Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

Share

Ethiopian Electric Utility is a public enterprise with the main responsibility of distributing electric power across the country.

Official page of Ethiopian Electric Utility.

01/06/2026

የተቋረጠው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመልሷል

ከደብረታቦር - አላማጣ 230 ኪቮ ከፍተኛ ሃይል አስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ከጋሸና ሰብስቴሽን ኃይል በሚያገኙት የፍላቂት፣ ገረገራ፣ መቄት ወረዳ፣ ጋሸና ከተማ፣ ዋድላ ወረዳ፣ ዳውንት ደላንታ፣ ጋዞ አጎት ወረዳ፣ ግዳን በከፊል እና ላስታ ወረዳ እንዲሁም ድብኮ ከተማ እና አካባቢው ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመልሷል።

የጥገና ስራ ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁን ክቡራን ደንበኞቻችን ከልብ እናመሰግናለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎ

01/06/2026

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

በአላማጣ-ኮምቦልቻ መስመር ብልሽት ምክንያት ዛሬ ግንቦት 24/2018 ከጠዋቱ 4:05 ጀምሮ በወልዲያ ከተማ፣ ስርንቃ፣ መርሳ፣ ጊራና፣ ወርጌሳ፣ መቻሬ ውሃ፣ አመያ መጫ፣ ሮቢት፣ ጎብየ፣ ሀራ እና ጭፋራ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።

በተጨማሪም ከደብረታቦር - አላማጣ 230 ኪቮ ከፍተኛ መስመር ማስተላለፊያ ብልሽት ምክንያት ከጋሸና ሰብስቴሽን ኃይል የሚያገኙት ፍላቂት፣ ገረገራ፣ መቄት ወረዳ፣ ጋሸና ከተማ፣ ዋድላ ወረዳ፣ ዳውንት ደላንታ፣ ጋዞ አጎት ወረዳ፣ ግዳን በከፊል እና ላስታ ወረዳ እንዲሁም ድብኮ ከተማ እና አካባቢው ላይ የኃይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ችግሩን ለመፍታት እየሰራ ሲሆን፣ ጥገናው እስከሚጠናቀቅ በትዕግስት እንድትጠብቁ በትህትና እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

31/05/2026

የተቋረጠው አገልግሎት ተመልሷል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ33 ኪ.ቮ ገቢ መስመር ላይ የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን በይርጋለም እና ዙሪያው አፖስቶ፣ ሎክ አባያ ፣ለኩ ፣በንሳ፣ ዳዬ፣ በዙሪያ ያሉ ሳተላይቶች ላይ ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ተመልሷል።

በተመሳሳይ ከጋምቤላ- ዳምቢዶሎ 66 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኃይል አስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በቄለም ወለጋ ዞን የዳምቢዶሎ ከተማ፣ በዳምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ፤ በሙጊ ከተማ፣ በሮገበቢያ ከተማ እና አካባቢዎቻቸው ተቋርጦ የቆየው የሃይል አቅርቦት ተመልሷል።

ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ስራ ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ስለጠበቃችሁን ከልብ እናመሰግናለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

31/05/2026

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

በጋምቤላ- ዳምቢዶሎ 66 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኃይል አስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በቄለም ወለጋ ዞን የዳምቢዶሎ ከተማ፣ በዳምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ፤ በሙጊ ከተማ፣ በሮገበቢያ ከተማ እና አካባቢዎቻቸው የሃይል አቅርቦት ተቋርጧል።

የተቋረጠውን የሃይል አቅርቦት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን እየገለፅን፤በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችንብልሽቱ ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

31/05/2026

የጥገና ሥራ ለማከናወን የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ 33 ኪ.ቮ ገቢ መስመር ላይ የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን በይርጋለም እና ዙሪያው አፖስቶ ፣ሎክ አባያ ፣ለኩ ፣በንሳ፣ ዳዬ፣ በዙሪያ ያሉ ሳተላይቶች ላይ የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል።

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Photos from Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት's post 30/05/2026

ለውድ ደንበኞቻችን መልካም ዜና ! የቅዳሜ ከሰዓት ልዩ ሥራ ዘመቻ ተጀምሯል

​ለቀልጣፋ አገልግሎት ምንጊዜም የምንተጋው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ በሥራ መደራረብ ምክንያት ሳይጠናቀቁ የቆዩ ጉዳዮችን በፍጥነት ለመቋጨት የሚያስችል ልዩ የሥራ ዘመቻ በይፋ ጀምሯል!

​ይህ ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ የሚከናወን ሲሆን፣ የእርስዎ የሆኑ በእንጥልጥል ላይ የቆዩ ጉዳዮችን ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

​በዘመቻው ምን ምን አገልግሎቶችን ያገኛሉ ?

• ​💡 አዲስ ኃይል ማገናኘት እና የጥገና ሥራዎች፣

• ​💳 የሽያጭ አገልግሎት እና የካርድ መሙላት፣

• ​💬 ለረጅም ጊዜ ሳይፈቱ የቆዩ ማናቸውንም የቅሬታ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እና ሌሎች የደንበኞች ጉዳዮች።

በአሁኑ ወቅት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ዘመቻውን በይፋ በመቀላቀል አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ ሌሎች ሪጅኖች እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትም በተከታታይ ዘመቻውን ተቀላቅለው እርስዎን ለማገልገል ዝግጁ ይሆናሉ።

​⏳ ያስታውሱ፡ ይህ ልዩ ዕድል የሚቆየው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ብቻ ነው።

​ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #ለደንበኞቻችን #ቅዳሜከሰዓት #ቀልጣፋአገልግሎት

Photos from Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት's post 30/05/2026

38 የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

በኦሮሚያ ክልል አገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አስር ወራት 28 የገጠር ቀበሌዎችን ከዋናው የኃይል ማከፋፈያ መስመር (ግሪድ) ጋር ለማገናኘት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ 29 ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድረግ የዕቅዱን 103.57 በመቶ ማሳካት ችሏል።

በዚህም መሰረት በዋናው ግሪድ የኃይል አቅርቦት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሆኑት ቀበሌዎች በሪጅን ሲታዩ በጭሮ 9፣ በሻሸመኔ 9፣ በአዳማ 5፣ በነቀምቴ 4፣ በአምቦ 4፣ በጅማ 3፣ በሮቤ 2 እንዲሁም በሸገር እና በመቱ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ቀበሌዎች ናቸው።


እነዚህን ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት 272.37 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር እና 504.04 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ ሲሆን፣111 ትራንስፎርመሮችም ተተክለዋል።

በተጠናቀቁት ቀበሌዎች 12 ሺህ 112 አዳዲስ ደንበኞች የቆጣሪ ተከላ ተደርጎላቸው የቀጥታ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ከዋናው የሃይል ቋት ግሪድ ርቀው የሚገኙ የገጠር አካባቢዎችን በታዳሽ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።


በዚህም በኦፍ ግሪድ (Off-grid) የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክት 16 ቀበሌዎችን የኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ 9 ቀበሌዎችን ማገናኘት ችሏል።


እነዚህ የኦፍግሪድ ተጠቃሚ የሆኑት አካባቢዎች በጭሮ ሪጅን 8 ቀበሌዎች እንዲሁም በሮቤ ሪጅን 1 ቀበሌ ሲሆኑ፣ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ 20.44 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር እና 64.46 ኪ.ሜት የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል።

እንዲሁም 25 የተለያዩ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች የተተከሉ ሲሆን፣ በዚሁ አማራጭ የኃይል አቅርቦት 1 ሺህ 135 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል።

ባለፉት 10 ወራት በኦሮሚያ ክልል በሁለቱም የኃይል አማራጮች 38 የገጠር ቀበሌዎችንና ከ13 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን ተጠቃሚ ያደረገው ፅህፈት ቤቱ፣ለተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም የኃይል አቅርቦት በማድረስ ለአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መነቃቃት ትልቅ መሠረት ጥሏል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

30/05/2026

🚗 የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎቹ የትይገኛሉ❓

✨ ሰዓሊተ ምህረት – ከማዕድን ሚኒስቴር ፊት ለፊት
✨ ፒያሳ – ኤሌክሪክ ህንፃ ግቢ ውስጥ | በቀድሞው የአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት

💵 የአገልግሎት ክፍያ

☑️ ከምሽቱ 4:00 እስከ ጠዋቱ 12:00 ድረስ):-14.85 ብር
☑️ ከጠዋቱ 4:00 አስከ ቀኑ 11:00 ድረስ):- 16.57 ብር
☑️ ከቀኑ 11፡00 እስከ ምሽቱ 4፡00 እንዲሁም ከጠዋቱ 12፡00 እስከ 4:00 ድረስ):-18.28 ብር

🚗⚡️

29/05/2026

ተቋርጦ የቆየው የሃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመልሷል

በኃይል ማሰራጫ መስመር ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት ተመልሷል።

በሸገር ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች የተቋረጠውን የሃይል አቅርቦት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን እየገለፅን፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ችግሩ ተፈትቶ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ስለጠበቃችሁን ከልብ እናመሰግናለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

29/05/2026

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

በኃይል ማሰራጫ መስመር ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች አንዳንድ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡

በአሁን ስዓት አብዛኞቹ መስመሮች የተመለሱ ሲሆን ቀሪዎችን ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን እየገለፅን፤ክቡራን ደንበኞቻችን አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Mexico, Singatera, Nib Bank HQ, Floor 7/17
Addis Ababa
1000