Ethiopian Federal Police

Call Directions Website Contact the organization

Ethiopian Federal Police በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል ! Protect With Courage; Serve with Compassion!

We strive to build a safe, secure, and peaceful environment where all people in Ethiopia can live with confidence and dignity.

ስትራቴጂክ አመራሮች በኢሬቻ በዓል
05/10/2026

ስትራቴጂክ አመራሮች በኢሬቻ በዓል

እንኳን ለኢፌዴሪ መንግስት ምስረታ በሰላም አደረሳችሁ!ትልቅ ሀገር፣  ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ! በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል !የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
05/10/2026

እንኳን ለኢፌዴሪ መንግስት ምስረታ በሰላም አደረሳችሁ!
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይ !

በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል !
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

05/10/2026

በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ የፖሊስ ኃይል የሀገርና የሕዝብ አለይኝታ ነው !

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ኮማንድ ኮንትሮል ማዕከል በቀጥታ አሁን ላይ በቢሾፍቱ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ያለው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር ክትትልና ቁጥጥር...
04/10/2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ኮማንድ ኮንትሮል ማዕከል በቀጥታ አሁን ላይ በቢሾፍቱ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ያለው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠‎አዲስ አበባ፤ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ):-የሆራ ፊን...
03/10/2026

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
‎አዲስ አበባ፤ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ):-የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉ አከባበር ሂደት ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ አዲስ አበባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮማንድ ኮንትሮል ማዕከል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ጥብቅ የክትትል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በተመሳሳይ በነገው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓልም በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ከሚገኘው ኮማንድ ኮንትሮል ማዕከሉ በቀጥታ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ጥብቅ ክትትል እያደረገ ይገኛል።

የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠‎አዲስ አበባ፤ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ):...
02/10/2026

የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
‎አዲስ አበባ፤ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ):-የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ ሥራ አጠናክሮ ቀጥሏል።

ኅብረተሰቡ ለፀጥታ ኃይሎች እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ በመቀጠል፤ የፀጥታ ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFP App)፣ በነፃ የስልክ መስመር (991)፣ በሰው አልባ ስማርት ፖሊስ ጣቢያ ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች ጥቆማ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪ እያቀረበ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ያስተላልፋል፡፡

ቀጥለው ያሉትን ሊንኮች በመጫን ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ፦
‎የአማርኛ ቋንቋ ገፅ
‎https://web.facebook.com/EthiopianFederalPolice1/
‎አፋን ኦሮሞ የፌስቡክ ገፅ፦
‎https://www.facebook.com/share/17XCJoHbNy/
‎እንግሊዝኛ የፌስቡክ ገፅ፦
‎https://www.facebook.com/share/17YzrnrEVk/
‎ዌብሳይት
‎www.federalpolice.gov.et
‎ቴሌግራም
‎https://t.me/efpmedia
‎ቲክቶክ
‎https://www.tiktok.com/...
‎የዩቲዩብ ገፅ
‎https://youtube.com/...

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠‎አ...
02/10/2026

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
‎አዲስ አበባ፤ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ):—የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ኃይል በማሰማራት ጥብቅ ክትትልና ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጾ ሕብረተሰቡ ለፀጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

ሕብረተሰቡ የፀጥታ ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFP App)፣ በነፃ የስልክ መስመር (991)፣ በሰው አልባ ስማርት ፖሊስ ጣቢያ ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች ጥቆማ እንዲሰጥ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ጥሪ እያቀረበ ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ያስተላልፋል።

02/10/2026
"በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣውን የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል የሁለትዮሽ የደህንነት ትብብር ከደህንነት ተግዳሮቶች ቀድሞ መገኘት አለበት’’ በኢትዮጵያ የቱርክዬ አምባሳደር ክቡር በርክ ባራ...
01/10/2026

"በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣውን የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል የሁለትዮሽ የደህንነት ትብብር ከደህንነት ተግዳሮቶች ቀድሞ መገኘት አለበት’’ በኢትዮጵያ የቱርክዬ አምባሳደር ክቡር በርክ ባራን
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
‎አዲስ አበባ፤ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦በኢትዮጵያ የቱርክዬ አምባሳደር ክቡር በርክ ባራን በዓለም ላይ የዲጂታል ስጋቶችና የሳይበር ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት እየጨመሩ በመምጣታቸው የሁለትዮሽ የደህንነት ትብብር ከደህንነት ተግዳሮቶች ቀድሞ መገኘት እንዳለበት የገለፁት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በቱርክዬ TIKA ኤጀንሲ ትብብር በሳይበር ወንጀሎች ዙሪያ ሲሰጥ በቆየው የሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ነው።

በኢትዮጵያ የቱርክዬ አምባሳደር ክቡር በርክ ባራን አያይዘውም የተሰጠው ሥልጠና አንድ ወገን ብቻ የተማረበት ሳይሆን የሁለቱም ሀገራት የፖሊስ ተቋማት አመራሮች ልምድና እውቀት የተለዋወጡበት መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስተዳደር ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ በበኩላቸው የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ፖሊስ ለፖሊስ አጋርነት፣ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የፀጥታ ትብብር ድንቅ ሞዴል መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፕሮፌሽናል የሰው ኃይልን በማልማት፣ የቴክኖሎጂ አቅምን በማሳደግ እና የሕግ ማስከበር ሥራዎችን በማዘመን ላይ ያተኮረ ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ ሪፎርም እያከናወነ እንደሚገኝ አንስተው ሥልጠናው የሪፎርም ግቦችን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ገልፀዋል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Federal Police posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Federal Police:

Shortcuts

Share