Akaki Kality woreda 10 communication -አቃቂ ቃሊቲ

Akaki Kality woreda 10 communication -አቃቂ ቃሊቲ

Share

የወረዳ 10 አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኝ ሲሆን ልዩ ስሙ ገላን ጉራ ይባላል -አቃቂ ቃሊቲ

31/05/2026
30/05/2026

ኢትዮጵያ ትመርጣለች !
የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር ይረጋገጣል!!

ምርጫ የሕዝብ ሉዓላዊነት እውነተኛ መገለጫ፣ የዜጎች የባለቤትነት እና የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር የሚረጋገጥበት ወሳኝ መድረክ ነው።

እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባውም፣ የሕዝብን ፍጹም ውሳኔ ሰጪነት በመቀበልና በማክበር ላይ ብቻ ነው። ሕዝብን "በምርጫ አትሳተፉ፣ አትምረጡ" በማለት ለማስፈራራት መሞከር፣ እንዲሁም “እኔ አውቅልሃለሁ" በሚል የተሳሳተ የሞግዚትነት መንፈስ የዜጎችን ነፃ ፈቃድ ለመቀማት መሻት ለሕዝብ ያለን ንቀት የሚያሳይ፣ ከዘመኑ የሕዝብ የፖለቲካ ንቃተ ሕሊና ጋር የማይሄድ ኋላ ቀር አካሄድ ነው።

ሕዝባችን ግን ከእነዚህ ሁሉ የተዛቡ የፖለቲካ አመለካከቶች እጅግ ልቆ የሄደ፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንዲሁም የሀገሩን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በራሱ ሚዛናዊነት መወሰን የሚችል እጅግ አስተዋይና እውነተኛ ዳኛ ነው። ለዚህም አንዱና ዋነኛው ማረጋገጫ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ከወዲሁ በንቃት በመመዝገብ የሀገራቸውን ብሩህ መጻኢ ዕድል ለመወሰንና የሚበጀውን ለመምረጥ ያሳዩት ከፍተኛ ዝግጁነትና ታሪካዊ ቁርጠኝነት ነው።

ስለሆነም፣ የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው። ይህ 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የአፍሪካ አህጉር የእውነተኛ ዲሞክራሲንና የሕዝብን የውስጥ አቅም በተግባር ለማሳየት የሚኖረው አዎንታዊ አንድምታ እና ምሳሌነት እጅግ የላቀ ነው።

#ዲሞክራሲ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Akaki Kality woreda 10 communication -አቃቂ ቃሊቲ's post 30/05/2026

የሰንበት ገበያ ነተለያዩ የግብርና'ና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ይዞ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል!

ግንቦት 22/2018 ዓ.ም /ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን/

የሰንበት ገበያ ነተለያዩ የግብርና'ና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ይዞ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 አስተዳደር የኑሮ ውድነት ለመቀነስ እና የዋጋ ንረትን ለመከላከል ከዓመታት በፊት መካሄድ የጀመረዉ የሰንበት ገበያ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።

በገበያዎ የተለያዩ የእህል አይነቶችን ጨምሮ እንደ ቀይ ሽንኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ጎመን ፣ ሌሎች የተለያዩ የጓሮ አታክልት እና ፍራፍሬዎች ፣ የእንስሳት ተዋፅዖ እና ለሎች የኢንዱስትሪ ምርቶች ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ቀርበዋል።

አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራባቸው ካሉ ጉዳዮች አንዱ የሰንበት ገበያ ሲሆን ‎ማህበረሰቡም በወረዳው በተመቻቹ የሰንበት ገበያዎች የቅዳሜ እና የእሁድ ገበያ የግብርና ኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ግብይት እንዲፈጽም የወረዳው ንግድ ጽ/ቤት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Photos from Akaki Kality woreda 10 communication -አቃቂ ቃሊቲ's post 30/05/2026

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ስርጭት እየተካሄደ ይገኛል

በክ/ከተማዉ ምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ስርጭት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ግንቦት 22/2018 ዓ.ም

Photos from Akaki Kality woreda 10 communication -አቃቂ ቃሊቲ's post 29/05/2026

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና በሸገር ከተማ መካከል የተቀናጀ የሰላምና ፀጥታ ማስከበር የጋራ ስምሪት ተሰጠ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና በሸገር ከተማ አዋሳኝ አካባቢዎች አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን እና ቅንጅታዊ የሰላምና ፀጥታ ስራን ለማጠናከር የ"ሰላም ሰራዊት" እና የ"ጋቸነ ሲርና" የአንድ ማዕከል የጋራ ፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።

በስምሪት መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ባደረጉት ንግግር ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የፀጥታ መዋቅሩንና ህዝባዊ አደረጃጀቶችን በቅንጅት ማሰማራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ይህ የአንድ ማዕከል ስምሪት በክፍለ ከተማውና በአዋሳኝ አካባቢዎች ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የሥራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስ በበኩላቸው፤ ሰላም ለሁሉም ልማት መሠረት በመሆኑ፣ በክፍለ ከተማው የወጣቶችና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ያለበት የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራቱ ውጤታማነቱን ይበልጥ እንደሚያሳድገው ጠቁመዋል።

የሸገር ከተማ ሰላምና ፀጥታ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ስዩም በበኩላቸው፤ በአዋሳኝ አካባቢዎች የፀጥታ ስራዎችን ለመምራት እንዲህ ዓይነቱ የተቀናጀ የጋራ ስምሪትና መድረክ መፈጠሩ የወንጀል መከላከል ሥራውን ይበልጥ ስልታዊና ስኬታማ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

ይህ የ"ሰላም ሰራዊት" እና የ"ጋቸነ ሲርና" የጋራ ስምሪት፤ በክፍለ ከተማውና በሸገር ከተማ የሚደረጉ ቅንጅታዊ የሰላምና ፀጥታ ማስከበር ሥራዎችን ይበልጥ በማጠናከር የህዝቡን ደህንነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያስጠብቅ ተመልክቷል።

28/05/2026

ማንኛውም ተዘዋዋሪም ሆነ ተቀማጭ የዕጩ ወኪሎች ግዴታ

1. የምርጫ ኃላፊው የሚሰጠውን ትዕዛዞች ማክበር አለበት፣
2. የምርጫ ሂደቱን ከሚያውኩ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣
3. አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅ መታወቂያውን ማሳየት አለበት፣
4. የምርጫ ሕጉን ማክበር አለበት፣
5. የምርጫውን ሂደት የመከታተል ተግባሩን ሲያከናውን መራጮች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው አስተያየት ከመስጠት ወይም ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር የለበትም፣
6. የምርጫ ቁሳቁሶችን መያዝ፥ ማንሳት፤ መነካካት ወይም በቁሳቁሶቹ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተግባራትን መፈጸም የለበትም፣
7. የምርጫ ጣቢያውን ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ከማስፈራራት ወይም ሥራውን ከሚያደናቅፉ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣
8. ወደ ድምፅ መስጫ ክፍሎች መግባት የለበትም፣
9. ቦርዱ የሚያወጣውን የሥነ ምግባር ደንብ መፈረም እና ማክበር ይገባዋል፡፡

ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 121

28/05/2026

ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (በጥሞና ወቅት) ጀምሮ ምን ምን ማድረግ አይቻልም?

1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
👉ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች
👉የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
👉የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠርጭት
👉የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ

2. የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት
👉የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
👉የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
👉ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ
"የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።"

የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ ሲል ምርጫ ቦርድ አስታውቋል::

Photos from Akaki Kality woreda 10 communication -አቃቂ ቃሊቲ's post 27/05/2026

በያቤሎ ከተማ የሚገኘው የቦረና ባሕል ማዕከል ዛሬ ተመርቋል።
‎በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ2013 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረውና ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህል ማዕከል፤ በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባ ሲሆን በ57.6 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው።

ማዕከሉ የገዳን ሥርዓት ለማሳየት በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረገ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ሰዎች ማስተናገድ አቅም ያለው የስብሰባ አዳራሽ እና የቅርስ ሙዚየምን አካቶ የተገነባ ነው። ማዕከሉ የቦረናን ህዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና ፍልስፍና ለትውልድ የማሸጋገር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል።

We inaugurated the Borana Cultural Center today in Yabelo town. The foundation stone for the center was laid in 2020 (2013 Ethiopian Calendar) by First Lady Zinash Tayachew, and it has now officially opened for service. Built using proceeds from the sale of the book Medemer, the center sits on 57.6 hectares of land.

The center was specially designed to showcase the Gadaa system. It features a conference hall with the capacity to accommodate up to 2,000 people at a time, as well as a heritage museum and is expected to play a key role in preserving and passing on the culture, history, and philosophy of the Borana people to future generations.

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Akakiy Kalitiy W10
Addis Ababa