Ethiopian National Archive and Library Agency-ወመዘክር

Ethiopian National Archive and Library Agency-ወመዘክር

Share

It was set up in 1943 with the name public library-Wemezekir.

The Ethiopian National Archives and Library Agency is a governmental body established by proclamation No.179/1999 as a legal frame work and a nation-wide level of responsibilities. The Agency has been delivering lots of services such as research and study services, reading services, training services, micro film reading services audio, audio-video recording services and consultancy services partic

Photos from Ethiopian National Archive and Library Agency-ወመዘክር's post 31/05/2026

ሀገራችንን የጽሑፍ ቅርሶች በዓለም የትውስታ ማኀደር ለማስመዝገብ በቅርሶች አሰባሰብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው መርሐ ግብር ተጠናቀቀ።

ኢሊሌ ሆቴል

ግንቦት 21/2018 ዓ.ም

የጽሑፍ ቅርሶችን የማስመዝገብ ጉዳይ ሀገራዊ ፖሊሲ ሆኖ ሊቀርብ ይገባዋል ተባለ።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሀገራችንን የጽሑፍ ቅርሶች በዓለም የትውስታ ማኀደር ለማስመዝገብ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተጠናቋል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዓለም ትውስታ (ትዝታ) ማኅደር (MOW) ኮሚቴን ሥርዓት የማሲያዝ ዕቅድ ለውይይት አቅርበዋል።

ኃላፊው ባቀረቡት የአሠራር ሥርዓት ማስያዣ ዕቅድ ላይ የአሠራር ሥርዓቱ በተቋሙ ሥርዓት ውስጥ መኾን ያስፈለገበት ምክንያቶች ሲገልጹ የኮሚቴው ተግባር በተቋሙ መዋቅር ውስጥ በብሔራዊ ደረጃ የትውስታ እና የጥንታዊ ጽሑፍ ቅርስ አስተዳደር መዋቅር ውስጥ ለማካተት፣የቴክኒክ አቅምን በማሳደግ እና የዩኔስኮን መመሪያዎች ተግባራዊ ለማድረግ፣ አገልግሎቱ ይህንን ውሕደት በመምራት ለኮሚቴው ዘላቂ መዋቅራዊ መሠረት እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የተቋማዊነት ዕቅድ ስኬታማ እንዲኾን የሚከናወኑ የሕግ ማኀቀፍ ተግባራት በተመለከተ የዩኔስኮ መርኆዎች በሚያስቀምጡት መርኀ መሠረት፣ የኮሚቴውን መተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ እና ማፀደቅ ፤ከአዋጅ ቁጥር 179/91 ጋር ወይም፣ በቅርቡ ይወጣል ተብሎ ከሚጠበቀው አዲስ አዋጅ ጋር ማጣጣም እንዲሁም የመንግስት ድጋፍ እና ዕውቅና ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ኃላፊው ባቀረቡት የአሠራር ሥርዓት ማስያዣ ዕቅድ ጽሑፋቸው ላይ አስፍረዋል።

በብሔራዊ ኮሚቴው አጠቃላይ ቅርሶችን በማስመዝገብ ሂደት ውስጥ እንዴት መሠራት እንዳለበት በዶ/ር አሉላ ፓንክረስ ጥቅል መረጃ ቀርቧል።

ብሔራዊ ኮሚቴው የአባ ገሪማ ወንጌላት እና የሐረር ጥንታዊ መዛግብት በዓለም የትውስታ ማኀደር ለማስመዝገብ የሚያስችል ስራ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ መሰራቱን ዶ/ር አሉላ ተናግረዋል።

ስራው እውቅና ተሰጥቶት እንዲሰራ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ብሔራዊ ኮሚቴው ጠቁሞ በተለይ ከወመዘክር የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ለማስመዝገብ በሂደት ላይ የሚገኙትን ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት ኮሚቴውን ቦታው ድረስ በመውሰድ ቅድመ ምልከታ የማድረግ ሥራ መሰራቱ ተገልጿል።

ከዩኔስኮ አቶ ጌቱ አሰፋ ስራዎችን ለመስራት ስራ ማስኬጃ ፈንድ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ሲያቀርቡ ክልሎች በአካባቢያቸው ቢመዘገቡ ያሏቸውን ሁለት ሁለት ቅርሶች ካሏቸው ታሪካዊ አመጣጣቸውንና እድሜያቸው አንጻር ዝርዝረው አቅርበዋል።

ብሔራዊ ኮሚቴው ሰርቶ ለዩኔስኮ እውቅና እንዲሰጣቸው የተላኩ የጽሑፍ ቅርሶች ይሁንታ የሚያገኙበት ጊዜን ውጤቱ በ2027 ሰኔ ወር ላይ እንደሚታወቅ ተጠቁሟል።

በMOW የተመዘገቡ የመረጃ ሀብቶች ጠቅላላ ብዛት 570 ስብስቦች
ከ72 አገሮች እና 4 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የመጡ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች (key Topics)
የሳይንስ አብዮት (scientific revolution)
የሴቶች አስተዋጽኦ-በታሪክ (women's contribution to history) እንደሆነ ተገልጿል።

በከሰዓቱ መርሐ ግብር በቀረበው የዕቅድ አሠራር ላይ ውይይት እና ብሔራዊ ኮሚቴው ስራውን በትኩረት ከመስራት አንጻር የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ትኩረት ማድረግ፤ከክልል አመራሮች ጋር የሚፈጠር የስራ ግንኙነት፤ ለወመዘክር ሪፖርት የማቅረብ ስርዓት መዘርጋትና ስራውን በዕቅድ ላይ በማካተት ቀጣይነት እንዲኖረው ማስቻል የሁሉንም ትብብር እንደሚጠይቅ በማመላከት ተጠናቋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

ቴሌግራም: https://t.me/wamezeker
ድረገጽ: https://www.nala.gov.et/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
ፌስቡክ: https://web.facebook.com/Wemezekr
ትዊተር:https//
ቲክቶክ፡https፡/tiktok.com/

Photos from Ethiopian National Archive and Library Agency-ወመዘክር's post 28/05/2026

ግንቦት 20/2018 ዓ.ም

በቅርሶች አሰባሰብ ዙሪያ በዕለቱ ለተሳተፉ ከዘጠኝ ክልሎችና ሁለት የከተማ መሥተዳድሮች ለተውጣጡ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ውይይት ተጀመረ።

ኢሊሌ ሆቴል
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ጥንታውያን የሀገራችንን የጽሑፍ ቅርሶች በዓለም የትውስታ ማኀደር ለማስመዝገብ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል።

የሚሰራው ሥራ ኢትዮጵያ ካላት ሀብት ውስጥ የተመዘገበው ውስን በመሆኑ እኛም እንደ ሌሎች ሀገራት ሀብቶቻችንን በዓለም ለማስተዋወቅ በጋራ መሥራት እንዳለብን የሚያስችል መድረክ እንደሆነም ተጠቁሟል።

በመድረኩ የዩኔስኮ በአዲስአበባ ዳይሬክተር ዶ/ር ሪታ ቢሶልት፣ፕሮፌሰር አሉላ ፓንክረስት፣ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያከ፣ተቋሙ የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አባተ ካሳው እና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ የጽሑፍ ቅርሶች አስመዝጋቢ ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተውበታል።

የዩኔስኮ በአዲስ አበባ ዳይሬክተር ዶ/ር ሪታ ቢሶኖት በውይይት መድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት ኮሚቴው
በህዳር ወር 2025 ሁለት ጥንታዊያን የሀገራችንን ታላላቅ የጽሑፍ ቅርሶች በዓለም የትዝታ (የትውስታ) ማኅደር UNESCO ለማስመዝገብ አስፈላጊውን ሰነድ የማሟላት ስራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የበርካታ ቅርሶች ባለቤት ብትሆንም እስካሁን በወመዘክር ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ከተመዘገቡት በዓለም አቀፍ የሰው ልጆች የአእምሮ ሀብትነት 12ቱን የጽሑፍ ቅርሶች የማስመዝገብ ስራ ብቻ መሰራቱን አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ ጥንታዊያን የጽሑፍ ቅርሶችን የማስመዝገብ ስራን ብሔራዊ ኮሚቴው በጥልቀት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የአገሪቷን ሀብት ለተተኪው ትውልድ ለማሻገር ኮሚቴው እያከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ በማስቀጠል ለማስመዝገብ በሂደት ላይ የሚገኙትን በተሻለ መልኩ አጠናክሮ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመረጃ ሀብቶች አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ስለሺ ሽፈራው የጽሑፍ ሀብቶች ጥበቃ እና እንክብካቤ የሚስተዋሉ ችግሮች እና የመፍትኤ ሃሳቦች ዙሪያ መነሻ ጽሑፍ ለውይይት ቀርቦ ከተሳታፊው ጥያቄዎችና የመፍትኤ ሃሳቦች ተሰጥተዋል።

በመቀጠልም በዩኔስኮ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሴክተር ኃላፊ አቶ አደራው ገነቱ አጠቃላይ የአለም የትውስታ ማኀደር UNESCO -MOW አወቃቀሩን፣ ቅርሶችን ለመመዝገብ መሟላት ያለባቸው ነገሮች፣አሰራሩንና አደረጃጀቱን እንዴት መሰራት እንዳለበት፣ ተግባርና ኃላፊነት አስመልክቶ በአፍሪካ፣ በአለምአቀፍ እና በብሔራዊ ደረጃ ያለውን ሂደት በዝርዝር አቅርበዋል።

በከሰዓቱ መርሐ ግብር በዕለቱ ከተሳተፉ ዘጠኝ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች ተወካዮች ያሏቸውን ቅርሶች ከማሰባሰብ አንጻር እያከናወኑ የሚገኙትን ተሞክሮ አቅርበዋል።

በአሰራር ሂደቱ ላይ እቅዶችን ከወመዘክር ጋር አስተሳስሮ ከመስራት አንጻር ክፍተት እንዳለና ትኩረት የሚሻው ጉዳይ እንደሆነም ተሞክሮ ባቀረቡት ተወካዮች በስፋት የተነሳ ሃሳብ ነበር።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችንን ይከታተሉ!!

ቴሌግራም: https://t.me/wamezeker
ድረገጽ: https://www.nala.gov.et/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
ፌስቡክ: https://web.facebook.com/Wemezekr
ትዊተር:https//
ቲክቶክ፡https፡/tiktok.com/
ኢ-ሜይል፡- [email protected]/" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]/

26/05/2026

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሒጅራ (የ2018 ዓ.ል) የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።

መልካም የዒድ አል-አድሃ በዓል!!

Photos from Ethiopian National Archive and Library Agency-ወመዘክር's post 25/05/2026

የሰኞ ንጋት «እንገናኝ እንሰናኝ» ሁለተኛውን የሠራተኞች መድረክ አገልጋይነትና በጎ ፈቃደኝነት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

ግንቦት 17/ 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በዛሬው የሰኞ ንጋት «እንገናኝ እንሰናኝ» መድረክ በበጎ ፈቃደኛው መሐመድ ካሳ አቅራቢነት አገልጋይነትና በጎ ፈቃደኝነት ከተቋማዊ አሰራር፣ ከማህበራዊ እሴትና ከአለም አቀፋዊ ተሞክሮዎች አንጻር በስፋት ተዳሷል።

በማንኛውም ዘመንና ሁኔታ ኃላፊነትን መወጣት፣ በቃል የነበረውን በወረቀት፣ የወረቀቱን ዲጂታይዝ አድርጎ በብዙ ውጣ ውረድ መጠበቅ፣ ዕውቀትን ከመጥፋትና ከመረሳት ታድጎ ከትውልድ ጋር ማሰናኘት በዚህ የተቋም የአገልጋይነት ዐብይ ጉዳይ እንደሆነ ተነስቷል።

የማህበራዊ እሴቶቻችን ለምሳሌ፦ የእርቅ ሥርዓቶች፣ የሐዘን የማርዳት ልማድ፣ እንግዳ ተቀባይነት፣ እንዲሁም የልምድ አዋላጆችና የወጌሻዎች ጥበብ የአገልጋይነት ትልቅ ማሳያዎች ናቸው። እነዚህ ተግባራት ማን እንዳደረገልን እስክንረሳ ድረስ ከታይታ በራቀ መልኩ በበጎነት የሚከናወኑ መሆናቸው ተብራርቷል።

በኢትዮጵያ ዓለም ስለ ሰብዓዊ መብት ማቀንቀን ከመጀመሩ በፊት የላቀ ሰብዓዊነት ይተገበር እንደነበር የአድዋ ጦርነትን በማጣቀስ ተገልጿል። በጦር ሜዳ የወደቁ የጠላት ወታደሮችን አስክሬን በሰብዓዊነት እስከ መቅበር፣ አልፎ ተርፎም ለቤተሰቦቻቸው የፍቅር ደብዳቤ በሚመስል ትሕትና የሐዘን መርዶ እስከ መላክ የደረሰ የላቀ ማንነት እንደነበረን ተወስቷል።

አገልጋይነት ለሰዎች የግል ስብዕና መቃናት፣ ለክህሎት ማደግና ለዕውቀት መበልጸግ የሌሎችን ምቾት ሳይነሱ የራስን አስተዋጽዖ ማበርከት ነው፤ ሁሌም በላጩ ሰው እንደሆነ ለሰዎች መልካም ነገርን በበጉ ፈቃደኝነት በመስራት ማሳየት አለብን የሚሉት በመድረኩ ትኩረት የተደረገባችው ርዕሰ ጉዳዮች ነበሩ።

በጎ ፈቃደኛ መሐመድ ካሳ ሰፊ የአገልጋይነትና የበጎ ፈቃደኝነት ተሞክሮ ያላቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል፦ በአፍሪካ የበጎ ፈቃደኝነት አምባሳደር በመሆን ማገልገላቸው፣ «ጥበብ ለተፈጥሮ» የሚል የአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያተኩር ንቅናቄን መምራታቸው፣ በመላው ኢትዮጵያ ለወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት ስልጠና መስጠታቸውና የ«ጉዞ አድዋ» መስራቾች መካከል አንዱ መሆናቸው ይጠቀሳሉ።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችንን ይከታተሉ!!

ቴሌግራም: https://t.me/wamezeker
ድረገጽ: https://www.nala.gov.et/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
ፌስቡክ: https://web.facebook.com/Wemezekr
ትዊተር:https//
ቲክቶክ፡https፡/tiktok.com/
ኢ-ሜይል፡- [email protected]/" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]/

ብርቅዬ ጥንታውያን የጽሑፍ ቅርሶቻችን በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት 24/05/2026

በተቋማችን ከሚገኙ ብርቅዬ ጥንታውያን የጽሑፍ ቅርሶቻችን ከፊል ቅኝት ይመልከቱ። ተጋብዘዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችንን ይከታተሉ!!
ቴሌግራም: https://t.me/wamezeker
ድረገጽ: https://www.nala.gov.et/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
ፌስቡክ: https://web.facebook.com/Wemezekr
ትዊተር:https//
ቲክቶክ፡https፡/tiktok.com/
ኢ-ሜይል፡- [email protected]/" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]/
https://youtu.be/h6BYvQUtJBM?si=xgtMPhA6jqCleynY

ብርቅዬ ጥንታውያን የጽሑፍ ቅርሶቻችን በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የጥንታውያን ጽሑፍ ቅርሶች ቤተ-መጻሕፍት ክፍል አጀማመር፣ ይዘትና አገልግሎት አሰጣጥ ለመረዳት ቪዲዮውን እ...

24/05/2026

"እንገናኝ እንሰናኝ!" የሠራተኞች የሠኞ ንጋት መድረክ በየኹለት ሳምንት የሚቀርበው መድረካችን ሁለተኛ ዙሩን ነገ ሰኞ ግንቦት 17/2018 ዓ.ም ማለዳውን ያካሒዳል።

Photos from Ethiopian National Archive and Library Agency-ወመዘክር's post 22/05/2026

የቻይና የትምህርት ዘርፍ ልዑካን በባህልና በእውቀት ላይ ከተቋሙ ጋር ለመስራት ተነሳሽነታቸውን ገለጹ

ኢትዮጵያ እና ቻይና ቀደምት የሆነ የስልጣኔ ታሪክ ያላቸው እንደመሆናቸው ይህንን ስልጣኔ በእኩል እይታ በጋራ ማሳደግ እንዳለባቸው የገለጹት የቻይና የባህል እና የትምህርት ዘርፍ ልዑካን ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ተቋሙን በጎበኙበት ወቅት ነው። በዚህም ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የንባብ፣ የታሪክና የመረጃ ሀብቶች ጋር በተያያዘ በጋራ ለመስራት ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

የቻይና ልዑካኑ ዛሀኦ ዚያንሺ በቻይና የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቴክኖሎጂ እና የትምህርት መርጃ ልማት ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ ሊ ጂንፔንግ በቻይና የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቴክኖሎጂ እና የትምህርት መርጃ ልማት ማዕከል የዲቪዥን ዳይሬክተር፣ ሺን ዩን በቻይና የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቴክኖሎጂ እና የትምህርት መርጃ ልማት ማዕከል የዲቪዥን ዳይሬክተር እና ኪን ዚዩቢንግ የቻይና ኢምባሲ በኢትዮጵያ የባህል ቢሮ ተቀዳሚ ጸሐፊ ናቸው።

ልዑካኑ በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ጉብኝታቸው በጣም መደሰታቸውንና ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ያስመዘገበቻቸው የጽሑፍ ቅርሶች የተቋሙ አካል ሆነው በማየታቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

በተለይም በጥንታዊ የስነ ጽሑፍ ሀብቶች ላይ በተቋሙ የተሰራው የማሰባሰብ እና የመጠበቅ ስራን የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

የልዑካን ቡድኑ ከተቋሙ በጋራ ለመስራት የሚያግዙ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንዲቻል በጉብኝቱ ማብቂያ ላይ ከዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው እና ከሰነድና መዛግብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ጠና ጋር ውይይት አድርገዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችንን ይከታተሉ!!

ቴሌግራም: https://t.me/wamezeker
ድረገጽ: https://www.nala.gov.et/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
ፌስቡክ: https://web.facebook.com/Wemezekr
ትዊተር:https//
ቲክቶክ፡https፡/tiktok.com/
ኢ-ሜይል፡- [email protected]/" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]/

Photos from Ethiopian National Archive and Library Agency-ወመዘክር's post 22/05/2026

የኃላውን ያላወቀ የወደፊቱን ለማወቅ ይከብደዋል፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረዘዳንት (ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ)

ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ለታላቁ የጥበብ ፈርጥ የበርካታ ግጥምና ዜማዎች ፕሮዲውሰር ያየህይራድ አላምረው እህት ወ/ሮ ሒሩት አላምረው እና ለአቶ ዘላለም አላምረው (ሼፍ ዚ) የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ፡፡

የዛሬዎቹ ተመስጋኞቻችን ወ/ሮ ሒሩት አላምረው እና ዘላለም አላምረው (ሼፍ ዚ) በዚሁ ዓመት በታኀሣሥ 22/2018 ዓ.ም የታላቅ ወንድማቸውን የጥበብ ፈርጥ የበርካታ ግጥምና ዜማዎች ፕሮዲውሰር ያየህይራድ አላምረው በሕይወት ዘመኑ ያሰባሰባቸውን ከአምስት ሺህ በላይ መጻሕፍት፣ ጋዜጣ፣የጽሑፍ እና የሙዚቃ ኅትመት ውጤቶችን ውድ ስብስቦች ራሱን የቻለ ቦታ በመስጠት የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በስሙ የተሰየመ የንባብ ክፍል በማዘጋጀት አደራጅቶ ለንባብ ክፍት በማድረግ ለተተኪው ትውልድ የሚጠቅም ታላቅ ስራ መሰራቱ የሚታወስ ነው፡፡

ዛሬ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም ወ/ሮ ሒሩት አላምረው እና አቶ ዘላለም አላምረው (ሼፍ ዚ) የታላቁ የጥበብ ፈርጥ የበርካታ ግጥምና ዜማዎች ፕሮዲውሰር ያየህይራድ አላምረው የጽሑፍ ሀብቶች በክብር ተጠብቆ ለአንባቢ ክፍት ወደተደረገበት እና በስሙ ለተሰየመው ቤተመጻሕፍት ለሚያነቡ ተገልጋዮች በቀላሉ ኮምፒውተሮች በወንድማቸው ስም ተሰይሞ ለሚገኘው ቤተ መጻሕፍት በስጦታ ሲያበረክቱ በተጨማሪ ለቤተመጻሕፍቱ ደህንነቱን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ደረጃውን የጠበቀ በሮችና መስኮቶችን በማስገጠም አበርክተዋል።

በእውቅና መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎትን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ መኮንን ከፋለ ተቋሙ በርካታ የአገር ሀብትን ጠብቆና ሠንዶ ለትውልድ የሚያስተላልፍ ሀገራዊ ተቋም በመሆኑ የዛሬ ተመስጋኞች የታላቁ አገር ወዳድ የጥበብ ሰው ያየህይራድ ቤተሰቦች ይሄንን ለአገር እና ለትውልድ የሚጠቅም ስራ በመስራታችሁ ተቋማችን ከልብ ያመሰግናችኋል ብለዋል።

የምስጋናና የእውቅና መርሐ ግብሩ ላይ በእንግድነት የተገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረዘዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ዛሬ ያየህይራድ በህይወት ባይኖርም ለትውልዱ በማሰብ የሰበሰባቸው ሀብቶቹ የሀገር ሀብት እንዲሆኑ ጠብቆ ያቆያቸውን ቤተሰቦቹ በዚህ መልክ ወደዚህ ሀገራዊ ተቋም ወደሆነው ግዙፍ ተቋም ተጠብቆ ለትውልዱ እንዲያገለግል በማድረጋችሁ ክብር ይገባችኃል። አክለውም ለንባብ ክፍት የተደረገው በወንድማችሁ ስም ለተሰየመው ቤተመጻሕፍት ቤት አንባቢ እንዲጠቀምበት ዘመኑን የማከለ ኮምፒውተር እንደሚያስፈልገው አውቃችሁ ለዚህ አገራዊ ተቋም በወንድማችሁ ስም በማበርከታችሁ ለእናንተም ለወንድማችሁም ትልቅ ደስታን ይሰጣል ብለዋል።የኃላውን ያላወቀ የወደፊቱን ለማወቅ ይከብደዋል።

ወ/ሮ ሒሩት አላምረው በምስጋና መርሐ ግብሩ ላይ ይህንን የወንድሜን ሕልም እውን እንዳደርግ በመጀመር እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ይመለከተናል በማለት በቅንነት ዓላማውን የተቀበሏቸውን የቀድሞው የተቋሙን ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡንና ከእሷቸው በመረከብ ስራው ተጠናክሮ እንዲሰራና እና ጥሩ አፈጻጸም አግኝቶ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ያደረጉትን የአሁኑን የተቋሙን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርጸ ፍሬስብሐትንና በተቋሙ የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎችን ስማቸውን በመጥቀስ አመስግነዋል።

ወ/ሮ ሒሩት ከምስጋናቸው በማስቀጠል በስጦታ ከተሰጡ ኮምፒውተሮች በተጨማሪ በወንድማቸው ስም ለተሰየመው ቤተመጻሕፍት አስፈላጊ ናቸው የሚባሉ ቁሳቁሶችን ሁሉ ከሟሟላት ወደኃላም እንደማይሉ ቃል ገብተዋል።

በመጨረሻም ከተቋሙ የተዘጋጀውን የእውቅና የምስክር ወረቀት ለሁለቱም በማበርከት ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

በእውቅናና የምስጋና መርሐ ግብሩ ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረዘዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ተወካይ እና የተቋሙ የአብያተ መዛግብትና አብያተመጻሕፍት ስልጠናና ምክር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ መኮንን ከፋለ፣ የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት እና የወ/ሮ ሒሩት አላምረው እና የአቶ ዘላላም አላምረው የቅርብ ወዳጆች ተገኝተዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችንን ይከታተሉ!!
ቴሌግራም: https://t.me/wamezeker
ድረገጽ: https://www.nala.gov.et/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
ፌስቡክ: https://web.facebook.com/Wemezekr
ትዊተር:https//
ቲክቶክ፡https፡/tiktok.com/
ኢ-ሜይል፡- [email protected]/" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]/

21/05/2026

የሕትመት ቅጂ ለቤተመዛግብት አገልግሎት እንዲቀርብ ተጠየቀ

ግንቦት 13 ፣ 2018 ዓ.ም ሀገሬ ቴቪ :- የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የትኛውም ዓይነት ህትመት 3 ቅጂ እንዲሰጠው በህግ የተደነገገ ቢሆንም አሳታሚዎች ህትመቶቻቸውን ለተቋሙ እየሰጡ አለመሆኑን አስታውቋል።

ቀደም ባሉ ዓመታት የህግ ቅጣትን በመፍራት እንዲሁም ህትመቶች ቅርስ ሆነው እንዲቀመጡ በማሰብ አታሚ ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ለወመዘክር የምስል፣ የመጻሕፍት እንዲሁም የትኛውንም የሕትመት ውጤት 3 ቅጂ ያቀርቡ እንደነበር የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰርጸ ፍሬስብሐት ገልፀዋል።

በቀጣይ እንደ ሀገር ቅርሶችን የማዳን ዘመቻ መጀመር እንዳለበት የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ቅጂዎች ከያሉበት ተሰብስበው መሰነድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የትኛውንም ቅጂ ለተቋሙ መስጠት እንደሚያስፈልግ በተለያየ መንገድ ግንዛቤ እየተሰጠ ስለመሆኑም የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይ የሕግ እርምጃዎች እንዲጀመሩ ግፊት እንደሚደረግ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በማሕበራዊ መገናኛዎቻችን መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ

👉 ፌስቡክ: https://www.facebook.com/hagerietv
👉 ትዊተር: https://twitter.com/HagerieT
👉 ኢንስታግራም:https://www.instagram.com/hagerie_television
👉 ቴሌግራም: https://www.t.me/Hagerie_TeleVision
👉 ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/hagerietv
👉 ዌብሲይት: https://www.hagerie.tv

Photos from Ethiopian National Archive and Library Agency-ወመዘክር's post 21/05/2026

በሕትመት ውጤቶች አሰባሰብና በአዋጅ ቁጥር 179/91 ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ

ግንቦት 13/ 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት አሳታሚዎች፣ ደራስያን፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ የመንግሥትና የግል ተቋማት ተወካዮች እና የተለያዩ ማህበራት በተገኙበት የሕትመት ውጤቶችን ማሰባሰብና በአዋጅ ቁጥር 179/91 አፈጻጸም ዙሪያ ያተኮረ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ አካሄደ።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "የተቋማችን ማንነት የቆመው እናንተ የፈጠራ ውጤት ውስጥ፣ እናንተ አእምሮ ውስጥና እዚህ ይቀመጥልን ብላችሁ በምታስቀምጡት ሀብት ላይ ነው" በማለት የባለሙያዎችንና የባለድርሻ አካላትን አስተዋጽኦ አጉልተዋል።

የመረጃ ሀብቶች አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ሽፈራው በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የራሷ ፊደልና ጥልቅ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ቢኖራትም እስካሁን የተሰባሰቡ የሕዝብ የአእምሮ ሀብቶች ካለን እምቅ አቅም አንጻር በቂ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 179/91 የተቀመጠው የሕትመት ውጤቶችን ለብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት የማስረከብ ግዴታ በተሟላ ሁኔታ ተፈጻሚ አለመሆኑን ጠቁመዋል።

በመድረኩ ላይ አዋጅ ቁጥር 179/91 በደራስያንና አሳታሚዎች ላይ ጫና ለመፍጠር ሳይሆን፡-
የቅርስና የፈጠራ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ፣
ፍትሐዊና ማዕከላዊ የመረጃ ተደራሽነትን ለመፍጠር፣
የዲጂታል ሕትመቶችን በማካተት የሀገሪቱን የዕውቀት ሀብት ሙሉ በሙሉ ለመመዝገብ የታለመ እንደሆነ ተብራርቷል።

የኦዲዮ ቪዥዋል ቅርስ ጥበቃ እና በሕግ ሥርዓት የማስቀመጥ ጠቀሜታ በአቶ ሠርፀ ፍሬ ስብሐት፣ ዲበ ውሂብ፡ ለሕትመት ጥራት እና ተደራሽነት በዶ/ር ደርብ አዶ፣ እንደዚሁም የመረጃ ሀብቶች አሰባሰብ ሥርዓት ከአዋጅ 179/1991 አኳያ በአቶ እስራኤል በዙ የቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ለውይይቱ መነሻ የሆኑ ሲሆን፤ ተሳታፊዎችም ተቋሙ ሥራዎቹን ይበልጥ ማስተዋወቅ እንዳለበት፣ የአዋጁ ተፈጻሚነት እስከ መጨረሻው የሕግ አግባብ መከተል እንደሚገባውና መሰል መድረኮች በቋሚነት እንዲቀጥሉ ምክረ-ሐሳብ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሠርፀ ፍሬ ስብሐት እንደገለጹት ተቋሙ የኢትዮጵያን የ2030 የዲጂታይዜሽን ግብ ለማሳካት ከኢኖቬሽንና ሳይንስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ዘመናዊ የዲጂታይዜሽን ማሽኖችን አስገብቷል። ይህም በተቋማችን የሕትመት ውጤቶችን ዲጂታይዝ የማድረግ ሰፊ ስራ ሲጠናቀቅ ጥበበኛው ሥራውን መስጠት ብቻ ሳይሆን ከሥራው መጠቀም የሚያስችለውን አሠራር ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

መድረኩ በአውዲዮ ቪዥዋል አውደ-ርዕይ ጉብኝት ተጠናቋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችንን ይከታተሉ!!
ቴሌግራም: https://t.me/wamezeker
ድረገጽ: https://www.nala.gov.et/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
ፌስቡክ: https://web.facebook.com/Wemezekr
ትዊተር:https//
ቲክቶክ፡https፡/tiktok.com/
ኢ-ሜይል፡- [email protected]/" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]/

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Yared Street, Wemezekir
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:45 - 19:30
Tuesday 08:45 - 19:30
Wednesday 08:45 - 19:30
Thursday 08:45 - 19:30
Friday 08:45 - 19:30
Saturday 08:45 - 19:30
Sunday 08:45 - 19:30