የካ ወረዳ 1 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ

የካ ወረዳ 1 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ

Share

መንገዳችን መደመር መዳረሻችን ብልፅግና ነዉ።

05/06/2026

ኢትዮጵያ አሸንፋለች በሕዝብ ድምፅ፣ በሰላም ጉዞ !

የኢትዮጵያ ሕዝብ የወደፊት ዕድሉን በገዛ እጁ ለመወሰን፣በሙሉ ነፃነት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመትመም ታሪካዊ የምርጫ ሂደትን አካሂደዋል። ይህ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ውድድር ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዲሞክራሲ ብስለቱንና ለሀገር ግንባታ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ለአለም ያሳየበት ታላቅ መድረክ ሆኗል።

በሀገሪቷ ክፍል ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍና በታላቅ ትዕግስት ተሰልፈው የሰጡት ድምፅ የሀገሪቱን የሥልጣን ምንጭ ሕዝብ መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።የምርጫው ሂደት የተለያዩ የፖለቲካ ራዕዮች በነፃነት የተንፀባረቁበት፣ የሀሳብ ብዝሃነት የተከበረበት እና ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የተረጋገጠበት በመሆኑ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ባህልን በሀገሪቱ ላይ ጥሏል።

ሂደቱ ምንም ዓይነት የጸጥታ ስጋት ሳይኖርበት፣ በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ መከናወኑ የሕዝባችንን አርቆ አሳቢነት እና ለሀገራዊ መረጋጋት የሰጠውን ከፍተኛ ዋጋ ያሳያል።
ይህ ምርጫ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ዲሞክራሲ በጋራ ያሸነፉበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። ኢትዮጵያ መርጣለች፤ ምርጫዋም ሰላም፣ ልማት እና የተባበረች ጠንካራ ሀገር መገንባት ነው።

#ምርጫ

04/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች!

ግንቦት 24/2018 ዓ.ም 7ኛው ዙር የተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ እና የመራጮች አስተያየት

04/06/2026

7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በታሪክ የሚዘከር ታሪካዊ አሻራ!

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ጉዞ ታሪክ ውስጥ የሚዘነጋ አይደለም። ይህ ምርጫ የፖለቲካ ተሳትፎ የጎለበተበት እና የሰላማዊ ውድድር ባህል የተጠናከረበት፣ የሕዝብ ድምፅ ክብር ያገኘበት ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ ይታወሳል።

የአንድ ሀገር ጥንካሬ በሕዝቦቿ ንቁ ተሳትፎ፣ በተቋማቷ ብስለት እና በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ነው። 7ኛው ሀገራዊ ምርጫም ኢትዮጵያ እነዚህን እሴቶች እያጠናከረች ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ሥርዓት መጓዟን ያሳየ ወሳኝ አጋጣሚ ነው።

ምርጫው የተለያዩ ሀሳቦች በሰላማዊ መንገድ የተወዳደሩበት፣ ዜጎች የወደፊት ሀገራቸውን በድምፃቸው ለመቅረጽ የተሳተፉበት እና የዴሞክራሲ እሴቶች በተግባር የታዩበት ፍትሀዊ መድረክ ነው።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

04/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ልዩ ድምቀቶች

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የፖለቲካ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም የዜጎች የሀገር ፍቅር፣ ልዩ መስዋዕትነት እና አስገራሚ የሕይወት አጋጣሚዎች በደመቀ ቀለም የተጻፉበት ታሪካዊ መድረክ እንጂ።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ የተስተዋሉ አንዳንድ ክስተቶች የምርጫውን ሂደት ከፖለቲካዊ ክንውንነት ባለፈ፣ የሰው ልጅን የፅናት ጥግ እና ለሀገር የመቆርጠጥን ሚስጥር ያሳዩ ነበሩ።

የምርጫ ጣቢያው ታዳሚዎችን ብቻ ሳይሆን መላውን የሀገሪቱን ህዝብ ያስደመመው ክስተት የተመዘገበው በአካል ጉዳት ምክንያት ሁለት እጆቹን ያጣው ወገናችን ነው። እርሱ ግን እጆች ባይኖረኝም መምረጥ እችላለሁ በሚል መንፈስ፣ የምርጫ ወረቀቱን በአፉ በመያዝ ድምጹን በምስጢር ሳጥን ውስጥ ከቷል።

በሌላ በኩል እናትነትና ሀገራዊ ግዴታ ፊት ለፊት የተጋፈጡበት አስደናቂ ታሪክ ተመዝግቧል። አንዲት ጀግና እናት አዲስ ህጻን ልጅ ወደዚህች ምድር ባመጣች በሁለት ሰዓት ልዩነት ውስጥ፣ በምጥና በድካም ዝላ ሳለች ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ድምፅ መስጠጥ ችላለች ።

ለብዙዎች የሰርግ ቀን ከጭፈራ፣ ከፎቶግራፍ ውጭ ሌላ ነገር አይታሰብበትም። ለነዚህ አዲስ ተጋቢዎች ግን የሰርጋቸው ምርጥ ማስታወሻ ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ ነበር።
የትዳራቸውን መጀመሪያ በሀገር የወደፊት እጣ ፈንታ ውሳኔ የባረኩት እነዚህ ሙሽሮች፣ የዕለቱ ደማቅ ድምቀት ነበሩ።

በዱላ እየተደገፉ፣ በልጆቻቸውና በልጅ ልጆቻቸው እየተመሩ ወደ ምርጫ ጣቢያ የጎረፉት አባቶችና እናቶች ሌላው የምርጫው ውበት ነበሩ።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኮሮጆ ውስጥ የገቡ ድምፆች ብቻ ሳይሆኑ፣ የዜጎች ተስፋና ህያው ታሪኮች የተሰነዱበት ክስተት ሆኖ ያልፋል።

04/06/2026

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የተምሳሌት ጉዞ ማሳያ!

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ታሪኳ ውስጥ አዲስና ብሩህ ምዕራፍ የከፈተችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። ይህ ምርጫ ተራ የድምፅ መስጠት ሂደት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በነፃነት፣ በሰላምና በብስለት የራሱን ዕድል በራሱ መወሰን እንደሚችል ለዓለም ያስመሰከረበት ታላቅ ሁነት ነው።

ምርጫው ኢትዮጵያ ማንኛውንም የውስጥ እና የውጭ ፈተናዎች እየተሻገረች ወደ ከፍታ የምታደርገው ግስጋሴ ለአፍታም እንደማይገታ ዳግም ያረጋገጠችበት ሲሆን፤ ለሀገራችን ሉዓላዊነት ተጠብቆ መዝለቅ የተጣሉ ፅኑ መሰረቶችን ጥንካሬም ማሳየት ችሏል፡፡

ይህ ታሪካዊ ምርጫ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በአጠቃላይ በአህጉሩ የእውነተኛ ዴሞክራሲ ተምሳሌት ለመሆን የምታደርገውን ጉዞ በተግባር ያበሰረ ነው። የምርጫው ሂደት በሰላማዊ መንገድ መከናወኑ፣ የዜጎች በነፃነት የመሳተፍ መብት መረጋገጡ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰለጠነ እና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ሃሳባቸውን የሚያቀርቡበት አውድ መፈጠሩ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ጉዞአችንን ከፍ አድርጎታል።

ኢትዮጵያውያን የሀሳብ ልዩነቶቻቸውን በግጭት እና በጦርነት ሳይሆን በንግግር፣ በውይይትና በህዝባዊ ውሳኔ መፍታት የሚችሉባቸው እሴቶች እንዳሏቸው ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳየት በኩልም 7 ኛው ሀገራዊ ምርጫ ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

04/06/2026
03/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች!
ምርጫ ለሃገር ግንባታና ለዘላቂ ሰላም!

​የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚረጋገጥበትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ዋናው ምሰሶ ሰላማዊ ፣ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ነው። ዜጎች ያለ ምንም ተጽዕኖ በነጻነት ድምፃቸውን የሚሰጡበትና መሪዎቻቸውን የሚመርጡበት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፥ ለሀገር የፖለቲካ መረጋጋትና ለሕግ የበላይነት መከበር ዋነኛው መሠረት ነው።

ይህ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫም ሕዝቡ በነቃ ተሳትፎ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ዕድል ከመስጠቱም በላይ፥ ልዩነቶችን በሐሳብና በምርጫ ካርድ ብቻ የመፍታትን የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል በሀገራችን ለመገንባት ትልቅ አቅም ይፈጥራል።​አንድነትንና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት በሕዝብ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ሕጋዊ መንግሥት መመሥረት ወሳኝ ነው።

ኢትዮጵያ በምርጫ ሂደት ውስጥ የምታሳየው ጥንካሬና ዲሞክራሲያዊ ጉዞ፥ የሀገሪቱን ብሔራዊ ክብርና ጥቅሞች ለማስከበር እንዲሁም ሁሉን አቀፍ ዕድገትን ለማረጋገጥ ትልቅ ዋስትና ነው።
በመሆኑም ኢትዮጵያ መርጣለች የሚለው መልእክት የዜጎችን የጋራ ድልና የወደፊት ተስፋ የሚያንጸባርቅ ሲሆን፥ የተመረጠው አካልም የሕዝብን አደራ ጠብቆ ሀገርን ወደተሻለ የልማትና እና የሰላም ምዕራፍ የማሸጋገር ታሪካዊ ኃላፊነት ይኖርበታል።

Photos from የካ ወረዳ 1 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ's post 02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች ፤ አሸንፋለች!

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተደመረ የመራጮች ድምፅ በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፍ መጀመሩን ተከትሎ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ውጤቱን እየተመለከቱ ይገኛሉ።

የፖለቲካ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድና በሕዝበ ውሳኔ መዳኘት የሰለጠነ ፖለቲካ ነው።

02/06/2026

ኢትዮዽያ አሸነፈች!!!

የሀገረ መንግስቱን ግንባታ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አቅጣጫ ውጭ ባንዳና ባዳ ጥምረት ፈጥረው በአመፅና በኃይል ሀገራችንን ወደ ጥፋት መንገድ ለመክተት ያሴሩትን ደባ ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊው ምርጫ እምቢተኝነቱንና ለሀገር ያለውን ፅኑ ፍቅር በተግባር በማሳየት አክሽፎታል።

በተለይ በአዲስ አባባ ረጃጅም ሰልፍ ቢፈጠርም ህዝቡ በእንቅልፍ እና በብርድ ሳይበገር ተራ እስኪደርሰው እስከ ለሊቱ 10:30 ሰአት ድረስ ተሰልፎ በሚገርም ጨዋነት፣ መሰጠት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት መርጧል።

የሀገራችን ፖለትከኞችና ልሂቃን ይህንን ታላቅ ጽኑ ጨዋና ቆራጥ ሕዝብ የምንረዳውና የሚንመጥነው መሆን ይጠበቅብናል።

ፈጠሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች!

​የኢትዮጵያ 7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ፍላጎትና ነፃነት የወደፊት እጣ ፈንታቸውን በራሳቸው እጅ ለመወሰን ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት በተግባር ያሳዩበት ቀን ሆኗል። ሕዝቡ በማለዳ ተነስቶ፣ በረጅም ሰልፎች በትዕግሥት በመቆም ድምፁን መስጠቱ አገራዊ አንድነትንና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ትልቅ ማሳያ ነው።

ዜጎች በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜትና በታላቅ ጨዋነት ሂደቱን በሰላም በማጠናቀቃቸው ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ ጠንካራ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ጥለዋል።

ይህ ሰላማዊ ሂደት አገራችን ወደተሻለ የፖለቲካ ብስለትና መረጋጋት እየተሸጋገረች መሆኑን ለዓለም ምስክርነት የሰጠ ታላቅ አጋጣሚ ነው።

​ከፊታችን የሚጠብቀን ትልቁና ወሳኙ ሥራ አገራችንን በጋራና በአንድነት ወደፊት ማራመድ ነው፣ የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን፣ አሸናፊውም ሆነ ተሸናፊው ወገን የአገሪቱን ዘላቂ ሰላም፣ አንድነትና ልማት ለማረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሰሩ ይገባል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


አዲስ አበባ
Addis Ababa