02/06/2026
የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች ፕሮጀክት በውስጡ ምን ምን ይዟል፦
👉 597 ሄክታር ቦታ የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት፤
👉 15 ሄክታር መሬትን በማልማት በአረንጓዴ ተሸፍኗል፤
👉 የ210 ቀፎ ዘመናዊ የንብ እርባታ፤
👉 የአበባ እና የእጽዋት ጋርደኖች ልማት፤
👉 የአካባቢውን ማህበረሰብ የስራ ባህል የሚዘክሩ ሃውልቶችና ቅርሶች ግንባታ፤
👉 22 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፤
👉 8 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤
👉 6 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፤
👉 4 ኪሎ ሜትር የሃይኪንግ መንገድ፤
👉 2 አዲስ የተሽከርካሪ ድልድዮች ግንባታ፤
👉 3 ነባር የተሽከርካሪ ድልድዮች ዕድሳት ስራ፤
👉 39 የውሃ መከላከያ ግድቦች ግንባታ (ቼክ ዳም) በስጡ አጠቃልሎ ይዟል።
01/06/2026
የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-
• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤
በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።
Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.
Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.
The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.
On this historic day:
* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;
The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.
It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.
30/05/2026
የንጋት ሐይቅ፣ የኢትዮጵያ የቱሪዝም እና የብሔራዊ ኩራታችን ምልክት!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተደጋጋሚ እንደሚያነሱት፣ "ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የፅናት፣ የአንድነት እና የብሔራዊ ኩራት ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ የልማት፣ የኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ ማዕከል ነው።" ይህ ራዕይ በግድቡ ዙሪያ የተፈጠረውን ግዙፍ ሰው ሰራሽ "ንጋት ሐይቅ"፣ የቱሪዝም ዘርፉን ወደ አዲስ ብርሃን እና ከፍታ ሊወስድ የሚችል ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ያደርገዋል። በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ምክንያት የተፈጠረው ይህ ሐይቅ፣ የግድቡን መሰረት ተከትሎ እየተፈጠረ ሰው ሰራሽ ተአምር ነው።
የንጋት ሐይቅ ልማት፣ የዜጎችን የመተባበር አቅም በማስተባበር በአገራዊ ግንባታ ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ሐይቁ ለአገር በቀል ኢኮኖሚ እንደ ሞተር በማገልገል፣ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እና የሀብት ማመንጨት አቅሙን በማጎልበት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አቅም ከፍ የሚያደርግ የጀርባ አጥንት ሆኖ ይወጣል።
ሐይቁ በዓይነቱ ለየት ያለ የቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ትልቅ አቅም አለው። ስሙ እንደሚያመለክተው፣ ይህ ሐይቅ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም አዲስ "ንጋት" ወይም መባቻን ያበስራል።
ይህ መዳረሻ በአገር በቀል የእውቀት እና የሀብት አጠቃቀም ላይ የተመሰረተ በመሆኑ፣ የአካባቢውን ምርቶች እና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ የኢኮኖሚ አሻራውን ያሰፋል።
የንጋት ሐይቁ በአገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የብሔራዊ አንድነት ምልክት ሆኖ እንደሚያገለግል ሁሉ፣ በቱሪዝም አማካኝነት በሚያመነጨው የውጭ ምንዛሬ እና የገበያ መስተጋብር አገራዊ የኢኮኖሚ ጥገኝነትን በመቀነስ በራስ መተማመንን የሚገነባ የኢኮኖሚ ማዕከል ይሆናል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ይህ ውኃማ ክፍል፣ ጨለማን አብርቶ ብርሃን እንደሚፈነጥቅ የንጋት ፀሐይ፣ አካባቢውን ለቱሪስቶች ተመራጭ መዳረሻ ያደርገዋል። ሐይቁ የሚፈጥረው እጅግ አስደናቂ የተፈጥሮ ገጽታ እና የውኃ ላይ መልክዓ ምድር፣ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ አገር ጎብኚዎች አዲስ የመዝናኛ መዳረሻ በመፍጠር የሀገራችንን የቱሪዝም ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ያደርጋል።
የኢኮ-ቱሪዝም እድገት በንጋት ሐይቅ አካባቢ እንደ አዲስ ቀን መወለድ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው። ሐይቁን የሚከብቡት ለምለም አካባቢዎች እና ደኖች፣ ለተፈጥሮ ወዳዶች እና ለወፍ ተመልካቾች ልዩ ዕድሎችን ይፈጥራሉ።
ዘላቂነት ባለው መንገድ የሚዘጋጁ ኢኮ-ሪዞርቶች፣ የአካባቢውን የብዝሃ-ሕይወት ጥበቃ ከቱሪዝም ልማት ጋር በማጣመር፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ አረንጓዴ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሐይቅ እንደመሆኑ፣ "የኢንዱስትሪ ቱሪዝም" ለሚፈልጉ ጎብኚዎች እንደ ብርሃን ማዕከል ሆኖ ያገለግላል። የኢንጂነሪንግ ስራውን ለማየት የሚመጡ ተመራማሪዎች፣ ተማሪዎች እና ታሪክን የሚወዱ ጎብኚዎች በሐይቁ ዳርቻ በሚቋቋሙ ሙዚየሞች እና የማሳያ ማዕከላት አማካኝነት ስለግድቡ ግንባታ ሂደትና ፋይዳ መማር ይችላሉ። ይህ ደግሞ ግድቡን ከቀላል የኃይል ማመንጫነት ወደ ታላቅ የትምህርታዊ ቱሪዝም ማዕከልነት ያሸጋግረዋል።
የንጋት ሐይቅ የቱሪዝም ልማት በኢትዮጵያ የባህልና የቱሪዝም ዘርፍ ዲፕሎማሲን ለማጠናከር እንደ ጧት ፀሐይ አድማስን ያሰፋል። ሐይቁን ማዕከል ያደረገ የተቀናጀ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ለክልሉ የተቀናጀ የኢኮኖሚ እድገት መነሻ ከመሆኑም ባሻገር፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የቱሪዝም ካርታ ላይ ያላትን ተጽዕኖ ከፍ ያደርገዋል። ይህ ስትራቴጂያዊ መዳረሻ፣ የሐገሪቱን ገጽታ በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል።
www.visitethiopia.et
ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት
http://mot.gov.et
https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins
https://web.facebook.com/
https://t.me/tourismethiopia
t.me/ethiopialandoforigins
https://x.com/https://x.com/ECBethiopia
30/05/2026
የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት እና የማህበረሰብ ተጠቃሚነት....!
ባለፉት ተከታታይ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ መንግስት የቱሪዝም ዘርፍን እንደ ዋነኛ የኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ በመቀመር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ አዳዲስ እና ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመገንባት ታላቅ ስራ ሲያከናውን ቆይቷል። እነዚህ መሰረተ ልማቶች በቀላሉ ውብ ስፍራዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ በአካባቢው ለሚገኙ ማህበረሰቦች ሁለንተናዊ የለውጥ ማዕከላት ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
በተለይም በከተማ መሃል የተገነቡት እንደ ወዳጅነት ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ እና እንጦጦ ፓርክ ያሉ የቱሪዝም ፕሮጀክቶች፣ እንዲሁም ከከተማ ውጪ በተለያዩ አካባቢዎች የተከናወኑ የገጠር እና የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎች፣ በአካባቢው ለሚኖረው ህብረተሰብ ቀጥተኛ የኢኮኖሚ እድል ፈጥረዋል።
ከእነዚህ እድሎች መካከል ዋነኛው የስራ እድል ፈጠራ ነው። እነዚህ መዳረሻዎች ለወጣቶች እና ለሴቶች በተለያዩ የቱሪዝም ተያያዥ አገልግሎቶች ማለትም በመስተንግዶ፣ በዕደ-ጥበብ ሽያጭ እና በትራንስፖርት ዘርፎች ሰፊ የስራ እድል አበርክተዋል።
በተጓዳኝ፣ የአነስተኛ ንግዶች መነቃቃት ሌላው ትልቅ ፋይዳ ነው። የመዳረሻዎቹ መገንባት በአካባቢው ያሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በማነቃቃት፣ የንግድ እንቅስቃሴን በማሳደግ የዘላቂ ገቢ ምንጭ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻዎች በሚገነቡበት ወቅት አካባቢው የተሻለ የመንገድ፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና የዲጂታል መሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ የአካባቢ ልማትን አፋጥነዋል።
አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማህበረሰቡን ከማህበራዊ እና ባህላዊ እሴቶች አንጻርም ተጠቃሚ አድርገዋል፦ የባህል ጥበቃን በተመለከተ፣ እነዚህ ስፍራዎች የኢትዮጵያን ብዝኃ-ባህላዊ እሴቶች የሚያንፀባርቁ በመሆናቸው፣ ማህበረሰቡ ባህሉን እንዲንከባከብና ለቱሪስቶች እንዲያስተዋውቅ በማድረግ የባህል ኩራትን እየገነቡ ይገኛል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ እንደ የመዝናኛ እና የጤና ማዕከላት ለከተማ ነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች ንጹህ አየር የተላበሰና ደህንነቱ የተጠበቀ የመዝናኛ ስፍራ በመሆን፣ የማህበረሰቡን የአእምሮና የአካል ጤንነት በመጠበቅ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ነው።
በአጠቃላይ፣ በቅርብ ዓመታት የተከናወኑት የቱሪዝም መሰረተ ልማቶች፣ ሀገሪቱ ያላትን ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ጸጋዎች በአግባቡ በመጠቀም ዘላቂ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተወሰዱ ስልታዊ እርምጃዎች ናቸው። እነዚህ መዳረሻዎች የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል ባሻገር፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነች የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን መሰረት የጣሉ፣ ለትውልድ የሚሸጋገሩ ታላላቅ የልማት ሥራዎች ናቸው።
www.visitethiopia.et
ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት
http://mot.gov.et
https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins
https://web.facebook.com/
https://t.me/tourismethiopia
t.me/ethiopialandoforigins
https://x.com/https://x.com/ECBethiopia
29/05/2026
በኢትዮጵያ የከተማ ቱሪዝም አዲስ ምዕራፍ....!
መንግስት ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ከባህላዊ ፣ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ መዳረሻዎች በማውጣት፣ ዘመናዊ መዋቅሮችን እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ አዲስ የኢኮኖሚ ምሰሶ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎችን አከናውኗል። ይህ የስትራቴጂ ለውጥ፣ ጥንታዊ ታሪካችንን ከዘመናዊነት ጋር በማዋሃድ ሀገሪቱን ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ ታቅዶ የተከናወነ ስኬታማ እንቅስቃሴ ነው።
በከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ የተጀመሩት ዘመናዊ የከተማ ልማት ሥራዎች የቱሪዝም ዘርፉን ገጽታ ቀይሮታል። እንደ አዲስ አፍሪካ የኮንቬንሽን ማዕከል እና የአድዋ ድል መታሰቢያን የመሰሉ ታሪካዊ ቦታዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚወዳደር ጥራት መገንባታቸው፣ የባህል ጥልቀትን ከዘመናዊ ሥነ-ህንፃ ጋር አዋህዶ ለቱሪስቶች አዲስ ልምድን ሰጥቷል። ይህ አቀራረብ ስብሰባዎችን፣ የማበረታቻ ጉዞዎችን፣ ኮንፈረንሶችን እና ኤግዚቢሽኖችን ያካተተ (MICE Tourism) ዘርፍ ዕድገት ወሳኝ መሰረት ጥሏል።
የከተማ ቱሪዝሙን የንግድ ገጽታ ለማጠናከር ባለፉት ዓመታት አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን ለማስተናገድ የሚያስችሉ ዘመናዊ የኮንፈረንስ እና የኤግዚቢሽን ማዕከላትን ገንብቷል። እነዚህ ማዕከላት የውጭ ምንዛሬን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እና የከተሞችን ዓለም አቀፍ ዝና ለመገንባት በዋና መሪነት እየሰሩ ይገኛሉ።
ይህ የልማት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ብቻ ያልተወሰነ ሲሆን፣ እንደ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ እና ድሬዳዋ ባሉ ከተሞችም በተቀናጀ መልኩ እየተስፋፋ ነው። እነዚህ ከተሞች በተፈጥሮ ፀጋቸው ላይ የከተማ ማዕከል ልማቶችን በማከል፣ የቱሪስት መዳረሻነታቸውን በማዘመን ላይ ናቸው። በተለይ በክልል ከተሞች እየተከናወኑ ያሉት የመናፈሻዎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች እና የኮሪደር ልማቶች፣ ጎብኚዎች ከአዲስ አበባ ወጣ ብለው በክልል ከተሞችም ዘመናዊ እና ምቹ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ አስችሏል።
በተለይ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ትስስር፤ ለአብነት የአየር መንገድ መስፋፋት እና ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች የቱሪስት መዳረሻዎችን እርስ በርስ በማስተሳሰር፣ ጎብኚዎች በከተሞች የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲያራዝሙ እና በዘመናዊ የኮሪደር ልማትና ፓርኮች ታጅበው እንዲንቀሳቀሱ አስችለዋል። መንግስት የቱሪዝም መዳረሻዎችን በዲጂታል መድረኮች በማስተዋወቅ የጎብኚዎችን ልምድ ቀይሯል። እነዚህ ስራዎች በአካባቢው ማህበረሰብ፣ በተለይም በወጣቶች የኑሮ ደረጃ ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ እየፈጠሩ ይገኛል።
እነዚህ በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶች በቅርብ ጊዜያት በማህበራዊ ሚዲያ ፈጣሪዎች አማካኝነት በስፋት እየተዋወቁ ይገኛሉ። በተለይም የአዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን እንደ አዳማ እና ባህር ዳር ያሉ ከተሞችን ውበት በፈጠራ ይዘት ለዓለም የሚያስተዋውቁ ወጣት የይዘት ፈጣሪዎች፣ አገሪቱ ያላትን የቱሪዝም አቅም ተደራሽ በማድረግ የላቀ ሚና እየተጫወቱ ነው። ይህም ጎብኚዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን የቆይታ ጊዜ እንዲያራዝሙ እና አዳዲስ ከተሞችን እንዲጎበኙ ከፍተኛ መነሳሳትን ፈጥሯል።
የከተማ ቱሪዝም ጉዞ የዘመናዊነት እና የባህል ውህደት ውጤት በመሆኑ፣ ለሀገር ኢኮኖሚ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። መንግስት የጀመራቸውን ሰፊ የመሰረተ ልማት ሥራዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ የግብይት ስልት በማጀቡ፣ የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባት እና በቱሪዝም ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን በማረጋገጥ ረገድ የላቀ ዕድል ከፍቷል።
www.visitethiopia.et
ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት
http://mot.gov.et
https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins
https://web.facebook.com/
https://t.me/tourismethiopia
t.me/ethiopialandoforigins
https://x.com/https://x.com/ECBethiopia
26/05/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
የላፍቶ ሆስፒታል ተመረቀ!
በኢትዮጵያ በተሻሻለው የመከላከል እና አክሞ የማዳን የጤና ፖሊሲ መሠርት ፣ ሀገራችንን ቀዳሚ የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ፣ ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ለሰነቅነው ርዕይ እና መሰል የረቀቁ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታን ለማስቀጠል የላፍቶ ሆስፒታል አሻጋሪ ምዕራፍ ነው።
በ5.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዘመናዊና ግዙፉ የላፍቶ ሆስፒታል እጅግ ዘመናዊ አቅሞች በመጠቀም እንደ ካንሰር፣ ውስብስብ የልብ ህመም እና ተያያዥ የህክምና ሁኔታዎችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ህክምና የሚሰጥ ሲሆን፣ ዜጎች እዚሁ ሀገራቸው ውስጥ ልዩ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል። ይህ ታላቅ ተቋም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ከመቀየር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እራሷን ለመቻልና ለሀገራዊ ልማት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው።
www.visitethiopia.et
ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት
http://mot.gov.et
https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins
https://web.facebook.com/
https://t.me/tourismethiopia
t.me/ethiopialandoforigins
https://x.com/https://x.com/ECBethiopia
26/05/2026
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ (አረፋ)በዓል አደረሳችሁ!
26/05/2026
የቱሪዝም ዘርፉን በዳታ ለማዘመን የሚያስችል የጋራ መግበቢያ ሰነድ ተፈረመ።
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም
የቱሪዝም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ማህበር በጋራ አብረው መስራት በሚያስችላቸውን ጉዳዮች ላይ የጋራ ስምምነት አድረጉ።
በስምምነቱ ዳታ መስረት ያደረገ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ቁጥር ለማወቅ፣ ቱሪዝም ለሥራ እድል ፈጠራ ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳየትና የቱሪዝም ሰታተቲስትክ የተመለከተ ስልጠና መስጠት የሚሉ ጉዳዶች ተካተዋል።
የመግባቢያ ሰነዱ የተፈራረሙት የቱሪዝም ሚኒስቴር ድኤታ አቶ ስለሺ ግርማ የቱሪዝም መረጃዎችን በመሰብሰብ ፣ የሚተነተንበትን እና የሚሰራጭበትን መንገድ በማዘመን፣ ቱሪዝምን ከስታቲስቲክስ ሳይንስ ጋር በማጣመር በማስረጃ እና በዳታ ላይ የተመሰረተ የቱሪዝም እቅድ ለመተግበር እንደማያስችል ገልጸዋል።
በአሁኑ ዘመን ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ (ዳታ) ለስኬታማ ጉዞ ዋነኛው መሪ ኮምፓስ ሲሆን የመግባቢያ ሰነድ መፈረም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የተቀናጀ የብሔራዊ ቱሪዝም መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል ።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ማህበር ፕሬዘዳንት ታደስ ካሳሁን /ዶ.ር/ በበኩላቸው ማህበሩ ያለውን የቴክኒክ እውቀት፣ ሙያዊ ስነ-ምግባር እና ዘመናዊ የአሠራር ስልቶችን በመጠቀም ይፋዊ የቱሪዝም ስታቲስቲክስ ተዓማኒነት፣ ግልጽነት እና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ እንደሚያቀርቡ አረጋግጠዋል ።
የአቅም ግንባታ ስልጠናን በተመለከተ በሁለቱም ተቋማት ውስጥ የመረጃ አሰባሰብ፣ ትንተና እና አጠቃቀም ቴክኒካዊ ክህሎቶችን ለማሳደግ የተቀናጁ የስልጠና ፕሮግራሞችን በጋራ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል ።
ይህ የተዘረጋው የትብብር ማዕቀፍ እውቀትን ለመጋራት፣ የጋራ ምርምርን ለማድረገረ እና ትልቅ የመረጃ ቋት በመፍጠር ዘላቂ ቱሪዝምን ለማረጋገጥ ትልቅ ጠቀሚታ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
www.visitethiopia.et
ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት
http://mot.gov.et
https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins
https://web.facebook.com/
https://t.me/tourismethiopia
t.me/ethiopialandoforigins
https://x.com/https://x.com/ECBethiopia