Ethiopian Technology Authority

Ethiopian Technology Authority

Share

The official page of the Ethiopian Technology Authority (ETA).

The Ethiopian Technology Authority (ETA) is a government organization established by Proclamation No. 1263/2021 to ensure the safety of the people, the environment and property from harmful effects of technology use and application in various industries and development sectors. The Authority has duties and responsibilities of regulating technology uses in industries with set regulatory standards a

Photos from Ethiopian Technology Authority's post 22/05/2026

በባለስልጣኑ ቢሮ የስራ ጉብኝት ተካሄደ
***************************************
የቻይና አቶሚክ ኢነርጅ ባለስልጣን ምክትል ሊቀመንበር H.E Mr.Liu Jing እና የቻይና አቶሚክ ኢነርጅ ባለስልጣን ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ቢሮ ተገኝተው የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ምክትል ሊቀመንበሩ የስራ ጉብኝት ያደረጉት ግንቦት 14/2018 ሲሆን ለስራ ጉብኝት መ/ቤቱ ሲደርሱ የባለስልጣኑ የበላይ ሀላፊዎችና ልዩ ልዩ የስራ ክፍል ተጠሪዎች ደማቅ አቀባበልና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልካም ምኞት መልዕክት አቅርበውላቸዋል፡፡ እንግዶቹ በስራ ላይ ጉብኝት ቆይታቸው በባለስልጣኑ የተመረጡ የስራ ክፍሎችና በቤተ-ሙከራ ክፍል እየተዘዋወሩ የስራ ላይ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በጉብኝቱ ወቅት በባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ጌታቸው(ዶ/ር) እና ም/ዋና ዳይሬክተር መብራቱ ገ/ማሪያም (ዶ/ር) እንዲሁም የስራ ክፍል ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስራ ሂደት ስለሚከናወኑ ተግባራት፣ በቤተ-ሙከራ ውስጥ የቁጥጥር ስራን ለማሳለጥ ስለሚሰሩ ተግባራትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ገለጻ ቀርቦላቸዋል፡፡ እንግዶቹ በነበራቸው የስራ ላይ ጉብኝት ቆይታ ስለባለስልጣኑ አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቂ መረጃ ማግኘታቸውን የገለጹ ሲሆን በተመለከቱት ነገር ሁሉ መደመማቸውን አመልክተዋል፡፡ የስራ ሀላፊዎቹ ጉብኝት ለባለስልጣኑ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች እንደሚያስገኝም በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ ላይ ተመልክቷል፡፡

08/05/2026

The first global instrument on spent fuel and radioactive waste safety? The Joint Convention on the Safety of Spent Fuel Management and on the Safety of Radioactive Waste Management.

Adopted under the auspices of the IAEA, the Joint Convention

✅ provides a framework that:
- Relies on encouragement through a peer review mechanism
- Facilitates collaboration among Contracting Parties
- Enables self-assessment of national safety frameworks
- Helps identify opportunities to enhance safety through reporting, dialogue and feedback

❌ it does not:
- Include enforcement mechanisms
- Establish a sanctions regime for non-compliance
- Create an international regulatory framework with inspection
- Mandate the IAEA with oversight authority

Today, 93 Contracting Parties are working side by side to protect people and the environment from harmful effects of ionizing radiation.

Learn more about the Joint Convention here: https://atoms.iaea.org/Joint-Convention

Photos from Ethiopian Technology Authority's post 06/05/2026

በሐረር ከተማ ለ12 አረጋውያንና አቅመ ደካሞች የተገነቡ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ተመረቁ።
==================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በሐረር ከተማ ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በምርቃት አስረክቧል።

ይህ የበጎ ፈቃድ ፕሮጀክት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ካለበት ሀገራዊ ተልዕኮ ጎን ለጎን፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና የአቅመ ደካማ ዜጎችን የኑሮ ሸክም ለማቅለል ካለው ቁርጠኝነት የመነጨ ነው።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ተገኝተው የዜጎችን ሕይወት የሚቀይር ሥራ በማጠናቀቃቸው የተሰማቸውን ላቅ ያለ ደስታ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ አክለውም አረጋውያንን መደገፍና መጠለያ ማበጀት ቀዳሚው የሞራልና የሰብዓዊነት ተግባር መሆኑን በአፅንዖት አመልክተዋል።

የተገነቡት 12 አዳዲስ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ለእያንዳንዱ አባወራ እና እማወራ አስፈላጊ የሆኑ የቤት ቁሳቁሶች የተሟሉላቸው በመሆናቸው፣ ተጠቃሚዎች በክብር እንዲኖሩ ያስችላቸዋል ተብሏል።

ከመኖሪያ ቤቶቹ በተጨማሪ ተጠቃሚዎቹ ኑሯቸውን በዘላቂነት መደጎም እንዲችሉ የፈሳሽ ዘይት ማምረቻ፣ የዶሮ እርባታ፣ የዳቦ መጋገሪያና የመሸጫ ሱቆች ተገንብተው ሥራ እንዲጀምሩ መደረጉን ክቡር ሚኒስትሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። ይህም ፕሮጀክቱ ከመጠለያ ባሻገር ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ አስችሎታል።በመጨረሻም መሰል የበጎ አድራጎት ተግባራት የአንድነታችን መገለጫ በመሆናቸው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ምርቃቱም በደስታ ተጠናቋል። ምንጭ Ministry of innovation and Technology (MinT) Telegram Page

28/04/2026

የጥራት ማረጋገጫ አሰራር ሥርዓት
***************************************
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የጥራት ማረጋገጫ አሰራር ሥርዓት የዘረጋ ሲሆን የህግ ማስፈጸም ስራዎችም የሚከናወኑት ይህን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ በዚህ አሰራር ስርዓት ውስጥ የሚከተሉት ጉዳዮች ይካተታሉ
የህግ ማስፈጸም ተግባራትን ማስተዳደር

የህግ ማስፈጸም ስራዎችን ማስተዳደር የተቆጣጣሪ አካል አንዱ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም የሚከተሉትን ተግባራት ይመለከታል
*የህግ ማስፈጸም ፖሊሲና የአሰራር ቅደም ተከተል ማዘጋጀት
*የህግ ማስፈጸም ዕቅድ ማዘጋጀት
*የሚወሰደውን የህግ ማስፈጸም እርምጃ አይነት መለየት
*ለህግ ማስፈጸም የሚውለውን ሀብት ማዘጋጀት እና ስራ ላይ ማዋል
*ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚከናወኑ የህግ ማስፈጸም እርምጃዎችን መለየትና በጋራ እና በትብብር መስራት፣ ከነዚህ አካላት ጋር የትብብር ስምምነት ማድረግ
*በሚወሰዱ የህግ ማስፈጸም ጉዳዮች ላይ የክትትል ስራ ማከናወን
*የተወሰዱት የህግ ማስፈጸም ስራዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባስቀመጣቸው የህግ ማዕቀፎችና የአሰራር ስርዓቶች መሰረት ስለመሆኑ ማረጋገጥ
*የባለሙያዎችን አቅም መገንባት

የህግ ማስፈጸም ሰነዶች አያያዝና አደረጃጀት

*የቁጥጥር ግኝቶችን እና የተወሰዱ የህግ ማስፈጸም እርምጃዎችን ሰንዶ ማስቀመጥና መረጃቹ በቀላሉ ሊገኙ እና ሊመረመሩ የሚችሉ ተደርገው ይቀመጣሉ።
*በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና በሚመለከታቸው ሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ከህግ ማስፈጸም ጋር ከተያያዙ ጉዳዮች ጋር የተደረጉ የመረጃ ልውውጦች ለወደፊቱ ለማጣቀሻ እንዲሆኑ በመዝገብ ተሰንደው እንዲቀመጡ ይደረጋሉ
የተከናወኑ የቁጥጥር ስራዎችና የተወሰዱ የህግ ማስፈጸም እርምጃዎችን ክለሳና ግምገማ

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህግ ማስፈጸም ስራውን ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን ለማረጋገጥ የቁጥጥር እና የህግ ማስፈጸሚያ የህግ ማዕቀፎችንና ተግባሮቹን የሚገመግምበትና የሚከልስበት የአሰራር ሥርዓት ዘርግቷል፡፡ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ካሉ በተዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆኑ ይደረጋል

24/04/2026

[4/24/2026 2:43 PM] ETA - Ethiopian Technology Authority:
የህግ ማስፈጸሚያ ስልቶች
***************************
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ለሚያከናውናቸው የህግ ማስፈጸም ስራዎች በህግ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት በማድረግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስልቶች ይጠቀማል፡፡
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ፈቃድ የወሰደው አካል ተጓድለው የተገኙ የቁጥጥር መስፈርቶችን ዝርዝር በደብዳቤ እንዲያውቅና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ይደረጋል

የህግ ማስከበር ትዕዛዝ መስጠት
ፈቃድ ለተሰጠው አካል በተሰጠው የጊዜ ገድብ ውስጥ ተጓድለው የተገኙ መስፈርቶች በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማያሟላ ከሆነ የሚጠቀምበትን የጨረራ ክፍል እንዲታሸግ ተባባሪ እንዲሆን ትዕዛዝ ይሰጠዋል፡፡ በዚህ ሂደት ሌሎች የጨረራ አምጪ ቁስ ብክለት ሊገኝባቸው የሚችሉ ተቋማት ቢኖሩ የባለስልጣኑ ባለሙያዎች በሚያደርጉት ክትትልና የቁጥጥር ስራ አካባቢው በጨረራ አመንጪ ቁስ መበከሉ ሲረጋገጥ የተበከለው አካባቢን በመከለል ተቋሙ ቀጣይ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ባለስልጣኑ ለተቋሙ ትዕዛዝ ይሰጣል
ፈቃድ መሰረዝ ወይም ማገድ
የህግ ጥሰቱን መጠንና ሌሎች የባለስልጣኑን የአሰራር ቅደም ተከተሎች መሰረት በማድረግ ተቋሙ የተሰጠውን ፈቃድ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ሙሉ ለሙሉ ማገድ
ክስ መመስረት
ከባድ በሆኑ ጒዳዮች ላይ ጥፋተኛ በሆኑ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ላይ የወንጀል ክስ መመስረት፡-
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህግ ማስፈጸም ባለሙያዎች በተለዩ/በተገኙ የህግ ጥሰቶች እና የተጓደሉ የደህንነት መስፈርቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በህብረተሰቡ እና አከባቢው ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ጉዳት ወይም ተጽዕኖ ከግምት በማስገባት የህግ ጥሰቱ/ የተጓደሉ የደህንነት መስፈርቶችና የጥፋቱ እርከን/ደረጃ በባለስልጣኑ የውስጥ ህግ ማስፈጸም የአሰራር ቅደም ተከተል መሰረት በመገምገም ሊወሰድ የሚገባውን የህግ ማስፈጸም እርምጃ ከኃላፊዎች ጋር በመወያየት ይወስናሉ። እነሱም
•የህግ ማስፈጸም ባለሙያዎች በቁጥጥር ሂደት ማለትም በመደበኛ ኢንስፔክሽን ወይም በድንገተኛ ኢንስፔክሽን ወቅት ተጓድለው የተገኙ የህግ ጥሰቶች እና የሬጉላቶሪ ቁጥጥር ደህንነት መስፈርቶች ጉድለቶችን ይገመግማሉ
•የህግ ማስፈጸም ባለሙያዎች በቁጥጥር ሂደት ማለትም በመደበኛ ኢንስፔክሽን ወይም በድንገተኛ ኢንስፔክሽን ወቅት ተጓድለው የተገኙ የህግ ጥሰቶች እና የሬጉላቶሪ ቁጥጥር ደህንነት መስፈርቶች ይገመግማል፤ የህግ ጥሰት እርምጃ የተከናወነበት ተግባር ማስተካከያ አድርጎ ሲገኝ የተወሰደውን እርምጃ ይሽራል
•የህግ ማስፈፀም እርምጃው ህዝብ ማወቅ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች ውሳኔ መሰረት መረጃው ለህዝብ እንዲሰራጭ ይደረጋል፤
•ከውሳኔው በኋላ የአፈጻጸም ሂደቱ ከአጋር አካላት (ፖሊስ፣ የጤና ጥበቃ ቁጥጥር ዘርፍ እና አቃቤ ህግ/ፍርድ ቤት) በመሆን በጋራ የሚፈጸም ሲሆን አብዛኛውም የህግ ማስፈጸም ተግባራት አስተዳደራዊ እርምጃዎች በመሆናቸው ከጤና ጥበቃ ቁጥጥር ዘርፍ በመተባበር ይከናወናሉ። በአስተዳደራዊ እርምጃዎች ያልተስተካከሉ/ያልታረሙ ተቋማተ/ግለሰብ ወይም የጥፋቱ እርከን/ደረጃው ከፍ ያሉ ጉዳዮች ከፖሊስና አቃቤ ህግ ጋር በመሆን ክስ በመመስረት በፍርድ ቤት በማስወሰን በገንዘብና እስራት እንዲቀጡ የማድረግ ስራዎች ይከናወናል
ግለሰብ ወይም ተቋም የህግ ማስፈጸም ውሳኔ በባለስልጣኑ ከተወሰደበት በኃላ ውሳኔውን በተመለከተ ባለስልጣን መስያ ቤቱን ውሳኔ ላይ ይግባኝ የመጠየቅ መብት አለው፡፡ ይግባኙ ተቀባይነት የሚኖረው የህግ ማስፈጸም ውሳኔ በተወሰደ በ10 ቀናት ውስጥ መቅረብ ያለበት ሲሆን የይግባኝ ቅፁን በመሙላት ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ይግባኝ መጠይቅ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በቀረበው ይግባኝ መሰረት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንደየሁኔታው በተወሰነው የህግ ማስፈጸም ውሳኔ እንደገና ሊታይና ሊመረመር ይችላል፤ በድጋሚ የውሳኔ ሂደት ወቅት የህግ ማስፈጸም የህግ ማስፈጸም ውሳኔ ላይ ተሳትፈው የነበሩ እና ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ይሳተፋሉ
[4/24/2026 2:43 PM] ETA - Ethiopian Technology Authority: ለፍርድ ማቅረብ
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የተቀመጡ የህግ ማዕቀፎች ተጥሰው ሲገኙ ህጉን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ ክስ የመመስረት ሥልጣን አለው። የወንጀል ክስ ለመመስረት የሚያስችል በቂ ማስረጃ እንዳለ እና የወንጀል ክሱ ሕዝብን ከጨረራና ኑክለር ቁሶችና ቴክኖሎጂ ጉዳትና አደጋ ለመታደግ ሲባል የሚመሰረት ክስ ይሆናል። የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ዋና ዓላማ የጨረራና ኑክለር ቁሶችና ቴክኖሎጂዎች ለሰላማዊ ጥቅም ሲውሉ ጉዳቶችና አደጋዎች እንዳይከሰቱ እንዲሁም ህገወጥ የጨረራን ኑክለር ቁሶች ዝውውር እንዳይኖር በመከታተልና በመቆጣጠር ተቋማትና ግለሰቦች ሕጉን አክብረው እየሰሩ መሆኑን ማረጋገጥ ቢሆንም ይህን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ ክስ መመስረት የህግ ማስፈጸም አስፈላጊ አካል ነው.፡፡ የህግ ጥሰቱን ክብደት እና በዚህ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የጉዳት መጠን በመመዘን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም አማራጭ ቅጣቶችን ሳይጠቀም ክስ ሊመሠርት ይችላል
ሕዝብና አካባቢን ከጨረራና ኑኩለር ቴክኖሎጂ ቁሶችና ቴክኖሎጂ ተጓዳኝ ጉዳቶች ለመከላከል የቁጥጥር ስራ ከተከናወነ በኋላ ከሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ክስ ለመመስረት በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል
•ሕጉን የማክበር እና በሕጉ የተደነገጉ መስፈርቶችን የማስጠበቅ አስፈላጊነት ላይ የደህንነት እና ጥበቃ ባህልን ለማጎልበት ሁኔታው ተገቢ መሆኑ ሲታመን እና ሌሎች ከተመሳሳይ ጥፋት ሊታደግ እንዲቻል ትምህርት ለመስጠት
•የህግ ጥሰቱ በወቅቱ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ ባለመወሰዱ በሰራተኞች ወይም ህብረተሰብ ወይም አካባቢ ላይ የሚያስከትለው ተፅእኖ ከፍተኛ እንደሚሆን ሲታመንበት
የተወሰደ የህግ ማስፈጸም እርምጃን ለህዝብ ይፋ ስለማድረግ
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ተቋማት ያደረጓቸውን ማስተካከያዎች እና የዕገዳ የተጣለባቸውን ተቋማት ዝርዝር መረጃ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል። በተጨማሪም ሕጉን የማክበር አስፈላጊነት ትኩረት እዲሰጠውና ተቋማት ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ሲባል ያስተምራሉ የሚባሉ ማንኛውንም ጥፋተኛነትና የተወሰዱ የህግ እርምቶች ይፋ ሊደረጉ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የጨረራና ኑክለር ቁሶችና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምና አያያዝ በተመለከተ ለሚከሰቱ የህግ ጥሰቶች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የህግ ማስፈጸም ጉዳዮችን ለማከናወን ስልጣን አለው።
•በማንኛውም ጊዜ የባለስልጣኑ የምርመራ ባለሙያዎች የጨረራ አመንጪ ቁስና ከዚህ ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ የስራ እንቅስቃሴዎች የሚገኙበት ቦታ ገብቶ ምርመራ የማድረግ
•ከጨረራና ኑክለር ቁሶችና ቴክኖሎጂዎች ጋር የተገናኙ ማናቸውንም የስራ ክፍሎች፣ ማሽኖች፣ መሣሪያዎች፣ ማስቀመጫዎች ወይም መያዣዎች፣ መዝገብ ወይም ሰነድ መመርመር፣ የጨረራ ልኬት ማካሄድ፣ ቪዲዮ መቅረፅ፣ ፎቶግራፍ ማንሣት
•አስፈላጊ ሪፖርቶችንና ሰነዶችን የህግ መተላለፍ ከሰራው አካል መጠየቅ
•ጉድለቶችን እንዲያስተካክል፣ መስተካከል ያለባቸው ክፍተቶች እስኪስተካከሉ ድረስ ስራ እንዲያቆም የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ህጉን ተላልፎ ለሚገኝ አካል መመሪያ መስጠት
•አስፈላጊ ሲሆን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የስራ ገደብ መጣል
•የተቀመጡትን መስፈርቶች ሳያሟሉ በሚሰሩ አካላት ላይ የቅጣት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎች ህግ የማስጸም ስልጣን
•የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎች በሚያደርጉት የቁጥጥር ስራ ተጓድለው የሚገኙ መስፈርቶች በሰው ጤና እና አካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የቁጥጥር የስራ ቅደም ተከተል መሰረት በማድረግ ለተፈጸመው የህግ ጥሰት በቦታው ላይ በዚያው ቅጽበት ተገቢውን የህግ የማስጸም ስራ የማከናወን ሙሉ ስልጣን አላቸው

Photos from Ethiopian Technology Authority's post 23/04/2026

በዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ
**********************************
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡ ውይይቱ የተካሄደው ሚያዚያ 15/2018 በአዳማ ከተማ ሲሆን በውይይቱ ሂደት ገንቢ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በመጨረሻም ጠንካራ አፈጻጸሞችን ማስቀጠልና ክፍተት የተስተዋለባቸውን አፈጻጸሞች ደግሞ በቀጣይ ለመስራት በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቶ የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል ::

09/04/2026

Save the date!
Ministers, policymakers and energy leaders from around the world will convene at the International Ministerial Conference on Nuclear Power this October in Incheon, Republic of Korea.
Organized by the IAEA and hosted by the 대한민국 과학기술정보통신부 , this conference comes at a pivotal moment when global cooperation and new conversations are essential to shaping the future of nuclear power.
As the world moves toward low-carbon energy systems, nuclear power remains a vital pillar that supports global energy security and climate goals. Today, 31 countries operate more than 400 reactors, while over 60 others are actively exploring the nuclear option as part of their future energy mix.
From 27–29 October 2026, this high-level forum will share national strategies and long-term visions for nuclear energy, address key challenges in developing, maintaining and expanding nuclear power programmes, and strengthen international collaboration on next-generation nuclear technologies and the future nuclear workforce.

08/04/2026

ለአዲሶቹ ተከታዮቼ ምስጋና! በመቀላቀልዎ ደስ ብሎኛል! Balli Guchi, አቡ መስኡድ አብዱረህማን, Tilahun Tafere, Alemseged Abebe, Selemon Tafese, Benu Alex, Enalew Kassa, Mesfin Getahun, Mulugeta Made

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Meksico Kera, Bulgariya Mazoriya, Yared Aregawi Building
Addis Ababa
20486CODE1000