የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ንግድ ፅ/ቤት Arada Woreda 2 Trade Office

የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ንግድ ፅ/ቤት Arada Woreda 2 Trade Office

Share

የአራዳ ክ//ከተማ ወረዳ 2 ንግድ ፅ/ቤት መሀል ከተማ ላይ የሚገኝና በርካታ የንግድ እንቅስቃሴ የሚከወንበት ወረዳ ነው።

14/09/2022

አዲስ የሲሚንቶ ዋጋ ተመን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እየጨመረ የመጣውን የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ለማስተካከል አዲስ የዋጋ ተመን ማውጣቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ለማስተካከል ፋብሪካዎች የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተጠይቀው ያወጡት ዋጋ እጅግ የተጋነነ በመሆኑ ነው በዘርፉ ያለውን የምርት ሂደት ጥናት የሚያደርግ ቡድን በማቋቋም አዲስ የዋጋ ተመን ይፋ ያደረገው፡፡

በዚህ መሰረት ሲሚንቶ ከፋብሪካ የሚወጣበት አዲሱ የዋጋ ተመን ዝቅተኛው 510 ብር ሲሆን÷ ከፍተኛው ደግሞ 683 ብር ከ44 ሳንቲም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ÷ አሁን ላይ የሲሚንቶ ምርት እጥረት በመኖሩ ለመንግስታዊ ስራዎች ቅድሚያ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም ማረጋገጫ በማምጣት ከፋብሪካዎች በቀጥታ ምርት የሚገዙበት መንገድ ተመቻችቷል ነው ያሉት፡፡

የግል ተጠቃሚዎችን በተመለከተም የሁሉም ከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ፍላጎት ምን ያህል እንደሆነ ስለሚታወቅ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና በተደራጁ ማህበራት በኩል እንደሚያገኙ አስረድተዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ይሁንታ ካገኙ አካላት ውጪ ሲሚንቶ ይዞ የሚገኝና በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ግብይቶች ህገወጥ በመሆናቸው ተቋሙ ማስታወቂያ ካስነገረበት ቀን ጀምሮ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

በከተሞች ላይ የሚኖረው ሽያጭም የትራንስፖርት፣ የጫኝና አውራጅ እንዲሁም የመጋዘን ኪራይን ታሳቢ በማድረግ የሚሸጥ ይሆናል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

27/07/2022

የሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያን በማይተገብሩ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያን በማይተገብሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 ከሐምሌ 5 ቀን 2014 ጀምሮ ተግባራዊ ቢደረግም÷ ከስርጭት ትስስርና ከመሸጫ ዋጋ ጋር ተያይዞ ለተጠቃሚው እየደረሰ አለመሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በተደረገ ክትትልም÷ ሲሚንቶ ከተቀመጠው የስርጭት መመሪያ ውጪ ከፋብሪካዎች እየወጣ በተለያዩ መጋዘኖችና የሽያጭ ቦታዎች እንደሚገኝ መረጋገጡን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በመሆኑም በየክልሉና ከተማ አስተዳደሩ ከሚመለከተው የፀጥታ ተቋም ጋር በመቀናጀትና የሲሚንቶ ግብይት ቁጥጥር ቡድን በማሰማራት÷ ከመመሪያ ውጪ እየተከናወነ የሚገኘውን ሕገ ወጥ የሲሚንቶ ግብይት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በአስቸኳይ ተገቢ እርምጃ እንዲወሰድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡

ተጠቃሚው የሲሚንቶ ምርት ማግኘት እንዲችል ለስርጭቱ የተመረጡ አካላት በአስቸኳይ ምርቱን ከፋብሪካ በመቀበል በተላለፈው ጊዜያዊ የመሸጫ ዋጋ እንዲያቀርቡ ሚኒስቴሩ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Photos from Mayor Office of Addis Ababa's post 19/07/2022
05/07/2022

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደረገ
*****************

ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ መሠረት፦

ቤንዚን …. 47 ብር ከ83 ሣንቲም በሊትር
ነጭ ናፍጣ …. 49 ብር ከ02 ሣንቲም በሊትር
ኬሮሲን… 49 ብር ከ02 ሣንቲም በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ … 53 ብር ከ10 ሣንቲም በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ … 52 ብር ከ37 ሣንቲም በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ … 98 ብር ከ83 ሣንቲም በሊትር መሆኑን አስታውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣሥ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ እና የትርፍ ህዳግ አሠራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ እና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

Photos from የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ንግድ ፅ/ቤት Arada Woreda 2 Trade Office's post 26/06/2022

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ንግድ ፅ/ቤ ከህብረት ስራ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ሳምንታዊ የእሁድ ገበያ የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲቀርቡ በማድረግ አጠናክሮ ቀጥሏል።ህብረተሰቡም በሚቀርበው ምርትና ዋጋ መደሰታቸውም እየገለፁ ነው።

Photos from የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ንግድ ፅ/ቤት Arada Woreda 2 Trade Office's post 19/06/2022

የህብረተሰባችንን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የጀመርነው የእሁድ ገበያ ዛሬም በቀን 12/10/2014 እንደቀጠለ ነው።ቀይ ሽንኩርት 30 ብር፣ድንች 15፣ቲማቲም 18፣ነጭ ጤፍ 47፣መኮረኒ 61፣ፕሪማ ፓስታ 33፣ምስር ክክ 130፣አተር ክክ 75፣ድፍን ምስር 118፣ዱቄት44 ወዘተ እየተሸጠ ይገኛል።
መጥተው ይሸምቱ
አድራሻ
አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 አቤት ሆስፒታል ጋ

13/06/2022

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል የመሠረታዊ ፍጆታ ምርቶችን በማቅረብ ገቢያውን በማረጋጋት የኑሮ ውድነቱ ለመቀነስ እየሰራ ነው።
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተመረጡ ሦስት (የካ፣ ልደታ እና ንፋስ ስልክ) ክፍለ ከተሞች ከዚህ በፊት የነበራቸውን የእሁድ ገበያ(ሰንደይ ማርኬት) የመሸጫ ቦታውችን ከ13 ወደ 34 በማስፋት ሸማቹና አምራቹ በምርት አቅርቦት፣ በዋጋና በጥራት በቀጥታ ተገናኝተው የሚገበያዬበት የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል። በዚህም የሰንደይ ማርኬት ከተጀመረ ጀምሮ በ31 ዙሮች ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብት መሰብሰብ ተችሏል።

እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል ተቋማትን፣ የግል ባለሃብቱን እና የከተማችን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ የከተማ ግብርናና በመጠቀም የጓሮ አትክልት ምርትን በስፋት ለማቅረብና የዳቦ መጋገሪያ ፍብሪካወችን በመገንባ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ከፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ዳቦ ለማቅረብ በቂርቆስ፣ልደታና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች ብቻ 13 የዳቦ ፋብሪካዎችን ለመገንባት ከሸማቾችና ከግል ባለሃብቶች ጋር የማምረቻ ቦታ እርክክብ በማድረግ እየተገነቡ ይገኛሉ።

ሁሉም የዳቦ ፍብሪካወች ግባታቸው ሲጠናቀቅ በቀን 936 ሽህ በላይ ዳቦ የማምረት አቅም ያላቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የ4 የዳቦ ፋብሪካዎች ግንባቸው በቅርቡ ተጠናቋል የዳቦ የምርት አገልግሎት መሰጠት ይጀምራሉ፡፡

የሸገር ዳቦ ፋብሪካን ጨምሮ እነዚህ የዳቦ ፋብሪካዎች የሚያቀርቡትን የዳቦ ምርት ለህዝቡ የሚሸጡበት 49 የመሸጫ ኮንቴነሮችም ተገንብተዋል።

በተመሳሳይ ከ 43 ሽህ በላይ አባውራ/እማውራን ተሳተፊ እና ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሁም 510 የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተሳተፋበት የከተማ ግብርና ስራም ልዬ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

በተመረጡ 5 ክፍለ ከተሞች ተጨማሪ 6 አዳዲስ ምገባ ማእከላትን በመገንባት የማእከላትን ከ6 ወደ 12 ከፍ በማድረግ የኑሮ ውድነቱን ለማሻሻል ሌላኛው ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ሲሆን በአዲስ መልኩ ለሚሰሩም ሆነ ለነባር የምገባ ማዕከላትን አስፈላጊው ግብዓት ተሟልቶላቸው ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ
ሰኔ 06/ 10/ 2014 ዓ.ም

Photos from የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ንግድ ፅ/ቤት Arada Woreda 2 Trade Office's post 12/06/2022

የእሁድ ገበያ ዛሬም በተነቃቃ ሁኔታ ቀጥሏል።ላገዛችሁን ሁሉ እጅግ አርገን እናመሰግናለን።በቀጣይም የህዝባችንን የእርካታ ደረጃ ለመጨመር የሚቀርቡ ምርቶች አይነትና መጠን ለመጨመር ተግተን እንሰራለን።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Addis Ababa