25/08/2022
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች ይህንን ይመስላል።
To see UA significantly contribute to household food security, income generation, job creation and b
25/08/2022
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች ይህንን ይመስላል።
09/06/2022
የጉለሌ ክፍለ ከተማ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ‹‹ ምግባችን ከደጃችን ፣ ጤናችን በእጃችን ›› በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ለሚገኘው የከተማ ግብርና ለማስፋፋት በሚደረገው ስራ በጓሮ አትክልት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሄዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪ ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደገለጹት በመንግስት ደረጃ ታቅዶ በስፋት እየተሰራበት የሚገኘው የከተማ ግብርና አንድም መሬት ጾም ማደር የለበትም በማለት የጓሮ አትክልትን ህብረተሰቡ በቀላል እንዲያመርት በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆን የራሱን ምግብ ከደጁ በማግኘት የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ በላይ የገቢ ምንጭ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አጸደ በቀለ በበኩላቸው ህብረተሰቡ የጓሮ አትክልትን ባለው ቦታ በማምረት እና በመጠቀም የዋጋ ንረትን በማስወገድ ጤናማ የአመጋገብ ስርዓትን በመከተል ውጤታማ እንዲሆን እየተሰራ እንዳለ ተናግረዋል ፡፡
በክፍለ ከተማው በተዘጋጀው ቦታ ላይ የጓሮ አትክልቶችን የተተከለ ሲሆን ከተለያዩ ማህበራት የመጡ የከተማ ግብርና ስራቸውን የማስተዋወቅና የግብይይት ስራ አከናውነዋል፡፡
26/05/2022
በከተማችን ያለውን የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የከተማ ግብርና ስራ በግልና በተቋማት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 እና 2 ያሉ ነዋሪዎች በከተማ ግብርና ስራ በተፈጠረለት ግንዛቤ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ተገለጸ
‹‹ምግባችን ከጓሯችን ››በሚል መሪ ቃል በሀገር ደረጃ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል በተጀመረው ተግባር ማህበረሰቡም ሆነ የተለያዩ ተቋማት ባላቸው ክፍት ቦታዎች ላይ የጓሮ አትክልቶችን በመትከል ፣ የምርት እጥረትን በመቀነስ እና ገበያውን በማረጋጋት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
በክ/ከተማው ሁሉም ወረዳዎች በትኩረት እየተሰራ ያለው የከተማ ግብርና ስራ የማህበረሰቡን የኑሮ ውድነት የሚያቃልሉና ጤናማ የአመጋገብ ስርዓትን በመፍጠር እንዲሁም የምግብ እጥረት ችግሮችን ከመቅረፍ አኳያ ያለው ፋይዳ ከፍ ያለ ነው።
19/05/2022
13/05/2022
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የ2014 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡
ጽ/ቤቱ ባለፉት 9 ወራት የከተማና የከተማ ዙሪያ ግብርናን በማስፋፋት፣ በማጠናከር እና በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን መቻሉን ገልጿል፡፡
ባለፉት 9 ወራት የከተማ ግብርና በከተማ ውስጥ እና በዙሪያው በአነስተኛ ቦታ በዘመናዊ አሠራር ለምግብና ለሌሎች ጠቀሜታዎች የሚውሉ እጽዋትን የማልማት፤ እንስሳትን የማርባት፤ ለግብርና ሥራ የሚያገለግሉ የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችን የማምረት፤ የማቅረብ እና የግብርና ምርት ውጤቶችን የማቀነባበር ሥራን ለነዋሪዎች ግንዛቤ የመፍጠር፣የማሰልጠንና ወደ ስራ እንዲገቡ ከማድረግ ባለፈ ድጋፍና ክትትል የማድረግ ተግባራት ተከናውነዋል ተብሏል፡፡
በእቅድ ውይይቱ ላይ የተገኙት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ አጸደ በቀለ ባለፉት 9 ወራት በከተማ ግብርና ዘርፍ ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች አጠናክሮ በማስቀጠልና በንቅናቄ የሚሰሩ ስራዎችን በማጠናከርና በቀሪ ወራት በክፍተቶች ላይ የጋራ ርብርብ በማድረግ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ጽ/ቤቱ በከተማ ግብርና ዘርፍ ባለፉት 9 ወራት ባከናወናቸው ተግባራት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የምስክር ወረቀት አበርክቶላቸዋል፡፡
03/05/2022
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የጓሮ አትክልት ልማት ተሞክሮውን አጋራ
**********************
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የጓሮ አትክልት ልማት ተሞክሮውን በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አጋራ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለምፀሐይ ጳዉሎስ እንደገለጹት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚለሙ የደ የጓሮ አትክልቶችን በማስጎብኘት እንዴት በአነስተኛ ቦታ እና ጠባብ ግቢ እንደ ቆስጣ፣ሰላጠና ጎመን ያሉ አትክልቶችን ማልማት እንደሚቻል ልምድ ማካፈል ተችሏል።
በጉብኝቱናንየልምድ ልውውጡ ላይ የተካፈሉ እናቶችም ይህን ልምድ ወስደው አትክልቶችን በትንሽ ቦታ ተክለውና ተንከባክበው በማሳደግ መጠቀም እንዲችሉ ያግዛል ብለዋል ሚኒስትር ድኤታዋ።
በእለቱ በጉብኝቱ ለተሳተፉ 55 እናቶች በግቢው ውስጥ ለምተው የደረሱ አትክልቶችን እንዲጋሩ መደረጉንም ወይዘሮ አለምጸሀይ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያለንን ተካፍለን እርስ በእርስ ተሳስበን እንኖር ያሉትን ጥሪ ተክትሎ ጸህፈት ቤቱ በግቢው ውስጥ ያለማቸውን የተለያዩ አትክልቶች ለእናቶች ማጋራቱንና ችግኞችን መስጠቱንም ሚኒስትር ድኤታዋ ተናግረዋል፡፡
(ኢ.ፕ.ድ)
28/04/2022
የአረንጓዴ ዐሻራ ጥረታችን የግብርና ምርታማነትን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲቻል በርካታና ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ነው ተባለ፡፡
ጉለሌ ወረዳ 9ኮሙኒኬሽን 20፣2014
በዛሬው ዕለት በክፍለ ከተማ የሱፐርቪዥን ብድን በወረዳው ተገኙተዉ ምልከታ አድረገዋል፡፡
የአፈርና ውኃ ጥምረት ለግብርና ምርታማነት ወሳኝ ነው:: እንደ ሀገር ለውኃ እና ለአፈር አያያዝ አሠራሮቻችን ትኩረት ሰጥተን መሥራት አስፈላጊ ነው ያሉት የወረዳው የከተማው ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ማርታ አበበ ተናግረዋል፡፡
14/04/2022
ምግባችን ከደጃችን በሚለው መሪ ቃል የከተማ ግብርና ንቅናቄን መነሻ በማድረግ የክላስተር 10 የብሎክ 31 ነዋሪ አቶ ይልማ ገብረወልድ ጥሩ ውጤት እያሱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
ጉለሌ ወረዳ 7 ኮሙኒኬሽን ሚያዚያ 06፣ 2014
በጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 7 አስተዳደር በክላስተር 10 ብሎክ 31 ነዋሪ የሆኑት አቶ ይልማ ገብረወልደ በክላስተሩ አመራር በተፈጠረላቸው ግንዛቤ መሰረት ባላቸው ቦታ በመጠቀም የጓሮ አትክል በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የሚከሰተውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋምና የምግብ ፍጆታን ከደጅ ለማግኘት ህብረተሰቡ ባለው ቦታ ሁሉ በከተማ ግብርና የጓሮ አትክልትን በማልማት ምግባችን ከደጃችን የሚለውን ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት ያወረዳውን አቅጣጫ በመከተል የክላስተሩ አመራር ከነዋሪው ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ አቶ ይልማ ባላቸው ቦታ የጓሮ አትክልትን በማልማት አበረታች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡
13/04/2022
ተቋማት የተጀመረው የከተማ ግብርና ስራ ተደረሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ተገለጸ፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ በክፍለ ከተማው በሚገኙ የተለያዩ ተቋማት እየተሰሩ ያሉ የአትክልት ልማት ንቅናቄ ስራዎችን ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
አስተባባሪ ኮሚቴው በክፍለ ከተማው በሚገኙ የተለያዩ የመንግስት፣የግል እና የሃይማኖት ተቋማት " ምግባችን በደጃችን"የጓሮ አትክልት ልማት የንቅናቄ መርሃ ግብር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል፡፡
በምልከታው የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ በተቋማት ውስጥ ያሉ ባዶ ቦታዎቸን በአግባቡ በመጠቀምና የሽቅብ ግብርናን (vertical farming) በመተግበር የኑሮ ውድነትን ማቃለልና ሁሉም ተቋም ሰራተኞቹን በማስተባበር የጓሮ አትልክት ፍላጎቱን እንዲሸፍን በማድረግ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች በሁሉም ተቋማት ጥሩ ጅማሮ ቢኖርም በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ ግን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ "ምግባችን በደጃችን"የጓሮ አትክልት ልማት የንቅናቄ መርሃ ግብር በተሰራው የተቀናጀ ስራ 159 የተለያዩ ተቋማት ያላቸውን ቦታዎች በመጠቀም ወደ ተግባር በመግባት በመስራት ላይ መሆኑን የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አጸደ በቀለ ገልጸዋል፡፡
16/03/2022
16/03/2022
የጉለሌ ክ/ከተማ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ከከተማ ከመጡ ሱፐርኺዥን ቲም ጋር የመሰክ ምልከታ እና ት/ቤቶችን ለቀጣይ ሰልጠነው ለሚወጡ ሰልጣኞች የቦታ ቅድመ ዝግጀት መዘጋጀቱን ምልከታ አደረገ