Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና

Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና

Share

You shall find a prosperity party at Bole S/C on this platform. "Welcome to Bole Prosperity! Together, let's build a brighter future!"

Join us in creating a thriving community with inclusive policies and economic growth.

17/10/2025
Photos from Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና's post 16/10/2025

በቦሌ ክፍለ ከተማ በመንግሥት ፕሮጀክቶች እና መሬት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት፣ መሬት ልማትና አስተዳደር፣ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት፣ ቤቶች ልማትና አስተዳደር አንዲሁም ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤቶች በተሳተፉበት በዚህ ውይይት በተቋማቱ መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሠራር በሚጠናከርበት ሁኔታ እንዲሁም የፍርድ ቤት ማስረጃ አሰጣጥን በተመለከተ በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት የተያዙ መዝገቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ውይይቱን የመሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት እና የመንግሥት በጀት በአግባቡ መጠቀም እና ሕጋዊ ሂደቶችን በተገቢው መንገድ ማስፈጸም የልማት ሥራዎችን በብቃት ለመፈጸም ወሳኝ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም እና መሬት ነክ ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ እንደሚያስፈልጋቸው ያመለከቱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በመሆኑም የሚመለከታቸው ሴክተር ጽ/ቤቶች በጋራና በቅንጅት የሕዝብና የመንግሥትን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ተግባራቱ እንዲከናወኑ የመሥራት ኃላፊነት እንዳለባቸው አክለው አስገንዝበዋል፡፡

ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም

Photos from Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና's post 16/10/2025

ግብር ለሀገር ክብር !

ዛሬ የከተማችንን ታማኝ ግብር ከፋዮች በታላቅ ድምቀት ሸልመናል ፤ ተሸላሚ ግብር ከፋዮቻችን እንኳን ደስ አላችሁ !

ዉድ ታማኝ ግብር ከፋዮች መዲናችን ከእናንተ በምትሰበስበዉ ገቢ በከተማችን በአስደናቂ ሁኔታ የተገበርናቸዉ ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት ፣ የህዝቡን የኑሮ ጫና ያቀለሉ ስራዎች ፣ የተማሪዎች ምገባ፣ ከተማችንን ለቢዝነስ እና ለመኖር የተመቸች ንፁህ ፣ ጤናማ አካባቢ እና በአለም አቀፍ ደረጃም ተመራጭና ተወዳዳሪ እየሆነች ይገኛል ፤ ይህ ለዉጥ በርግጥ ለእናንተም ተጨማሪ አሴት፣ለቢዝነስ ማህበረሰቡ ተጨማሪ የሀብት መፍጠሪያ ምንጭ ነዉ።

በቀጣይ በግብር አሰባሰብ ዙሪያ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ይበልጡን ዲጂታላይዝ በማድረግ ፣ በማዘመን እና ተጠያቂነትን በማስፈን ክፍተቶችን እየሞላን ፣ እፀፆችን እያረምን የሁለንተናዊ ብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማን እየገነባን እንሄዳለን ።

በዛሬዉ የእዉቅና እና የሽልማት መርሃ ግብር ለእዉቅና የበቃችሁ ግብር ከፋዮቻችን ለታማኝነታችሁ ምስጋናዬ የላቀ ነዉ ፣ በተለይም የወርቅ እና የፕላቲኒየም ደረጃ ግብር ከፋዮች የዘርፉ አምባሳደሮቻችን በመሆናችሁ በከተማችን በየትኛዉም መንግስታዊ አገልግሎት እና ኩነት የቅድሚያ ቅድሚ እንድትስተናገዱ እና VIP ፕሮቶኮል እንዲሰጣችሁ መወሰናችንን ስገልፅ ሌሎችም የእናንተን አርአያነት እንደሚከተሉ በማመን ነዉ ።

ግብር ለሀገር ክብር !

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና's post 16/10/2025

በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲያችን አመራሮች የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን ከመገምገም ጎን ለጎን በለሚኩራ ክ/ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል።

መሰል ጉብኝቶች መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት እና በተቋማት መካከል ቅርርብን ለማጠናከር እንደሚያግዙ ተመላክቷል።

በጉብኝቱ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ም/ ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ፣ የለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የለሚኩራ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ለማንቾ እና ሌሎችም የከተማ ፣ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Photos from Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና's post 10/10/2025

ረቡዕ በሀላባ እና ከምባታ ዞኖች የነበረንን የሞዴል የገጠር መንደሮች ርክክብ ሥነሥርዓት በመቀጠል ዛሬ ደግሞ በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡትን አስረክበናል። እነኚህ ባለሶስት መኝታ ቤት መኖሪያዎች ለማብሰል የሚያገለግል የባዮጋዝ መሣሪያ፣ የፀኃይ ኃይል ማመንጫ፣ የዶሮ ማርቢያ፣ የተለየ የእንስሳት በረት የተሟላላቸው ሲሆን በተመጣጣኝ አነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ከማስገኘት አንፃር ለገጠሩ ማኅበረሰብ ብልጽግና ያለንን ሕልም የሚያሳይ ነው።

እንደ ማኅበረሰብ አዲስ ሀሳቦች ሲፈልቁ “አይቻልም” በሚለው የቆየ አስተሳሰብ የመፈተን ተግዳሮት ይደቀንብን ይሆናል። ይሁንና በተጨባጭ በሚታየውና በተገኘ ውጤት ላይ ወደ አለማመን እና አለመቀበል በሚመራን የሀሳብ ወጥመድ ውስጥ መውደቅ የለብንም። ዜጎች ለውጥ እንደሚቻል ሀብቶቻችንን ወደ ትክክለኛ የቅድሚያ ትኩረቶቻችን ካዋልንም ማኅበረሰብን በርግጥም ማሻገር እንደምንችል ማመን ይገባቸዋል። በአራቱ ዞኖች የተሠራው ሥራ በመላው ክልሉ መደገም ይኖርበታል። የክልሉ አመራር ይኽን ታላቅ ስራ እንደሚፈጽመውም እምነት ጥያለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

Photos from Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና's post 09/10/2025

ከሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ ምላሽ እንዲያገኙ የሕዝብ ተመራጮች እያከናወኑ ባለው እንቅስቃሴ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሪት ፋይዛ መሐመድ ገለጹ፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ የመራጭ ተመራጭ መድረክ በተካሄደበት ወቅት ምክትል አፈ ጉባኤዋ እንደገለጹት ባለፉት አራት ዓመታት እንደ ከተማ እና እንደ ቦሌ ክፍለ ከተማ በርካታ የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ያገኙ ሲሆን፣ የተገኙት ውጤቶችም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ በስኬት ጎዳና እንዲቀጥል ያስቻሉ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ “በምክር ቤታችን በርካታ የሕዝብ ጥያቄዎችን በማቅረብ እና አፈጻጸማቸውን በመከታተል ተግባራዊ ምላሽ እንዲያገኙ ለማስቻል ውጤታማ ተግባር አከናውነናል” ያሉት ወ/ሪት ፋይዛ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ከሕዝብ የሚነሱ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ነዋሪው ኅብረተሰብ በባለቤትነት መንፈስ ላደረገው የነቃ ተሳትፎ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ምክር ቤት እና አስተዳደሩ ጥያቄዎቹ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ በትጋት በመሥራትና በቅርበት በመከታተል ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር አቶሜ አበበ በኩላቸው የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ያስመዘገበው አንጸባራቂ ስኬት የሕዝብን ጥያቄ በአግባቡ በማድመጥና መፍትሄ በመስጠት ባከናወነው ተግባር የተገኘ መሆኑን ገልጸው፣ የሕዝብ ተመራጮች የወከላቸውን ሕዝብ ፍላጎት ለአስተዳደሩ በማቅረብ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከታቸውን አመልክተዋል፡፡ አሁንም ከኅብረተሰቡ የሚነሱ የልማትና የተጠቃሚነት ጥያቄዎችን ለክፍለ ከተማ አስተዳደሩ እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማቅረብ ምላሽ እንዲያገኙ የክፍለ ከተማው ተመራጮች እንደሚሠሩ ዶ/ር አቶሜ አክለው አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት የክፍለ ከተማው ኅብረተሰብ በሚመለከቱት ጉዳዮች ላይ በንቃት የመሳተፍ ልምዱ እያደገ መምጣቱን የተናገሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ የመራጭ ተመራጭ መድረክ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጥ፣ የመራጭ ተመራጭ መድረኩ ተመራጮች የወከሉትን ሕዝብ ጥያቄዎች ለሚመለከተው አካል ከማቅረብ ባለፈ አፈጻጸማቸውን ለመረዳት እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በጋራ ለመቀየስ ምቹ መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ባለፉት ዓመታት እንደከተማ እና እንደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ ለውጥ የተመዘገበባቸው ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው፣ ይህ ስኬት እንዲመጣ የአዲስ አበባ ከተማ እና የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች የሕዝብን ጥያቄ አድምጠው በአግባቡ ምላሽ መስጠታቸው ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተገኙ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ያልተፈቱ ችግሮችም ምላሽ እንዲያገኙ መድረኩ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸው፣ በክፍለ ከተማው ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን ችግሮች ለመፍታት የሕዝብ ተመራጮች እና አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡

መስከረም 29/2018

Photos from Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና's post 08/10/2025

በከተማችን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን ቀጥለናል።

ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ከተማን የመሶብ የአንድ መዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ስናስጀምር ቅርንጫፎችን በፍጥነት ለማስፋት በገባነው ቃል መሰረት፣ ዛሬ 12 የከተማ አስተዳደር እንዲሁም 3 የፌደራል ተቋማትን በመያዝ 96 የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶች የሚሰጠውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ቦሌ ቅርንጫፍን ስራ አስጀምረናል ።

የቦሌ ክፍልከተማ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ስራ ያስጀመርነው ባለ 6 ወለል ህንፃ በ4 ወራት ገንብተን፣ አስፈላጊውን ቴክኖሎጂ እና ግብአት አሟልተን እንዲሁም የሰው ሀይል አሰልጥነን ነው።

ይህንን የአዲስ መሶብ የአንድ መአከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት በአጭር ጊዜ ግንባታው እንዲጠናቀቅ እና በአስፈላጊው ቴክኖሎጂ እንዲዘምን ለደገፉን አካላት በሙሉ፣ በተለይም የኢትዮዽያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ለከተማችን አመራሮች በተገልጋዩ ህብረተሰብ ስም ከልብ አመሰግናለሁ። ተገልጋዩ ህብረተሰብም በማዕከላቱ በመገኘት አገልግሎቶቹን እንድትጠቀሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

06/10/2025

Tattaaffiin dippiloomaasii fi nagaa qabeessa Naayilii fi Galaana Diimaa irratti xiyyeeffate cimee itti fufa – Preezdaant Taayyee Atsikee Sillaasee

Pireezidaantiin FDRE Taayyee Atsikee Sillaasee haasaa baniinsaa koongirasiiwwan lamaaniif taasisaniin, yaa’iiwwan afran bara 2018. Mootummaan Itoophiyaa dhimma alaa fi qajeelfama siyaasaa idil-addunyaa akeekaniiru.

Xiyyeeffannoon jalqabaa nageenya biyyaalessaa lammiilee giddugaleessa godhate mirkaneessuu akka ta’e preezdaant Taayyeen eer Nageenya fi kabaja lammiileef dursa isaa akka ta'e ibse.

Paalistaayin seeraan alaa to’achuun lammiileen karaa seera qabeessaan socho’uu akka danda’an fi carraa hojii mirkaneessuun xiyyeeffannoo olaanaa ta’uu ibsaniiru.

Kallattiin xiyyeeffannaa biroo dippiloomaasii cimsuu fi tattaaffii nagaa Naayiliifi Galaana Diimaa irratti xiyyeeffate ta’uu pireezidaantichi eeraniiru. Mootummaan Itoophiyaa waliigaltee fi faayidaa waliigalaa Naayiliif dursa kenna jedhaniiru.

Naayil fi galaana diimaa gidduutti kan argamtu Itoophiyaan bishaan lamaan waliin waan wal qabatuuf gocha haqa hin taaneen ajjeefamuun sirrii miti jette.

Fuulduratti garuu Ityoophiyaan galaana Naayilii fi Diimaa irratti fayyadamummaa haqa qabeessa mirkaneessuuf kan hojjetu ta’uu mootummaan ibseera.

Waggoota kurnan sadii booda dhimmi balbala galaanaa marii idil-addunyaa ta’uu isaa dhiphisaniiru, waliigaltee fi hidhata fedhii misooma waliigalaa cimsuuf carraaqqii dippiloomaasii fi nagaa itti fufna jedhaniiru.

‘Dursa ollaaf’ jedhu cimsuun xiyyeeffannoo mootummaa biraa ta’uu kan himan pireezidaantichi. Bu’uura kana bu’uura godhachuun waggoota darban biyyoota ollaa waliin walii galchuuf carraaqqiin taasifamuus hubachiiseera.

Hojiiwwan misoomaa fi waljijjiiruu daldalaa bu’uuraalee diinagdee biyyoota ollaa waliin cimsan cimuu danda’u.

Xiyyeeffannoon mootummaa inni afuraffaan sarara humna idil-addunyaa keessatti madaallii eeguuf, cimsuufi babal’isuu karaa waliigalteetiin fayyadamummaa olaanaa qabaachuu pireezidaantichi himaniiru.

Mootummaan hirmaannaa fi daawwattoota idil-addunyaarratti qabdu guddisuuf, fayyadamtoota ishee guddisuuf, Ityoophiyaan dhimmoota murteessoo ta’an keessatti gahee olaanaa akka qabaattuuf xiyyeeffannoon ni hojjeta jedhaniiru.

Kanaafis pireezidaanti Taayyeen ijaarsa dhaabbataafi qajeelfamni poolisii barbaachisaa ta'e hojiirra akka oolu yaada kennaniiru.



Photos from Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና's post 06/10/2025

“መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን በማረም የብልጽግና ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ያደርጋል” --- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

“መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን በማረምና የብልጽግና ማሻሻዎችን ተግባራዊ በማደረግ ውስን ከሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎች ወደ ባለብዙ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለመቀየር በትኩረት እየሠራ መሆኑን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አያይዘውም ኢኮኖሚውን ከእዳ ጥገኝነት በማላቀቅ ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉኣላዊነት ለማሸጋገር ወቅታዊ ምዕራፍ መከፈቱን አስረድተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ለሁለቱ ምክር ቤት አባላት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ አገሮች አምባሳደሮች፣ የኃይማኖት መሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥን እንግዶች በተገኙበት ለሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

የኢኮኖሚ መሠረቶችም በአገሪቱ ያላትን አቅምና በችግር ውስጥ ዕድልን በማየት በፈጠራና በፍጥነት የተለያዩ አቅሞችን በማሰባሰብ ዘላቂ ግቦችን በማሳካት ያተኮሩ በመሆናቸው በራስ አቅም ችግሮችን በመፍታት ከአግላይ ኢኮኖሚ ወደ አሳታፊና ምቹ የኢኮኖሚ ሥርዓት በመሸጋገር የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት የአገሪቱ የኢኮኖሚ የዕድገት 8.8 በመቶ የተመዘገበ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት 9 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ መንግሥት በትኩረት የሚሠራ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም በ2016 በጀት ዓመት በግብርናው ዘርፍ 1.2 ቢሊዮን ኩንታል ምርት የተመረተ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት 1.7 ቢሊዮን ኩንታል ምርት በመመረቱ ከቀደመው ዓመት የ24.7 በመቶ ብልጫ ስላለው የግብርና ምርት የማምረት አቅም ከ59 በመቶ ወደ 65 በመቶ ማደጉን አመላክተዋል፡፡

የወርቅ ምርትም በ2016 በጀት ዓመት ከነበረበት 3.9 ቶን ወደ 38.87 ቶን ማደጉን፣ የሲሚንቶ ምርት በ2016 በጀት ዓመት 7.5 ሚሊዮን ቶን በ2017 በጀት ዓመት ደግሞ ወደ 9.1 ሚሊዮን ቶን ከፍ ማለቱን ፕሬዚዳንቱ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች በመሆኗ በ2017 በጀት ዓመት ከ150 ኮንፍረንሶችን ማዘጋጀቷ በዓለም አቀፍ እና በአህጉር ደረጃ ያላት ተሰሚነት እየጨመረ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

ኢትዮጵያ የነበረባትን ጫና ተቋቁማ ታላቁን የሕዳሴ ግድብና የመጀመሪያውን የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት አጠናቃ ማስመረቋ፣ ሁለተኛውን የተፈጥሮ ጋዝ ለማስጀመር እና የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ መጣሏ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ራሷን ለመቻል ጥረት እያደገች ለመሆኑ አመላካች እንደሆነ ጨምረው አብራርተዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 8.3 ሚሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ ስላስመዘገበች ከአለፈው በጀት ዓመት የ116 በመቶ ብልጫ እንዳለው ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው አመላክተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በተሠራው ሥራም በ2016 በጀት ዓመት 19.9 በመቶ ከነበረበት በ2017 ተመሳሳይ ወር ላይ 13.9 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቁመው፣ በ2018 በጀት ዓመት ወደ ነጠላ አኃዝ ለማውረድ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡



06/10/2025

ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግሥት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ከፍ ባለ ትጋት ፈርጀ ብዙ እና አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።

እነዚህ ውጤቶችም የሀገራችንን የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚና ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና በማሻሻል የታሪክ እጥፋት ምንጭ፣ የኩስመና ታሪክ ማብቂያ እና የኢትዮጵያ ማንሰራራት መንስኤ ሆነዋል።

በቀጣይ ዓመታትም ይህንን ድል በማስፋት የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወደ ማይቀለበስበት ምዕራፍ እንዲሸጋገርና ኢትዮጵያ በአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን መንግሥት አበክሮ ይሰራል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ


Photos from Prosperity Party Bole Branch- ብልፅግና's post 06/10/2025

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ - ሥርዓት።



Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Bole Gabon Street
Addis Ababa