የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council

Share

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማው ህግ አውጪ ተቋም ነው!

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council's post 01/06/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በየካ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል::

የተከበሩ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና ከምርጫው በኃላ እንደተናገሩት የምመርጠው ለራሴ ብቻ ሳይሆን ለሀገርና ለትውልድ ግንባታ አዎንታዊ ሚና መጫወት ስላለብኝ ነው ብለዋል::

!

Photos from Buzena Alkedir's post 24/05/2026
Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council's post 23/05/2026

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የተቀናጀ የከተማ ግብርና ማዕከል በምስል፦

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council's post 16/05/2026

"የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የወጣቶች ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከየካ ክፍለ ከተማ ምክርቤት ጋር በመሆን "የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የወጣቶች ሚና በሚል ለየካ ክፍለ ከተማ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በመድረክ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ሀገር የምትገነባው በወጣቶች መሆኑን እና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ወጣቶች የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው መንግስት ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት በርካታ ተግባራትን በመከወን ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

"የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የወጣቶች ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ በደ/ር ዋጋሪ ነገሪ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጏል ።

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council's post 08/05/2026

ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ዕጩዎች ሹመትን አጸደቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱን የፍትሕና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ዕጩዎች ሹመት አጽድቋል፡፡

የተከበሩ አቶ በላይ ደጀን በምክር ቤቱ የፍትሕና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን አቅም እና ተደራሽነት ይበልጥ ለማጠናከር በቀረበዉ ሹመት መሰረት፡

1ኛ. ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ - የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ

2ኛ. የተከበሩ ረ/ፕ ነብዩ ባዬ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል

3ኛ. አቶ ሠለሞን ካሳ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል

4ኛ. የተከበሩ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል

5ኛ. ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር) - የሥራ አመራር ቦርድ አባል

6 ኛ. ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድ - የሥራ አመራር ቦርድ አባል ሆነዉ ተሹመዋል፡፡

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council's post 08/05/2026

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ አጀንዳዎችን እና ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ።

በዚህም መሰረት:-
- አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አሰግደዉ ኃ/ጊዮርጊስ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ሰለሞን ዲባባ - የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል::

08/05/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉብኤውን ማከናወን ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ ሲሆን እንዲሁም በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የሚያጸድቅ ይሆናል።

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council's post 08/05/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በመዲናዋ የተገነቡ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የምክር ቤት አባላት አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ የተሰራው ስራ እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልጸው በዚህም መዲናዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል::

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council's post 08/05/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት በከተማዋ የተገነቡ የልማት ስራዎች በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ::

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


ካዛንቺስ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ECA ጎን
Addis Ababa
55698