31/03/2026
Lemi Kura woreda 10 Communication
Lemi Kura Woreda 10 Communication
31/03/2026
31/03/2026
31/03/2026
ፈተናን ወደ ዕድል የቀየረ የዲፕሎማሲ ከፍታ፦ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት ስምንት ዓመታት የተከተለው ንቁና ስልታዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ የሀገራችንን የውጭ ግንኙነት ለዘመናት በተዛባ መልኩ ይዞት ከነበረው “በጠላቶች የመከበብ እይታ” በማላቀቅ ለላቀ ዓለም አቀፋዊ ከፍታ የሚመጥን መሠረት ጥሏል።
በዚህም "ቅድሚያ ለጎረቤት" የሚለው መርህ ከቃላት ባለፈ በተግባራዊ ዲፕሎማሲ በመተርጎሙ ቀጣናዊ ግንኙነታችን ከጥርጣሬ አጥር ወጥቶ ወደ ጽኑ ስልታዊ አጋርነት ተሸጋግሯል።
የለውጡ መንግሥት የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ዋነኛ መለኪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ነው። ሀገራችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የራሷን የሉዓላዊነትና የልማት ፍላጎት ማዕከል ያደረገ የውጭ ግንኙነት መርህን ስትከተል ቆይታለች።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሙንን ዓለም አቀፍ ጫናዎች በብቃት በመቋቋም እና የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶችን በማጠናከር እንደ BRICS አባልነት ያሉ የሀገራዊ ክብራችን ማሳያ የሆኑ ስኬቶችን አስመዝግበናል።
ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነትና የውሳኔ ሰጪነት ዐቅም በተግባር ያረጋገጠ ነው።
ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ የትስስር ማዕከል በመሆን በታዳሽ ኃይል፣ በመንገድ፣ በመጠጥ ውሃ እና በባቡር መሠረተ ልማቶች የቀጣናውን ሀገራት ዕጣ-ፈንታ ከራሷ ጋር አስተሳስራለች። ይህ የጋራ ዕድገት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ምሰሶ ብቻ ሳይሆን፣ የማይበገርና መሪ ቀጣናዊ ኃይል እንድትሆን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል።
ዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ አቅጣጫችን የመንግሥታችን ሕዝባዊ ወገንተኝነትና ጽኑ ቁርጠኝነት መገለጫ ነው። ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆ በህጋዊ መንገድ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እንዲሆን ከማድረግ ጀምሮ በተለያየ መንገድ ከሀገር የወጡና ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ዜጎችን ወደ እናት ሀገራቸው ለመመለስ የተከናወኑ ተግባራት መንግሥት ለሕዝቡ ያለውን አለኝታነት ያሳዩና በዜጎች ዘንድ የላቀ ብሔራዊ ኩራትና መተማመንን የፈጠሩ ታሪካዊ ክስተቶች ናቸው።
በዓለም ዲፕሎማሲያዊ መድረኮች ተፅዕኖዋ እየጎላ እና ጥንካሬዋ እየጎለበተ የመጣው ሀገራችን አሁንም የፓን አፍሪካኒዝም ማማና የፅናት ተምሳሌት መሆኗን ለዓለም በድጋሚ ያረጋገጠ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ተገኝታለች።
ባለፉት ስምንት ዓመታት እንደሀገር የተመዘገቡት ስልታዊ የዲፕሎማሲ ድሎች የኢትዮጵያን ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ወደ ላቀ ከፍታ አሸጋግረውታል። ዛሬ ሀገራችን በውጭ ግንኙነቷ የምትታወቀው ድጋፍ በመጠየቅ ሳይሆን የቀጣናዊ አጀንዳዎች ምንጭና የመፍትሔ አካል በመሆን ነው። ይህ አዲስ ገጽታችንና እየተገነባ ያለው ብሔራዊ ኩራት ለሚገጥሙን ማናቸውም ጫናዎች እንዳንበረከክ አቅምና የልማት ጉልበት ሆኖናል።
የድላችን ጉዞ አይቆምም! ዜጎች ለተገኘው ውጤት ጠባቂ ለቀጣዩ ስኬት ደግሞ ባለቤት እንዲሆኑ መንግሥት ጥሪ ያቀርባል።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
31/03/2026
31/03/2026
በወረዳው የተከናወኑ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታዎች የነዋሪዎችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እየመለሱ መሆኑ ተገለጸ
ለሚ ኩራ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን
መጋቢት 22/2018ዓ.ም
በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች ሲከናወኑ የቆዩ የውስጥ ለውስጥ የኮብልስቶን ንጣፍ ስራዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ተከትሎ፣ ነዋሪዎች በተከናወነው መሠረተ ልማት መደሰታቸውን ገለጹ። ይህ የልማት ስራ መንግስት የህዝቡን የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየዘረጋቸው ካሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑ ተጠቁሟል።
ከዚህ ቀደም በክረምት ጭቃ፣ በበጋ ደግሞ አቧራ ይፈታተናቸው እንደነበር የሚያስታውሱት የአካባቢው ነዋሪዎች፤ አሁን የተነጠፈው የኮብልስቶን መንገድ የአካባቢውን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎችም ፦
"ቀደም ሲል መንገዱ ለትራንስፖርትም ሆነ ለእግረኛ በጣም አስቸጋሪ እና ዝናብ በዘነበ ቁጥር አካባቢው ላይ ጨቃ በመሆኑ በተለይ ለህፃናትና ለአረጋውያን ትልቅ ፈተና ነበር። አሁን ግን መንግስት ጥያቄያችንን ሰምቶ ይህንን የኮብልስቶን ንጣፍ ከነዋሪው ጋር ልማቱን በማከናወኑ አካባቢያችን ጽዱ ሆኗል፤ እንቅስቃሴያችንም ተመቻችቷል" ብለዋል።
ሌው ነዋሪ በበኩላቸው፣ የልማት ስራው በመንግስትና በህዝብ ትብብር የተሳካ ውጤት የታየበት መሆኑን ጠቅሰው፣ የተገነባውን መሠረተ ልማት እንዳይጎዳናበ እንዳይበላሽ መንከባከብ ረገድ ሁሉም ነዋሪዎች ድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
መንግስት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በተለይም በከተማ ውስጥ የሚታዩ የመሠረተ ልማት ክፍተቶችን ለመሙላት በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር አካላት የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የፍሳሽ ማስወገጃዎችን በመገንባትና የአካባቢ ውበትን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሱ ይገኛሉ።
ይህ የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ የወረዳውን ነዋሪዎች ጥያቄ ከማቀለል በላይ፣ ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ረገድም የራሱ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በቀጣይም በወረዳው መሰል የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በዕቅድ እየተሰራ መሆኑን ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለተጨማሪ መረጃ
1.tiktok.com/.kura.worda.10
2.https://chat.whatsapp.com/HVRWtHveiUcLBfYcW58KXk?mode=gi_t
3.https://t.me/lemikuraworeda10
4.https://www.youtube.com
5.https://www.instagram.com/lk_werda_10_communication?igsh=dWNzc3dsZ21icnk0
ለአስተያየትና ጥቆማ 👇
https://forms.gle/G25er1c3DDdDx7R5A
29/03/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Lemi Kura Werda10 Meri Babur Tabiya
Addis Ababa
