Bita woreda women children snd youth affairs office

Bita woreda women children snd youth affairs office

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bita woreda women children snd youth affairs office, Government Organization, Bita, Addis Ababa.

02/04/2023

በአዲሱ የካሣ ህግ ለህዝብ ጥቅም መሬት ለማስለቀቅ ስለሚፈፀም ሥነ-ሥርዓት
==========================
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 ከአንቀጽ 5-10 ድረስ እንደተመለከተው፣
1. #የሚለቀቀው መሬት ለሕዝብ ጥቅም መሆኑን ስለመወሰን
አግባብ ያለው የፌዴራል አካል ወይም የክልል፣ አዲስ አበባ ወይም ድሬደዋ ካቢኔ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሻለ ልማት ያመጣል ብሎ በመሬት አጠቃቀም እቅድ ወይም በልማት እቅድ ወይም በመሠረተ ልማት መሪ ፕላን መሠረት የሚለቀቀውን መሬት ለሕዝብ ጥቅም መሆኑን ይወስናል፡፡
በዚህ መሠረት ለመወሰን መሪ ፕላኑ ዝርዝር የማስፈፀሚያ ፕላን ሊኖረው ይገባል፡፡
ለሕዝብ ጥቅም መሬት አንዲለቀቅ ሲወስን ለካሣ እና መልሶ ማቋቋም የሚያስፈልግ በጀትና በጀቱ በማን እንደሚሸፈን አብሮ መወሰን አለበት።
የመሬት ባለይዞታዎች በዚህ በላይ የተገለፀው መስፈርት ሳይሟላ መሬታቸው ለሕዝብ ጥቅም እንዲለቀቅ የሚሰጥ የሕዝብ ጥቅም ውሳኔ ላይ አቤቱታ ሊያቀርቡ ይችላል፡፡
እንደአስፈሊጊነቱ የክልል፣ የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ካቢኔ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ማስለቀቅ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣኑን ለከተማ ወይም ለወረዳ አስተዳደሩ በውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡
2. #መሬት የማስለቀቅ ሥልጣን
ለሕዝብ ጥቅም አንዲለቀቅ ውሳኔ የተሰጠበትን መሬት የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር መሬቱ የማስለቀቅ እና የመረከብ ሥልጣን አለው፡፡
3. #ለባለይዞታዎች ቅድሚያ የማልማት መብት ስለመስጠት
በከተማ ለመልሶ ማልማት በተከለለ ቦታ ውስጥ ያለ ባለይዞታ በፕላኑ መሠረት ይዞታውን በግልም ሆነ በጋራ ቅድሚያ የማልማት መብት አለው፡፡
የገጠር መሬት ባለይዞታ ለእርሻ ስራ የሚለቀቅ ሲሆን አቅሙ ካለው ይዞታውን በግልም ይሁን በቡድን በመሬት አጠቃቀም ፕላኑ መሠረት ቅድሚያ የማልማት መብት አለው፡፡
በዚህ መሰረት ለተነሺው ቅድሚያ የማልማት መብት የሚጠበቅለት በፕላኑ መሠረት ለማልማት አቅም ማሳያ ማቅረብ ሲችል ነው።
ቅድሚያ የማልማት መብት የሚሰጥበት ዝርዝር ሁኔታ እና አቅም ማሳያ መጠንና የጊዜ ገደብ በደንብ ይወሰናል፡፡
4. #መሬት የሚለቀቅበት ሥርዓት
የከተማ አስተዳደር ወይም የወረዳ አስተዳደር መሬት ሲያስለቅቅ መከተል ያለበት ቅደም ተከተል፡-
ሀ/ ተነሺዎች ከመነሳታቸው ቢያንስ ከአንድ ዓመት በፊት ስለልማቱ ዓይነት፣ ጠቀሜታና አጠቃላይ ሂደት በማወያየት እንዲያውቁት ማድረግ አለበት፡፡
ለ/ በዚህ አንቀፅ ፊደል ተራ (ሀ) የተጠቀሰው ቢኖርም የሚመለከተው የፌዴራል ወይም የክልል መንግስት ሀገራዊ ወይም ክሌላዊ ፋይዳ ላለው ለአስቸኳይ ልማት መሬት እንዲለቀቅ ከወሰነ ተነሺዎች ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ስለልማቱ አይነት፣ ጠቀሜታና አጠቃላይ ሂደት በማወያየት እንዲያውቁት ሊደረግ ይችላል፡፡
ሐ/ እንዲለቀቅ በተወሰነው ቦታ ላይ ከሚገኙ ተነሺዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የባለመብትነት ማስረጃ እና ካሣ የሚከፈልባቸውን ንብረቶች የልኬትና የመጠን መረጃ መሰብሰብ አለበት። ተነሺዎች ስለልማቱ እንዲያውቁት ከተደረገ በኋላ የተጨመሩ ማናቸውም ንብረቶች ካሳ አይከፈልባቸውም፡፡
መ/በዚህ ንዑስ አንቀጽ ፊደል ተራ “ሐ” መሠረት የተሰበሰበውን መረጃ አጣርቶ ለልማት ተነሺ የሚሰጥ መብት ተጠቃሚነት ይወስናል፣ የካሣ መጠኑንም አስልቶ ካሣና ሌሎች ተያያዥ መብቶችን ክፍያ ይከፈላል፡፡
ሠ/ ለሕዝብ ጥቅም እንዲለቀቅ በተወሰነው ቦታ ላይ ለሚገኝ ተነሺ ወይም ሕጋዊ ወኪል የሚገባውን የካሣ መጠን እና/ወይም ምትክ ቦታ ስፊትና አካባቢን ወይም ቤት በመግለጽ በጽሑፍ የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡
ረ/ የሚለቀቀው ይዞታ የመንግሥት ቤት የሰፈረበት ከሆነ የማስለቀቂያ ትዕዛዙ የሚደርሰው ቤቱን ለሚያስተዳድረው አካል እና ቤቱን ለተከራየው ሰው ይሆናል፡፡
ሰ/ ተነሺን ከቦታው ማስነሳት የሚችለው ለተነሺው ካሣ ከከፈለ እና ምትክ ቦታ ወይም ቤት ከሰጠ በኋላ መሆን አለበት፡፡
ሸ/ መሬት የማስለቀቅ ስርዓት ዝርዝር አፈጻጸሙ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ይወሰናል፡፡
2. ተነሺ ወይም ሕጋዊ ወኪል ባለመብትነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም ሠነድ በገጠርም ሆነ በከተማ መሬት የማስተዲደር በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል በሚያወጣው መርሐ-ግብር መሠረት ማቅረብ አለበት፡፡
3.ተነሺው የካሣ ግምት በጽሑፍ እንዲያውቅ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ፦
ሀ/ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሣ ካልተከፈለው በመሬቱ ላይ ከቋሚ ተክልና ግንባታ በስተቀር ሌሎች ሥራዎችን መስራት ይችላል።
ለ/ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሣ ካልተከፈለው በመሬቱ ላይ ማንኛውንም በፕላን የሚፈቀድ እና ቀጣይ የቦታውን የልማት ወጪ በመንግስት ላይ የማያዛባ ሥራ መስራት ይችላል፡፡
ሐ/ በዚህ ንዑስ አንቀጽ በፊደል ተራ “ሀ” እና “ለ” መሰረት የተሰራ ሥራ ወይም የተደረገ ለውጥ በካሣ ስላቱ ውስጥ እንዱገባ መደረግ አለበት፡፡
4. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ ትዕዛዙ በደረሰው በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ካሣ እና ምትክ ቦታ ወይም ቤት መውሰድ አለበት፡፡
5. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 መሠረት በተቀመጠ ጊዜ ገደብ ውስጥ የካሣ ክፍያውን ካልወሰደ በከተማው ወይም በወረዳው አስተዳደር ስም በሚከፈት ዝግ የባንክ ሂሳብ እንዲቀመጥለት ይደረጋል፡፡
6. ለባለይዞታ የሚሰጠው የመልቀቂያ የጊዜ ገደብ ካሣና ምትክ ቦታ ከተቀበለ ወይም ካሣው በዝግ ሂሳብ ከተቀመጠበት ቀን ጀምሮ ከ 120 (አንድ መቶ ሀያ) ቀናት መብለጥ የለበትም፡፡
7.በሚለቀቀው መሬት ላይ ሰብል፣ ቋሚ ተክል ወይም ቋሚ የሆነ ሌላ ንብረት ከሌለ ባለይዞታው የልማት ተነሽ ካሣ ከተከፈለው በኋላ በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ይዞታውን ለከተማ ወይም ለወረዳ አስተዳደር ማስረከብ አለበት፡፡
8. በሕገ-ወጥ መንገድ በተያዘ ቦታ ላይ ለሰፈረ ንብረት ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ ለ30 ቀናት የሚቆይ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ እንዲለቀቅ ይደረጋል፡፡
9. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ ወይም ባለንብረት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ እና (2) በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያለ በቂ ምክንያት መሬቱን ካላስረከበ የከተማ ወይም የወረዳ አስተዳደሩ መሬቱን በራሱ ይረከባል። አስፈሊጊም ሲሆን ለመረከብ የፖሊስ ኃይል ትብብር ሊጠይቅ ይችላል፡፡

5. #መሬት እንዲለቀቅለት የተወሰነለት አካል ኃላፊነት
መሬት እንዲለቀቅለት የተወሰነለት አካል ለሥራው የሚፈለገውን መሬት መጠንና የሚገኝበትን ትክክለኛ ስፍራ የሚያሳይ ውሳኔ የተሰጠበት ማስረጃ ቢያንስ ሥራው ከመጀመሩ ከአንድ ዓመት በፊት ለከተማው ወይም ለወረዳው አስተዳደር ማቅረብ አለበት፡፡
መሬቱ ለሕዝብ ጥቅም እንዱውል ሲወሰን የመሬት ይዞታቸውን እንዱለቁ ለሚደረጉ ባለይዞታዎች የሚከፈለውን ካሣ እና የመቋቋሚያ ድጋፍ ወጪ እንዱሸፌን ከተወሰነ ገንዘቡን ለከተማው ወይም ለወረዳው አስተዳደር ገቢ ያደርጋል፡፡
ገንዘቡ ገቢ ተደርጎ ለተነሺዎች ካልተከፈለ የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር መሬት አያስለቅቅም፡፡
6. #የአገልግልት መስመሮች ስለሚነሱበት ሥርዓት
የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር በሚለቀቀው መሬት በላይ ወይም በታች የአገልግልት መስመር መኖር አለመኖሩን የአገልግልት መሥመር ባለቤት ለሆኑ ተቋማት ምላሽ እንዱሰጡበት በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ አለበት፡፡
ጥያቄ የቀረበለት ተቋም ንብረት ካለው ለሚነሳው ንብረት ካሣ እውቅና ባለው ገለልተኛ ገማች በማስተመን ከነዝርዝር ማስረጃው ጥያቄው በደረሰው በ30 (ሰላሳ) ቀን ውስጥ በጽሑፍ ለጠያቂው አካል ይልካል፡፡
የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳዳር ግምቱ በደረሰው በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ለባለንብረቱ የንብረቱን ግምት ካሣ ይከፈላል፡፡
የአገልግልት መስመሩ ባለቤት ክፍያው በተፈጸመለት በ60 (ስልሳ) ቀናት ውስጥ ካሣ የተከፈለበትን የአገልግልት መስመር አጠናቆ ማንሳትና መሬቱን መልቀቅ አለበት፡፡
የአገልግልት መስመሩ ባለቤት ክፍያው በተፈፀመ በ120 (አንድ መቶ ሀያ) ቀናት ውስጥ ውስብስብነት ያላቸውን የመሰረተ ልማት መስመሮች አጠናቆ ማንሳትና መሬቱን መልቀቅ አለበት፡፡
በዚህ በላይ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ልማቱ ካልተነሳ በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 9 መሰረት በማስነሳት ይዞታው የሚወሰድ ሲሆን በወቅቱ ተገቢውን ስራ ያልተወጣ የመሰረተ ልማት ተቋም ለሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
©℗®

https://t.me/Consultancy2012
Call us for
©Tsegaye Demeke - Lawyer

Photos from Bita woreda women children snd youth affairs office's post 14/03/2023

"እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ" በሚል መሪ ቃል በአለም ለ112ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ47ኛ ጊዜ የሚከበረው አለማቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በቢጣ ወረዳ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋራ ዉይይት ተካሂዷል

29/07/2022

በረከታቸው ይደርብን በፁዕ አቡነ ጴጥሮስ!

29/07/2022

#እሰይይይ እልልልል የተዋህዶ ልጆች

#እንኳን አደረሳችሁ

29/07/2022

ሐምሌ 22
👉 በነጎድጓድና በመባርቅት ላይ ለተሾመ ለመልአኩ ለቅዱስ #ዑራኤል አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉በመላእክት ከተማ በራማ ካሉት ሦስት ነገዶች ዉስጥ አንዱ ነገድ ሥልጣናት ይባላል፡፡ በሥልጣናት ላይ ከተሾሙ ሊቃነ መላእክት ዉስጥ አንዱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሱርያል ይባላል፡፡ሱርያል የሚለዉ ስም በአንዳንድ ድርሳናት ካልሆነ በስተቀር እምብዛም አይታወቅም ትርጉሙም ‹‹‹ዐለቴ እግዚአብሔር ነዉ››› ማለት ነዉ፡፡ ሱርያል የቅዱስ ዑራኤል ሌላ ስሙ ነዉ፡፡ ዑራኤል ማለት ‹‹‹እግዚአብሔር ብርሃን ነዉ›››ማለት ነዉ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም በስፋት የሚተወቀዉ ስም ዑራኤል የሚለዉ ስም ነዉ፡፡/ድርሳነ ዑራኤል 1991 ገጽ 14/ በመጽሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ስለ ቅዱስ ዑራኤል በስፋት የምናገኘዉ በመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ነዉ፡፡
👉ዕዝራን ይራዳዉ የነበረ ፤ለዕዝራም ጠፍተው የነበሩ የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን እንደ ገና እንዲጽፋቸዉ ጽዋ ልቦና አጠጥቶ ምሥጢር የገለጠ ቅዱስ ዑራኤል ነዉ፡፡(ዕዝ ሱቱ2 )፡፡
‹‹‹በመብረቅና በነጎድጓድም ላይ የተሾመ ታላቅ መላክ ነዉ››››ሄኖክ 6፡2
👉ምሥጢረ ሰማይም ለሄኖክ ያሳየዉ ዕዉቀትን የገለጠለት እርሱ ቅዱስ ዑራኤል መሆኑን ጽፏል፡፡(ሄኖክ 28፡13-14)፡፡
👉እመቤታችንም በኪደተ እግርዋ ኢትዮጵያን በዞረች ጊዜ ቅዱስ ዑራኤል ያገለግላት እንደነበርና እንዳስጎበኛትም በድርሳነ ዑራኤል ተጽፏል ፡፡
👉ለአዳም የድህነትን ዜና የነገረዉ ቅዱስ ዑራኤል ነዉ ዮሴፍን ብርታት ሰጥቶ ከብእሲት ጲጥፋራ ያዳነዉ ቅዱስ ዑራኤል ነዉ ለእዝራ ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነዉ የሚያረጋጋ ለኃጢያተኞች ምህረት የሚለምን መልአክ ነዉ፡፡(ስንክሳር ጥር)
👉ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በሐይቅ እስጢፋኖስ ለገዳሙ መነኮሳት እህል እየፈጨ ዉሃ እየቀዳ እመቤታችንን እየተማጸነ ሲኖር አንድ ቀን ከሥዕሏ ሥር እየሰገደ ሳለ መልአኩ ዑራኤል ተገልጦ ጽዋህ ልቦና አጠጣዉ፡፡ከዚያ ጀምሮ ምሥጢረ ሰማይ ወምድር ተገልጦለት ከ 40 በላይ መጻህፍትን ደርሷል፡፡ (መጽሐፈ አርጋኖን )
👉 በእለተ ስቅለት የጌታ ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎ በዓለም የረጨ ቅዱስ ዑራኤል ነው
👉ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትእና እዝራ ሱቱኤልን የእውቀት ጽዋ ያጠጣበት ነው በአምላኩ አማላጅነቱን ኑና ተማጸኑት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እርሩህ መልአክ ነው። አሁንም ይህ ዓለም በአማላጅነቱ አምኖ ጸበሉን ቢጠጣ ከክፉ በሽታ እንደሚፈወሱ ቃለ ኪዳን ተሰጥቶታል፣በፍጹም መጠበቅን ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን አምላካችን ክብርና ምስጋን አምልኮትና ውዳሴ ይድረሰውና ይህን ታላቅ መልዕክ በችሎታችን መጠን እንድናመሰግን ና እንድናገለግል እግዚአብሔር ይርዳን አምላክ ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ከመልዐኩ ከቅዱስ ዑራኤል በረከት ረድኤት ያሳትፈን፡፡
👉ለእዝራ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ዕዉቀትን የገለጸ መልአክ ለኛም ይለመነን "አሜን"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

18/05/2022

✴️✳️ የለውዝ /ኦቾሎኒ/19 የጤና በረከቶች ✳️✴️

✅ ለውዝ ወይም ኦቾሎኒ ከ1,6ዐዐ ዓመት በፊት በፔሩ የተገኘ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከዛም በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት ላይ ተሠራጭቶ በዓለም ታዋቂ ሆኗል፡፡ ለውዝ ከምግብነት ባሻገር ለጤናም ሰፊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገራል፡፡ እነዚህን ጠቀሜታዎች በዝርዝር አስቀምጠናል እንሆ…

1. በተለምዶ ከሚባለው ጋር በተዛመደ መልኩ በዕርግጥም ለውዝ ለተዋልዶ ስርዓት ጤንነት ተመራጭ ነው፡፡ በተለይም ከእርግዝና በፊትና በዕርግዝና ወቅት ለውዝ መመገብ በውስጡ የሚገኘው ፎሊክ አሲድ በእርግዝና ወቅት በጽንሱ ዕድገት ላይ ሊያጋጥም የሚችለውን ችግር 70 በመቶ ያህል ያስወግዳል፡፡

2. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላል – በለውዝ ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚገኘው ማንጋኒዝ ለስብና ለካርቦሀይድሬት መፈጨት፣ ለካልሲየም በሰውነታችን ህዋሳት መዋሀድና በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን የተስተካከለ እንዲሆን ያስችላል፡፡

3. በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ጥሩው ኮልስትሮል እንዲጨምርና መጥፎው የኮልስትሮል ዓይነት ደግሞ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ በለውዝ ውስጥ የሚገኘው የመዳብ ማዕድን ሰውነታችን በልብ ህመም እንዳይጠቃ ይከላከላል፡፡

4. የሐሞት ጠጠር እንዳይከሰትና የሐሞት ከረጢት ጤናን ያስጠብቃል፡፡

5. ድብርትን ይከላከላል፡፡

6. የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፡፡

7. የልብ ህመም፣ ካንሰርን፣ የነርቭ ህመሞችን እንዲሁም ከቫይረስና ከፈንገስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎችን ይከላከላል፡፡

8. የአእምሮ ብቃትን ከመጨመርም በተጨማሪ እንደ ፓርኪንሰንና አልዛይመር ዓይነት በሽታዎች እንዳይከሰቱ
ይረዳል፡፡

9. በካንሰር መጠቃትን ይቀንሳል፡፡

10. ሐይል ሰጪ ከመሆኑም በላይ ጥቂት በልተው ለረጅም ሰዓታት እንዳይርቦት ስለሚያደርግ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

11. በእርግዝና ወቅት ለውዝ መመገብ የሚወለዱ ህጻናት እንደ አስም በመሳሰሉት በሽታዎች እንዳይጠቁ ያደርጋል፡፡

12. ለታዳጊዎች የአካል ግንባታ ለውዝ እጅጉን ተመራጭ ነው፡፡

13. በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡

14. የጸጉር ስሮችን በማጠንከር ለጸጉር ጤንነት ተመራጭነው፡፡

15. ስትሮክ የሚሰኘውን ወደ አንጎል በሚሄደው የደም ፍሰት መዛባት ሳቢያ የሚከሰተውን የአንጎል ላይ አደጋ ይከላከላል።

16. ፍሪ ራዲካል በተሰኙት ሞሎክዩሎች ሳቢያ በሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ይቀንሳል።

17. እብጠትና ሌሎችን ከቆዳ ጋር የተያያዙ ህመሞችን ይከላከላል። ቆዳን ከውስጥ በማለስለስ የተለያዩ የቆዳ ችግሮችን ይከላከላል።

18. ለውዝ በተለያዩ የቫይታሚን ዓይነቶች የበለጸገ ነው።

19. ለውዝ በፖታሲየም፣ ማንጋኒዝ፣ መዳብ፣ ካልሲየም፣ ማግኒዚየም፣ ብረት፣ ሴሬኒየም እና ዚንክ በመሳሰሉት ማዕድናት የበለጸገ ነው። ቡናን መጠጣት ከጤና አኳያ
ያለው ጠቀሜታ፡-
– የማስታወስ አቅምን ይጨምራል
– ድብርትን ያስወግዳል
– ለራስ ምታት እና አስም ፍቱን ነው
– በኩላሊት ጠጠር እንዳንጠቃ ይከላከላል
– ጉበታችን እንዳይታወክ ይከላከልልናል
– በሰውነታችን ላይ በስራ ብዛት የሚፈጠሩ ህመሞች እንዳንጠቃ ይረዳል
– ለድንገተኛ ሞት የሚያበቃ የልብ በሽታ እንዳንጠቃ ይጠብቃል
– በስኳር በሽታ ከመያዝ ይከላከላል
– በነቀርሳ በሽታ እንዳንያዝ ይረዳል

ምርጥ መጣጥፎች
ሼርርርር

18/05/2022

ቅድስ ስላሴ
እናምናለን
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብለን
የስላሴ ረድኤት በረከት አይለየን
ሀገራችንን ሰላም ያድርጉልን
የአብረሀምን ቤት የጎበኙ የኛንም ቤት ይጎብኙልን

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Bita
Addis Ababa