተደረገ፤
3. ዋና የትምህርት ማረጃ student copy ጨምሮ በpdf scan የተደረገ፤
ለበለጠ መረጃ ፡- በስራ ሠዓት በስልክ ቁጥር ፡- +251-15-15-7432 በመደወል፤ እንዲሁም በኢሜል አድረራሻ፡- [email protected] ወይም [email protected] ላይ በመፃፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ፍትሐ ብሔር
ምድብ ችሎት ባለጉዳዮች በሙሉ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡-የይግባኝ አላላክን ማኑዋልን መነሳቱን ይመለከታል
ከዚህ ቀደም በፍታብሔር ይግባኝ አስራር ባለጉዳዩ ለእኛ ፍ/ቤት መዝገብ ይምጣልኝ ማመልከቻ አቅርቦ መዝገብ ይምጣ እየተባለ ሲመራ መቆየቱ ይታወሳል ፡፡ይሁን እንጂ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በቁጥር ጠ/1-29/4655 በቀን 22/12/2017ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ይህ አሰራር ለባለጉዳይ ምልልስ ምክንያት መሆኑን ግንዛቤ ተወስዶ አሰራሩ እንዲቀርና በስነ ስርአት ሕጉ 327 መሰረት እንዲከናወን ባሳወቁን መሰረት የይግባኝ አመጣጡ ስርአቱ ቀሪ መሆኑን አዉቃችሁ ከጳጉሜ 03/13/2017 ዓ/ም ጀምሮ ይግባኝ ማለት የፈለገ ባለጉዳይመዝገቡ ይምጣልኝ ብሎ ለእኛ ማመልከት ሳያስፈልገዉ ዉሳኔዉን ለሰጠዉ _ ለስር ፍ/ቤት መጠየቂያዉን አቅርቦ ግልባጩን በሚያመጣዉ መሰረት የይግባኝ መዝገቡ የሚከፈት መሆኑን አሳዉቃለሁ ፡፡
ከሰላምታ ጋር🙏👍✍️
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/13 ዋና ዋና ነጥቦች
ሙአለ ንዋይ ሰነዶች ግብይት ምንድን ነው?
የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037/0983337690
1. የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ታሪካዊ ዳራ....
ኢትዮጵያ ብዙ የህግ ታሪክ ስለ ካፒታል ገበያ እንደሌሎች ሀገራት እንደሌላት የተለያዩ ስለካፒታል ገበያ የተመለከቱ የኢትዮጵያን ታሪክ መመልከት የሚቻል ነው። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ታሪካዊ ዳራን ስናጤን በአጼ ዘመነ መንግስት እ.ኤ.አ በ1867 ዓ.ም በአጼ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት የኢትዮ ጅቡቲን ሀዲድ ለመዘርጋት የ40 ሚሊዮን ፍራንክ አክስዮን በፈረንሳይ ሀገር መሸጣቸው ታሪክ ያወሳል።በእሳቸው ዘመን የተቋቋመው የመጀመርያው ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ ሲመሠረት አክሲዮኖቹ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ኒውዮርክ፣ ፓሪስ፣ ለንደንና ቪየና እንደተሸጡ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ እ.ኤ.አ. በ1956 የኢትዮጵያ የቄራዎች ድርጅት ለሕዝብ ሽያጭ የወጣ ሲሆን፣ እሱን ተከትሎ እ.ኤ.አ. ከ1957 እስከ 1963 ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ጠርሙስ ፋብሪካ (Ethiopian Bottling Company)፣ ኢንዶ-ኢትዮጵያን ጨርቃ ጨርቅ፣ ኤችቪኤ ኢትዮጵያ፣ ሳባ ጠጅ፣ ተንዳሆ ተክልና የአዲስ አበባ ባንክ ለሕዝብ ሽያጭ መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪ እ.ኤ.አ. በ1959 ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ለሕዝብ ሽያጭ የቀረበ ድርጅት መሆኑንና በወቅቱ በሦስት ወራት ውስጥ ከአክሲዮን ሽያጭ 2.5 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፣ ኤችቪኤ የተባለው የሆላንድ ኩባንያ አብዛኛውን አክሲዮን መግዛቱ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ሕዝቡም ቀላል ሊባል በማይችል መልኩ በግብይት መሳተፉንና ድርሻ መግዛቱን ጄዲቮን ፒስኬ የተባለ ጸሐፊ፣ «አክሲዮንና የአክሲዮን ግብይት በአዲስ አበባ» በሚለው መጽሐፉ ከትቦት ይገኛል፡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ1960 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ (State Bank of Ethiopia) ውስጥ የአክሲዮን ግብይት መምርያ መቋቋሙ የአክሲዮን ግብይቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ ይህንን መምርያ ማደራጀት የአክሲዮን ገበያን ለማስፋፋት በመንግሥት የተወሰደ የመጀመርያው ተቋማዊ አደረጃጀት ዕርምጃ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በወቅቱ የተለያዩ ኢንቨስተሮችን በግብይት በማሳተፍና ዋጋ እንዲሰጡ በማድረግ፣ እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ዋጋ እንዲወሰን ይደረግ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ1965 የአክሲዮን ግብይት እያደገ በመሄዱ፣ የሕዝብን እምነት በማግኘቱ፣ ኢኮኖሚውም ዕድገት በማሳየቱ፣ አዳዲስ ኀይለስላሴ ዘመነመንግስት የካፒታል ገበያ የህግ ማእቀፍ ኖሮት የተለያዩ አስፈጻሚ ተቋሟት የማቋቋም የማደራጀት እና የመነቃቃት ስራዎች ተሞክረዋል። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለመገንባት በተደረገው ህዝባዊ ንቅናቄም ብዙ የቦንድ ሽያጭ ለዜጎች፣ ሀገር በቀል ድርጅቶች ፣ ለትውልደ ኢትዮጲያን ፣ ዲያስፖራ ለሌሎችም ተሳታፊ አካላት ተሽጦ በብዙ ቢሊዮን ብር ተሰብስቦ ታላቁን ህዳሴ ግድብ ተገንብቷል። ይህ ህጉ ከመውጣቱ በፊት ባልተማከለ አሰራር የተፈጸመ ቢሆንም የካፒታል ገበያ ስረአት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል። ከዚህም ባለፈ የገበያ መር ስረአት የሚደግፍ ሲሆን ለነጋዴዎች፣ለባለሀብቶች፣ ለሀገር እድገት መንሰራራት፣ለአለምአቀፍ የገበያ ትስስር፣ለዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ፣ለአጠቃላይ የገበያ እድገት እንቅስቃሴ ከፍተኛ በርን የከፈተ ሲሆን እኝህን መሪዎችንና እና ተባባሪዎቻቸውን አለማመስገን ንፉግነት መሆኑ ያነበበኩት እና ለመመረቂያ ጽሁፌ ያጠናውት " The Challenges and Opportunities of the capital market proclamation implementation " ማለትም በአማረኛ ለማስገንዘብ ያህል "የካፒታል ገበያ አዋጅ አፈጻጸም ተግዳሮት እና መጻኢ እድል" በሚል በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የታተመው ጹሁፍ ምስክር ይሆኑኛል። ይሁን እንጂ የደርግ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ የሶሻሊስት ስረአት መንግስትን ባህርይ ያለው መሆኑን ተከትሎ የካፒታል ገበያ የህግ ማእቀፍ እንዳይኖረው እንዲሁም የገበያ መር ስረአትን የማይከተል በመሆኑ የካፒታል ገበያ ቦታ እንዳይኖረው አድርጎታል።
2. አሁን ላይ የካፒታል ገበያ ህግ የህግ ማእቀፍ ምን ይመስላል?.....
አሁን ባለንበት የኢፊድሪ ህገመንግስት ዲሞክርያሲያዊ እና ገበያ መር ስረአትን ፈቃጅ ሲሆን ይህን ተከትሎም ለሀገር እድገት የሚበጁ የንግድ ስረአታችንን የሚያዘምኑ ከአለም የገበያ ስረአት ጋር እኩል የሚሄዱ ህጎች እየወጡ የሚገኙ ሲሆን አንዱም የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ አዋጅ ቀጥር 1248/13 ሲሆን ይሀውም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም የወጣ ነው። በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 ላይ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተቋቋመ ሲሆን ይህን ተከትሎም የተለያዩ ደንብ እና መመሪያዎች በመውጣት ላይም ይገኛሉ።
ይህ ለሀገራችን እድገት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ሌሎች ህጎችም ሊደግፉ እና ተጣጥመው ሊተገበሩ የሚገባ በመሆኑ የብሔራዊ ባንክ አዋጅ፣የንግድ ባንክ አዋጅ፣ የኢፊድሪ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ሌሎች የፋይናንስ እና የንግድ ተቋማት ህጎች በመውጣት በመሻሻል ላይ ይገኛሉ። በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/13 ስር የሚታቀፉ ወይም የታቀፉ ዘርፈ ብዙ ተቋማት የሚገኙ ሲሆኑ ዋናው ጉዳይ ግን የሙአለ ንዋይ ሰነድ ገበያን ተፈጻሚ የሚያደርጉ ሲሆኑ የሙአለ ሰነድ ገበያ በዋናነት ለመጥቀስ ያህል በአዋጁ አንቀጽ 31 መሠረት የሚመሰረት ሲሆን ይህን በተመለከተ የኢፊድሪ መንግስትም ስራ መጀመሩን አብስሯል። ይህ ዋናው የአዋጁ መቋቋም መሠረታዊ አላማ ነው። ሌላው የመወእለ ሰነዶች አስቀማጭ ክፍያ አጣሪ ፈጻሚ ኩባንያ በአዋጁ የህግ እውቅና የተሰጠው ሲሆን ይህ ግብይት የሚፈጸምባቸውን ሰነዶች ክፍያ አፈጻጸም ከእዳና ከተለያዩ ክፍያዎች ነጻ ስለመሆኑ በማጣራት ሰነዶችን በመለየት የሚያስቀምጥ ነው። በዚህ ረገድ ብሔራዊ ባንክም ስልጣን የተሰጠበት አግባብ በአዋጁ ላይ ተዘርዝሮ የተቀመጠ ነው።
2.1 የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት...
ሌላው ትኩረት የምናደርግበት በአዋጁ አንቀጽ 64 መሠረት የተቋቋመ ሲሆን ይህም የካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት ነው። ይህ ፍርድ ቤት ሙእለ ሰነዶች ግብይት ላይ አስመልክቶ በዚህ አዋጅ ሽፋን ስር በሚወድቁ አጠቃላይ ተግባራት ላይ በባለስልጣኑ ውሳኔዎች ላይ በሚሰጡ በሚተላለፉ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ክስ አቅርቦ የሚታይበት ሲሆን በዚህ ፍርድ ቤት የሚሰጡ ውሳኔች ላይ ቅር የተሰኘ ወገን በመሠረታዊ የህግ ስህተት ላይ ብቻ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የሚጠየቅበት ይሆናል። ይህ ማለት የፍሬ ነገር ክርክር ጉዳዮች በተመለከተ የክርክር ሂደት እዚሁ የካፒታል አስተዳደር ፍርድ ቤት የሚያልቅ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ የሚገባው ነው። በዚህ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት የሚሾሙ ዳኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን በዚህ ዘርፍ የተለየ በእውቀት በልምድ በስልጠና በሀገር ወጭም ጭምር የዳበሩ ልዩ እውቀትና ልምድ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል። ይህ ካልሆነ ከፈጣን እና ፍትሀዊ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር በቶሎ ውሳኔ የማይሰጥበት ከሆነ በዚህ ዘርፍ ለሚሳተፉ ኢንቨስተሮች፣ተቋማት ለሙአለ ሰነድ ግብይት ስራ ዘርፍ እና ኢትዮጲያ ሀገራችን ለጀመረችው የዚህ የካፒታል ገበያ እድገት ጎታች ሊሆን ስለሚችል ይህ ኢንቨስተሮችን የሚያርቅ ተስፋ የሚያስቆርጥ ይልቁንም የማይሰተማምን ተገማችነትን የሚያሳጣ መሆን የለበትም ። ከዚህ አንጻር የፍርድ ቤቱ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች፣በወንጀል ጉዳይ ደግሞ መርማሪዎች፣አቃቢ ህጎች በተለየ እውቀት ፣ ልምድ፣ ስልጠና የዳበሩ ሊሆኑ ያስፈልጋል። ይህም ማለት ዳኞችን በዋናነት ጨምሮ ስለ ሙአለ ንዋይ ሰነዶ ምንነት፣ባህርይ፣ግብይት፣ ህግና መመሪያዎቻቸውን በዚህ ዘርፍ የሚሳተፋትን ኩባንያ፣ኢንቨስተሮችን፣ፍቃድ የተሰጣቸውን አገልግሎት ተቋማትን በተሳታፊ ኩባንያ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች መብትና ግዴታዎችን የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ስልጣኑንና ተግባሩን ኀላፊነቱን ተጠያቂነቱን በዚህ ዘርፍ ስር የሚገኙ ሰራተኞችን መብት ግዴታ አሰራሮቻቸውን ማወቁ በሚመለከተው ፍርድ ቤት ፍትህ አሰጣጥ እጅግ ጠቃሚ ነው።
2.2.. ሙአለ ንዋይ ሰነዶች ምን ምንድን ናቸው?....
የሰነደ ሙዓለ ንዋይ (Securities) ማለት በገንዘብ ሊተመን የሚችል ባለቤትነትን የሚገልጽ ሰነድ ማለት ሲሆን ሊሸጥ፣ ሊለወጥ ወይም በዋስትና ሊሰጥ የሚችል መብት የሚያቋቁም ሰነድ ነው፡፡ በእኛ አገር የሚታወቁት የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ዓይነቶች አክሲዮን፣ ቦንድና የግምጃ ቤት ሰነድ ናቸው፡፡ ባደጉት አገሮች የተለያዩ ዓይነት የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ይገበያያሉ፡፡ እነዚህም አክሲዮኖችን (Shares)፣ የዕዳ ሰነዶችን (Debt Instruments)፣ ብድሮችን (Loans)፣ ቦንዶችንና ሌሎች ወደ ኩባንያ ካፒታልነት ሊቀየሩ የሚችሉ ስምምነቶችን ያካትታል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም በመንግሥት ወይም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የወጡና ለግብይት የሚውሉ የሕዝብ የብድር ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን፣ ለወደፊት የሚፈጸሙ የውል ዓይነቶችን (Futures)፣ ያለ ግዴታ የመግዛት ወይም የመሸጥ መብት ለገዥው የሚሰጡ ሰነዶችን (Options)፣ ተዛማጅን (Derivatives) እና በጋራ የኢንቨስትመንት ፈንድ ውስጥ ያለ የድርሻ ክፍልፋይ (Units in a Collective Investment Scheme) ይይዛል፡፡
እነዚህንና ሌሎች የካፒታል ገበያ ሰነዶችን በአገራችን በተማከለ ገበያ ለማገበያየት እንዲያመች እንደ ሌሎቹ አገሮች የራሱ የሆነ ሒደትን መዘርጋት፣ መደገፍ፣ መቆጣጠር ብሎም መከታተል የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የካፒታል ገበያ አዋጅ ወጥቶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/13 አንቀጽ 2(62) መሠረት ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ማለት ከላይ በሌሎች አገሮች ግብይት ይደረግባቸዋል የተባሉትን ሰነዶች ጨምሮ፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ናቸው ብሎ የሚወስናቸውን ማናቸውም በግብይት የድርሻ ባለቤትነትን የሚያረጋግጡና በባለሥልጣኑ ፈቃድ መሠረት የሚተላለፉ ሰነዶችን ይጨምራል፡፡
2.3. በሙአለ ሰነዶች ገበያ መመዝገብ እና መሠረዝ ያለባቸው ሰነዶችችና ኩባንያዎች....
ሌላው ደግሞ በዚህ መግቢያ መነሳት ያለበት ነጥብ በሙአለ ሰነዶች ገበያ የሚመዘገቡ ሰዶች ሲሆኑ በዚህ የሚሳተፉ ተቋማት አስፈላጊውን መሥፈርት አሟልተው በጥንቃቄ ተመርምረው የሚመዘገቡ ናቸው። እነዚህም የተመዘገቡ ኩባንያዎች listing companies ሲባሉ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት በግብይት ሂደት ውስጥ መረጃ በማሳሳት ገብተው ወይም ወንጀል ፈጽመው ወይም ግዴታቸውን ሳይወጡ ቀርተው እንደሆነ ከገበያው የሚሰረዙበት ስረአት በህጉ የተቀመጡ ሲሆን ከገበያው የተሰረዙ ኩባንያዎች/delisting campany/በመባል ይታወቃሉ። እነዚህን የካፒታል ገበያ አላማ ከዳር ለማድረስ መንግስት በራሱ ብቻ የሚከውነው ሳይሆን ለተለያዩ አገልግሎት ብቁ የሆኑ የግል አግልግሎት ሰጪዎች ብቁ ሆነው ከተገኙ ፍቃድ በሚሰጥበት አግባብ የሚጠበቅባቸውን መስፈርት የሚያሟሉ ከሆነ ፍቃድ ተሰጥቶአቸው የሚሰሩበት አግባብ እንዳለ በአዋጁ አንቀጹ 55 ላይ በዝርዝር ተቀምጧል።
3. ሲጠቃለል ....
ይህን አዋጅ ባቀፈው ህግጋት እና አላማ ልክ ተፈጻሚ ለማድረግ ያሉን መልካም አጋጣሚዎች እንደ ሀገር ምን ምን እንደሆኑ መታየቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። የዚህን አዋጅ ተፈጻሚነት ከዳር ከማድረስ አንጻር በሚደረገው ከፍተኛ ትንቅንቅ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮች ምን ምን ናቸው ለእነዚህስ መሠረታዊ የሚሆን መፍቴዎች ምንድን ናቸው በሚሉ በዝርዝር አስፈላጊ በሚባሉ ነጥቦች ላይ መሠረታዊ ትንተና ሊሰጥበት የሚገባ ሲሆን የሌሎች ሀገረች ልምድና ተሞክሮ ጭምር የመፍትሄ አካል ሆኖ መወሰዱ ወሳኝ ነገር ነው።
በአጠቃላይ የካፒታል ገበያ ህግ ለሀገራችን እጅግ ጠቃሚ ከመሆነ የተነሳ ከ19ኛ ክ/ዘመን ወዲህ ጀምሮ ባለተማከለ የገበያ አሰራር የሙአለ ሰነድ ሽያጮች ይከናወኑ እንደነበሩ እና በዚህ ለሀገራችን እድገት ወሰኝ የነበረ ሲሆን ይህንና አለምአቀፍ ልምዶች ህጎች ትስስሮች በመረዳት በተማከለ የካፒታል ገበያ ስረአት ውስጥ በመጓዝ ሀገርን እና ዜጎችን በኢኮኖሚ እድገት ከፍ ለማድረግ የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/13 ይህንንም ተከትሎ ሌሎች ሊያሰሩ የሚችሉ ደንቦችን መመሪያዎችን በማውጣት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ በፊት የነበሩ የንግድ ባንክ፣የፋይናንስ ህጎችን በመሻሻል ይገኛሉ።መንግስትም ይህን የሚመጥን በህግ ማእቀፉ እንደተቀመጠው በቴክኖሎጂ የታገዙ ተቋማትን መገንባት የሚገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሰው ሀይል ማብቃትም በተመለከተ ትኩረት ሊወሰድበት የሚገባው ነው። ማህበረሰቡ ኢንቨስተሩ ኩባንያውም በዚህ ልክ እንዲነቃቃ አስፈላጊውን ግንዛቤ ሊሰጠው ያስፈልጋል። የካፒታል ገበያ ባለስልጣኑም በአዋጁ የተሰጠውን ትልቅ ኀላፊነት ለመወጣት አስፈላጊውን ዝግጅት ሊወስድ የሚገባ ሲሆን በግብይት ሂደት ተሳታፊ የሆኑ ቅን ባለሀብቶችን መብት ጥበቃ ሊያደርግ የሚያስፈልግ ሲሆን አጭበርባሪዎችን ለአሰራር እንቅፋት የሚፈጥሩትን በመለየት እንዲታረሙ ከማድረግ አንጻር ተገቢውን ጥረት ሊያደርግ የሚገባው ነው። ይህ ሲሆን የካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/13 ተፈጻሚ በማድረግ ለሀገራችን ትልቅ የኢኮኖሚ ፋይዳ ያለው ስለመሆኑ አያጠያይቅም።
18/11/2025
ሰነዱን ሰጠ የተባለው ተቋም ሲጠየቅ በዚህ ቁጥር የሚታወቅ ሰነድ የለም በማለት ምላሽ በመስጠቱ ብቻ ሰነዱ ሐሰተኛ ሰነድ ነዉ የማያስብል ስለመሆኑ።
ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት፣ በመፍጠር ወይም በመገልገል የወንጀል ክስ ሲቀርብ የተገለገለዉ ሰነድ ሀሰተኛ እንደሆነ እና ሀሰተኛ ሰነድ የፈጠረዉ ተከሳሽ መሆኑ በተገቢዉ ማስረጃ መረጋገጥ አለበት።
ሰነዱን ሰጠ የተባለው ተቋም ሲጠየቅም በዚህ ቁጥር የሚታወቅ ሰነድ የለም በማለት ምላሽ በመስጠቱ ብቻ ሰነዱ ሐሰተኛ ሰነድ ነዉ የማያስብል ስለመሆኑ።
ሰ/መ/ቁ.247213 (ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም)
ሠ/መ/ቁ 222041
በጽሁፍ መልስ ላይ መቃወሚያ በሚል ርዕስ ያልተፃፈ መቃወሚያ
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በጽሁፍ መልስ ላይ መቃወሚያ በሚል ርዕስ ባይፃፍም በፍሬ ነገር መልስ ላይ ከተገለፀ ጉዳዩን የሚመለከተው ፍ/ቤት ይህን ክርክራቸው እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቆጥሮ በቅድሚያ እልባት ሊሠጠው የሚገባ ነው።
ክስ ቀርቦብኝ ከዚህ ቀደም በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ተዘግቶ ነበር የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በፍሬ ነገር ክርክሩ ላይ እስከተነሳ ድረስ ፍ/ቤቱ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ወስዶ በቅድሚያ እልባት ሊሠጠው የሚገባ እና ፍ/ቤቱ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አስቀድሞ ሊመለከተው የሚገባ ስለመሆኑ ።
05/11/2025
ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም
በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ አስተዳደራዊ ተግባርን ለማከናወን በተሰማሩ ሰራተኞች የሚነሱ የስራ ክርክሮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች የስራ ክርክሩን ተቀብለው አከራክረው ለመወሰን ህጋዊ የዳኝነት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ ትርጉም ተሰጠ
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 ስር እንደተደነገገው አምስት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠን ትርጉም በተለያዩ ምክንያቶች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት እንዲታይ እንደሚደረግ እና በዚህ መልኩ የሚሰጠው የህግ ትርጉም ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በማናቸውም ደረጃ ለሚገኝ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት አስገዳጅ እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡
በዚህ መሰረት ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 234706 “በሲኖዶስ ትዕዛዝ መሰረት እንደ ተጠሪዎች ያሉ አካላት ካልተፈጸሙ ባላቸዉ አሠራር መሰረት በአስተዳደር ረገድ እንዲፈጽሙ ከሚደረግ በቀር ተጠሪዎች በፍርድ ተገደዉ ውዝፍ ክፍያ እንዲፈጽሙ፣ ….. የሚወሰንበት አግባብ የለም፤ የስር ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ መሰረት አድርገው በፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር 9(1) እና 231(1/ለ) መሰረት መዝገቡን መዝጋት አለባቸው” በማለት የተሰጠው ትርጉም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 መሰረት በሰበር መዝገብ ቁጥር 265878 ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት ተለውጦ ‹‹በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ አስተዳደራዊ ተግባርን ለማከናወን በተሰማሩ ሰራተኞች የሚነሱ የስራ ክርክሮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች የስራ ክርክሩን ተቀብለው አከራክረው ለመወሰን ህጋዊ የዳኝነት ስልጣን አላቸው›› የሚል ትርጉም ተሰጥቷል፡፡
“የእናት ፓርቲ ክስ ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ትችት እና አደጋ ላይ ያለው የስትራቴጂክ ክርክር እና በሕዝብ ጥቅም መርሆዎች ክርክር
ዳንኤል ፍቃዱ የህግ ቢሮ
የእናት ፓርቲን ክስ ውድቅ ያደረገው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ውስጥ በሰፊው የተንሰራፋውን ጠበቅ ያለ ባህላዊ የክስ ማቅረብ ስልጣን (Locus Standi) መርህን ያንጸባረቀ ነው፡፡ በዘመናዊ የሰብአዊ መብቶች አተገባበር ግን የሕዝብ ጥቅም ክስ (Public Interest Litigation – PIL) እሳቤ እና በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት ግን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ትችት ሊነሳበት የሚችል በመሆኑ ይህን የትችት ፅሁፍ / commentary/ መፃፉ ተገቢ ሆኗል፡፡
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 11(3) ፡- 11(4)- ማንኛዉም በጉዳዩ መብት ወይም ጥቅም ያለዉ ሰዉ ወይም ጉዳዩን ለማቅረብ በቂ ምክንያት ያለዉ ሰዉ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን ለማስከበር አቤቱታ የማቅረብ መብት አለዉ፡፡
1. የክስ ማቅረብ ስልጣን (Locus Standi) እና የባህላዊው አቋም
በባህላዊ የፍትሐብሔር ሕግ መርህ መሠረት፣ አንድ አካል ክስ ለማቅረብ የግድ ቀጥተኛ ጥቅም (Vested Interest) ሊኖረው ይገባል ። ይህ ማለት ክሱ የሚመለከተው ጉዳይ በቀጥታ ከሳሹን የሚመለከት መሆን አለበት ።
• የውሳኔው ትንተና: የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፓርቲው ንብረት የለውም፣ ተከራይ ነው፣ ስለዚህ በንብረት ግብር መመሪያው ላይ ቀጥተኛ ጥቅም (Vested Interest) የለውም ብሎ መወሰኑ፣ ይህንን ባህላዊና ጠባብ የህግ አቋም የተከተለ ነው። ፍርድ ቤቱ የንብረት ግብር ጉዳይ የፓርቲውን የግል ጥቅም በቀጥታ አይነካም በማለት የሕጉን መንፈስ የተከተለ ይመስላል።
• ሆኖም ይህ ጠባብ አመለካከት በሕዝብ ጥቅም ክስ መርህ ተፈትኖ የወደቀ አስተሳሰብ ነው። የሕዝብ ጥቅምን የሚመለከት ክስ ሲሆን፣ ለክሱ ምክንያት የሆነው ጉዳይ በቀጥታ ከሳሹን ባይመለከትም ክስ ማቅረብ እንደሚቻል በጊዜ ሂደት ተቀባይነት እያገኘ የመጣ አሠራር ነው ። የፓርቲው ክስ "በኑሮ ውድነት የጎበጠው ሕዝባችን ላይ" የተጫነን "ሕገ ወጥ" አዋጅ ይመለከታል የሚለው አላማው ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ሰፊ የሕዝብ ጥቅም ክስ የሚታይ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ይህንን ሊበራል አዝማሚያ ውድቅ አድርጓል።
2. የአዋጅ ቁጥር 1234/2013 እና ይዞት የመጣው የመክሰስ ስልጣን
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶችን ለማስከበር ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ዳኝነትን በተመለከተ አዲስ ድንጋጌ ይዟል ።
• የአዋጁ ድንጋጌ: አንቀጽ 11(4) ማንኛውም በጉዳዩ መብት ወይም ጥቅም ያለው ሰው ወይም ጉዳዩን ለማቅረብ በቂ ምክንያት ያለው ሰው መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶችን ለማስከበር አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዳለው ይደነግጋል ።
• የአዲስ አሠራር ትርጉም: ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው፣ ክስ የሚያቀርብ ሰው መብትና ጥቅም ያለዉ መሆኑን ማሳየት ሳይጠበቅበት ክሱን ለማቅረብ በቂ ምክንያት ያለዉ መሆኑን ካሳየ መክሰስ እንደሚችል ነው ። "በቂ ምክንያት" ማለት ጉዳዩ በቀጥታ ከሳሽን የሚመለከት ባይሆንም፣ የሌላን ሰው ወይም ቡድን መሠረታዊ መብት ለማስከበር በቂ የክስ ምክንያት መኖሩን ማሳየት ነው ።
• የእናት ፓርቲ ክስ የአዲስ አበባ አስተዳደር የጫነው የንብረት ግብር ሕገ-ወጥ በመሆኑ የሕዝብን የንብረት የማፍራት እና የመጠቀም መብት የሚነካ ነው በማለት በቀጥታ ወደ መሰረታዊ መብቶች ማስከበር ማምጣት ይቻል ነበር። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ግን በጉዳዩ ላይ መብትም ሆነ ጥቅም የሌለው በማለት የሰጠው ብይን፣ የአዋጁ አንቀጽ 11(4) የሰጠውን "በቂ ምክንያት ያለው ሰው" የሚለውን ሰፊ ሥልጣን ውድቅ ያደረገ ይመስላል።
3. የውክልና እና የሕገ-መንግስት ሰፊ ትርጉም
ፍርድ ቤቱ የፓርቲውን የመክሰስ ስልጣን ከነፈገባቸው ምክንያቶች አንዱ "ፓርቲው እንዲከራከር የወከለው አካል የሌለ በመኾኑ" የሚለው ነው። ይህ የቡድን ጥቅም የመወከል ጉዳይ ከሕገ-መንግስት አንቀጽ 37(2) ጋር ተያይዟል ።
• ሕገ-መንግስታዊ አቋም: ሕገ-መንግስቱ ማንኛውም ማህበር የአባላቱን የጋራ ወይም የግል ጥቅም በመወከል፣ እንዲሁም ማንኛውንም ቡድን ወይም ተመሳሳይ ጥቅም ያላቸውን ሰዎች የሚወክል ግለሰብ ወይም የቡድን አባል በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ የመጠየቅና የማግኘት መብት እንዳለው ይደነግጋል ።
• የፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝብ ጥቅም ጉዳይ ላይ በሕዝብ ስም የመቆም ህዝባዊ ግዴታ አለባቸው። የፓርቲው ክስ የበርካታ የከተማዋን ተከራዮች እና ነዋሪዎችን የሚመለከት ስለሆነ፣ ፓርቲው እንደ "ተመሳሳይ ጥቅም ያላቸውን ሰዎች የሚወክል" አካል ተቆጥሮ ክስ የማቅረብ ስልጣን ከሕገ-መንግስቱ ማግኘት ይቻል ነበር። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ፓርቲው የግል ወካይ የለውም በሚል የሰጠው ውሳኔ፣ ይህንን ሰፊ የሕገ-መንግስት ድንጋጌ አላገናዘበም::
ማጠቃለያ
በፓርቲው ክስ ላይ የተሰጠው ውሳኔ፣ የኢትዮጵያን ፍትሕ ሥርዓት የለመደውን ጠባብ የክስ ማቅረብ መርህ (Vested Interest) የተከተለ ነው። የሕዝብ ጥቅም ክስ (PIL) አሠራር ውስንነት በኢትዮጵያ የፍትህ ስርአት ውስጥ ከፍተኛ ችግር የፈጠረ መሆኑን በዘርፉ የተሰሩ ጥናቶች ያመላክታሉ ፣ ለችግሮቹ እንደ ምክንያት የሚነሱት ፡- ለዳኞች በቂ ስልጠናና ልምድ አለመኖር ፣ የሕዝብ መብቶችን የሚዳኝ ልዩ ፍርድ ቤት አለመኖር / ከ1234 በሁዋላ በተወሰነ መንገድ ሊቋቋሙ የሞከሩተም / ከፍተኛ የትኩረት ማነስ የታይባቸዋል እና በዚህ ረገድ የማህበረሰቡ ግንዛቤ አናሳ መሆን ይገኙበታል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሕጉን የቆየ ባህላዊ አተረጓጎም ያጸና በመሆኑ፣ የሕዝብን ሰፊ ጥቅም የሚመለከቱ አዋጆች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪል ማህበራት በህግ አደባባይ መቃወም እንዳይችሉ የሚያደርግ ነው። ይህ ደግሞ በሕገ-መንግስት የተረጋገጡትን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ለማስከበር በቀጥታ ለፍርድ ቤት በመቅረብ ዳኝነት የመጠየቅን (Strategic Litigation) አሰራር ያደናቅፋል።
- ይህ ትችት የፓርቲውን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የወጣ ልጥፍ ተከትሎ የተሰጠ ነው፡፡”
By Daniel Fikadu:
የ ኮንስትራክሽን ውል እና ኣይነቶቹ
1. Lump sum contract
💫የአንድ ጊዜ ድምር ውል በአንድ ጊዜ ኮንትራት ውስጥ የሁሉም ስራዎች አጠቃላይ ዋጋ ፕሮጀክቱ ከመጀመሩ በፊት አስቀድሞ ተወስኗል::
ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን በቋሚ ዋጋ ለማጠናቀቅ ተስማምቷል ይህም በአጠቃላይ የሥራ ወሰን እና ዝርዝር መግለጫዎች ላይ የተመሰረተ ነው::
በፕሮጀክቱ ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ለውጦች ወይም ማሻሻያዎች ተጨማሪ ወጪዎችን ሊያስከትሉ እና የለውጥ ትዕዛዝ ሊፈልጉ ይችላሉ።
2.Bill of Quantity Or Unit Rate Contract
💫የቢል መጠኖች ወይም የንጥል ተመን ኮንትራት: በመጠን ወይም በክፍል ተመን ውል ውስጥ ፕሮጀክቱ ወደ ተለያዩ ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን ለእያንዳንዱ አካል የተወሰነ መጠን እና የክፍል ተመኖች ኮንትራክተሩ የሚከፈለው በተጠናቀቀው የሥራ መጠን ላይ በመመስረት በክፍል ተመኖች ተባዝቶ ነው።
ይህ ዓይነቱ ውል በዋጋ አወጣጥ ላይ የበለጠ ተለዋዋጭነት እና ግልጽነት ይሰጣል።
3.Cost Plus Fixed Fee Contract
💫የወጪ እና ቋሚ ክፍያ ውል በወጪ እና ቋሚ ክፍያ ውል ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ለወጣው ትክክለኛ ወጪ እና አስቀድሞ የተወሰነ ክፍያ ወይም የትርፍ ህዳግ ይከፈላል።
ይህ ዓይነቱ ውል በተለምዶ የሥራው ወሰን እርግጠኛ በማይሆንበት ጊዜ ወይም በማደግ ላይ በሚሆንበት ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል እና የወጪ መጨናነቅ አደጋን ወደ ባለቤቱ ይለውጣል.
4. Cost Plus Percentage of Cost Contract
💫የወጪ ኮንትራት መቶኛ በወጪ እና የወጪ ውል መቶኛ ፣ ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ለወጣው ትክክለኛ ወጪ እና ከጠቅላላ ወጪዎች መቶኛ እንደ ትርፍ ህዳግ ይከፈላል።
ኮንትራክተሩ ትርፋቸውን ለመጨመር ወጪዎችን ለመጨመር ማበረታቻ ሊኖረው ስለሚችል ይህ ዓይነቱ ውል የጥቅም ግጭት የመፍጠር አቅም አለው።
5. Item Rate or Schedule of Rates Contract
💫የንጥል ተመን ወይም የዋጋ መርሃ ግብር ኮንትራት በንጥል ተመን ወይም የዋጋ መርሃ ግብር ውል ውስጥ ፣ የተለያዩ የስራ እቃዎች ዋጋ በኮንትራክተሩ በቀረበው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ አስቀድሞ የተገለጹ ናቸው።
ኮንትራክተሩ የሚከፈለው በእያንዳንዱ የተጠናቀቀው የሥራ ዕቃ መጠን በሚመለከታቸው ተመኖች ተባዝቶ ነው።
ይህ ዓይነቱ ውል ለተለያዩ የፕሮጀክቱ አካላት የዋጋ አሰጣጥ ላይ ግልጽነት ይሰጣል::
6.Labour Contract
💫የሠራተኛ ውል - በሠራተኛ ውል ውስጥ ኮንትራክተሩ የሠራተኛ አገልግሎቶችን ብቻ ይሰጣል እና ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች በባለቤቱ ይሰጣሉ::
ኮንትራክተሩ የሚከፈለው በተስማሙት የሰዓት ተመኖች ወይም ለሚሰጠው የሠራተኛ አገልግሎት ደሞዝ ነው።
7.Hybrid Contract
💫የተለያዩ የኮንትራት ዓይነቶችን አካላትን በማጣመር የፕሮጀክቱን ልዩ ፍላጎት ለማሟላት ለምሳሌ የሁለቱት የተለያዩ ኮንትራክተሮች የአንድ ጊዜ ድምር ውል እና የወጪ እና የቋሚ ክፍያ ውልን ሊያካትት ይችላል።
ይህ ዓይነቱ ውል በዋጋ እና በአደጋ ምደባ ላይ ተለዋዋጭነትን ይፈቅዳል።
8. Special Contract
💫ልዩ ውል - ልዩ ውል ለአንድ የተወሰነ ፕሮጀክት ልዩ መስፈርቶች የተዘጋጀ ውል ነው።
ልዩ ኮንትራቶች በመደበኛ የኮንትራት ቅጾች ውስጥ የማይገኙ የተወሰኑ አንቀጾችን ፣ ውሎችን እና ሁኔታዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ።
ይህ ዓይነቱ ውል የተወሰኑ የፕሮጀክት ፍላጎቶችን እና ታሳቢዎችን ለማስተናገድ ያስችላል።
የፌደራል ፍ/ቤቶች ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም የበጀት ዓመቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል።
መልካም የሥራ ዘመን ለሁላችን ይሁን !!!
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገልጋዮች በሙሉ
የፍትሐብሄር ይግባኝ ችሎት የስራ ቦታ ለውጥ
**********
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሄር ይግባኝ ችሎት አራት ኪሎ ባለው የኢትዮ-ፓስታ ህንፃ ላይ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ከጥቅምት 3 ቀን (ሰኞ) 2018 ዓ.ም ጀምሮ የፍትሐብሄር ይግባኝ ችሎቱ አራት ኪሎ ከአብረሆት ላይብረሪ ወደ ፒያሳ መሄጃ 100 ሜትር ወረድ ብሎ ፍርድ ቤቱ እያስገነባ ወደሚገኘው አዲሱ ህንፃ ተዛውሮ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን እየገለፅን ከላይ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የይግባኝ ችሎቱ ተገልጋዮች አገልግሎት ማግኘት የሚችሉት በአዲሱ ህንፃ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በአማራጭ የጎግል ማፕ (google map) ሊንክ 2QH6+VC7, Addis Ababa በመጠቀም አቅጣጫውን ማግኘት ይችላሉ።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Website
Address
Addis Ababa
