ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለኢድ አል አድሃ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
Semma Tiruneh_ሰማ ጥሩነህ
አገራችን ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚገጥማትን ፈተና በፅናትና በድል መሻገር የቻለችው በህዝቦቿ በተባበረ ክንድ እና አይበገሬነት ነው።
27/04/2026
የቀድሞው የአማራ ክልል አፈ-ጉባኤ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት አምባሳደር ያለው አባተ አሁን ከመሸ ማረፋችውን ሰማሁ::
አምባሳደር ያለው አባተ ከሰው ጋር ተግባቢና ቅን አሳቢ ነበሩና እግዚአብሔር ነፍሱን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን እያልሁኝ ለመላው ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመዶችና የሥራ ባለደርቦች ልባዊ መፅናናትን እመኛለሁ::
11/04/2026
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል አደረሳችሁ!!!
እንኳን ታምፁናስ ውላዋ!!!
ዝመተኛው ዘንገና ሐይቅ ትልቁ አንጡራ ሀብታችን እና የወደፊት የቱሪስት መስህብ ሁነኛ አቅማችን!!!
19/03/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447 ኢድ አል ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
ኢድ ሙባረክ!!!
03/02/2026
የዛሬ ሦስት ዓመት በጥር ወር መጨረሻ ላይ የትምህርት ገበታ የጀመርንበትን የከሣ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃውን ለማሳደግ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠን ሥራ ጀመርን::
ምንም እንኳ የትምህርት ቤቱ ግንባታ ሥራ በአከባቢው ማህበረሠብና ተወላጆች እንዲሁም ሀገር ወዳድና ለጋስ በሆኑ ኢትዮጵያዊ ባለሐብቶች እርዳታ አማካኝነት በአራት ወራት ውስጥ ማለትም ሰኔ 2015 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ትምህርት ለመጀመር ዝግጁ ማድረግ ተቻለ::
ይሁንና በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ዘገይቶ የህዝብ ጥያቄ የነበረው የዘንገና ኃይቅ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዚህ ዓመት ተማሪዎችን ተቀብሎ ትምህርት ጀምሯል::
ተማሪዎች በሠፈራቸው ትምህርታቸውን ለመከታተል የተሻለ ዕድል ተፈጥሮላቸው እንዲህ መመልከት ከደስታዎች ሁሉ በላይ ነው:: በተለይ ደግሞ 10 እና ከዚያ በላይ ኪ.ሜ ተጉዘው ለመማር ለሚቸገሩ የድሃ አርሶ አደር ለጆች ፋይዳው እጥፍ ድርብ ነው::
ድሮ ትምህርት ቤት በሰፈራችን ባለመኖሩ ትምህርታቸውን ያቋረጡ እጅግ ጎበዝ ተማሪዎችን ስናስታውስ እስካሁን ፀፀቱ ከባድ ነበር::
እነሆ ዛሬ ግን ይህ እንዳይደገም እና በተሽከርከካሪ አደጋ ተማሪዎች ህይወታቸውን እንዳያጡ ለማድረግ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት በሠፈራቸው ተገንብቷላቸዋል::
ይህ በጎ ተግባር ይፈፀም ዘንድ ገንዘብ የለገሣችሁትን አስተባብራችሁ ያሠራችሁትን የኮሚቴ አባላት እጅግ ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረብሁ የባንጃ ወረዳ እስተዳደርም በጀት መድቦ ትምህርት በማስጀመሩ ለማመስገን እወዳለሁ::
የብዙ ዓመታት አኩሪ ገድል
የህዝብ አርበኝነትና ተጋድሎ ምልክታችን!!!
29/01/2026
በቅድሚያ እንኳን ለ86ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ሁላችንንም በሠላም አደረሰን!!!
ታምፁናስ ውላዋ!!!
ህዝባችን ለሀገራችን ሉዓላዊነትና አንድነት በየጊዜው ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል:: ታላቅ ገድልም ፈፅሟል:: አርበኝነቱንም አስመስክሯል:: በእነዚህ ጊዚያት ሁሉ ፈረሰኛ እና ፈረስ ታላቅ ቦታ ነበራቸው::
ዛሬም ይህ ታላቅ የሀገር አርበኝነትን ለማሰብና ለመዘከር ሲወርድ ሲወራረድ እነሆ 86ኛ ዓመቱን ለማክበር ዋዜማው ላይ ደርሰናል::
በመሆኑም የአባቶቻችንን የጀግንነት ገድልና ገናና ታሪክ በደማቅ አሻራ ለማስቀመጥ ትውልዱ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል:: ይኸው ጅምር ሥራ ዳር እንዲደርስም ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይገባናል::
አርቴን ውላ ይዛሂ እንኳን ዴስ ኒናስ !
ካቮ ታምፁናስ!!!
19/01/2026
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ጥምቀት በሠላም አደረሳችሁ:: አደረሠን!
10/01/2026
የብልፅግና ፖርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የስድስት ወር አፈፃፀም ግምገማና ቀጣይ አቅጣቻዎች ላይ ለመወያዬት ተፈጥሮ ሁሉን ነገር በተቸረቻትና የበለጠ እየተዋበች በምትገኘው ባህር ዳር ከተማ ተገኝተናል::
በመሆኑም በግምገማችን ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የፖለቲካና የእቅም ግንባታ ሥራዎች ማለትም የሠላም ግንባታ ሥራችን አፈፃፀም፤ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሠራናቸው ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶችን፤ የገዥ ትርክት ግንባታ ሥራችን የደረሠበትን ደረጃ፤ የአገልግሎት አሠጣትና የሥራ ዕድል ፈጠራ የፖለቲካ እንቅስቃሴያችን ፤ የአመራርና የአባላት ሁኔታችንና እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሥራችን በጥልቀት ይገመገማሉ::
ከዚህ ባለፈ በቀጣይ ፖለቲካዊ ሥራዎች በተለይም የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ስኬታማ በሆነ መልኩ ለመፈፀም የሚያስችሉ ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር የሚሠሩ ሥራዎች ዙሪያ መግባባት እንፈጥራለን::
በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም በመገኘትም ስታድየሙ የደረሰበትን ድንቅ አፈፃፀም ከመመልከት ባለፈ የወንድማማችነትና እህትማማችነትን የሚያጠናክር የወዳጅነት ጨዋታ አድርገናል::
በተረፈ የአማራ ክልልና ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለአደረግልን ደማቅ አቀባበልና መስተንግዶ ከልብ አመሠግናለሁ::
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa , Arat Killo
Addis Ababa
200080
