28/04/2026
የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል አገልግሎት ለየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል
ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
በሃገር አቀፍና በከተማችን የመጀመሪያ የሆነው የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል አገልግሎት በዛሬው ዕለት በየካ ክፍለ ከተማ ሾላ መብራት አካባቢ በመገኘት በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት ለማግኘት የተቸገሩ ለነዋሪዎችን ባሉበት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቅርቡ ተመርቆ ስራ የጀመረው “የአዲስ መሶብ” ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ሰጥቷል።
በክፍለ ከተማ ደረጃ በተሰጠው ተንቀሳቃሽ አገልግሎቱ ላይ ተገኝተው የተገለገሉት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ እንደገለፁት አገልግሎቱ ብልሹ አሰራርን ያስቀረና ነዋሪው ፈጣንና በአቅራቢያው የፈለገውን አገልግሎት ካለ ምንም ድካም እንዲያገኝ ያስቻለ ነው ብለዋል።
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስራ በመጀመር በየአካባቢው የከተማችን ነዋሪ የአገልግሎቱ ተጠቃሚነት እንዲሆን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።
የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ማስረሻ አገልግሎቱ የ8 ተቋማትን ስራ በአንድ ተንቀሳቃሽ አውቶብስ ውስጥ በተሟላ መንገድ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህም የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት፣ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ፣ የገቢዎችና የንግድ አገልግሎት፣ የኢትዮ ፖስታ እና የኤሌክትሪክ ቅድመ ክፍያ አገልግሎቶች በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የተጠቀመ ሲሆን፣ የኔትወርክ መቆራረጥ እንዳያጋጥመውና ያልተቋረጠ የኃይል አቅርቦት እንዲኖረው በሶላር ኢነርጂ የሚሰራ መሆኑንም አክለዋል።
28/04/2026
አዲስ አበባ የዓለም አቀፉን "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" ልታስተናግድ ነው
የዓለም አቀፉ የብስክሌት ሕብረት (UCI) ዕውቅና የሰጠውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
ይህ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ብስክሌተኞች የሚሳተፉበት ታላቅ ውድድር የፊታችን ሚያዝያ 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ የሚከናወን ይሆናል።
ውድድሩ በዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች ይከታተሉታል ተብሎ ይጠበቃል።
አዲስ አበባ እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ ተመራጭ መሆኗ፣ በከተማዋ በስፋት እየተገነቡ ያሉት ዘመናዊ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ውጤት መሆኑ ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ዘርፍ ለኢኮኖሚ ግንባታና ለትውልድ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት የጀመራቸው የልማት ሥራዎች፣ ከተማዋን የዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ማዕከል እያደረጓት ይገኛል።
28/04/2026
አሁን በመካሄድ ላይ!
‘’የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው እና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የሚቀርቡበት የምክክር መድረክ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።
ባለፉት ስምንት አመታት በተለይም በትምህርት፣ ጤና፣ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በባህል፤ በኪነ-ጥበብና ስፖርት እንዲሁም በሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳዮች የተመዘገቡ ውጤቶች በስፋት የሚተነተኑበት መድረክ ነው።
28/04/2026
የበጋ መስኖ እርሻ፤ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሰረትን የጣልንበት ምዕራፍ ነው።
የውሃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)
27/04/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ጋር በሳይንስ ሙዚዬም ያደረጉት ጉብኝት በምስል፡-
27/04/2026
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራዎችን አቀናጅቶ በመስራት በሁሉም ዘርፎች አዳጊና ውጤታማ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት “የየካን የብልፅግና ከፍታ ማሳያ” ለማድረግ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ፣ በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች አበረታች ውጤቶችን በርካታ ማስመዝገብ ተችሏል።
አስተዳደሩ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በከተማ ግብርና፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ብልሹ አሰራሮችን ለመቀነስ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ውጤታማነት ለማረጋገጥ፣ በሰላምና ጸጥታ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ በሰው ተኮር ተግባራት፣ የፋይናንስ አጠቃቀምን ውጤታማ ማድረግ እና ችግር ፈቺ ተግባራትን መፈጸም፣ ህገ-ወጥነትን መከላከል እና የረዥም ጊዜ የነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለአብነት ከመስራት ጋር በተያያዘ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በዘላቂነት መፍታት መቻሉን ገልፇል።
በልማት ስራዎች የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የትምህርት ተቋማት ማስፋፊያ ግንባታዎች፣ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች እና የሰው ተኮር ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን እንዲሁም ኢኒሼቲቭ ስራዎች በልዩ ትኩረት መፈጸማቸው ተጠቅሷል።
በተጨማሪም የነዋሪውን ሁሉንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ከባለድርሻ አካላት እና ከመላው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ስኬታማ ተግባራት ተከናውኖል።
በክፍለ ከተማው የዜጎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ለ34,223 ዜጎች በተለያዩ የስራ ዘርፎች አዲስ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። የኑሮ ውድነትን ጫና ለመቀነስ በገበያ ማዕከላት፣ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እና በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት የምርት አቅርቦት እንዲጨምር ተደርጓል።
በከተማ ግብርና ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ ነዋሪዎች ለቤተሰብ ፍጆታ የሚውሉ ምርቶችን በራሳቸው እንዲያመርቱ ድጋፍ ተደርጓል።
በትምህርትና በጤና ዘርፍ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የማስፋፊያ ህንፃዎች ከመገንባት በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል።
በተለይም የእናቶችና የጨቅላ ህፃናት ጤና ለመጠበቅ የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ ነበሩ። በሌላ በኩል የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ የመፍጠር ስራ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት 165 ብሎኮች ሞዴል እንዲሆኑ ተደርጓል።
የፕሮጀክቶች አፈፃፀምን በተመለከተ የአስተዳደር፣ የጤና፣ የትምህርት እና የተለያዩ የኢኒሼቲቭና ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ በትኩረት ተሰርቷል።
ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና በሰላም ኮንፈረንሶች በማሳተፍ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ተደርጓል።
በተጨማሪም ተቋማት አገልግሎታቸውን እንዲያዘምኑ የግብዓት ድጋፍ ተደርጓል፤ አገልግሎቶችም በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ ተደርጓል።
እንዲሁም ሞዴል ተቋማትን በመፍጠር የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ተችሏል፤ በሌሎችም ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት ተከናውኗል።
አስተዳደሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገቡት እነዚህ ስኬቶች በጠንካራ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎች ተሰርቷል።
ሚያዝያ 18/2018 ዓ•ም የካ ኮሙኒኬሽን
26/04/2026
በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኙት የቶዮ፣ ኦርጅን፣ ሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎች እና የኤች.ዜድ (HZ) ጋዝ ፋብሪካ።
አስተዋፅዖቸው በአንድ ምስል!
Toyo, Origin, Lumintech Solar Factories, and the HZ Gas Plant, all within Hawassa Industrial Park.
Their contribution in one picture!
25/04/2026
የራስ ኃይሉ የስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከልን ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማካሄድ በሚያስችል ደረጃ በማደስ እና ተጨማሪ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ወደ አገልግሎት እንዲገባ አድርገናል።
ማዕከሉን ቀደም ብሎ መርቀን አገልግሎት መስጠት ካስጀመርን በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አገልግሎቱ ተቋርጦ ቆይቷል። የቴክኒክ ችግሩ እንዲፈታ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን እንዲያሟላ የሚያስችሉ ተጨማሪ መሰረተ ልማቶች እንዲካተቱለት በማድረግ አገልግሎቱን በድጋሚ እንዲጀምር አድርገናል።
ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ስታንዳርድን የተጠበቀ የመዋኛ ገንዳዎች፤ ሁለገብ ጅምናዚየም፤ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የቮሊ ቦል፣ የቦክስ፣ የማርሻል አርት ውድድሮችን ማካሄድ የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች፤ የሚዲያ ማዕከል፤ የቴኒስና የእግር ኳስ ሜዳዎች፤ ካፍቴሪያ እና ሱቆችን እንዲሁም መናፈሻ እና የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችን አካቶ የያዘ ዘመናዊ የስፖርት ማዕከል ነው።
በአካልም በአዕምሮም ዳብሮ የተገነባ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለመገንባት በሰነቅነው ራዕይ በከተማችን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን እና የስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን በማስፋፋት ህጻናት እና ታዲጊዎች ስልጠናዎችን እና ልምምዶችን እንዲያገኙ በስፖርት የዳበሩ፣ ጤናቸው የተጠበቀ እና ተወዳዳሪ ብሎም አሸናፊ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ማዕከሉ ከዛሬ ጀምሮ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን፣ ልምምዶችን እና ስልጠናዎችን ጨምሮ በተሟላ መልኩ አገልግሎት መስጠት የጀመረ በመሆኑ ተገልገሉበት፣ ጠብቁት፣ ተንከባከቡት።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይበርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
24/04/2026
የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ተቀብያለሁ። ይኽ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጠንካራ እና ዘላቂ ግኙነት የሚያሳይ ነው። ትብብራችንን እና የጋራ ፍላጎቶቻችን ለማጠናከር የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት እንደምናደርግ እምነቴ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
23/04/2026
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ አለዎት!
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በመሾምዎ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የጥረታቸው ፍሬ በአፍሪካ ደረጃ እውቅና አግኝቶ ለዚህ ሹመት መብቃታቸው ለኢትዮጵያን ሁሉ ኩራት ነው ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
23/04/2026
አዲስ ገቢር ነበብ የፖለቲካ ኢኮኖሚ:-
ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበረው ግትር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አስተሳሰብ ተላቃ፣ ትኩረቱን በተግባራዊ አፈጻጸም ላይ ያደረገ አዲስ ገቢር ነበብ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እይታ የተቃኘ የፖሊሲ ማዕቀፍ መከተል ከጀመረች ሰነባብታለች።
ይኅው አዲስ አቅጣጫ፤ ሀገሪቱ ለወቅታዊ የዓለምና የሀገር ውስጥ ነባራዊ ሁኔታዎች ምላሽ የሚሰጡ ተግባራዊ መፍትሄዎችን እንድትቀይስ አስችሏታል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የሪፎርም ጉዞ፣ መንግሥትንና የግሉን ዘርፍ እንደ ወሳኝ አጋር በማየት፣ በውጤትና በውጤታማነት ላይ የተገነባ አዲስ የመንግሥት የሥራ ባህልን ተቋማዊ አድርጓል።
በዚህ ገቢር ነበብ እይታ አማካኝነት፣ በሚከተሉት ስምንት ቁልፍ ምሰሶዎች ወሳኝ ስኬቶች ተመዝግበዋል፦
• በኢኮኖሚ ዕይታ ረገድ፦ የመንግሥትን ሚና ዳግም በመተርጎም፣ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና ዘርፈ-ብዙ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎች አማካኝነት የገበያ ውድድር እንዲሰፍንና የኢኮኖሚ አቅም እንዲጎለብት ተደርጓል።
• በአማራጭ ፋይናንስ ዘርፍ፦ የካፒታል ገበያ ልማትን በማብሰር፣ የመንግሥትና የግል አጋርነትን በማጠናከር እና ዘመናዊ የገንዘብ ገበያ በመፍጠር የሀገሪቱን የፋይናንስ አማራጮች ማሳደግ ተችሏል።
• በኢኮኖሚ አመራር በኩል፦ በመደበኛ ክትትልና ግምገማ፣ በማክሮ ኮሚቴና በዘርፍ ካውንስሎች የተቀናጀ አሰራር አማካኝነት የገንዘብ ፖሊሲና የፕሮጀክቶች አስተዳደር ይበልጥ ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆን ተደርጓል።
• የግል ዘርፍ ሚናን በማሳደግ፦ የግሉ ዘርፍ ከማህበራዊ ኃላፊነት ባለፈ የኢኮኖሚው መሪና ዋና ሞተር እንዲሆን በማድረግ እንደ ትልቅ የልማት አጋር እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል።
• በልማት አጋርነትና ንግድ ትስስር ፦ የብድር ሽግሽግና አዲስ ፋይናንስን በማረጋገጥ፣ ለዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት የሚደረገውን ሂደት በማፋጠንና የAfCFTA ትግበራን ውጤታማ በማድረግ የሀገሪቱ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ተወዳዳሪነት ከፍ ብሏል።
• በማህበራዊ ደህንነት ረገድ፦ አካታችነትን፣ ተደራሽነትንና ጥራትን መሠረት ያደረገ የሰው ተኮር ድጋፍ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ማድረግ ተችሏል።
• በፍትሃዊ የመሰረተ ልማት ስርዓት ፦ የአካባቢ ጸጋን መሠረት ያደረገ፣ በግልጽ የሕግ ማዕቀፍ የሚመራና ያለፉ የፍትሃዊነት ክፍተቶችን የሚሞላ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥርዓት ተግባራዊ ሆኗል።
• በስርዓት ግንባታ በኩል፦ ብሔራዊ አካታች ምክክርን በማካሄድ፣ በፍትህና በሲቪል ሰርቪስ ዘርፎች ሪፎርም በማድረግ እንዲሁም የዲሞክራሲ ተቋማትን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል።