Ministry of Water and Energy - Ethiopia

Ministry of Water and Energy - Ethiopia

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ministry of Water and Energy - Ethiopia, Government Organization, Haile G/Selassie Road, Addis Ababa.

The Ministry of Water, Irrigation and Energy of Ethiopia is a federal organization established to undertake the management of Water and Energy resources of Ethiopia. This involves development, planning and management of water and energy resources, development of polices, strategies and programs, develop and implement water and energy sector laws and regulations, conduct study and research activiti

31/05/2026
Photos from Ministry of Water and Energy - Ethiopia's post 28/05/2026

የውሃ ሃብትን ለቀጣናዊ ትስስር ማጠናከሪያነት ማዋል እንደሚቻል የሕዳሴ ግድብ ማሳያ ነው

ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአህጉሪቱን የውሃ ሀብት ለዜጎች ተጠቃሚነትና ለሀገራት የእርስ በርስ ትስስር ማጠናከሪያነት ማዋል እንደሚገባ ገለጸ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 63ኛውን የአፍሪካ ቀን የሚዘክር ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

ኮንፈረንሱ የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ዓመታዊ መሪ ሃሳብ በሆነው "የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውሃ ተደራሽነትን እና አስተማማኝ የንፅህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ" ላይ ያተኮረ ነበር።

በዚህም የውሃ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የንፅህና አጠባበቅ ሥርዓት፣ የማህበረሰብ የመቋቋም አቅም፣ ሳይንስና ኢኖቬሽን፣ ፓን-አፍሪካኒዝም እና አንድነት እንዲሁም ዘላቂ መጻኢ እድል በሚሉ ስድስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ በስፋት ተመክሯል።

ኢትዮጵያ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ያላትን ግዙፍ ተሞክሮ ያጋራች ሲሆን፤ በተለይም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሀገሪቱን የውሃ ደህንነትና አረንጓዴ ኢነርጂ ፍላጎት ከመመለስ ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ የኃይል አቅርቦትና ቀጣናዊ ትስስርን በመፍጠር ረገድ እንደ ትልቅ ስኬት ቀርቧል።

ግድቡ የውሃ ሃብትን ለቀጣናዊ ትስስር ማጠናከሪያነት ማዋል እንደሚቻል ዓይነተኛ ማሳያ መሆኑ ተገልጿል።

የተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን በጋራ በማስተባበር ረገድ ውጤታማ የሆነው "የተቀናጀ የውሃ፣ የንፅህና እና የጤና አጠባበቅ (One WASH National Program)" ተሞክሮዋ ለተሳታፊዎች ቀርቧል።

በመድረኩ ለፈጣን የከተሞች ዕድገትና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ክፍተቶችን በአጋርነት ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ በመድረኩ እንዳሉት፤ የጋራ የውሃ ሀብቶችን ለጠንካራ የሃይድሮ-ዲፕሎማሲ ስራ መጠቀም ይገባል።

በአህጉሪቱ ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች በመኖራቸው የውሃ ሀብት አስተዳደር ቀጣናዊ ትብብር መጎልበት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሀገር ውስጥ የፋይናንስ አቅም መገንባቱን አስታውሰው፤ ግድቡ ለቀጣናዊ ትስስር አስተዋጽኦ በማድረግ ለአፍሪካ ሀገራት በምሳሌነት እንደሚጠቀስ አንስተዋል።

በመድረኩ የክልል የውሃ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል።

Photos from Ministry of Water and Energy - Ethiopia's post 28/05/2026

63ኛው የአፍሪካ ቀን እየተከበረ ነው።

ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር ያዘጋጁትና "የአፍሪካ ቀን 2026"ን የሚዘክርና 63ኛውን የአፍሪካ ቀን እየተካሄደ ይገኛል።

ኮንፈረንሱ “የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና አስተማማኝ የንፅህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ” /"Assuring Sustainable Water Availability and Safe Sanitation Systems to Achieve the Goals of Agenda 2063"/ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ በአህጉሪቱ የውሃ ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ኮንፈረንስ ነው።

ኮንፈረንሱ 63ኛው የአፍሪካ ቀን በአፍሪካ የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማትን ለማሻሻል የሚያስፈልገውን አስቸኳይ የፋይናንስ ድጋፍ ላይ ትኩረት ያደረገም ነበር።

የውሃ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የንፅህና አጠባበቅ ስርዓት፣ የማህበረሰብ የመቋቋም አቅም፣ ሳይንስና ኢኖቬሽን፣ ፓን-አፍሪካኒዝም እና አንድነት፣ እንዲሁም ዘላቂ መፃኢ እድል በሚሉ ስድስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ሰፊ ውይይት እየተደረገ ነው።

በመድረኩ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የውሃ ደህንነትና አረንጓዴ ኢነርጂ ፍላጎትን ከማሳካት ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ የኃይል አቅርቦትና ቀጣናዊ ትስስርን በመፍጠር እንደ ትልቅ ስኬትም ቀርቦ፤ ኢትዮጵያ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ያላትንም ተሞክሮ አጋርታለች።

የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን በጋራ በማስተባበር ረገድ ውጤታማ የሆነው "የተቀናጀ የውሃ፣ የንፅህና እና የጤና አጠባበቅ (One WASH National Program)" ተሞክሮም ለተሳታፊዎች ቀርቧል።

ለፈጣን የከተሞች ዕድገትና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ክፍተቶችን በአጋርነት ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችም በመድረኩ ተመላክቷል።

ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ አለምአቀፍ ሚዲያዎች፣ አካዳሚክና ፕሮፌሽናል ምሁራኖች በመድረኩ ተሳታፊ ናቸው።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/

27/05/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በያቤሎ ወረዳ ያደረጉት የቦረና ውሃ ኔትዎርክ ጉብኝት( Ethiopia PM Abiy Ahmed yabelo clean drinking water supply Infrastructure visit)

Photos from Ministry of Water and Energy - Ethiopia's post 27/05/2026

ግዙፉ የገልጨት-ሰሪቴ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ህይወት የሚቀይር ነው። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት እንደሚያመለክተው፣ በምሥራቅ ቦረና እና በቦረና ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት የሚቀይር ግዙፍ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክት እየተገነባ ነው ብለዋል።

አክለውም ይህ ፕሮጀክት ለህብረተሰቡ አስተማማኝ ንጹህ ውኃ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን የሚዘልቁ የቧንቧ መስመሮች፣ ዘመናዊ የውኃ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም ሰፋፊ የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ያካተተ ዘላቂ መሠረተ ልማት እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ ድርቅን ከመከላከል ባለፈ የሕዝብ ጤናን በማስጠበቅ፣ የነዋሪዎችን መተዳደሪያ አቅም በማጠናከር እና መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም በማዘጋጀት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል።

ፕሮጀክቱ በቦረና ቀጣና የሚኖሩ ህብረተሰቦችን ቀጣይነት ያለው የንጹህ ውኃ ተደራሽነት ማረጋገጡንም ተጠቁሟል።

27/05/2026

በፊና ኦሮሚያ የመስኖ ፕሮጀክቶች አማካኝነት በጎሞሌ ወረዳ ቦረና ዞን የመስኖ ግድቦች ግንባታ መጠናቀቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም የውሃ መሠረተ ልማትን የማረጋገጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር በትስስር ገፃቸው ገልፅዋል። ይኸው እጅግ አስፈላጊ የሆነ መሠረተ ልማት በደሴ ጎራ ከ190 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር በላይ የሚሆን ከፍተኛ የውሃ ክምችት መያዝ የሚችል አቅም ያለው ሲሆን፣ አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው የውሃ አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል። አክለውም ፕሮጀክቶቹ ከ14,500 ሄክታር በላይ የሚሆን የግብርና መሬትን በመስኖ የማልማት አቅም ያለው መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም እያንዳንዱን ቤተሰብ በቀጥታ ለመደገፍ፣ የምግብ ምርትን ለማጠናከር እና ለከብቶች የሚሆን የውሃ ሀብትን በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ ያስችላሉ ብለዋል።

Photos from Ministry of Water and Energy - Ethiopia's post 27/05/2026

ከ34 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለ115 ከተሞች ተሰጠ።

ግንቦት 19/ 2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ በውሃ ልማት ፈንድ የሚተገብራቸው የድጋፍ ማዕቀፎች በአገሪቱ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሻሻልና የሳኒቴሽን አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው ተገለጸ።

ሚኒስቴሩ በዘርፉ የሚተገብራቸው የድጋፍ ማዕቀፎች በሁለት ዋና አቅጣጫዎች የተደራጁ ሲሆን፣ አንደኛው “ቀጥታ ድጋፍ” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በኢትዮጵያ የውሃ ፖሊሲ መሠረት “ወጪን በማስመለስ” መርህ ላይ የተመሠረተ የብድር ሥርዓት መሆኑን የውሃ ልማት ፈንድ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዶጊሶ ጎና ገልጸዋል።

በቀጥታ ድጋፍ ማዕቀፍ ስር የሚሰጠው ድጋፍ በፌዴራል መንግስት፣ በልማት አጋሮችና በተለያዩ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት የሚደገፍ ነው ያሉት መሪ ሰራ አስፈጻሚው በቀጥታ ለክልሎችና ለከተሞች በመተላለፍ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች እንዲገነቡ ያግዛል ብለዋል ።

ይህ ድጋፍ በተለይ ለገጠር መንደሮችና መለስተኛ ከተሞች አገልግሎታቸውን ለማስፋፋት ጠቃሚ መሆኑንም ገልጸዋል።

በሁለተኛው የድጋፍ ማዕቀፍ ስር ደግሞ ለመካከለኛና ትላልቅ ከተሞች ለመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ፋይናንስ በብድር መልክ የሚያገኙ ሲሆን፣ ብድሩ በረጅም ጊዜ የሚከፈልና በአነስተኛ ወለድ የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት መሪ ስራ አስፈጻሚው ይህም የውሃ ተቋማት በፋይናንስ ራሳቸውን እንዲችሉና ዘላቂ የአገልግሎት ሥርዓት እንዲፈጥሩ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ብለዋል ።

በውሃ ልማት ፈንድ ስር በሚተገበሩ ፕሮግራሞች አማካኝነት በ115 ከተሞች (133 ፕሮጀክቶች) ከ 34 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመጥ ውሃ አቅርቦትና ለሳኒቴሽን መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ባለፉት 15 ዓመታት የተሰጠ ሲሆን ይህ የፋይናንስ ድጋፍ አዳዲስ የውሃ መገኛ ቦታዎችን ለማልማት፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንኮችን ለመገንባት፣ የስርጭት መስመሮችን ለማስፋፋትና የፓምፕ ሥርዓቶችን ለማዘመን ወሳኝ ሚና መጫወቱን አቶ ዶጊሶ አክለው ገልጸዋል።

እስካሁን ከተደገፉት 115 ከተሞች ( 133 ፕሮጀክቶች) ውስጥ በ97 ከተሞች የውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ አገልግሎት የገቡ ሲሆን፣ ከ8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ንፁህና ዘላቂ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ በከተሞች ውስጥ የውሃ እጥረትን በመቀነስ፣ የህብረተሰቡን ጤና በማሻሻልና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በማጠናከር ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሆነም ነው መሪ ስራ አስፈጻሚው የገለጹት።

በተጨማሪም ቀሪ 17 የመጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች በተለያዩ የግንባታ ደረጃዎች ላይ እንደሚገኙና ሲጠናቀቁም ተጨማሪ ዜጎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል።

በሌላ በኩል “ባስኬት ፈንድ” በተባለው ፕሮጀክት 43 ከተሞች የውሃ ፕሮጀክቶች የተገነቡ ሲሆን፣ ይህ ፈንድ የተለያዩ የልማት አጋሮች (ከአውሮፓ ኢንቨስት መንት ባንክ ፣ ከጣሊያን እና ከፈረንሳይ ልማት ድርጅቶች የፋይናንስ ድጋፍን በአንድ ማዕቀፍ በማሰባሰብ እና ከክልሎች በሚዋጣ የፕሮጀክት መዋጮ ጋር በተቀናጀ መልኩ ለመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እንዲውል ማስቻሉን አክለው ነግረውናል።

ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል ከ88ሺ በላይ ዜጎችን ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርገውና ከ383 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሾኔ ከተማ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ የውሃ መገኛ ልማት፣ የማጠራቀሚያ ታንኮች ግንባታ፣ የስርጭት መስመሮች ዝርጋታ እና የቧንቧ ትስስር ሥራዎችን በማካተት የተገነባ መሆኑንና ለከተማዋ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በእጅጉ እንደሚያሻሽል መሪ ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Haile G/Selassie Road
Addis Ababa
5744AND5673

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30