የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

Share

Federal Democratic Republic of Ethiopia Public Servant Social Security Administration

04/06/2026

INVITATIONS TO BID

(International Competitive Bidding)

Bid Ref. No. PSSSA/ICB/001/2018

1. Public Servants' Social Security Administration hereunder referred as (PSSSA) is desirous of hiring an Engineering Firm for Design-Build Construction Work for Wastna Smart Village Development Project (Phase 1 – Hotel-Mall) to be developed near Addis Ababa at Koye Fetche Sub City inside Sheger City.

2. Public Servants' Social Security Administration (PSSSA) now invites eligible bidders of Category One Engineering firms with relevant experience and valid licenses or its equivalent as first class firm in their origin of country valid for the year 2018 Ethiopian Calendar, to submit sealed tenders for Design-Build Construction Work for Wastna Smart Village Development Project (Phase 1 – Hotel-Mall).

3. The building shall have an estimate minimum total floor area of 300,000 m2 fulfilling the minimum FAR requirement of the local development plan and an estimated net floor area of not less than 80% and in no way its maximum total floor area shall be more than 320,000 m2.

4. Interested bidders can purchase a full set of tender documents by paying Birr 500.00 in cash to the Public Servants’ Social Security Administration’s (PSSSA) Finance Directorate.

5. All bids must be accompanied by a bid security of ETB 2,000,000.00 /Two Million Birr or equivalent amount in USD as per the selling price of USD to ETB at Ethiopian National Bank 28 days before the date of Bid Closing, in the form of CPO or unconditional Bank Guarantee valid for 73 calendar days from bid opening in the form provided in the Bid Document payable to the Employer at the first demand without any contestation whatsoever, and must be submitted at the address of:-

6. The bid will be closed at 2:00 P.M on the 41st day from the date of the bid announcement and will be opened on the same day at 2:30 P.M in the presence of bidders or their legal representatives at the Office of the Procurement Directorate of the Public Servants’ Social Security Administration. If the 41st day is a weekend or holiday, the bid will be opened at the above time on the next working day.

7. Bids shall be valid for a period of seventy three (73) calendar days after bid closing.

8. The Public Servants’ Social Security Administration reserves the right to accept or reject any or all bids.

Public Servants’ Social Security Administration (PSSSA)
Arat Kilo, Queen Elizabeth Street
Addis Ababa, Ethiopia
Tel:- 011-1 23-26-96
Floating Date May31/2026

Photos from የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር's post 03/06/2026

የሕንጻ ኪራይ ማስታወቂያ 🏢

======//======

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ሊሴ ገ/ማሪያም ት/ቤት አከባቢ የሚገኘውን ዋስትና የንግድ ማዕከል ቁ. 2 ህንጻ ለተለያየ የንግድ ዘርፍ ለተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ማከራየት ይፈልጋል። 🏗

ሕንጻው ፡-

👉🏽 ለቢሮ አገልግሎት🖥፣
👉🏽 ለካፌና ሬስቶራንት☕️🍽፣
👉🏽 ለህክምና መስጫ ማዕከላት🏥፣
👉🏽 ለተለያዩ መዝናኛዎች የሚሆን እና 🎉
👉🏽 ለሌሎችም የንግድ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎች አሉት፡፡

ሕንጻው የሚገኝበት አካባቢ፡-

👉🏽 አስተማማኝ የደህነት ካሜራ ያለው📹፣
👉🏽 ለዕይታ ማራኪ🌆፣
👉🏽 በቂ የመኪና ማቆሚያ🚗 እና
👉🏽 የከርሰ ምድር ውሃ ያለው ነው💧።

ለመከራየት ፍላጎት ያለችሁ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች አራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ የህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 209 በመገኘት መከራየት የምትፈልጉትን የቦታ ስፋትና ወለል በመጥቀስ የኪራይ ፍላጎት ማሳወቂያ ማስገባት የሚትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 📝

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-

👉🏽 0910919629📱፣
👉🏽 0913586337📱 እና
👉🏽 0911936275📱

በመደወል መረጃውን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር

26/05/2026

🌙 እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🌙

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም፣ በጤና እና በህይወት አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል! ✨

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችን ነው።

✨ ኢድ ሙባረክ! ✨

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
#የአረፋበዓል #የመንግስትሠራተኞችማህበራዊዋስትናአስተዳደር #ማህበራዊዋስትና

Photos from የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር's post 20/05/2026

አስተዳደሩ የዕውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ግንቦት 12/2018 ለሠራተኞቹ የምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት መርሃ ግብር አካሄደ።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሸጉ ኬሎ እንዳሉት ተቋሙ በተለያዩ ከተሞች ያስገነባቸውን ስምንት ዘመናዊ የቢሮና የንግድ ሕንጻዎች ግንባታ አጠናቆ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ማስመረቁ በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በትጋት በማከናወናቸው የተገኘ ውጤት በመሆኑ ሁላችሁም ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

ወደፊትም እንዲህ አይነት ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ በመሆኑ አሁንም መደጋገፍን መሠረት በማድረግ በአንድነትና በጋራ ሆነን የተቋሙን ስኬት ማስቀጠል ይጠበወቅብናል ብለዋል።

አስተዳደሩ በዋናነት የተቋሙን የመፈጸም አቅም በማሳደግ የመንግሥት አገልግሎት ጡረታ ዐቅድን የማጠናከርና የማስፋት፤ የኢንቨስትመንት ፈንዱን በማዳበር የጡረታ ባለመብቶችን ገቢ በየጊዜው የማሻሻል እና በፈንድ አስተዳደር ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቁርጠኝነት በመቅረፍ የጡረታ ፈንዱን ቀጣይነትና አስተማማኝነት የማረጋገጥ ኃላፊነቶች በማቋቋሚያ ደንቡ ላይ ተቀምጠውለታል። በመሆኑም እነዚህን ዓላማዎች ለማሳካትና የጡረታ ባለመብቶችን ህይወት ለመለወጥ በትብብር በመስራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የላቀ አገልግሎት የሚሰጥ ጠንካራ ተቋም ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት አስተዳደሩን በኃላፊነት በመምራት አሁን ለደረሰበት ስኬት እንዲበቃ በማድረግ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የቀድሞው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳባ ኦሪያ ምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።

በዋና መ/ቤት በተካሄደው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባና የመሃል ሪጅን ጽ/ቤት ሠራተኞች ተካፍለዋል።

Photos from የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር's post 14/05/2026

አስተዳደሩ የዘጠኝ ወራት ዕቀድ አፈጻጸሙን ገመገመ
============ #============
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከግንቦት 2 – 4/2018 ድረስ በአዳማ ከተማ ገመገመ።

የአስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሸጉ ኬሎ እንዳሉት አስተዳደሩ ያስመዘገባቸው ስኬቶች የሁሉም ሠራተኞች ጥረት ውጤት ነው። ይህ ውጤትም ተጠብቆ በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት መደጋገፍን መሰረት በማድረግ በጋራ መስራት ይጠበቃል። በዚህ መድረክም በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎችን በመቀጠል በቀሪ ወራት ውስጥ ልንፈጽማቸው የሚገቡ ቀጣይ ስራዎቻችን ላይ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል ብለዋል።

በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩ ላይ በቀረበው ሪፖርት እንደተገለጸው ለ166,252 የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መለያ ቁጥር መሰጠቱንና ለ48,436 አዲስ ጡረታ ለወጡ ባለመብቶች የጡረታ አበል ተወስኗል።

የተቋሙን ስራዎችና አገልግሎቶች ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግም በ8926 ነጻ ስልክ መስመር፣ በህትመት፣ በተለያዩ የአስተዳደሩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እና በመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን የማሰራጨት ስራ ተሰርቷል።

በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን በተመለከተም በ5,243 መ/ቤቶች ላይ የመዋጮ ገቢ ምርመራ ተደርጓል። በዚህም ውዝፍ የተገኘባቸው ተቋማት ገቢ እንዲያደርጉ ተደርጓል። አመታዊ የጡረታ ባለመብቶች መታወቂያ እድሳት 97% ተከናውኗል።

የተቋሙን የመፈጸም አቅም ለማሳደግም በየደረጃው ለሚገኙ 1,785 አመራሮችና ባለሙያዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል ተብሏል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትም አስተዳደሩ የሪፎርም ስራዎች ትግበራን በማጠናከር፣ የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ፣ መረጃዎችን ለሶፍትዌር ዝግጁ በማድረግ እንዲሁም የክፍያ ክትትልና ቁጥጥርን በማጠናከር ላይ ትኩረት በማድረግ በተሰሩ ስራዎች የተገኙ ውጤቶችም ለውይይት ቀርበዋል።

ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች እና የሪጅን ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

05/05/2026

እንኳን ለ85ኛው የአርበኞች መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🇪🇹

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞቻችን፣ ለጡረታ ባለመብቶች፣ ለመንግስት ሠራተኞችና ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እንኳን ለዚህ ታላቅ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

የዛሬው ማንነታችን የትላንት ድል ውጤት ነው። አስተዳደራችን በተለያዩ ጊዜያት ሀገራቸውን በታማኝነትና በጀግንነት ያገለገሉ የመንግስት ሠራተኞችንና አርበኞችን ማህበራዊ ዋስትና በማረጋገጥ ረገድ የበኩሉን አሻራ ሲያኖር ቆይቷል።

ዛሬም እንደ ትላንቱ ሁሉ የአርበኞቻችንን የክብርና የጀግንነት ታሪክ እየዘከርን፣ የተረከብነውን የማህበራዊ ዋስትና ተልዕኮ በላቀ አገልግሎትና በዘመናዊ አሰራር በማጠናከር ለዜጎቻችን የማህበራዊ ዋስትና ጋሻ ለመሆን እንተጋለን።

"የአርበኞች ድል ለዛሬው ስራችን ጥንካሬ፣ ለነገው ተስፋችን ዋስትና ነው!" 💪✨

ክብርና ሞገስ ለጀግኖች አርበኞቻችን! 🎖️

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

Photos from የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር's post 04/05/2026

ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ሸጉ ኬሎ የዋስትና ህንጻዎች ምረቃ መረሃ-ግብር ላይ ያተላለፈ መልዕክት

ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ፤ የኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፤ የዕለቱ የክብር እንግዳ፤
ክቡራትና ክቡራን ሚኒስትሮች፤
ክቡር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክር ኢዮበ ተካልኝ፤
የተከበሩ አቶ ግርማ ብሩ የአስተዳደሩ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሰቢ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካር ሚኒስትር፤
የተከበራችሁ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች፤
የተከበራችሁ የአስተዳደሩ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት፤
ክቡራትና ክቡራን፤

በመጀመሪያ በዚህ ታሪካዊ ዕለት፤ የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለደረሰበት ውጤት ክብር ለመስጠትና የውጤቱ ተካፋይ ለመሆን በመካከላችን ስለተገኛችሁ፤ በራሴና በአስተዳደሩ ስም እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ።
ዛሬ የምንገኘው፤ የተቋሙ አዲስ ምዕራፍ በሚበሰርበትና የዓመታት የድካም ፍሬዎችን በምናይበት የደስታ ቀን ላይ ነው። እነዚህ ዛሬ የምናስመርቃቸው ዘመናዊ ሕንጻዎች ለተቋማችን ተራ የቁስ ሀብቶች ብቻ ሳይሆኑ፤ ይልቁንም የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ዋስትና ከነበረበት የህልውና ትግል ወጥቶ ወደ ስኬት ጎዳና መሸጋገሩን የሚያመላክቱ ሕያው አሻራዎቻችን ናቸው።

ክቡራትና ክቡራን፤
ተቋሙ ትላንት የነበረበትን ፈታኝ ሁኔታ መለስ ብሎ ማስታወስ፤ የዛሬውን ስኬት ትርጉም ይበልጥ ጎልቶ እንዲታይ ያደርገዋል። ለበርካታ ዓመታት የጡረታ ፈንዱ በከፍተኛ የመሸርሸር አደጋ ውስጥ ወድቆ፤ የነገው ዋስትና 'ይቀጥል ይሆን?' በሚል አጠራጣሪ ምዕራፍ ውስጥ አልፏል። ያ-ወቅት ተቋሙ ከነበረበት አስከፊ የቁልቁለት ጉዞ የተነሳ፤ ለመንግሥት ሠራተኞች የተስፋ ብልጭታ ያላሳየ፤ ለጡረታ ባለመብቶች ደግሞ ክብርንና መተማመንን ያልሰጠ ጭጋጋማ ጊዜ ነበር። ሆኖም በለውጡ መንግሥት ቁርጠኝነትና በወሰድናቸው የሪፎርም እርምጃዎች፤ ያ- ስጋት ዛሬ ወደ መልካም ዕድልና ብሩህ ተስፋ ተቀይሯል።

በተሻሻለው የጡረታ አዋጅና የመቋቋሚያ ደንብ በተገኘው ምቹ የሕግ ማዕቀፍ በመታገዝ፤ አስተዳደሩ ራሱን በጠንካራ የፋይናንስ መሠረት ላይ ለመገንባት እየታተረ ይገኛል። ተቋሙ የመገኘቱ ዋነኛ መሠረት ለሆኑት የጡረታ ባለመብቶች ተጠቃሚነት ሲል ሰፊ ርቀት ተጉዟል። ምንም እንኳን የጡረታ ባለመብቶች ብዛት በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 597,059 በ33 በመቶ ዕድገት በማሳየት 800,000 ቢደርስም፤ ከቁጥራዊ ዕድገቱ ባሻገር የባለመብቶችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ አምስት ጊዜ የጡረታ አበል ክፍያ ማስተካከያ አድርጓል። ይህም በ2010 ዓ.ም ብር 744.00 የነበረው ዝቅተኛ የጡረታ አበል ክፍያ ከአምስት እጥፍ በላይ ዕድገት በማሳየት ወደ ብር 4,669.00 እንዲደርስ ተደርጓል። ይሁን እንጂ አስተዳደሩ ይህም በቂ እንዳለሆነ ይገነዘባል።

የተከበራችሁ እንግዶች፤

አስተዳደሩ ፈንዱን ከመፍረስ ከመታደግ አልፎ አዋጭ በሆኑ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በመሰማራት በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ መሳተፍ ችሏል። ዓመታዊ የጡረታ አበል ክፍያ አቅም በ2010 ዓ.ም ከነበረበት ብር 5.9 ቢሊዮን ከአምስት እጥፍ በላይ በማደግ ብር 36.5 ቢሊዮን ደርሷል። በእነዚህ ስምንት ዓመታት፤ ጠቅላላ የጡረታ ፈንዱም ከስድስት እጥፍ በላይ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል። ከዚህ ቀደም ከአንድ በመቶ በታች በሆነ የትርፍ ምጣኔ በአንድ መስክ ተወስኖ የነበረው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ዛሬ ወደ አምስት አዋጭ መስኮች እንዲሰፋ በመደረጉ፤ ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ገቢያችን ከብር 591 ሚሊዮን ወደ ብር 40 ቢሊዮን ሊያድግ ችሏል። ይህም ተቋሙ የጡረታ አበል ክፍያ ወጪውን የመሸፈን ምጣኔ ከነበረበት 10 በመቶ ሙሉ በሙሉ ወደመሸፈን እንዲሸጋገር ለማድረግ አግዟል።

ዛሬ በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በሐረር እና በጅማ ከተሞች የምናስመርቃቸው ባለግርማ ሞገስ የቅይጥ አገልግሎት ሕንጻዎች፤ ተቋሙ ዜሮ ሊባል ከሚችል ቋሚ ሀብት ድርሻ ተነስቶ በብር 30 ቢሊዮን የሚገመት ሀብት ለማፍራት አስችለዋል።

ወደፊት በምናደርገው ጉዞ፤ በግንባታውም ሆነ በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች የምናደርገውን ተሳትፎ አጠናክረን የምንቀጥል ቢሆንም፤ ዋናው ትኩረታችን ተቋሙን በመላው ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የዘመነ፤ ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ ላይ ይሆናል። ይህንን ለማሳካትም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን በማፋጠን የጡረታ ባለመብቶች የሚገባቸውን ክብርና ዋስትና ያለ እንግልት ከቤታቸው ሆነው የሚያገኙበትን ወረቀት አልባ ሥርዓት እንገነባለን። ከዚህ የቴክኖሎጂ ሽግግር ጎን ለጎን ተቋማዊ አደረጃጀታችንን እና የሰው ኃይል አቅማችንን በወቅቱ ካለው ተወዳዳሪነት ጋር ለማጣጣም የሚያስችሉ ጥልቅ የሪፎርም ሥራዎችን ተግባራዊ እናደርጋለን። ይህም ዘመናዊ መሣሪያዎችን በዕውቀት፣ በታማኝነትና በላቀ የሥራ ሥነ-ምግባር የሚያንቀሳቅስ ብቁ የሰው ኃይልና ውጤታማ አሠራር በመፍጠር ህልማችንን ዕውን ያደርጋል።

በመጨረሻም፤
ለዚህ ስኬት መመዝገብ መሠረት ለሆናችሁ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፤ ስትራቴጂካዊ አመራር ለሰጣችሁ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትና ለባለድርሻ አካላት ምስጋናዬ የላቀ ነው።
ይህ ስኬት እውን እንዲሆን፤ ርዕዩን ተጋርታችሁ ሌት ተቀን ስትደክሙ ለነበራችሁ የአስተዳደሩ አመራሮችና ሠራተኞች የላቀ አክብሮትና ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ሁሉንም ነገር በትዕግስትና በተስፋ ለጠበቃችሁ የጡረታ ባለመብቶች ደግሞ፤ "ይህ ድል የእናንተ ነው፤ ይህ ተቋም የእናንተ የክብር ማማ ነው!" ለማለት እወዳለሁ። ሁላችንም ያሉንን መልካም አጋጣሚዎች በጋራ በመጠቀም፤ ተቋማችንን የከፍታ፣ የጥራትና የክብር ተምሳሌት እናድርግ!

ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!
አመሰግናለሁ!

Photos from የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር's post 02/05/2026

" አስተዳደሩ ስጋቱን ወደ ስኬታማ ኢንቨስትመንት ቀይሯል" — አቶ ታገሰ ጫፎ

የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ያስገነባቸውን ዘመናዊ ሕንፃዎች ዛሬ በይፋ አስመርቋል።

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተቋሙ ለዘመናት የነበረበትን የስጋት ደመና በማስወገድ ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ መሸጋገሩን አብስረዋል።

እሳቸው ያነሱት ዋና ዋና ነጥቦች፦

ከስጋት ወደ ዕድል፦ ተቋሙ ላለፉት 70 ዓመታት የሠራተኛው ዋስትና ሆኖ ቢቆይም፣ የጡረታ ፈንዱን ወደ ኢንቨስትመንት የመቀየር አቅም ማጣቱ ለረጅም ጊዜ ስጋት ሆኖ ቆይቷል። አሁን ግን በሪፎርሙ አማካኝነት ይህ ስጋት ወደ መልካም አጋጣሚ ተቀይሯል።

የሕግ ማዕቀፍ ለውጥ፦ በለውጡ መንግሥት አማካኝነት የጸደቁት አዳዲስ አዋጆችና ደንቦች ተቋሙ ፈንዱን ከማስጠበቅ ባለፈ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን አስችለውታል።

የሕንፃዎቹ ትርጉም፦ አፈ ጉባኤው "ሕንፃዎቹ የተገነቡት ከድንጋይና ከብረት ብቻ አይደለም፤ በእያንዳንዱ ጡብ ውስጥ የጡረታ ባለመብቶች ክብርና የሠራተኞች ላብ አለ" በማለት ግንባታዎቹ የባለመብቶችን እርካታ ለማረጋገጥ ያላቸውን ፋይዳ ገልጸዋል።

የወደፊት ራዕይ፦ የፈንዱን ዘላቂነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋፋትና አገልግሎቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በመጨረሻም አቶ ታገሰ መንግሥት ለተቋሙ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል በመግባት፣ ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Queen Elizabeth Street
Addis Ababa
1030

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30