10/02/2026
በቅ/ፅ/ቤቱ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ
በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ንግድ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የደረጃ "ሀ" እና የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች አዲስ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን በሆኑት ወ/ሮ የሁሉ ዋሴ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን ስልጠናው የገቢ ግብር አዋጁ ማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ዋና ዓላማዎች፣ የግብር ከፋይ ደረጃዎችና አከፋፈል ሁኔታዎች፣ ስለ አማራጭ አነስተኛ ግብር አከፋፈል፣ ለበጎ አድራጎት ዓላማ የሚደረጉ ስጦታዎች፣ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ስላለባቸው ግብር ከፋዮች ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
እንዲሁም የጥሬ ገንዘብ ክፍያ አፈጻጸም ዘዴዎች፣ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ምጣኔዎች፣ የኪራይ ገቢ ግብር ምጣኔዎች፣ በንግድ ሥራ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች፣ ሌሎች (ሠንጠረዥ “መ” ) ገቢዎች፣ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሶ ስለማስቀረት እና ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ላይም ስልጠናው ተሰጥቷል።
በመድረኩም ከሠልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ድጋፍ እና የህግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር የስራ ሂደት በሆኑት በአቶ መላኩ ደርሶ እና የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን በሆኑት ወ/ሮ የሁሉ ዋሴ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
16/01/2026
በቅ/ፅ/ቤቱ አዲስ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

11/12/2025
በቅ/ፅ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጡን አስመልክቶ ከመማክርት ጉባኤ አባላት እና ከነጋዴ ተወካዮች ጋር ዉይይት ተካሄደ
በቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን በተመለከተ ከመማክርት ጉባኤ አባላት ፣ከአጋር አካላት፣ ከሀይማኖት አባቶች ለተወከሉ እና ከነጋዴ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂዷል።
የዉይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቅ/ፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋጡማ ሐሰን ይህ የውይይት መድረክ ዋና አላማ በገቢ አሰባሰቡ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማሠባሠብ እና የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የከተማዋን ገቢ በብቃት በመሠብሠብ ስኬቱን አስቀጥሎ ለመሄድ ያስችላል ብለዋል።
እንዲሁም የአገልግሎት አሠጣጡንም የተሻለ በማድረግ ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ መንገዶችን በመዝጋትና በመዋጋት ከተማዋ የምትፈልገውን ገቢ በብቃት መሠበሠብ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
በመድረኩ የዉይይቱን ሰነድ ያቀረቡት የቅ/ጽ/ቤቱ ታክስ ከፋዮች ትምህርት ድጋፍና ሕግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መላኩ ደርሶ በበኩላቸዉ የቅ/ጽ/ ቤቱ በአገልግሎት አሰጣጥና በመልካም አስተዳደር ችግር ዙሪያ አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ፣ ጥራት ያለው አግልግሎት ምንነት፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ተቋሙ የሚሰራቸው ስራዎችን፣ አገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ የተሰሩ ስራዎችን፣ያጋጠሙ ችግሮች እና የቀጣይ መፍትሄ አቅጣጫዎች በተመለከተ በዝርዝር አቅርቧል።
በዉይይቱ ላይ ከተሳተፉ የመማክርት ጉባኤ አባላት ፣የአጋር አካላት፣ ከሀይማኖት አባቶች የተወከሉ እና ከነጋዴ ተወካዮችም በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ቀርቧል።
በውይይት ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችም የቅ/ፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋጡማ እና የቅ/ፅ/ቤቱ የሞደርናይዜሽን ኮርፖሬት ስራዎች ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ግሩም በቀለ ሰፊ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
03/11/2025
በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በህግ ተገዥነታቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ግብር ከፋዮች ስልጠና ተሰጠ
በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ንግድ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የሕግ ተገዥነታቸው ዝቀተኛ ለሆኑ ግብር ከፋዮች በህግ ተገዥነት ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው በንግግር ያስጀመሩት የቅ/ፅ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ስራዎች ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ኮማንደር ደራራ ጫላ ሲሆኑ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ በህግ ተገዥነታቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ግብር ከፋዮች ስልጠናው መሠጠቱ ስለ የታክስ አስተዳደራዊ ቅጣቶች፤ የወንጀል ቅጣቶች እና የህግ ተገዥነት ግዴታዎች ተረድተዉ መብታቸዉን እንዲጠይቁና ግዴታቸዉንም ተወጥተዉ ከአላስፈላጊ ቅጣት እራሳቸዉን እንዲያድኑ ይጠቅማል ብለዋል ።
ስልጠናው በቅ/ጽ/ቤቱ ታክስ ከፋዮች ትምህርት ድጋፍና ሕግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መላኩ ደረሶ የተሰጠ ሲሆን በታክስ ደረሰኝ ምንነት፣ አይነቶች እና ጠቀሜታ፣በሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ጠቀሜታ እና በሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም፣ የህግ ተገዥነት ባህረያትና የመስተንግዶ ዓይነቶች እንዲሁም የታክስ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣት አይነቶች በሚሉ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮችን በተመለከተ በዝርዝር አቅርበዋል።
በመደረኩም ከሠልጣኞችም በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀረበው ለተነሱት ጥያቄዎች ፤አስተያየቶች እና በስራዎቻቸው ስለሚገጥማቸው ችግሮች ላይ ም/ስራ አስኪያጁ ኮማንደር ደራራ ጫላ እና የቅ/ጽ/ቤቱ ታክስ ከፋዮች ትምህርት ድጋፍና ሕግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መላኩ ደርሶ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
03/11/2025
በቅ/ፅ/ቤቱ በስጋ ቤት ዘርፍ ለተሰማሩ ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በስጋ ቤት ዘርፍ ተመዝጋቢ ግብር ከፋዮች በአጠቃላይ ታክስ ዓላማና ምንነት እና ስለ ደረሰኝ አጠቃቀም መመሪያዎች፣ በታክስ ደረሠኝ ህትመት አጠቃቀም እና አወጋገድ ፣ በታክስ ከፋይ ምዝገባ እና ሥረዛ እንዲሁም በአስተዳደራዊ ቅጣቶች ላይ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቅ/ፅ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ስራዎች ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ኮማንደር ደራራ ጫላ ሲሆኑ ስልጠናው መሠጠቱ በደረሰኝ ላይ የተደገፈ ግብይት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ ግብር ከፋዩ ከማወቁም ባሻገር በህግ ላይ የተመሠረተ የታክስ ከፋይ ምዝገባና የስረዛ ስርዓት መኖሩ በግብር ከፋዩ መካከል የታክስ ስርዓቱ የተመጣጠነ እና የተጣጣመ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል።
የቅ/ጽ/ቤቱ ታክስ ከፋዮች ትምህርት ድጋፍና ሕግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መላኩ ደርሶ ሲሆኑ በስልጠናውም አጠቃላይ ታክስ ዓላማና ምንነት፣ ስለ ደረሰኝ አጠቃቀም መመሪያዎች፣ በታክስ ደረሠኝ ህትመት አጠቃቀም እና አወጋገድ ፣ በታክስ ከፋይ ምዝገባ እና ሥረዛ፣ በደረሰኝ አቆራረጥ ፣የግብር ከፋዮች መብትና ግዴታ እንዲሁም በአስተዳደራዊ ቅጣቶች ላይ በደረሰኝ ላይ የተደገፈ ግብይት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በዝርዝር አቅርበዋል ፡፡
በመድረኩም ከሠልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም አሠልጣኙ አቶ መላኩ ደርሶ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
24/10/2025
በቅ/ፅ/ቤቱ ለሴት ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ንግድ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አዲስ ሴት ግብር ከፋዮች የግብር ምንነት ፤የአከፋፈል ሂደት፤ በታክስ ደረሠኝ ህትመት፤ አጠቃቀም እና አወጋገድ ፣ በታክስ ከፋይ ምዝገባ እና ሥረዛ አስመልክቶ እንዲሁም በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 የተደረጉ ለውጦች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናውም የተዘጋጀው ኬር ኢትዮጵያ በቦሌ ክ/ከተማ ለሚገኙ አዲስ ወደ ታክስ መረቡ ለገቡ ሴት ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲሰጡ በጠየቀዉ መሰረት ነው።
በተለያየ ዘርፍ ለተሰማሩ ሴት ግብር ከፋዮች በአራት ዙር ስልጠናውን የሰጡት በቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አበራ ዱፌራ ሲሆኑ ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ በሰልጣኞች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተዋል ።
በስልጠናው ወቅት ለተነሱት ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና በስራዎቻቸው ላይ ስለሚገጥማቸው ችግሮች አሰልጣኙ አቶ አበራ ሰፊ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።
01/10/2025
በቅ/ፅ/ቤቱ አዲስ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ንግድ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የደረጃ "ሀ" እና የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች አዲስ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አበራ ዱፊራ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን ስልጠናው የገቢ ግብር አዋጁ ማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ዋና ዓላማዎች፣ የግብር ከፋይ ደረጃዎችና አከፋፈል ሁኔታዎች፣ ስለ አማራጭ አነስተኛ ግብር አከፋፈል፣ ለበጎ አድራጎት ዓላማ የሚደረጉ ስጦታዎች፣ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ስላለባቸው ግብር ከፋዮች ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
እንዲሁም የጥሬ ገንዘብ ክፍያ አፈጻጸም ዘዴዎች፣ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ምጣኔዎች፣ የኪራይ ገቢ ግብር ምጣኔዎች፣ በንግድ ሥራ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች፣ ሌሎች (ሠንጠረዥ “መ” ) ገቢዎች፣ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሶ ስለማስቀረት እና ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ላይም ስልጠናው ተሰጥቷል።
በመድረኩም ከሠልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ድጋፍ እና የህግ ተገዥነት ስጋት ስራ አመራር የስራ ሂደት በሆኑት በአቶ መላኩ ደርሶ እና የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አበራ ዱፌራምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
20/09/2025
በቅ/ፅ/ቤቱ አዲስ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ንግድ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የደረጃ "ሀ" እና የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች አዲስ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አበራ ዱፊራ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን ስልጠናው የገቢ ግብር አዋጁ ማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ዋና ዓላማዎች፣ የግብር ከፋይ ደረጃዎችና አከፋፈል ሁኔታዎች፣ ስለ አማራጭ አነስተኛ ግብር አከፋፈል፣ ለበጎ አድራጎት ዓላማ የሚደረጉ ስጦታዎች፣ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ስላለባቸው ግብር ከፋዮች ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
እንዲሁም የጥሬ ገንዘብ ክፍያ አፈጻጸም ዘዴዎች፣ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ምጣኔዎች፣ የኪራይ ገቢ ግብር ምጣኔዎች፣ በንግድ ሥራ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች፣ ሌሎች (ሠንጠረዥ “መ” ) ገቢዎች፣ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሶ ስለማስቀረት እና ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ላይም ስልጠናው ተሰጥቷል።
በመድረኩም ከሠልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ድጋፍ ቡድን በሆኑት በወ/ሮ የሁሉ ዋሴ እና የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አበራ ዱፌራምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
06/07/2025
በቅ/ጽ/ቤቱ በታክስ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 አስመልክቶ ለሴት ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በቦሌ ክ/ከ/አ/ግ/ቅ/ጽ/ቤት ለሚገኙ ለደረጃ ሀ እና ለደረጃ ለ የሒሳብ መዝገብ መያዝ እያለባቸዉ ላልያዙ ሴት ግብር ከፋዮች በሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አበራ ዱፌራ በስልጠናው ላይ ስለ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ በታክስ ግብር ከፋዩ መያዝ ያለበትን የሰነድ አይነት እንዲሁም ሂሳብ መዝገብ መያዝ ያለባቸዉ እነማን ናቸዉ የሚለዉን በዝርዝር ሰነድ አቅረበዋል ።
ግብር ከፋዩም በዚህ ስልጠና ስለ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 አዉቀዉ ስለ መብትና ግዴታቸዉ ተረድተዉ መብታቸዉን እንዲጠይቁና ግዴታቸዉንም ተወጥተዉ ከአላስፈላጊ ቅጣት እራሳቸዉን እንዲያድኑ አሰልጣኙ አስረድድተዋል ።
በመድረኩም ከሠልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ቡደን ወ/ሮ የሁሉ ዋሴ እና የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አበራ ዱፌራ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
27/06/2025
በቅ/ጽ/ቤቱ በታክስ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 አስመልክቶ ለግብር ከፋዩ ስልጠና ተሰጠ
በቦሌ ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ት/ጽ/ቤት ለሚገኙ ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል::
በቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አበራ ዱፌራ በስልጠናው ላይ ስለሒሳብ መዝገብ አያያዝ ግብር ከፋዩ መያዝ ያለበትን የሰነድ አይነት እንዲሁም ሂሳብ መዝገብ መያዝ ያለባቸው እነማን ናቸው የሚለዉን በዝርዝር ሰነድ አቅርበዋል ።
ግብር ከፋዩም በዚህ ስልጠና ስለ ሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 ጠንቅቀዉ አውቀው ሰለ መብትና ግዴታቸዉ ተረድተው መብታቸውን እንዲጠይቁና ግዴታቸውን ተወጥተው ከአላስፈላጊ ቅጣት እራሳቸዉን እንዲያድኑ እንደሚረዳቸውም አሰልጣኙ አስረድተዋ።
በስልጠናዉም ላይ በርከት ያሉ ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝና ስለተለያዩ ተያያዥ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኦዲት ሥራ ሂደት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ በዕውቀት ምንያምር ሰፊ ማብራሪና ምላሽ ሠጥተዋል::
13/06/2025
በቅ/ፅ/ቤቱ ለግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት ለደረጃ "ሀ" እና "ለ" አዲስ እና ከወረዳ ወደ ክ/ከተማ ላደጉ ግብር ከፋዮች በታክስ ደረሠኝ ህትመት፤ አጠቃቀም እና አወጋገድ ፣ በታክስ ከፋይ ምዝገባ እና ሥረዛ አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አበራ ዱፌራ በስልጠናው በደረሰኝ ላይ የተደገፈ ግብይት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በህግ ላይ የተመሠረተ የታክስ ከፋይ ምዝገባና የስረዛ ስርዓት መኖሩ በግብር ከፋዩ መካከል የታክስ ስርዓቱ የተመጣጠነ እና የተጣጣመ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል።
ከሠልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ቡደን ወ/ሮ የሁሉ ዋሴ እና የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አበራ ዱፌራ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
17/05/2025
በቅ/ፅ/ቤቱ ለአዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ለአዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ግብር ከፋዮች በአጠቃላይ ታክስ ዓላማና ምንነት እና ስለ ደረሰኝ አጠቃቀም መመሪያዎች እንዲሁም በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አበራ ዱፌራ ሲሆኑ በስልጠናው በታክስ / ግብር/ ምንነት፣ የታክስ አላማ፣የታክስ አይነቶችና ጠቀሜታ፣በደረሰኝ ህትመት፣ አይነትና ጥቅም፣ በደረሰኝ አቆራረጥ ፣የግብር ከፋዮች መብትና ግዴታ እንዲሁም በደረሰኝ ላይ የተደገፈ ግብይት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በህግ ላይ የተመሠረተ የታክስ ከፋይ ምዝገባና የስረዛ ስርዓት መኖሩ በግብር ከፋዩ መካከል የታክስ ስርዓቱ የተመጣጠነ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል።
ከሠልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ቡድ
ን ወ/ሮ የሁሉ ዋሴ እና የቅ/ፅ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አበራ ዱፌራ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።