በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን, Government Organization, 4 kilo behind ministry of Education, Addis Ababa.

23/05/2026
Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 23/05/2026
22/05/2026

የፕሮግራም ለውጥ መኖሩን ስለማሳወቅ

ባለስልጣኑ ከመጋቢት እስከ ግንቦት እያከናወናቸው ያሉ የትምባሆ ግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ ማጠቃለያ ፕሮግራም አስመልክቶ የተዘጋጀው መርሃ ግብር ቀኑ የተቀየረ መሆኑን ያሳውቃል
==============
ግንቦት 14/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ39ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ "ለኒኮቲንና ትምባሆ ሱሰ አጋላጭ የሆኑ ስልቶችን እናጋልጥ!" በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲያካሄድ ለነበረው የጸረ ትምባሆ ንቅናቄ ቅዳሜ ግንቦት 15/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካ አዳራሽ ማጠቃለያ ፕሮግራም እና በአራዳ ፓርክ ደግሞ 9፡30 ጀምሮ የወጣቶች ስፖርታዊ ውድድር ሩጫ ቀኑ የተቀየረ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ፕሮግራሙ በከተማ አስተዳደሩ ተደራራቢ ፕሮግራም መሰረት የተራዘመ ሲሆን ፕሮግራሞችን ለማስኬድ ሲወሰን ወደፊት ቀኑን የምናሳውቅ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን ፡፡

Photos from በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን's post 22/05/2026

“የትንባሆ ውጤታማነት ከቅጣት ወደ ሽልማት”

ግንቦት 13/2018 ዓ.ም
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና የቁጥጥር ፎረም አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ከትንባሆ ጭስ ነጻ የሆኑ ተቋማትን ጎብኝቷል።

መርሃ ግብሩ በከተማው ውስጥ ከትንባሆ ጭስ ነጻ የሆነ የስራና የአገልግሎት አካባቢ ለመፍጠር፣ የትንባሆ ቁጥጥር ሕግና መመሪያዎችን በተገቢው ሁኔታ ለሚተገብሩ ተቋማት እውቅና ለመስጠት እና ሌሎች ተቋማትንም ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የተጎበኙ ተቋማት የትንባሆ ጭስ ነጻ ፖሊሲዎችን በተግባር በማስፈጸም፣ ለደንበኞችና ለሰራተኞች ጤናማ አካባቢ በመፍጠር እንዲሁም የሕግ ተገዢነትን በማሳየት አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸው ተገምግሟል።

በዚሁ መሰረት ከትንባሆ ጭስ ነጻ ለሆኑ ተቋማት ለህዝብ ጤና ጥበቃ እያደረጉት ላለው አስተዋፅኦና ለሕግ ተገዢነታቸው እውቅና በመስጠት የምስጋና ሰርተፌኬት ተበርክቶላቸዋል።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊዎች እንደገለጹት አቶ ሸበላው የትንባሆ ጉዳትን ለመቀነስ የሚደረገው ትግል በቅጣት ብቻ ሳይሆን ሕጉን በአግባቡ ለሚተገብሩ ተቋማት እውቅናና ሽልማት በመስጠት የተሻለ ውጤት ማስገኘት እንደሚቻል ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ በቀጣይም ከትንባሆ ጭስ ነጻ የሆኑ ተቋማትን በማበረታታት፣ የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት ጤናማና ከትንባሆ ጭስ ነጻ የሆነ ማህበረሰብ ለመገንባት ጥረቱን እንደሚቀጥል ገልጿል።

20/05/2026

ፕሬስ ሪሊዝ

ባለስልጣኑ ከመጋቢት እስከ ግንቦት እያከናወናቸው ያሉ የትምባሆ ግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ ማጠቃለያ ሊያካሂድ ነው፡፡
==============
ግንቦት 12/2018ዓ.ም

የአዲስ አበባ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ39ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ "ለኒኮቲንና ትምባሆ ሱሰ አጋላጭ የሆኑ ስልቶችን እናጋልጥ!" በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ በውይይት ማለትም (ከትምህርት ቢሮ አደረጃጀቶች ፣ ከሰላምና ፀጥታ አካላት፣ከደንብ ማስከበር፣ ከወጣትና ሴት አደረጃጀቶች ፣ከከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ እና ከሌሎች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተከናውኗል፡፡

በተጨማሪም በትምህርት ቤት ሚኒሚዲያ ክበብ ግንዛቤ የማስረፅ ስራ፣ ከወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር የሩጫ ስፖርታዊ ውድድርም ጭምር ተሰርቷል ፣ ህዝብ በሚሰበሰብባቸው አደባባዮች አውደ ርዕይ በማዘጋጀት ሰፊውን ህዝብም አስተምሯል፡፡

የዚህ ፐሮግራም አንድ አካል የሆነዉ ክብርት ከንቲባን ጨምሮ የተለያዩ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እና ከ2500 በላይ ልየልዩ ተሳታፊዎች በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ግንቦት 15/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካ አዳራሽ የማጠቃለያ ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

ፕሮግራሙ እኔም ለጤናዬ ባለስልጣን ነኝ ትምባሆን በጋራ እንከላከል; በሚል ልዩ የማነቃቂያና ማጠቃለያ ዝግጅት ሲሆን ሁሉም የከተማዋ ባለድርሻ ሴክተር ተቋማት በትምባሆ ቁጥጥር ጉዳይ ድርሻቸውን እንዲወጡ አቅጣጫ የሚሰጥበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ባለስልጣኑ ይህን ትልቅ ጉዳይ የሚዲያ አካላትም በቦታው ተገኝተው መረጃውን ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲያደርጉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


4 Kilo Behind Ministry Of Education
Addis Ababa