የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት

Share

It's a governmental organization which works on women's,children's and gender equalities issues.

30/05/2026

አፋልጉኝ 👇👇

ተፈላጊዋ ዩስራ ሐ/ጀማል አመደሌ ትባላለች በቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ገደባ ቀጠና ሜጦማ ቀበሌ ftc አካባቢ በዛሬው ዕለት ግንቦት 22/2018 ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ በወቅቱ ብጫ ሹራብና ጥቁር ጉርድ ለብሳ ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም።

ተፈላጊዋን ያየ ወይም ያለችበትን ለጠቆመን ወረታ ከፋይ ነን ይላሉ ቤተሰቦቿ ።

ስልክ

0928700953
0985091660
0977878477

Photos from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት's post 26/05/2026

ብልፅግና ፓርቲ ከለውጡ ወዲህ በሁሉም ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ፓርቲ እንደሆነ ተገለፀ

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የሁሉም ማህበራዊ መሰረት የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት ደማቅ ቅስቀሳ መርሐግብር አካሂዷል።

በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ክብርት መነቴ ሙንድኖ በምርጫው ቀን ሁሉም መራጭ ከሌሊቱ 12:00 ጀምሮ በጋራ ወጥቶ ለፓርቲው ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

የሀላባ ህዝብ በሁሉም የልማት ተሳትፎ በአንድነት ተሳትፎ አድርጎ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደቻለና በዚህ ምርጫም ህዝቡ በጋራ ወጥቶ ፓርቲውን በመምረጥ አንድነቱን እንደሚያሳይ እምነታቸው መሆኑን አስረድተዋል።

የሀላባ ዞን ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሐመድከማል ኑርዬ ብልፅግና ፓርቲ አካታች ፓርቲ ነው ያሉ ሲሆን የመደመር ዕሳቤን በማንገብ አካታችነትን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዞናችን ከለውጡ ወዲህ በርካታ የልማት ስራዎች እንደተከናወኑና በዚህም ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን አብራርተዋል ።

ፓርቲው ባለሀብቶችን እንደሚያበረታታ ጠቁመው በሀላባ ዞንም ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች እንዲሰማሩ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠሩንና በባለሀብቶችም በኩል አበራታች ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አ/መጂድ ፊጣሞ ፓርቲው በማህበራዊ በኢኮኖሚያዊና በፖሎቲካዊ ዘርፎች በርካታ የልማት ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ መሆኑን ገልፀው የማዕድ ማጋራት፣ ቤት በማደስና በመገንባት እንደሆነ ገልፀው የተማሪዎች የምገባና የኮሪደር ልማት ስራዎችም በትኩረት እንደተሰራ አብራርተዋል።
ሀላባ ቲቭ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

Photos from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት's post 25/05/2026

ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!!

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ቀበሌዎች የብልጽግና ፓርቲ አባላት በነዋሪውና በአርሶ አደር ግንባር የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ።

‎ብልጽግናን መምረጥ የሰላምን፣ የዲሞክራሲን እና የልማትን ቀጣይነት ማረጋገጥ ነው።

‎ ፓርቲያችን ሀገራዊ ከፍታን እና የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል።

‎ መጪው ጊዜ ከብልፅግና ጋር ብሩህ ነው!!

‎መጪው ጊዜ የብልፅግና እና የከፍታ ነው!!

‎የምርጫ ምልክታችን የሆነውን የስንዴ ነዶን በመምረጥ የኢትዮጵያን እና የከተማችንን የብልጽግና ጉዞ እናፋጥን!

‎ ብልጽግናን መምረጥ የኢትዮጵያን ከፍታ ማረጋገጥ ነው!!

‎ የአብሮነት እና የዕድገት ምልክት የሆነውን ስንዴ ነዶን ይምረጡ!


የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ.ጽ.ቤት

Photos from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት's post 25/05/2026

7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ቀበሌዎች በነዋሪው ግንባር የብልጽግና የፓርቲ አባላት በቤተሰብ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር እያካሄዱ ይገኛል።

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር 7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ በሁሉም ቀበሌዎች በነዋሪው ግንባር የብልጽግና የፓርቲ አባላት በቤተሰብ ደረጃ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር እያካሄዱ ነዉ።

‎ የፓርቲያቸውን የምርጫ ምልክት የሆነዉን የስንዴ ነዶ በቤተሰብ ደረጃ በማስተዋወቅ ብልጽግና የሰላምና የዲሞክራሲ ቀጣይነትን ለመምረጥ አባላት ቃል ገብተዋል።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከተማ ግብርና ጽ/ቤት

Photos from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት's post 22/05/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የጎዳና ላይ የማስተዋወቅ ስራ ተካሄ።

‎የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር (የአስተዳደርና ማህበራዊ ዘርፍ) የብልጽግና ህብረት አባላት የተሳተፉበት ሰፊ የምርጫ ቅስቀሳና የቡና ጠጡ ፕሮግራም ተካሂዷል።

‎በመርሃ-ግብሩ ላይ የፓርቲው የምርጫ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ የማስተዋወቅ ስራ በስፋት የተሰራ ሲሆን፣ ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡ የብልጽግና ትሩፋቶችም ለህዝቡ ይፋ ሆነዋል።

‎የፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር የፓርቲው አባላትና የመንደር 39 ነዋሪዎች በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በመዟዟር ባደረጉት የቅስቀሳ ስራ፣ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች በመጪው ግንቦት 24 በሚካሄደው ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የሆነውን "የስንዴ ነዶ" በስፋት ማስተዋወቅ ስራም ተሰርቷል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” የማድረስ ታላቅ ራዕይን ለማሳካት እያንዳንዱ አባል የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበትና ለብልጽግና ፓርቲ ድምፃቸውን እንድሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

‎የአባላቶቻችንና የአመራሮቻችን ንቁ ተሳትፎ ፍትሐዊ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫን በማሳካት የብልጸግና ጉዟችንን ይበልጥ ያፋጥነዋል ብሏል።

‎ምርጫችን ብልጽግና
‎ምልክታችን የስንዴ ነዶ
‎ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ.ጽ.ቤት

Photos from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት's post 19/05/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት 4ተኛ ዙር ሞዴል ቀጠና እቅድ ክንውን ግምገማ መድረክ አካሄዱ

==========
ግንቦት 11/2018
ሀላባ ቁሊቶ

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ አብደላ 4ተኛ ዙር ሞዴል ቀጠና እቅድ ክንውን ግምገማ መድረክ አካሄደዋል ።

‎በግምገማ መድረኩ ላይ ሞዴል ቀጠናዎች ላይ የተሰሩ ስራዎች የደረሱበት ሁኔታ በቡድን መሪው ቀርቦ ተገምግሟል::

‎4ተኛ ዙር ሞዴል ቀጠና ፣የሴቶች የቁጠባ ላይ፣ በሴቶች ልማት ህብረት ላይ እንዲሁም በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል ።

‎በመድረኩ ላይ የጽ/ቤቱ ማኔጅመንት አካላት ባለሙያ እና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተዋል::


የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት

▶በ Facebook https://www.facebook.com/100076971182266/posts/app=fbl ላይ ይከታተሉን
▶በቴሌግራም በ https://t.me/womensandchildrensaffairsoffice ላይ ይከታተሉን !!

Photos from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት's post 18/05/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት የስራ ስነ-ምግባር እና የሞራል እሴቶች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
==========
ግንቦት 10/2018
ሀላባ ቁሊቶ

በመድረኩ ላይ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ አብደላ አንድ ተቋም ስኬታማና ተወዳዳሪ ሊሆን የሚችለው በዕውቀትና በክህሎት የበለፀገ የሰው ኃይል ሲኖረው ብቻ ሳይሆን፣ ጠንካራ የስራ ስነ-ምግባርና የማይናወጥ የሞራል እሴት ሲገነባ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ስነምግባር ኦፊሰር ሸ/ፈቱ ሸ/ሙሽኬ የስልጠናው ዋና ዓላማ፦ ሙያዊ ኃላፊነትን በታማኝነት መወጣት፣ የስራ ቦታ ግንኙነቶችን ማጠናከር እና የተቋማችንን መልካም ስም ለማስጠበቅ እንደሆነ ተናግረዋል።

​በመሆኑም፣ በዕለታዊ የስራ እንቅስቃሴያችን ውስጥ ግልፅነትን፣ ታማኝነትን፣ እርስ በርስ መከባበርንና ተጠያቂነትን ይበልጥ ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ "የስራ ስነ-ምግባር እና የሞራል እሴቶች" የዓቅም ግንባታ ስልጠና ተዘጋጅቷል።

ከሰልጠናው ተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል::
ይህ ስልጠና ከተራ የስራ መመሪያዎች ትንተና ባለፈ፣ በየቀኑ በምናከናውናቸው ተግባራት ውስጥ ታማኝነት፣ ግልፅነት፣ እርስ በርስ መከባበር እና ተጠያቂነት ምን ያህል ወሳኝ መሆናቸውን በጥልቀት እንድንገነዘብ አድርጎናል። በስራ ቦታ የሚያጋጥሙንን የሞራል ፈተናዎች እና ጥቅምና ግጭቶችን በስነ-ምግባር የታነፀ ውሳኔ እንዴት መፍታት እንደምንችልበት ትልቅ አቅም አግኝተንበታል ሲሉ ተሳታፊዎች በውይይት ወቅት ሀሳባቸውን ተሰጥተዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት

▶በ Facebook https://www.facebook.com/100076971182266/posts/app=fbl ላይ ይከታተሉን
▶በቴሌግራም በ https://t.me/womensandchildrensaffairsoffice ላይ ይከታተሉን !!

Photos from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት's post 15/05/2026

ሴቶችና ምርጫ ቡና ጠጡ ፕሮግራም በዞቤቻሜ ቀበሌ በሙራሳ በር ቀጠና ተካሂዷል።
============
ሀላባ ቁሊቶ
ግንቦት 07/09/2018 ዓ/ም

ፕሮግራሙ በዋነኝነት ሴቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አንድነትና ተሳትፎ ለማጠናከር ያለመ እንደሆነና 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ እንዲሆን የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ለማድረግ መሆኑን የዞቤቻሜ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ተናግረዋል።

የዞቤቻሜ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሰይፉ ፓርቲው ሴቶች ላይ ያለው አመኔታ የላቀ ነው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለሀገር በርካታ እድል ጭምር የሚፈጥር በመሆኑ ሴቶች ነቅተው መሳተፍ እንዳለባቸው ጠቁመዋል ።

ሴቶች የአንድ ሀገር ግንባታ መሰረት በመሆናቸው ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅና የዴሞክራሲ ስርዓቱ እንዲሰርፅ የሚያደርጉት ጥረት የላቀ እንደመሆነ የዛሬው ፕሮግራም ይሄንኑ ግንባር ቀደም ሚና ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነም አስረድተዋል።

በለውጡ ዓመታት በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካው መስክ በርካታ ውጤቶች የተቻለበት መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሁሉም ድርሻ መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ የዞቤቻሜ ቀበሌ ሴ/ህ/ጽ/ቤት ኃላፊ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች የቁሊቶ ከተማ ጤና ባለሞያዎች የቀጠና ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት የልማት ህብረት ሰብሳቢና አባላት እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል::

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት

▶በ Facebook https://www.facebook.com/100076971182266/posts/app=fbl ላይ ይከታተሉን
▶በቴሌግራም በ https://t.me/womensandchildrensaffairsoffice ላይ ይከታተሉን !!

Photos from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት's post 15/05/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት በፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር የሴቶች የብልጽግና ህብረት 3ኛ ዙር የአባላት ኮንፍረንስና የምርጫ ቅስቀሳ መርሀግብር ተካሄደ!!!

‎የሴቶች ክንፍ በፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር የብልጽግና ህብረት አባላት ንቅናቄ፣ ሴቶች በልማትም ሆነ በፖለቲካው መስክ ያላቸውን ሚና ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

‎በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ሴቶች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ምርጫውን በስኬት ለማጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተገልጿል።

‎ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገርነት ለማሻገር በሚደረገው ጉዞ ላይ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሴቶች ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል

‎የሴቶች ህብረትን በማጠናከር በፐብሊክ ሰርቫንቱ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በጋራ ዓላማ ዙሪያ እንድወያዩና እና በ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ድምጻቸውን ለብልጽግና ፓርቲ እንድሰጡ ቅስቀሳና መድረክ ተካሄዷል።

‎ሴት የመንግስት ሰራተኞች በስራ ገበታቸውም ሆነ በፖለቲካዊ ተሳትፎአቸው ንቁ እንዲሆኑ ፓርቲው በአደረጃጀት በማሳተፍ እየሰራ እንደሆነ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ም/ሀላፊ ወ/ሮ ሙናጃ መሀመድ ገልጿል።

‎የምርጫ ቅስቀሳዉ የብልጽግና ፓርቲን ራዕይ እና እቅዶች ለሴት ሰራተኞች በማስተዋወቅ የደጋፊነት መሰረቱን የማስፋት ስራ ተሰርቷል።

‎የፓርቲውን የሴቶች ክንፍ እስከ ታችኛው ህብረት ደረጃ ድረስ ንቁ ለማድረግ ብልጽግና ፓርቲ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

‎የዕለቱን የውይይት መድረክ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ሙናጃ መሀመድ እና የፐብሊክ ሰርቫንት የሴቶች ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰላማዊት ዮሐንስ በጋራ መርተዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ.ጽ.ቤት

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Abeba To Arbamichi Main Rod
Addis Ababa
HALABAZONE