13/01/2023
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለ11 ተቋማት የላቀ የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና ሰጠ
**********************
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በህክምና ላብራቶሪ፣ በፍተሻና ንጽጽር ዘርፍ ለ11 ተቋማት የላቀ የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና ሰጠ።
የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ መሰረት ተሰማ እንደገለፁት የላቀ ብቃት የጥራት ማረጋገጫ አክሬዲቴሽን የተሰጣቸው በህክምና ላቦራቶሪ እንዲሁም በፍተሻና ካሊብሬሽን፣ የሚጠበቅባቸውን የሙያና ክህሎት ደረጃ መድረሳቸው ለተረጋገጠ ተቋማት ነው።
የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር፣ የሸጋው ሞጣ ጄነራል ሆስፒታልና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል ትናንት በአዳማ አክሬዲቴሽን ከተሰጣቸው መካከል መሆናቸውን አንስተዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የብሔራዊ የሳንባ ነቀርሳ ላቦራቶሪና የኢትዮጵያ ቴክስታይል ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትም የላቀ የጥራት ማረጋገጫውን ካገኙት መካከል መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
የጥራት ማረጋገጫው የሀገር ውስጥና የወጭ ምርቶች ጥራትን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲዘምኑ እንዲሁም ምርትና ምርታማነት ላይ የሚታዩ የጥራት ችግሮችን ለመፍታት ያግዛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/
25/10/2021
It is time to work hard to change the country`s trade practices.
06/10/2021
ክቡር አቶ ገብረመስቀል ጫላ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ሆነው በመሾሞ እንኳን ደስ አሎት እያልን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎ እንመኝሎታለን!!!
23/09/2021
የባለሥልጣኑ ሰራተኞች እና የስራ ኃላፊዎች ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2013ዓ.ም ነጩን ፖስታ ለነጩ ቤተመንግሥት ልከዋል!!!
14/09/2021
የባለሥልጣኑ ሰራተኞች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ውይይት መሰረት ለአገር መከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደሞዛቸው ብር 750,000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ለግሰዋል፡፡ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ደም የለገሱ ሲሆን በቀጣይም አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
06/09/2021
ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ !እዘምራለሁ! በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ሰራተኞች ክቡር ኢ/ር ዑሌሮ ኡፒየው የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በተገኙበት ዛሬ 2፡30 ላይ ኢትዮጵያዊነትን በመዘከር ለኢትዮጵያ ክብር በአንድነት እንቆማለን በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርን በመዘመር እና ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ስነ-ስርዓት አክብረዋል፡፡
16/08/2021
የናጄሪያው ግዛዋ የምርት ገበያ ድርጅት የስራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣንን ጎበኙ!
የናጄሪያው ግዛዋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የምርት ገበያ ደርጅት የስራ ኃላፊዎች ነሃሴ 7 ቀን 2013ዓ.ም በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በጉብኝቱም ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ኡሌሮ ኡፒየው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ስለኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን አሰራር በተመለከተ በባለሥልጣኑ የኢኮኖሚ ትንተና ዳይሬክተር በአቶ ኡርጌሳ ባይሳ ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ በተመሳሳይ በሉዑካን ቡድኑ የድርጅታቸውን አሰራር የተመለከተ ገለጻ በማቅረብ ውይይት ተካሄዷል፡፡
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ዑሌሮ ዑፒየው ለሉዓካን ቡድኑ ስለተቋሙ ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን አገራችንን ለማስተዋወቅ የሚረዱ መረጃዎችን በማጋራት እና የኢትዮጵያን ቡና ለማስተዋወቅ ለቡድኑ አባላት የቡና ስጦታ አበርክተዋል፡፡
በመጨረሻም ባለስልጣኑ ገበያውን እና የግብይት ስርዓቱን ለመቆጣጠር የሚያስችለው በከፍተኛ በጀት ያስገነባውን የመረጃ ቴክኖሎጂን ጉብኝት በማድረግ ተጠናቋል፡፡
Delegates from Nigeria GEZAWA commodity Market Ltd made work visit to Ethiopian Commodity Exchange Authority!!!
Delegates of GEZAWA Commodity Market Ltd of Nigeria have visited the experience of Ethiopian Commodity Exchange Authority for experience sharing on July 13, 2021.
Mr. Mohammed Rabiu El-Yakub, CEO of the market and Mr. Umar Farourq Mohammed, head of Compliance of the market were the delegates who visited the authority.
During their visit Engineer Olero Upiew, the Director General of ECEA made a welcome speech to the visitor and briefly explained on the establishment and the role of authority. He added also the main regulatory practices of the authority.
Additionally Mr. Urgessa Baysa, Economic analysis director of ECEA have presented the overall practices and mission of the organization.
Moreover, the questions raised from the delegates have been given answer explanation from the management members of the ECEA.
Finally, the team members visited the ICT system of the authority