03/06/2026
ዛሬ በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ከሆኑት ንስቲያን ክርስተንሰን ጋር ውይይት አድርገናል።
በመጪው መስከረም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኖርዲክ - አፍሪካ ኢቪ ሰሚት (Nordic Africa EV Summit) ላይ በጋራ በምንሰራቸው ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሩ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ከተማችን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን የማስተናገድና በብቃት የመወጣት ልምድ ያካበተችና ተመራጭ እየሆነች የመጣች በመሆኗ ይህንንም ጉባኤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እናሳካዋለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!
Today, we held discussions with H.E. Stian Christensen, Ambassador of Norway to Ethiopia.
We had a productive exchange with the Ambassador on areas of mutual cooperation in preparation for the upcoming Nordic Africa EV Summit, which will be held in Ethiopia this September.
During our discussion, I emphasized that our city has developed considerable experience and capacity in successfully hosting major continental and international events and is increasingly emerging as a preferred destination for such gatherings. I assured the Ambassador that, in close collaboration with all relevant stakeholders, we will organize this summit with the highest standards of professionalism and excellence.
Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
03/06/2026
የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። የተከበሩ ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፣ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ
03/06/2026
“የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል” - ኡሁሩ ኬንያታ
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አስመልክቶ የመጀመሪያ ዙር የግምገማ ውጤት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ባሳዩት ድንቅ የሆነ አፈጻጸም በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል ብለዋል።
“ኢትዮጵያውያን ከማለዳው ጀምሮ በቁርጠኝነት ለመምረጥ ተሰልፈዋል፤ ይህን ታላቅ ሁነት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ተመልክተነዋል፤ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የታዘብነው ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ሲሉ አጠቃላይ ሁኔታውን ገልጸውታል።
“ኢትዮጵያውያን ታሪክ ይሠራሉ፤ ቀኝ ገዢዎችን በጋራ ተዋግተዋል፤ ይህም በአፍሪካ ብቸኛ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል፤ የአፍሪካ የነፃነት ምልክቷ ኢትዮጵያ ነች” ብለዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ምርጫውን ለመታዘብ ቀጠሮ ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የምርጫውን ታማኝነት እና ዴሞክራሲያዊነት ስንከታተል ነበር ያሉት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ የሠራው ሥራ መራጮች ሳይደናገሩ ድምፅ እንዲሰጡ እንዳስቻለ አንሥተዋል።
በምርጫው ዕለት የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት በነጻነት ሲከታተሉ እንደነበር ጠቁመው፣ “በዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያለውን ታላቅ ቁርጠኝነት የታዘብንበት ነበር” ብለዋል።
03/06/2026
በሀገር በቀል እዉቀት ፣ በህዝብ እና በመንግስት ትብብር የተገኘ ድንቅ ውጤት !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
03/06/2026
የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ
የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡
ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡
02/06/2026
ኢትዮጵያ መርጣለች ፤ አሸንፋለች!
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተደመረ የመራጮች ድምፅ በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፍ መጀመሩን ተከትሎ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፅናት ለሊት ቀን ሳይል ወጥቶ በነቂስ የመረጠውን ውጤቱን እየተመለከቱ ይገኛሉ።
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ የሚመራውን ሕጋዊ መንግሥት ለማቋቋም ያለው ጉጉት እጅግ በጣም የላቀ መሆኑን ትልቅ አስረጅ ሆኖ በፖለቲካ ታሪካችን ውስጥ ተመዝግቧል።
የፖለቲካ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድና በሕዝበ ውሳኔ መዳኘት የሰለጠነ ፖለቲካ ነው።
02/06/2026
ለዚህ አስደናቂ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች ማህበረሰብ ስለሰራንለት ደስ ይለናል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ በተመረቀው የእንጦጦ እስከ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ ለአካባቢው ታታሪ ማህበረሰብ መስራት በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የቀጨኔና እንጦጦ ነዋሪዎች በሸማና ሸክላ ስራ የሚደነቁ ቢሆንም የሚገባቸውን ክብር አላገኙም ያሉት ከንቲባዋ፣ ፕሮጀክቱ ይህንን የተሳሳተ አመለካከት እንደሚቀይር ጠቁመዋል።
ቀደም ሲል የሚመረተውን አክምባሎ በማስታወስ፣ የእጅ ጥበብ ስራዎች ለጎብኚዎች የሚቀርቡባቸው ሱቆች መዘጋጀታቸውንና የባህል ማስታወሻ ቅርጻ ቅርጾች መካተታቸው ለአካባቢው ሙያተኞች “ስራችሁ ክቡር እንጂ የሚታፈርበት አይደለም” የሚል መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑን ገልጸዋል።
አካባቢው በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ በዚህ ልማት አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑ እስከ 10 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል አግኝተዋል።
ወጣቶችም ከአደገኛ ሁኔታዎች ርቀው በካፌዎች፣ ልብስ ስራና ስፖርት ማዕከላት ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።
እያንዳንዱ ተቋም የራሱ ታሪክ እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ሲሆን፣ የሀገር ባህልን ከሚያንጸባርቁ ቅርጻ ቅርጾች ባሻገር የኢትዮጵያን ክብር ያሳዩ አትሌቶችን የሚዘክሩ ሃውልቶችም ተቀምጠዋል። ከንቲባዋ ነዋሪዎች የጋራ ሀብታቸው የሆነውን ስፍራ እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም ለማህበረሰቡ፣ ለወጣት ኮንትራክተሮችና ፕሮጀክቱን በግንባር ቀደምትነት ላስተባበሩት የከንቲባ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ምስጋና አቅርበው፣ ወንዙን በማጽዳት ሂደት የተከፈለውን መስዋዕትነት አድንቀዋል።
የተሰራው ስራ ታሪካዊ ስኬት መሆኑን በመግለጽም “እኛ እናልፋለን፤ ታሪክ ግን አያልፍም” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።