29/10/2021
በፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ወንድም ስም ከተቀመጠ ገንዘብ ለማውጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት ቡድኑ አባል በፈትለወርቅ ገብረእግዚያብሔር ወንድም ስም በባንክ ከተቀመጠ ገንዘብ 267 ሚሊየን ብር ለማውጣት የሞከሩ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በወንጀሉ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች ውስጥ 2 ዳኞች መሆናቸው ተገልጿል።
በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናስ እና ንግድ ነክ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ በሰጡት መግለጫ÷ ወንጀሉ የተፈፀመው በህግ ባለሙያዎች ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ነው።
የሽብር ቡድኑ አባል ፈትለወርቅ ገብረእግዚያብሔር ወንድም ዳዊት ገብረእግዚያብሔር በሀሰተኛ ስሙ ቱሉ በዳዳ(ቶፊቅ ሙላት አበራ) በስራ ግንኙነት እዳ አንዳለበት በመስማማት ሀሰተኛ ሰነድ በህግ ባለሙያዎች በማዘጋጀት ፍርድ ቤት ለግልግል ዳኝት ጠይቀዋል።
በሀሰተኛ መንገድ በተዘጋጀውን የግልግል ፍርድ ተጠርጣሪዎቹ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ እንዲሰጣቸው ሐምሌ 16 ቀን 2013 መጠየቃቸው በመግለጫው ተነስቷል።
ዳኞቹ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በነበራቸው የጥቅም መመሳጠር የፍርድ ባለእዳ ዳዊት ገብረእግዚአብሄር ባልቀረበበት፤
ተጠርጣሪዎቹለፍርድ ባለመብት በሀሰተኛ ስሙ ቱሉ በዳዳ (ቶፊቅ ሙላት አበራ ) እና ጉዳይ አሰፈፃሚ ግብረ አበሮች እና በዜናዊ ወርቅነህ ገንዘብ አቅራቢነት 400 ሺህ ብር ለቅድመ ስራው ጉቦ በመስጠት አፈፃፃም እንዲወጣ አድረገዋል።
ሁለቱ ዳኞችም የፍርድ ባለእዳው ባልቀረበበት ትዕዛዝ እንደማይሰጥ እያወቁ ከተጠሪጣሪዎች ጋር ባላቸው የጥቅም መመሳጠር ለፍርድ ባለመብት ሆኖ ለቀረበው በሀሰተኛ ስሙ ቱሉ በዳዳ(ቶፊቅ ሙላት አበራ) 267 ሚሊየን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጪ ሆኖ በቡና ባንክ ገቢ እንዲደረግ ውሳኔ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገንዘቡ ግብይት ጥያለውን ጥርጣሬ ለፋይናስ ደንህነት አገልግሎት በሰጠው ጥቆማ ወጪ የሚደረገው 267 ሚሊየን ብር ታግዶ እንዲቆይ በማድረግ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ምርመራ ሲደረግ መቆየጡ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
በዚህም ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጪ ተደርጎ ለጊዜው ስሙ ባልተጠቀሰው ቡና ባንክ ቅርንጫፍ ስራ አሰኪያጅ በመሆኑ እና አስቴር ኪሮስ በተባለች የቤት ሰራተኛው የወር ደሞዟን ባንክ አስቀምጥልሻለው በሚል የባንክ ደብተር በመክፈት እና ቢሮ በማስቀመጥ ገንዘቡ ወደ ሰራተኛው ደብተር ገቢ ሳይሆን በአየር ላይ ቱሉ እስቀምጥልሻለው ብሎ ቡክ በማስከፈት፤ገንዘቡ ወደ ባንኩ ሳይገባ የስራ ሃላፊነቱን ተጠቅሞ ለተጠርጣሪው በሀሰተኛ ስሙ ቱሉ በዳዳ ለመስጠት መዘጋጀቱም ተገልጿል።
በተደረገው ረጅም ጊዜ የፈጀ ምርመራ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 13 ግለሰቦች ተጠርጣረው 10 በቁጥጥር ስው ማዋል መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
ውሳኔውን ያስተላለፉ ዳኞች የመጀመሪያው ጉዳይ ለማስፈጻም 400 ሺብር የተቀበሉ ሲሆን÷ ገንዘቡ ከወጣ ተጨማሪ የሚከፈላቸው በ3 የተለያዩ ቼኮች የተጻፉ 2 ሚሊየን ብር ፣ 3 ሚሊየን ብር እና የ5 ሚሊየን ብር ደረቅ ቼክም በቁጥጥር ስር ውሏል።
የዳዊት ገብረእግዚያብሄር ህጋዊ ተወካይ ረቂቅ ዜናዊ ትዕዛዝ በመቀበል ከዳሽን ባንክ 650 ሺህብር ወጪ በማድረግ ከግብረ አብሮቿ ጋር ታስፈፅም የነበረ ዜናዊ ወርቅነህ በቁጥጥር ስር መዋሏም ታውቋል።
የአሸባሪው ቡድን አባል ፈተለወርቅ ገብረእግዚያብሄር የፋይናስ ደንህነት አገልግሎት ማዕከል ምክትል ዳሬክተር ሆና ስታገለግል፤ ወንድሟ ዳዊት ገብረእግዚያብሄር ከ276 ሚሊየን ብር ምንም አይነት ምርመራ ሳይደረግ እንዲያወጣ ስለማድረጋቸው በመግለጫው ተነስቷል።
በረቀቀ መንገድ የተፈጸመው የሙስና ወንጀል በጊዜ ተደርሶበት ባይያዝ ኖሮ ለሽብር ቡድኑ የጥፋት ማስፈጸሚያ በመዋል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትል ይችል እንደነበር ተጠቁሟል።
አሁን ላይም ጉዳዩ ምርመራው ተጠናቆ ለአቃቤ ህግ በጉዳዩን ላይ ክስ እንዲመሰርት ተላልፏል።
በበላይ ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
21/10/2021
የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ አስራት ንጉሴ ያስተላለፉት መልዕክት፡፡
መስከረም 21/2014ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በዓሉን አስመልክተዉ ባስተላለፉት መልዕክት የኢሬቻ በዓል የተኮራረፈው ይቅር ተባብሎ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ፤ ፈጣሪ መጪውን ጊዜ ብሩህ እንዲያደርግ የሚለመንበት እና ሕዝብ በመሰባሰብ በጋራ ደምቆ የሚያከብረው ብሎም ማህበረሰቡ ማህበራዊ ትሥሥሩንና ግንኙነቱን የሚጠናክርበት ታላቅ በዓል ከመሆኑም ባሻገር በገዳ ስርዓት ውስጥ የሚገኝ የኦሮሞ ህዝብ ነባር እሴት ነዉ ብለዋል።
እሬቻ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር የአንድነትን ፣ የአብሮነትን እና የመተባበርን ስሜት የሚፈጥር ታላቅ በዓል መሆኑን ሀላፊዋ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡
ኢሬቻ የምስጋና ፣ ፍቅር ፣ ዕርቅ ፣ ሰላም እና አብሮነት በመሆኑ በህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማጠናከር የጋራ የሆኑ እሴቶቻችንን ለማጎልበት የሚያግዝ ነዉ ያሉት ሀላፊዋ በህዝብ መሰባሰብ አብሮነትን በሚያሳይ መልኩ ደምቆ የሚከበር በመሆኑ ማህበረሰቡ በዚህ ወቅት ይህን ታላቅ የኢሬቻ በዓል ሲያከብር የኮቪድ ወረርሽኝ መከላከልን ታሳቢ በሆነ መንገድ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን የሚያጎለብት በዩኔስኮ የተመዘገበ የዓለም ብሎም የመዲናችን አዲስ አበባ ሀብት በመሆኑ ሁሉም በእኔነት ስሜት በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የጋራ እና ከፍተኛ በሆነ ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓሉን ለማጠልሸት ለሚፈልጉ አካላት ምንም አይነት ክፍተት ባለመፍጠር በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ማክበር እንደሚገባ ገልጸዋል።
በዓሉ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የድል ፍሬ መታየት በጀመረበት እና በዓሉ እንዳይከበርና በወንድማማቾች መካከል መከፋፈልን ሲፈጥር የነበረው ሀይል አደብ እንዲይዝ ስራዎች እየተከናወኑ ባሉበት ወቅት መከበሩ ለየት ያደርገዋል ሲሉም አክለው ገልፀዋል፡፡
21/10/2021
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ፅ/ቤት ባልደረባ የሆኑት ወ/ት ወላንሳ ቶሎሳ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በድንገት ከእዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። 💔💔💔
ባልደረባችን ትህትና መለያዋ የሆነ ታታሪ ለትልቅ ትንሹ ታዛዥ እና አዛኝ የነበረች ሲሆን ለሁሉም ወዳጅ የሆነች እህታችንን በማጣታችን የተሰማን ሀዘንም መራር ነው💔 ነገር ግን ሁሌም በልባችን ህያው ሆና ትኖራለች💔💔
ፈጣሪ ነብሷን በአፀደ ገነት ከደጋጎቹ ጎን ያኑርልን.... ለቤተሰቦቿ፤ ለወዳጆቿ እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቿ መፅናናትን እንመኛለን።🖤
21/10/2021
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ ለወረዳ ኮር የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች ምደባ አደረገ፡፡
በዚህ መሠረት
ለወረዳ 1 አስተባባሪ የተመደቡ
*አሜን ቅጣው ሀይሌ - ዋና ስራ አስፈጻሚ
*ሰላማዊት ጥላዬ ታረቀኝ - ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
* ኡመር አብዲ ዮሱፍ-ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ሳልያ አህመድ ያሲን - ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*ስንታየሁ ማርቆስ ሀብቴ- ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 2 አስተባባሪ የተመደቡ
*ለይላ ከማል- ዋና ስራ አስፈጻሚ
*ሁሴን መሐመድ ይማም - ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*እንየው ከበደ እንዳለማው-ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ኡሼጦ አደም ፈቱ- ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*ደስታ ለብሴ- ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 3 አስተባባሪ የተመደቡ
*አብረሃም ጃባሞ ዱቅሶ - ዋና ስራ አስፈጻሚ
*ሰሚራ አያሌው ጣሂር- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*አሰበ ታፈሰ በቲ- ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ሔለን ለገሰ- ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*መዲና ካይሩ- ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 4 አስተባባሪ የተመደቡ
*ትዕግስት ለገሰ- ዋና ስራ አስፈጻሚ
*አብረሃም መኮንን- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*ሃይማኖት ደረጀ- ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ሳምራዊት ቱሉ- ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*ፈትያ ናስር- ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 5 አስተባባሪ የተመደቡ
*ጌትነት አይናለም - ዋና ስራ አስፈጻሚ
*ሻረው ደፋሩ አደሬ- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*እንዳለ ካሳ ልማ- ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ጌታነህ ከፍያለው- ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*ጌጤ ሀብቴ ወርቅ- ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 6 አስተባባሪ የተመደቡ
*ጠይባ ሸኩር የሱፍ- ዋና ስራ አስፈጻሚ
* አብነት አብረሃም ይስማው- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*ጋረደው ቦከና ገመቹ- ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*በሬሳጅራ ፍቃዱ አራርሶ- ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*አምስል ፀጋዬ የማታው- ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 7 አስተባባሪ የተመደቡ
*ደኜ አሰፋው- ዋና ስራ አስፈጻሚ
*መታሰቢያ ምህረት በየነ- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*ተስፋዬ ዱሜቻ ዱላ- ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ተመስገን አተዑ - ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*ያሬድ ተፈራ- ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 11 አስተባባሪ የተመደቡ
*በስራው መሠለ በቀለ- ዋና ስራ አስፈጻሚ
*ሔኖክ በላይ- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*አዳነ ታደሰ መርጊያ- ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ማንደፍሮ ተመስገን አዱኛ- ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 12 አስተባባሪ የተመደቡ
*እስከዳር አበበ- ዋና ስራ አስፈጻሚ
*ሔኖክ ጫንያለው አማረ- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*በላይነህ ምህረቴ- ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ሙሉነሽ ተፈራ- ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*አብረሃም ልንገር ዘውዴ - ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 13 አስተባባሪ የተመደቡ
*ሱራፌል ባያብል - ዋና ስራ አስፈጻሚ
*አሰግድ ሮሪሳ ቱፋ- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*ታደሰ ጌቱ - ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ዳሳለኝ እውነቱ ገዛሃኝ- ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*ፍላጎት ግዛው ኦቶሮ-ለድርጅት ጉዳይ
ለወረዳ 14 አስተባባሪ የተመደቡ
*ሃና መቆያ ካሳዬ - ዋና ስራ አስፈጻሚ
*ሀሚድ ከይሩ አበበ- ለፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ
*ከፊያለው ተፈራ - ለምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
*ሞላ መንገሻ ሲሳይ- ምክትል ፓርቲና ፖለቲካ ዘርፍ
*ትእግስት ሚሊዮን ደራራ-ለድርጅት ጉዳይ ተመድበዋል።
ጥቅምት 11/2014
መረጃዎቻችንን በአማራጭ ለማግኘት: -
በትዊተር: twitter.com/bole_comm
በዩቲዩብ: https://www.youtube.com/channel/UCTc1t2_k9iNhr80vlG5zMJg
በቴሌግራም: https://t.me/bolecommunication