07/06/2026
በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት Kolme Woreda Govt Communication Servic
This page is Konso zone Kolme woreda gov't communication Deputy affairs page
07/06/2026
06/06/2026
"ተግባራትን በማቀናጀት አስፈላጊውን ልማት ለማረጋገጥ ሁሉም የአንበሳውን ሚና መጫወት አለበት! "
ክብርት ሲስተር አዳነች ኩሼታ
(በኮንሶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ምክትል የመንግሥት ተጠሪ)
#ደልቤና ግንቦት 29/2018 ዓ/ም የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ሲስተር አዳነች ኩሼታ "በየደረጃ ያሉት የወረዳው መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና መላው ህብረተሰብ በምርጫው ድባብ ወደ ልማት ሥራዎች ፊቱን ማዞር አለባቸው ፤የምርጫ አስፈላጊነት ቁልፍ ጉዳይ በህገ መንግስቱ መሠረት በየ አምስት ዓመታት ውስጥ ህዝቡ ይመራኛል " የሚለውን ፓርቲ የሚመርጥበት ሀገራዊ ኩነት ነው ፤ስለሆነም ከምርጫው ማግስት ከዚህ ቀደም ተጀማምረው ያሉ መሠረት ልማቶች ላይ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት " ሲሉ መክረዋል ።
"አመራሩ ተቀናጅቶ ከህዝብ ዘንድ የሚነሱ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንዲችሉ በየጊዜ የተግባር ዕቅድ መወጣት አለበት" ያሉት ክብርት ሲስተር አዳነች ኩሼታ 'የተፈለገውን ልማት ህዝቡ እስኪያገኙ ድረስ በየደረጃ ያለው አመራር በጊዜ የለንም መንፈስ መሥራት አለባቸውም' ብለዋል ።
የኮልሜ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ በበኩላቸው : ከምርጫው ድባብ ወጥተን የህዝባችን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ሙሉ አቅማችንን መጠቀም አለብን ። ህዝባችን ከሥራ የማይነጠል በሰው ጉልቤት የማይቻሉ ትላልቅ መሠረተ ልማቶችን ተባብሮ መሥራት የሚችል አኩሪ ህዝብ መሆኑን በማሰብ አሁንም ከወትሮው በላይ ህብረተሰቡን አስተባብረን ከጅምር የቀሩ ሥራዎችን ለቅመን መተግበር ይጠበቅብናል " በማለት አሳስበዋል ።
በድህረ ምርጫ ባለው ጊዜ ውስጥ ህብረተሰቡ እንደከዚህ ቀደም ጊዜያት የመንገድ ሥራዎችን ፣እና የመሣሠሉት የልማት ሥራዎች ላይ መረባረብ አለባቸው ያሉት :የመድረኩን ሐሳብ ያዘለ ሰነድ ያቀረቡት የወረዳው ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ኩሜዳ ጉቶ " በወረዳው ደረጃ እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለማስጨረስ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሥራት ያስፈልጋል " ብለዋል ።
ወረዳውን የሚደግፉ የዞን አመራሮችም :በቀጣይ በየደረጃ ያለው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከህብረተሰቡ ጋር በልማታዊ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት ማካሄድ እንዳለባቸው አሳስበው ፤ቅንጅታዊ የልማት ሥራዎችን ደግሞ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
በአጠቃላይ በውይይት መድረኩ የተሳተፉት የወረዳው ደጋፊ የዞን አመራሮች እና የወረዳው ሁሉም አመራሮች "ያሳለፍነው ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ህዝቡ በሠላማዊ መንገድ ይበጀኛል ያለውን ፓርቲ መምረጥ የቻለበት ሀገራዊ ኩነት በመሆኑ ፤ በቀጣይ ጊዜም ሠላማዊ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና ውጤታማ ለመሆን መትጋት ያስፈልጋል" በማለት ሐሳብ አስተያየት ሰጥተው መድረኩ በስኬት ተጠናቀቀ ።
መረጃው :-የኮልሜ ወረዳ የመንግሥት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ነው ።
06/06/2026
በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ ስለ ድህረ ምርጫ ወቅታዊ ሁኔታ እና ቀጣይ ተግባራት ዙሪያ የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ፤
#ደልቤና ግንቦት 29/2018 ዓ/ም የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ሲስተር አዳነች ኩሼታን ጨምሮ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና ወረዳውን የሚደግፉ የዞን የሥራ ኃላፊዎች እና ሁሉም የወረዳው አመራሮች በተገኙበት ስለ ድህረ ምርጫ ሁኔታዎችና ቀጣይ የልማት ሥራዎች ዙሪያ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛሉ ።
በውይይት መድረኩ የኮልሜ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ "ሁሉም የወረዳችን አመራሮች ከምርጫው ድባብ ወደ ልማታዊ ሥራዎች ፊቱን አዙረው በቀጣይ የህዝባችንን የመልማት ጥያቄዎችን መመለስ ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል ።
ስለ አጠቃላይ ተግባራት እና ቀጣይ ልማታዊ ሥራዎች ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ በወረዳው ዋና የመንግሥት ተጠሪ በአቶ ኩሜዳ ጉቶ እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ፤
ዝርዝር የውይይቱ ሐሳብን ተከታትለን ሲጠቃለል የሚንዘግብ ይሆናል!
መረጃው :-የኮልሜ ወረዳ የመንግሥት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ነው ።
05/06/2026
"ክንዴ ብርቱ ህዝባችን ልዩ ትኩረቱን ልማት ላይ ማድረግ አለባቸው"!
ክቡር አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ
(በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ)
05/06/2026
በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ የሻሎ ቀበሌ ህብረተሰብ "ከምርጫ ድባብ ወደ ልማት እመርታ" በሚል መሪ ሃሳብ በህዝብ ተሳትፎ የሚሠሩ የመንገድ ጥገና ሥራዎችን አጠናክረው ቀጥለዋል ።
#ደልቤና :ግንቦት:28/2018 ዓ/ም በኮልሜ ወረዳ ሻሎ ቀበሌ በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሠሩ ያሉ አዳዲስ የመንገድ ከፈታዎችና ጥገናዎች በከፍተኛ የህዝብ ተነሳሽነት እየተከናወኑ ይገኛሉ ።
የሻሎ ቀበሌ አመራሮች የመንገድ ሥራውን አስመልክቶ ባስቀመጡት ሐሳብ መሠረት "ህብረተሰባችን የመንገድ ተደራሽነት ችግርን ለመቅረፍ ሲሉ በገዛ ጉልበታቸው አዳዲስ መንገዶችን የማስከፈት እንዲሁም በውሃ የተቦረቦሩትን በመጠገን ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆን ይሠራሉ " ብለዋል ።
የመንገድ ሥራው ከካርታቦ ሞራ ጀምሮ ወደ ኩርባናና ታሾና መንደራት የሚያደርስ ሲሆን ለትራንስፖርት እስከሚበቃ ድረስ በተቀጣይነት የሚሠራ መሆኑም ተመላክቷል ።
መረጃው :-የኮልሜ ወረዳ መንግሥት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ነው ።
05/06/2026
04/06/2026
#ደልቤና :የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ እና ግልጽ በሆነ መልኩ ተካሂዷል - የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር
የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ እና ግልጽ በሆነ መንገድ ተካሂዷል አለ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር።
ማሕበሩ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎና ደኅንነት ለመገምገም ያከናወነውን የምልከታ ሥራ መሠረት ያደረገ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።
በዚህም በበጎ ፈቃደኝነት የተሰማሩ 60 ታዛቢዎችን በዘጠኝ ክልሎችና በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ 136 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ማሰማራቱን ገልጿል።
በምርጫው ላይ የታዛቢ ቡድኑ ምልከታ ባደረገባቸው ጣቢያዎች በአብዛኛዎቹ ሰላማዊ እና ግልጽ በሆነ መልኩ የምርጫው ሂደት መጠናቀቁን አመልክቷል።
በምርጫ ጣቢያዎች የነበረው አጠቃላይ ሁኔታ ሁሉንም ያካተተና ስልታዊ የሆኑ መዋቅራዊ ጥሰቶች ያልታዩበት መሆኑንም ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።
በሂደቱ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በግልጽ የታየ በተለይም ነፍሰ ጡር እናቶች፣ የሚያጠቡ ሴቶች፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ድምፅ እንዲሰጡ የተደረጉበት አዎንታዊ አሠራር ተስተውሏል ነው ያለው።
ማሕበሩ አሁን ያወጣው ሪፖርት የመጀመሪያ ደረጃ መግለጫ መሆኑን በመጠቆም ከምርጫ በኋላ ያለውን ሁኔታ መከታተሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ሙሉ የመረጃ ትንተናን ያካተተ የመጨረሻ ሪፖርቱን ወደፊት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪዎቹን ለመምረጥ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱን ለመጠቀም ያሳየው ተነሳሽነት የሚደነቅ እንደሆነም አመልክቷል።
ግንቦት 27/2018 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Website
Address
Konso
Addis Ababa
