01/08/2016
የስናን ወረዳ ብአዴን ፅ/ቤት ከ22-23/11/2008ዓም ከወረዳ አመራሩ ፣ከቀበሌ ከመጡ የካቢኔ አባላት፣የግብርና ፣የጤና ተጠሪዎች፣ስራስኪያጆች፣የወጣትና የሴት ሊግ መሪዎች፣የወጣትና የሴት ማህበር አመራሮች ሞዴል የህዋስ መሪዎች በአጠቃላይ ከ255 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት የ2008 ዓም የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ኦረንቴሽን በመስጠት የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው 5 ቀበሌዎችና 17 ምርጥ የህዋስ መሪዎች የማበራታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
17/07/2016
የስናን ወረዳ አስተዳዳር ዛሬ በ10/11/2008 ዓም ከገዳማዊት ቀበሌ የብአዴንአባላት ጋር በአረንጎዴ ልማት ሥራዎች በተለይ ልቅ ግጦሽን ከማስቆም አኳያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።በመድረኩ ከ280 በላይ አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
06/07/2016
Andm members conference in sinan woreda (29/10/08) at all rural kebeles.
08/06/2016
በምስራቅ ጎጃም ዞን የስናን ወረዳ የመሬት አስተዳደር ጉባኤ የወል መሬት ወረራ ማስመለስና መከላከል፡የመሬት ማስተቸት፡ለአረንጓዴ ልማት ለተደራጁ ወጣቶች መሬት በማመቻቸት፡በአገልግሎት አሠጣጥና የጠራ መረጃ አያያዝ ዙሪያ ትኩረት በመሥጠት ጉባኤዉ ችግሮችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማመላከት መክሯል።
08/06/2016
በምስራቅ ጎጃም ዞን የስናን ወረዳ የመሬት አስተዳደር ጉባኤ ሰኔ1ቀን 2008 ሲካሔድ የቀበሌና የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን በጉባኤውም የወል መሬት ወረራ አመላለስ ሥራችን፡የመሬት ማስተቸት ሥራችን፡የመረጃ አያያዝ ጥራት፡የአገልግሎት አሠጣጥ ችግሮችን የትኩረት ነጥቦች በማድረግ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
05/06/2016
በስናን ወረዳ አበዛዥ ወይበይኝ ቀበሌ የ25ኛ ዓመት የግንቦት 20 የብር ኢዮብልዮ በዓል በሠላማዊ ሠልፍና በፓናል ውይይት ሲከበር ከፊል ገፅታ
04/06/2016
በስናን ወረዳ ብአዴን ፅ/ቤት የ25ኛ የግንቦት 20 የብርኢዮቢልዮ በዓል ከ14/09/2008ጀምሮ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች/ስፖርታዊ ውድድሮች፣በቀበሌ በሰላማዊ ሰልፎች፣በከተማ በፅዳትና የልማት ሥራዎች ወዘተ ሲከበር የቆየ ሲሆን በ26/09/2008 ደግሞ አጠቃላይ የከተማ መንግስት ሠራተኛና ልዩ ልዩ ተወካይ የህ/ብ ክፍሎች በተገኙበት በወረዳው እየተገነባ ያለውን የቴ/ሙ/ኮሌጅ እንዲሁም በረ/ገበያ ጤና ጣብያ ተገብቶ የተጠናቀቀውን የእናቶች ቀዶ ጥገና ክፍል ከተጎበኘ ብኋላ የማሽቆልቆል ምዕራፍ ተዘግቶ የዕድገት ምዕራፍ የተከፈተበት የሩብ ምዕተ ዓመት የትግልና የድል ጉዞ በሚል ርዕስና በብዝሃነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በማካሄድ በዓሉ በድምቀት ተከበረ።
25/05/2016
በስናን ወረዳ ብአዴን ፅ/ቤት የከተማ ምሁራን አባላት ኮንፈረንስ ከ15-16/09/2008 ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአዲስ ራዕይ መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4 የተካሄደ ሲሆን በኮንፈረንሱ የተሃድሶ መስመራችን፣የፀረ_ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉና ፈተናዎቹ፣ስለጤና መድህን እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ የፖለቲካና ድርጅት ሥራዎች ጋር ተያይዞ ሰፊ ውይይት ተካሂዶል።በውይይቱ የ25ኛ ዓመት የግንቦት 20 የብር ኢዩብልዮ በዓልም በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮል።
04/05/2016
በስናን ወረዳ ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት የልማት እና የሠላም አቅሞች ናቸው በሚል መሪ ቃል ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት በክልሉ በተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ውጤቶች እና በሂደቱ በገጠሙ ተግዳሮቶች ላይ የተስተካከለ ግንዛቤ በመፍጠር ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት በተስተካከለ ግንዛቤ ውስጥ ሆነው ባላቸው ዕውቀት እና በተጨማሪ በአጫጭር ስልጠናዎች በሚያገኙት ክህሎት ተጠቅመው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን በሚጠቅሙበት የልማት ሥራዎች እንዲሳተፉ እናለወረዳው ዕድገት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ በሚችሉበት ሁኔታ በ20/08/08 ወደ119 ተሳታፊዎች በተገኙበት የምክክር መድረክ ተካሄደ።
28/04/2016
በስናን ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የመጀመሪያው ዙር የፖልዮ ክትባት/0_5ዓመት/ዘመቻ ከ14-17/08/08።
23/04/2016
በስናን ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት በዚላን አምስትያ ቀበሌ በSLM ኘሮጀክት የተከናወኑ የግብርና የተፋሰስ ሥራዎች በተለይም በደጋ ፍራፍሬ በአፕል ልማት ሥራ የተሠሩ ሥራዎችንየመስክ ጉብኝት በ15/08/2008 ተካሄደ።በጉብኝቱ ሁሉንም የግብርና ኤክስቴንሽን ተግባራትን አቀናጅተው በመፈፀም ውጤታማና ተጠቃሚ የሆኑ ሞዴል አርሶ አደሮች ተጎብኝተዋል።
16/04/2016
በስናን ወረዳ በስናን ማረያም ቀበሌ አ/አደሩ ከሰብል ልማት የተግባር ስልጠና ጎንለጎን የእንስሳት ጤና ኬላ እየገነባ ።