ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ - Freedom and Equality Party

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ - Freedom and Equality Party

Share

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ
ሚዛናዊ እና ምክንያታዊ ፖለቲካ

03/06/2026

የነእፓ ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ ያስተላለፉት መልእክት።

የተከበራችሁ የነእፓ ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት
የተከበራችሁ የነእፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት
የተከበራችሁ የብሄራዊ፣ የክልል እና የዞን ምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴዎች አባላት
የተከበራችሁ የነእፓ አባላት፣ ደጋፊዎች እና መላ የሀገራችን ህዝቦች

በቅድሚያ እጅግ የከበረ ሰላምታየ በያላችሁበት ይድረሳችሁ

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማ ለመሆን ላለፉት ጥቂት ወራት በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት ጊዜያችሁን፣ ጉልበታችሁን፣ ገንዘባችሁን፣ እውቀታችሁን ሳትሰስቱ ለምርጫ ስራ በማዋል ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ተወጥታችኋል። የፖለቲካ ትግል ከፍተኛ መስወአትነት የሚጠይቅ፣ ፍሬው ረዢም ጊዜ እና ትእግስት የሚሻ ስራ እና ኃላፊነት ነው። ከሰራነው ስራ እና ከድካማችን አንጻር የምንጠብቀው ውጤት ትንሽ ሊዘገይ ይችል ይሆናል። ውጤት መምጣቱ ግን አይቀሬ ነው።

ባለፉት በርካታ አመታት እንደ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በጋራ አላማ ዙሪያ ተሰባስበን፣ በአንድ ሀገር ልጅነት እጅ ለእጅ ተያይዘን በሚዛናዊነት እና ምክንያታዊነት የትግል ስልት የሰለጠነ ፖለቲካ አካሂደናል። በዚህም በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ ትንሽም ብትሆን በጎ አበርክቶ አስቀምጠናል ብለን እናምናለን።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እጅግ በርካታ ስራዎችን እየተመካከርን እና እየተጋገዝን ሰርተናል። ለሀገራችን ህዝቦች በየዘርፉ አማራጭ ፖሊሲዎችን አቅርበናል። ሚዛናዊ እና ምክንያታዊ ፖለቲካን በተግባር አሳይተናል። በእርግጠኝነት የዚህ ስራችን ውጤት ለፓርቲያችን ብሎም ለሀገራችን እና ለህዝባችን ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እናያለን።

በ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ በተለያዩ ክልሎች የክልል ምክር ቤት እንዲሁም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይብዛም ይነስም ወንበሮችን እንደምናሸንፍ እንጠብቃለን። የምርጫውን የተጠቃለለ ውጤት በሚቀጥሉት ቀናት የምናውቅ ይሆናል። በዚህ ምርጫ ከምናሸንፈው የወንበር ቁጥር ባልተናነሰ ምርጫን የማስተዳደር እና የመምራት ከፍተኛ ልምድ አግኝተናል።

በዚህ ምርጫ ያገኘነው ተሞክሮ እና ልምድ በ6ኛ ጠቅላላ ምርጫ ካገኘነው ልምድ ጋር ተዳምሮ ፓርቲያችን በቀጣይ ምርጫዎች የተሻለ ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ ፋይዳ አለው ብየ አምናለሁ። በምርጫ የነበረንን ተሳትፎ፣ ጠንካራ ጎኖች እና ውስንነቶች በሚገባ አጠናቅረን ለቀጣይ የምርጫ ተሳትፎአችን ግብአት እንዲሆነን ሰንደን እናስቀምጣለ።

ውድ የነእፓ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች

ፓርቲያችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማ ይሆን ዘንድ ላደረጋችሁት ከፍተኛ መስዋአትነት እና ለከፈላችሁት ዋጋ በብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስም የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ። በተመሳሳይ ነእፓን ወክለው በምርጫ ለተሳተፉ እጩዎቻችን፣ ለምርጫ ስራችን ድጋፍ ላደረጉልን የነእፓ አባላት እና ደጋፊዎች፣ በምርጫው እለት በምርጫ ጣቢያዎች እና ምርጫ ክልሎች ለተሳተፉ የፓርቲ ወኪሎቻችን፣ በምርጫው ድምጻቸውን ለሰጡን ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ድምጻቸውን ላልሰጡን፣ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ድጋፍ ላደረጉን የጸጥታ አካላት እና የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ሌሎች በተለያየ መንገድ ድጋፋቸውን ለሰጡን ሁሉ ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ።

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ባገባደድንበት እለት ማግስት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ፣ ወደ ቀጣይ ትግል እና ቀጣይ ስራዎች ለመሸጋገር ራሳችንን እንድናዘጋጅ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ትግላችን በሀገራችን ነጻነት፣ እኩልነት እና ፍህት እስኪረጋገጥ ይቀጥላል።

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
አብዱልቃድር አደም
ሊቀመንበር

ግንቦት 25፣ 2018

01/06/2026

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና ህግ ጉዳይ ዘርፍ ሀላፊ ጠበቃ አዲስ መሀመድ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

ለጠበቃ አዲስና በምርጫ ክልሉ ለሚወዳደሩ የነእፓ እጩዎች መልካም እድል እንመኛለን።

Photos from ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ - Freedom and Equality Party's post 01/06/2026

በኢፌድሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታና የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወ/ሮ ነቢሀ መሀመድ አብድልሀኪም በሀላባ ምርጫ ክልል ቁጥር አንድ በሸኖ ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

01/06/2026

ጠንካራ ፓርቲ!! ጠንካራ መንግስት!!
ጠንካራ ሀገር!!

01/06/2026

አንድ ድምጽ ልዩነት ያመጣል!!
በየትኛውም ሁኔታ ድምጽዎን ለነእፓ ይስጡ!!

Photos from ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ - Freedom and Equality Party's post 01/06/2026

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ዘኑር አብዱልወሀብ በቅበት ምርጫ ክልል ሻድገር አምቢቾ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ሰጡ

ለአቶ ዘኑር እና በክልሉ ለሚወዳደሩ የነእፓ እጩ ተወዳዳሪዎች መልካም እድል እንመኛለን

Photos from ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ - Freedom and Equality Party's post 01/06/2026

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር አብድልቃድር አደም ድምፃቸውን ሰጡ።

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብድልቀ‍ኣድር አደም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ወረዳ 4 ምርጫ ክልል 24 በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

01/06/2026

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም
ለ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል 24 ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 4
አሊቦ ግሪን ኤሪያ ምርጫ ጣቢያ
(ዓለም ባንክ አደባባይ አካባቢ)
ከረፋዱ 3፡30 ድምጻቸውን ይሰጣሉ።

01/06/2026

ነጻነትን ይምረጡ!!
እኩልነትን ይምረጡ!!
ፍትህን ይምረጡ!!
ልማትን ይምረጡ!!
ሰላምን ይምረጡ!!

01/06/2026

መላ ኢትዮጵያ ብዕርን ይመርጣል!!
ብዕርን ይምረጡ !!

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Adot Building
Addis Ababa