07/01/2022
Yeka wereda 07 vital event registration
This page gives full information's about the service of our offive
07/01/2022
25/04/2021
25/04/2021
The pride of African
24/01/2021
በሚበልጥ እንጂ በሚያንስ ድርጊት አንመላለስም!!!!
ዓለማችን በመልካምነት በታነጹ ብቻ ሳይሆን በፈረሱ መሪዎች ሕሊናም ትተዳደራለች። አንድ ማኅበረሰብ የመጣበትን መንገድ ቆም ብሎ እንዲፈትሽ የሚያደርጉት እንቢተኞች ናቸው። የፈጠርነው ሰው አሜን ብቻ ባይ አለመሆኑ የተሠወሩትንና የተገለጡትን ደግመን እንድናይ መንገድ ይከፍትልናል። ያለንበትን የፖለቲካ፣ የዘር፣ የሃይማኖት፣ የጾታ፣ የታሪክ ጉዳይ ከደረስንበት የቅርብ እውነታ ጋር እንድናገናዝብ ያስገድደናል። ለአብነት ያህል ፈላስፋው ዘርዐ ያዕቆብን ማንሣት እንችላለን። በተለይም ፈላስፋው ከቅዱሳት መጻሕፍት እስከ ተለያዩ የሃይማኖት እሴቶችና ተግባራት ድረስ መመርመርና መፈተሸ እንዳለበት በጽኑ ያምን ነበር። አንድን ነገር ለመቀበልና ላለመቀበል፣ ለማመንና ላለማመን አሳማኝ ምክንያት ሊኖር እንደሚገባ ያትታል። በዚህም አስተሳሰቡ ምክንያት በጊዜው እምቢታውንና ትችቱንም ያሰማባቸው ጉዳዮች ዛሬም አነጋጋሪነታቸው አልበረደም።
ዓለም በአሜን ባዮች ስለተከበበች በየጊዜው መንታ መንገዶች ላይ ቆማ ወደ ፊት ለመራመድ ታመነታለች። “ለምን?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ይዘን የመጣናቸውን ፍሬዎች በነሲብ ከመብላታችን በፊት በጥንቃቄ እንድንመዝናቸው ያነቃናል። ምክንያቱም ሁሉም የሐሳብ ፍሬ አይበላም። የተበላሹ ፍሬዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። በመዳፋችን የያዝናቸውን መልካም በረከቶችና ክፉ መርገሞችን እናነጻጽራለን። እጃችን ላይ ያለው ምንድነው? ምንስ እናድርግበት?
ለምሳሌ ዓለም በእጃቸን ነው። እናፍርሰው ወይስ እንሥራው? አገር በእጃቸን ነው። እናልማው ወይስ እናጥፋው? ቤተሰብ፣ ልጆች በእጃችን ናቸው። በመልካምነት ወይስ በክፋት እንቅረጻቸው? ትላንት በእጃችን ነበር። በታሪክነቱ ተቀብለነው ወይስ ክደነው እንለፍ? ዛሬ በእጃችን ነው። በአግባቡ እንጠቀምበት ወይስ በከንቱ እናባክነው? ነገ በእጃችን ነው። መጪውን እንለውጥበት ወይስ ትላንትን እንድገምበት? ታሪክ በእጃቸን ነው። እናድምቀው ወይስ እንሰርዘው? አንድነት በእጃችን ነው። ለሥራ እንነሣበት ወይስ ለጥፋት እናብርበት? ፍቅር በእጃቸን ነው። እንዋደድበት ወይስ እንዋቀስበት? ሰላም በእጃቸን ነው። በደኅና እንደር ወይስ እንታወክበት? በእጃችን ላይ ባሉት በረከቶች መልካምና ክፉ ነገሮችን ማጨድ እንችላለን።
የፈጠርነው ሰው እንቢተኝነት ሌላስ ምን ይሠራልናል? ብለን ልንጠይቅ እንችላለን። በእንቢተኝነቱ ተክበው የነበሩ የውሸት ተራራዎችን ይንድልናል። በበጎነት ድልድይ ፈንታ የተገነቡ የጥላቻ ግንቦችን ይሰብርልናል። ለዘመናት የሚሻገርን ተመሳሳይ ተረክ ያስቆምልናል። ለምን? ሲለን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ይከፍትልናል። የሕንጻዎችን የዓለት መሠረትነት ይፈትንልናል።
ዓለማችን በመልካምነት በታነጹ ብቻ ሳይሆን በፈረሱ መሪዎች ሕሊናም ትተዳደራለች። ራእየ ቢስ መሪዎች የእነርሱ ባልሆነ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ። “እምቢ” ሲል እነዚህን ግለሰቦች ጭምር ነው። ሁሉም መሪዎች የእውነትን መንገድ አይከተሉም። መሪ የሚወጣው ከቤተሰብና ኅብረተሰብ ውሰጥ ነው። ማኅበረሰብ የበጎነት እሴቱ ሲቀጭጭ የሚፈጠሩ መሪዎችም የዚያው ነጸብራቅ ይሆናሉ። አስተዋይ መሪ ከፈረሰ አገር፣ ማኅበረሰብና ቤተሰብ የመውጣት ዕድሉ እጅግ ዝቅተኛ ነው። አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ አሉ። ‘አሜን’ በማለት ያለፍናቸው ተራ ድርጊቶች የማይሻሩ ፈርጣማ ሥርዓቶች ሆነው ቁጭ ብለዋል። እንደ ግለሰብ፣ ማኅበረሰብና ሕዝብስ በበጎነት የተሠራ መሪ እንዲኖረን ምን ዓይነት አስተዋጽዖ አድርገናል?”
ፍርቱና “የፈጠርነው ሰው ጠቢብነት ከየት ይነሣል?” ብላ ጠየቀችው።
16/06/2020
እባካችሁ በ ጥንቃቄ ተገልገሉ። የምታዬት ፎቶ የጤና ባለሙያዎች ዛሬ 09/10/2012 አገገልግሎት ለማግኘት የሚያደርጉት ግርግር ነው ከማን እንማር እንግዲህ?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
