Gullele woreda 3 Communication

Call Directions Website Contact the organization

Gullele woreda 3 Communication ይህ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የፌስ ቡክ ገፅ ነው
ፔጃችንን ፎሎው በማድረግ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎችን ያግኙ!! ፔጃችንን ላይክ በማድረግ በወረዳችን የሚከናወኑትን አበይት ጉዳዮች መረጃ ያግኙ

ሳምንታዊ ቅዳሜና እሁድ ገበያ የተለያዩ የግብርና ምርቶች ለሸማቹ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡************************************************(ጉለሌ ወረዳ 3...
10/10/2026

ሳምንታዊ ቅዳሜና እሁድ ገበያ የተለያዩ የግብርና ምርቶች ለሸማቹ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
************************************************
(ጉለሌ ወረዳ 3 ኮሙኒኬሽን 30/01/2019ዓ.ም)
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለልና የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር የተጀመሩት የቅዳሜና እሁድ የሰንበት ገበያ የግብርና እና የኢንደስትሪ ምርቶችን፤ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባደረገው ምልከታ በመነን አደባባይ በሚገኘው የገበያ ቦታ ማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በስፋት እየተገበያየ እና በርካታ ግብዓቶችም የቀረቡ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቃሚዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

10/10/2026

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር " ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ !! " 3ኛ ዙር የብክለት ንቅናቄ የጽዳት ንቅናቄ መዝጊያ መርሃ ግብር

መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ምአዲስ አበባጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦   #የመደመርመንግሥት
10/10/2026

መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦

#የመደመርመንግሥት

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ጀምረናል።ባለፉት አምስት ዓመታት ከገባነው ቃል በላይ በመፈጸም ያስመዘገብነውን ስኬት መነሻ በ...
10/10/2026

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ጀምረናል።
ባለፉት አምስት ዓመታት ከገባነው ቃል በላይ በመፈጸም ያስመዘገብነውን ስኬት መነሻ በማድረግ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከበፊቱ የላቀ ዉጤት ለማምጣት የ5አመት እና የ2019 በጀት አመት እቅድ አዘጋጅተንየላቀ ለዉጥ ለማምጣት ተዘጋጅተናል።
የሥራችን ስኬት የሚመዘነው በተሠሩ ሥራዎች ብዛት ብቻ አይደለም። ዋናው መመዘኛ የሕዝባችንን የኑሮ ጫና ምን ያህል እያቀለልን ነዉ፣ አገልግሎቶችን ምን ያህል አሻሽለናል፣ ለወደፊትስ የሚቀጥል ምን ዓይነት ተቋማዊ አቅም ገንብተናል የሚለው ነው።
የመደመር መንግስት እንደ መሆናችን የተቋማትን፣ የሀብቶችንና የእውቀትን አቅም በማቀናጀት፣ የዛሬን ውጤት ወደ ነገ አቅም፣ የዛሬን ስኬት ወደ ዘላቂ ብሔራዊ ብቃት እየቀየርን የጋራ ሀገር ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን።
አዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ከተሞች ምሳሌ፣ ከዓለም ከተሞች ጋር ተወዳዳሪና ለሕዝቧ የተሻለ ኑሮ የምታረጋግጥ ከተማ መሆን አለባት። ይህንንም የምናረጋግጠው በተቀናጀ አመራር፣ በጠንካራ ተቋማትና በሰዉ ተኮር አፈጻጸም ነው።
የዛሬ ሥራችን የነገ አቅማችን ነው፤ የዛሬ ውጤታችን የነገ የኢትዮዽያ ሥልጣኔ መሠረት ነው!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ See less

10/10/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ ሾመዋል። Prim...
10/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ ሾመዋል።
Prime Minister Abiy Ahmed reappoints Getachew Reda as East Africa Affairs Advisor to the Prime Minister with a rank of Minister.
See less

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ መካከል በተደረገ አጋርነት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባውን ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመሩን ...
10/10/2026

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ መካከል በተደረገ አጋርነት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባውን ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመሩን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው።
‎
‎በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው ይህ የማጣሪያ ፋብሪካ፤ በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት ለመጨመር፣ የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ ለማጠናከር እና ሀገራችንን በውድ ማዕድናት ማጣሪያ ረገድ ቀጣናዊ ማዕከል ለማድረግ ለተጀመረው ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው።
‎
‎ይህ ውጥን፤ ሀብቶቻችንን ከኢንዱስትሪ አቅም ጋር በማስተሳሰር ወጭ ንግድ ገቢን ለማሳደግ፣ የሰለጠነ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ እንዲሁም ይበልጥ ግልጽ እና ተወዳዳሪ የሆነ የወርቅ እሴት ሰንሰለት ለመገንባት የመደመር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
‎
‎ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር ድረስ በሀገራችን ውስጥ የላቀ እሴት እየፈጠርን እንገኛለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) See less

‎የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር እና ልዑካቸውን ዛሬ አግኝቻለሁ።‎በቆይታችን በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን ጠንካራና የቆየ ወዳጅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ...
09/10/2026

‎የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር እና ልዑካቸውን ዛሬ አግኝቻለሁ።
‎በቆይታችን በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን ጠንካራና የቆየ ወዳጅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ሲሆን፤ ከሰሞኑ በሕንድ ካደረግኩት ጉብኝት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ከነበረኝ ቆይታ ተከትሎ በተጠናከረ ትብብርና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወዳጅነታችንን ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተነጋግረናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የመደመር መንግሥት ምስረታ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፦1. ክቡር ዳንኤል ክብረት - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ...
09/10/2026

የመደመር መንግሥት ምስረታ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፦

1. ክቡር ዳንኤል ክብረት - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ ኃላፊ

2. ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የENFI ክትትል ዘርፍ ኃላፊ

3. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

4. አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

5. ዶ/ር ደረጀ ድጉማ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

6. አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

7. አቶ ሀብታሙ ሲሳይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ

Address

Haile Melekot Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gullele woreda 3 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gullele woreda 3 Communication:

Shortcuts

Share