16/10/2025
ካዛ እንደ አዲስ
በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ሰፋፊ ፕሮጀክቶችና ሰው ተኮር ተግባራት በትኩረት ጥራትንና ፍጥነትን ባማከለ አግባብ እየተተገበሩ ይገኛሉ። ከዚህ አንጻር የአድስአበባን ብልጽግናዊ ተምሳሌትነት ዕውን ለማድረግ በየካ ክ/ከተማ ታላላቅ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ ይገኛሉ።
የካ በከፍታ ላይ የምትገኝ እንደመሆኗ መጠን የመዲናዋ የከፍታ ምልክት ለመሆን እጅግ አመርቂ ስራዎችን ተከውነዋል። አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና ውብና ነዋሪዎቿ ተስማሚ ከማድረግ በዘለለ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በትጋት እና በቁርጠኝነት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት እየተጠናቀቁ ናቸው፦ በየካ ካዛ!
ካዛን የከተማዋ ማራኪ የውበትና የታሪክ፤ የምርምርና የዕውቀት ማእከል ለማድረግ ከሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች በተጨማሪ ፕሮጀክቶቹ የአካባቢውን ገጽታ በመቀየር የስራ ዕድል በመፍጠርም ታላቅ ሚና ያላቸው ባለዘርፈ ብዙ ናቸው።
ወረዳችን ፕሮጀክቶች ተጠናቀው በተመረቁ ማግስት ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን የሚጀምር ከምንም በላይ ለዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በመትጋት ለሰው ተኮር የልማት ስራዎች ቅድሚያ በመስጠት እየሰራ ይገኛል። ወረዳው ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጡ ዋነኛ ቁልፉ ሰው ተኮር ልማቶች ላይ ትኩረት ማድረጉ ነው።
18/08/2025
ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ።
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡
በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡
በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ነው ያለው።
ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21 ሺህ 492 ወደ ብር 39 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።
የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 የሚሻሻል መሆኑን ገልጿል።
ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አስታውቋል።
ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል ያለው ኮሚሽኑ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ብሏል።
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፦https://www.facebook.com/100069672641659/posts/1084297830569295/?app=fbl
14/07/2025
የተፈጥሮ ህግ!
በመትከል ማንሰራራት አረንጓዴ መሬት
ዘመንን መዋጀት ማፅናት የወል እውነት
የትውልድ ምንዳ ተሻጋሪ ውርስ
በህብራዊ ትጋት ኢትዮጵያ ስትለብስ
አረንጓዴ አሻራ ጊዜን የቀደመ
የተፈጥሮ ሚዛን ስብራት ያከመ
ምድርን ተንከባከብ አምላካዊ ቃሉ
በእሷ ኑረህ ትጋ አስውባት በሁሉ
ምግብና መጠጥህ መኖሪያህ ነች ጥላ
በላብህ በወዝህ ጥረህ ግረህ ብላ
አትራቆት መሬት አረንጓዴ አልብሳት
በመደመር መንገድ በአርበኝነት ትጋት
ነገን ዛሬ ትከል ይኑርህ አሻራ
ምንዳን ለትውልዱ እናውርስ በጋራ
የተፈጥሮ ህግ ነው በጠበቅ መሬትን
በአረንጓዴ አሻራ እንቀጥል ህይዎትን‼
17/11/2024
አምስት ወርቃማ ዓመታትን በስኬት እንደተጓዝን በተግዳሮቶች ሳንበረከክ በጋራ ተመን የጋራ ሀገርን ዕውን እናደርጋለን።
ወርቃማ 5 ዓመታት
!"
https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/
Yekaprosperity.org.et
12/12/2023
ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በፉክክር እና በትብብር መካከል ሚዛን በመጠበቅ፣ ተቃርኖዎችን በማስታረቅ የሚጓዝ መሆን እንዳለበት ያምናል።
ሃገራዊ ክብርን ያስቀደመ፣ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ፣ ጎረቤት አገራትን ያስቀደመ የውጭ ግንኙነት፣ ቀጣናዊ ትብብርና የኢኮኖሚ ውህደት የሚሉት ብልፅግና ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አንኳር ጉዳዮች ናቸው።
የፓርቲያችን የውጭ ግንኙነት እሳቤ የሚመጨው ጥቅምን ከማሳደድ ሳይሆን ግንኙነትን እና መልካም ትብብርን ከማስቀደም ነው። በዚህም ረገድ ብልፅግና ግንኙነትን ማደስ ብሄራዊ ጥቅምን ለማስከበር አዎንታዊ ሚና እንዳለው ያምናል።
ብሄራዊ ጥቅም በአንድ ወገን ሊበየን የማይችል እና ወጥና የማይለወጥ እንዳልሆነ ከግንዛቤ በማስገባት የአገሪቷን እሴቶች ተከትሎ በትብብርና በንግግር ጥቅምን ማስከበር እንደሚገባ ብልፅግና ያምናል።
የውጭ ግንኙነታችን ሌላው አንኳር ነጥብ ብሄራዊ ክብርን በማስጠበቅ አገራችን ሉዓላዊነቷን አረጋግጣ፣ ታፍራና ተከብራ የምትኖር ጠንካራ አገርን በማረጋገጥ ረገድ ብልፅግና ተግቶ ይሰራል።
የለውጡ አመራር ወደ ሃላፊነት ከመጣ በኋላ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ዜጎችን ከነበሩበት ፈታኝ ሁኔታ በማላቀቅ ወደ ውድ አገራቸው እንዲመለሱ የማድረግ ተግባር ተከናውኗል። የዜጎች ክብር የብሄራዊ ክብራችን አይነተኛ መገለጫ እንደሆነም ፓርቲያችን ያምናል። ለዚህም ጠንክሮ ይሰራል።
ፓርቲያችን ከጎረቤት አገራት ጋር የሚኖር ግንኙነት በመነጋገርና በመተባበር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ሲሰራ ቆይቷል፤ ወደ ፊትም አጠንክሮ ይቀጥልበታል። የኢትዮጵያና የጎረቤቶቿ እጣ ፈንታ የተሳሰረ በመሆኑና የጋራ ጥቅማችንን መሰረት ያደረገ መተጋገዝና ትብብር መመስረት እንደሚገባ ብልፅግና ያምናል።
በቀጠናው ከሚገኙ አገራት ጋር የሚፈጠር ግንኙነት በፍፁማዊ የጋራ ጥቅም ላይ ተመስርቶ ቀስ በቀስ እያደገ ሄዶ ወደ ጠንካራ ምጣኔ ሃብታዊ ጥምረት እንዲያድግ ፓርቲያችን አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ያደርጋል።
ፓርቲያችን የጋለ የአገር ፍቅር ስሜት ያላቸው፣ በትምህርትና ስልጠና የካበተ ልምድ ያላቸውና በማህበረሰቡ ቅቡልነትና እውቅና ያላቸው ግለሰቦችን በተለያዩ አገራት በአምባሳደርነት በመመደብ የአገሪቷ ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር ይሰራል።
በዲፕሎማሲው ጎራ ብቃት ያላቸው ዲፕሎማቶችን ለማፍራት የሚያስችሉ የምርምርና የስልጠና ልህቀት ማዕከላትን በማስፋፋት ኢትዮጵያ ጠንካራ የውጭ ግንኙነት እንዲኖራት ፓርቲያችን ይተጋል።
የተጠናከረ የውጭ አገራት መስተጋብርን በመፍጠር ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ወደ አገራችን እንዲመጣ ዲፕሎማሲያችን አብይ ሚናውን እንዲወጣ ብልፅግና ያላሰለሰ ስራ ይሰራል።
11/12/2023
ዴሞክራሲና እውነተኛ ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ሊነጣጠሉ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች!
ለፌዴራሊዝም ስርዓት ግንባታ ከሚያስፈልጉ ወሳኝ ነገሮች መካከል ዴሞክራሲ ዋነኛው ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ አብሮነት የሌለበት ፌዴራሊዝም እውነተኛ ፌዴራሊዝም ሊሆን አይችልም።
ለዚህም ነው ዴሞክራሲና ፌዴራሊዝም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው የሚባለው፡፡
ዴሞክራሲያዊ ህብረ-ብሄራዊነት የቋንቋ፣ የባህል፣ የስነ-ልቦና፣ የሀይማኖትና ተጓዳኝ ልዩነት አለን ብለው የሚያምኑ በአንድ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦችን አስማምቶ ማልማትና ማበልፀግ የሚችል አማራጭ ነው፡፡ ይህንን በአግባቡ የተጠቀሙበት ሀገሮች የልማትና የብልፅግና ማማን ተጎናፅፈዋል፡፡
ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራሊዝም ከማንነት ጋር የተያያዘ ብዝሀነት በሌለባቸው ማለትም አንድ ብሄር፣ አንድ ሀይማኖት ላላቸው ሀገራት ትልቅ አጀንዳ ሊሆን አይችልም፡፡
ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራሊዝም እንደ እሳቤ ሊነሳ የሚችለውና የሚመረጠው ብዝሀ-ማንነት ላላቸው ሀገሮች መሆኑን ስዊዘርላንድ፣ ካናዳ፣ ኔዘርላንድ እና ሌሎች ልዩነቶቻቸውን በማቻቻል ብዝሀነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሰያዊ አንድነት የገነቡ አገራትን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።
ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ህዝቦች ማንነታቸውን ሳይክዱ በመግባባትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት የሚገነቡበት ስርዓት ነው፡፡
የምንገነባው ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያዊያንን እውነታ የተገነዘበ እና ከነባራዊ እውነታው የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከሌሎችም ሀገራት ስኬትና ውድቀት ተሞክሮ የቀሰመ ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶች ያሉን፣ ረጅም ዘመናትን በአብሮነት ያሳለፍን፣ በጋራ ተጋድሎአችን አኩሪ ታሪክ ያስመዘገብን ብቻ ሳይሆን በጉዞአችን ከፍተኛ የባህል፣ የወግና ልማድ ውህደትና ጠንካራ ትስስርም ፈጥረናል።
ይኸው የባህልና የወግ ልማድ ትስስር ሂደት የቋንቋ መወራረስን ያጎለበተ ጭምር በመሆኑ የህዝብ ለህዝብ ትስስሩ ያደገና በሂደት እየተገነባ የመጣ ነው፡፡
በጋብቻና በልዩ ልዩ የደምና ስጋ ትስስር በተገነቡ የአብሮነት እሴቶች የተጋመድን መሆናችንንም ማንም የሚረዳው እውነታ ነው። እነዚህ የኢትዮጵያውያን የአብሮነት እሴቶች ለህብረ-ብሄራዊ ፌደራሊዝም ወይም ለእውነተኛ ፌደራሊዝም ግንባታ መሰረቶች ናቸው፡፡
ህብረ-ብሄራዊ ህዝቦች የቆየ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው ናቸው፡፡ የቆየ ታሪካዊ ትስስር ብቻ ሳይሆን የወደፊት የጋራ ተስፋ ያነገቡ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦችን ወንድማማችነትና እህትማማችነት የማጎልበት ትልቅ እምነትም ተጥሎበታል ዴሞክራሲያዊና ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም፡፡
ብሔር ብሔረሰቦች የአካባቢያቸውን ጉዳይ በራሳቸው በነፃነት ማስተዳደርና መወሰን የሚችሉት ዴሞክራሲ ሲዳብር ሲሆን በአገር አቀፍ ጉዳይ ላይ ተመጣጣኝ፣ ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ሊወሰኑ የሚችሉትም ዴሞክራሲ ሲያብብ ነው፡፡
ህብረ-ብሄራዊነት በሰፈነባቸው ኢትዮጵያን በመሳሰሉ አገራት ዴሞክራሲን ማረጋገጥ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡
ህብረ-ብሄራዊነት የቋንቋ፣ የሀይማኖትና ሌሎች ልዩነቶች ለሀገራዊ አንድነት ስጋት ይሆናሉ ብሎ አያምንም፡፡ ህብረ-ብሄራዊነት በሰፈነበት ሁኔታ ብሄርተኝነት ከዴሞክራሲ የተነጠለ ከሆነም የከረረ ብሄርተኝነት ይሰፍናል፡፡
ህብረ-ብሄራዊነት ተፈጥሮዋ በሆነችው ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ ለመኖር የሚወስኑትና የሚችሉት ዴሞክራሲና ፌደራላዊ ስርዓት ሲረጋገጥ ነው፡፡ ህብረ- ብሄራዊነት በዴሞክራሲያዊነት ከተቃኘ መልክአምድርን ጨምሮ ሌሎች ትስስሮች ይበልጥ ይጋመዳሉ።
ህብረ-ብሄራዊነት በአግባቡ የሚስተናገደው ዴሞክራሲያዊ ውክልናን በማረጋገጥም ነው፡፡
ህብረ-ብሄራዊነት በአግባቡ የሚስተናገደው ብሔር ብሔረሰቦች የራሳቸውን አከባቢያዊ ጉዳዮች በራሳቸው እየወሰኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም መስኮች የተመጣጠነ ዴሞክራሲያዊ ውክልናቸው ሲረጋገጥ መሆኑን በመረዳት ከአገራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ባይተዋር ሆነው የቆዩ ብሔር ብሔረሰቦች ፍትሃዊ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተለይም ከለውጡ በኋላ ተስፋ ሰጭ ተግባራት መከናወን ጀምረዋል፡፡
ዴሞክራሰያዊ ስርዓት በተግባር መገለፅ ሲችል እና በክልሎች መካከልና ክልልሎች ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ያላቸው ዴሞክራሰያዊ ግንኙነት ሲጠናከር በፌዴራላዊ ስርዓት የሚፀናው ህብረ-ብሔራዊ አብሮነትን እንደሚጎለብት በማመን በትኩረት ይሰራል።
ዴሞክራሲ ሲቀጭጭ ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ይታመማል። ከአብሮነት ይልቅ ተገንጣይነት ከተቀነቀነ ፌዴራሊዝም ይታወካል፤ በአንድነት ስም አንድ አይነትነት ከተሰበከ ፌዴራሊዝም ይመነምናል፤ ስርዓት አልበኝነት ይነግሳል፤ የአገር እና የህዝብ ህልውናም አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በተለያዩ አገራት በተጨባጭ እየሆነ ያለውና አገራችንንም ዋጋ እያስከፈለ ያለው ጉዳይም ይኸው ነው።
ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ብዝሀነት በአግባቡ እንዲስተናገድ ፅኑ መሰረት ነው። እውነተኛ ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ደግሞ ብዝሀነትን እንደ ስጋት ሳይሆን እንደ ፀጋ በመቁጠር ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት መዳበር መደላድል ይፈጥራል። ፓርቲያችንም እውነተኛ ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም እና ዴሞክራሲ የብዝሀነት ፀጋ ላላት አገራችን ወሳኝ መሆናቸውን በመረዳት ለተግባራዊነታቸው ህዝባችንን ከጎኑ አሰልፎ ቀን ከሌት ይተጋል።
መልካም የስራ ሳምንት
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
11/12/2023
የመደመር እሳቤ ኃይል በማስባሰብ መርህ ያምናል። አብሮ የማደግ እሴትም እንዲዳብር ይሠራል!
ብቸኝነት ጉድለት መሆኑንና ጉድለትም እንደሚያስከትል መደመር ይረዳል። ጉድለትን ሟሟያ ኃይል የማሰባሰብና በጋራ ለማደግም አማራጭ ነዉ ።መደመር ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ማጠናከሪያ ሰንሰለት ሲሆን የብዝሃነትን ተፈጥሯዊነት መረዳት፣ መቀበልና ማክበር ደግሞ የመደመር እሳቤ ተቻችሎ የመኖር አንዱ መገለጫ ነዉ።
የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ የፖለቲካ አመለካከት ወዘተ... ልዩነቶች ተፈጥሯዊ ፀጋዎች፣ ህብረ ቀለማዊ ዉበቶች በመሆናቸዉ ከፉክክርና ከመገፋፋት ይልቅ ለትብብር ቅድሚያ በመሥጠት ለሀገር ግንባታዉ ሂደት መደላድል በጋራ መሠለፍ ጠቃሚ ነዉ።
ከፉክክር ይልቅ ትብብርን ማፅናት ለጋራ ብልጽግናዉ ጉዞ መሳካት መሠረት ነዉ። 'የኔንና እኔን ብቻ ' ከሚል ቁንፅል እይታ ተሻግሮ የ ' እኛናት' ን እሳቤ ማጠናከር ኢትዮጵያ ከተጋረጡባት ቀዉሶች እንድትወጣ ድርሻን ማበርከት ይችላል፡፡
ልዩነቶችን ያከበረ እሳቤ መፍጠር ፣ እሳቤዉንም የጋራ በማድረግ ትልቋ ኢትዮጵያ በሚመጥናት የትልቅነት ደረጃ ላይ እንድትደርስ የዜግነትና የሞራል ኃላፊነታችንን እንወጣ።የጠላቶቻችን የጥፋት አጀንዳ በቀላሉ ሊመክን የሚችለዉ በመደመር እሳቤ ዉስጥ ሆነን ትግላችንን ሰናጠናክር ነዉ።
01/10/2023
#ኢሬቻ በውብ #ህዝቦች የሚከበር ውብ #ባህል ነው!
የኢሬቻ ባህል #እኩልነት እና #አንድነት የሚሰበክበት ነው።
በዚህ ከምንጊዜውም በላይ አንድነታችን #ለሀገራችን በሚያስፈልግበት ሰዓት ላይ እንዲህ #አንድነትን የሚያጠናክሩ ውብ #ባህሎቻችን መከበራቸው ለሀገር ፋይዳው የጎላ ነው።