05/06/2026
ለኮሪደር ልማት አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ የሰረቀ ግለሰብ በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተያዘ።
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በረከት አረጋ የተባለ ግለሰብ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ጉስቋም ቅድስት ማርያም አካባቢ ከምሽቱ 4:00 ሠዓት ላይ ነው።
ተጠርጣሪው በሠዓቱ ለኮሪደር ልማት ተዘርግቶ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብል በመጋዝ ቆርጦ በመውሰድ በውሃ ፍሳሽ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ገብቶ ለመሰወር ቢሞክርም በወቅቱ ስራ የነበሩ የፖሊስ አባላት ተከትለው በመግባት ሁለት ሰአት በፈጀ ፍለጋ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጦር ስር በማዋል አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ገልጿል ።
ወንጀል ፈፃሚው በወቅቱ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር እንዲውል ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ትብብር ማድረጉ የሚያስመሰግን ተግባር ነው ያለው ፖሊስ ህዝብ ሲተባበር ወንጀል ፈጻሚዎችን በቀላሉ ለህግ ማቅረብ እንደሚቻልም አመላክቷል ብሏል።
የክፍለ ከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያም ከአስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የፍሳሽ መውረጃ ትቦ ውስጥ ገብተው ተጠርጣሪውን ለያዙት አባላት ማበረታቻና ሽልማት እንደሚሰጥም አሳውቋል።
*
ዘገባ፦ ም/ሳጅን ሳምሶን ሠለሞን
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
04/06/2026
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያን የቴክኖሎጂ አቅም ለማጎልበት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ።
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ሲደርሱ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ የዋና ጠቅላይ መምሪያው አዛዥ፣ የወንጀል መከላከል ም/ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ፣ የወንጀል ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።
7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በስኬት አጠናቀን ወደ መደበኛው ስራ በገባንበት ማግስት ዋና ዳይሬክተሩ በተቋማችን ለጉብኝት መምጣታቸው እንዳስደሰታቸው የገለጹት ሌተናል ጀነራል አስራት ዋና ጠቅላይ መምሪያውን ለማዘመንና አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከልዩ ልዩ ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት አዛዡ ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንትለጀንስ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የኢንስቲትዩቱ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በሀገራችን ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም በርካታ ተቋማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረው የመዲናችን ፖሊስ ቴክኖሎጂውን ተጠቅሞ ሠላምንና ደህንነትን ለማረጋገጥ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ተቋማቸው ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
የፖሊስ ስራን በዲጂታል ስርዓት የታቀፈ ለማድረግ በፎረንሲክ ሳይንስ፣ በደህንነት ካሜራ መረጃ መቀበያ መተግበሪያዎችን እንዲሁም በድሮን ካሜራ ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፍ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
*
ዘገባ፦ ዋ/ሳጅን አምሳሉ መብራቴ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
03/06/2026
ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እና ቆጠራው በስኬት እና በሠላም ተጠናቋል፡፡ ህዝብ ፣ ምርጫ አስፈፃሚዎች እና የፀጥታ አካላት የስኬቱ ባለቤት ናቸው፡፡ ስኬታችንን ማፅናት ይጠበቅብናል ሲሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የፀጥታ አካሉ ወገንተኝነቱ ለህገ-መንግስቱና ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገው ለሚወጡ ህጎች ነው፡፡ በህገ-መንግስታችን የስልጣን ባለቤት ህዝብ እንደሆነ እና የመንግስት ስልጣን መያዝ የሚቻለው በምርጫ ብቻ መሆኑ ተደንግጓል፡፡
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ህዝብ በነቂስ በመውጣት መሪዎቹን ሲመርጥ ውሎ አምሽቷል፡፡ ምርጫው ህግን መሰረት በማድረግ እንዲፈጸም መላው የፀጥታ አካላት ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ርብርብ በማድረጋቸው እና የህዝቡ ድጋፍ ታክሎበት ቅድመ ምርጫ እና የምርጫ እለትን በስኬት ማጠናቀቅ ችለናል፡፡ ድህረ ምርጫውንም በሠላም እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ምርጫው በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት እንዲከናወን ነዋሪው ያደረገው የነቃ ተሳትፎ በተለይ በድምፅ መስጫው እለት የነበረው ታጋሽነት የሚደነቅ እና ምስጋና የሚቸረው ተግባር ነው፡፡
መላው የፀጥታ አካላት አመራሮችና አባላት ደከመን ሰለቸን ሳትሉ የተጣለባችሁን ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት በብቃት በመወጣታችሁ ኮርተናል፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሁሌም ለስራችን ስኬታማነት ከጎናችን በመቆም እያደረጋችሁት ላለው ቀና ትብብር በዋና ጠቅላይ መምሪያው ስም ምስጋናዬን ሳቀርብ ክብር ይሰማኛል፡፡
ምርጫውን ለማደናቀፍ ፀረ-ሠላም ኃይሎች ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ ያልሸረቡት ሴራ፣ ያልወጡት ዳገት፣ ያልወረዱቱ ቁልቁለት የለም፡፡ ሴራቸው በህዝብና በፀጥታ የጋራ ጥምረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያም መርጣለች ከተማችን አዲስ አበባም መርጣለች፡፡
የመንግስት ስልጣን መያዝ የሚቻለው በምርጫ መሆኑን ህዝቡ ድምፁን በመስጠት መልዕክቱ አስተላልፏል፡፡ የስልጣን ባለቤት የሆነውን የህዝብ ድምፅ ማክበር ከሁሉም ይጠበቃል፡፡
የምርጫው ሦስተኛው ምዕራፍ ቀጥሏል፤ ውጤት ተገልፆ መንግስት እስኪመሰረት ያለው ሂደት በተመሳሳይ ስኬታማ እንዲሆን የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እና የፀጥታ ተቋማት ወትሮ ዝግጁነት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
ሀገርን የማፅናት ተግባር የጋራ ርብርብን ይጠይቃል፤ በሀገራዊ ምርጫ የተረጋገጠው ይኸው ነው፡፡ የጠላት ሴራን በማክሸፍ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲሰካ ተልኳችሁን በብቃት የተወጣችሁ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሀገር መከላከያ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር፣ የከተማችን ደንብ ማስከበር፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር፣ የሠላም ሰራዊት አመራሮች እና አባላት የምርጫውን ደህንነት የማረጋገጥ ዓላማችሁ ተሳክቷል፡፡ ሌት ተቀን የድከማችሁበት እንዲሁም የለፋችሁበት ተግባር በስኬት ተጠናቋል፡፡ ለፈፀማችሁት አኩሪ ተግባር በምርጫ ኮማንድ ፖስቱ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
02/06/2026
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የድምፅ መስጫ ሂደቱ እስከ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ሲከናወን ቆይቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ግንቦት 24 ቀንም ሆነ ሌሊት ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙ ተገልጿል።
ድምጽ የመስጠት ስርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ መራጩ ህዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ መላው የጸጥታ አካላት ኮማንድ ፖስቱ ምስጋናውን አቅርቧል።
ድምጽ ቆጠራው ቀጥሏል።
ድህረ ምርጫ ያለው ሂደት በተመሳሳይ በስኬት እንዲከናወን ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት ጥሪውን አቅርቧል።
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
01/06/2026
በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተጣለበትን ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ ስለመሆኑ ማምሻውን ገመገመ።
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ እና በአዲስ አበባ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ሊዲያ ግርማ በተመራው መድረክ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዦች ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድና ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ እና የየተቋማቱ የጸጥታ አመራሮች በተገኙበት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የጸጥታ ሁኔታ ማምሻውን ተገመገመ።
የምርጫ ኮማንድ ፖስቱ ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተጣለበትን ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ ስለመሆኑ እንዲሁም በምርጫው ዋዜማና በምርጫው ዕለት የተከናወኑ ተግባራትን በጥልቀት ገምግሟል።
ግምገማው የክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ኃላፊዎች ከነ ማኔጅመንታቸው በዙም በተደረገ ስብሰባ ጭምር የተደረገ ሲሆን አጠቃላይ በመዲናዋ እየተከናወነ ያለው የምርጫ ሂደት ሠላማዊ እንደሆነም ተገልጿል።
ጥምር የጸጥታ ኃይሉ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስም የጸጥታና ደህንነት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
*
ዘገባ፡- ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
30/05/2026
በምርጫና ድህረ ምርጫ ቀናት በሚከናወኑ የፀጥታ ማስከበር ተግባራት ምርጫው ሠላማዊ እንዲሆን አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ሠላም አዳራሽ በቅድመ ምርጫ የተከናወኑ ተግባራትን ለመገምገም በተዘጋጀው መድረክ የአዲስ አበባ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ፣ የከተማው ሠላምና ጸጥታ ቢሮ አስተዳደር ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዦች ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እና ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ፣ የአስራ አንዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ እና የወረዳ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የጸጥታ አካላት አስቀድመው የጋራ እቅድ በማውጣት ወደ ተግባር በመግባታቸው ቅድመ ምርጫው በጥሩ ሁኔታ ማከናወን እንደተቻለ በውይይቱ ተነስቷል።
የምርጫን ደህንነት የማረጋገጥ ተግባር ልዩ ጥንቃቄን የሚሻ ተግባር መሆኑን ሌ/ጀነራል አስራት በውይይቱ ላይ ገልፀው ቀሪ ተግባራት ካሉ ማጠናቀቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በምርጫው ላይ አሉታዊ ጫና ለማሳደር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች እንዳሉ በመረዳት በምርጫ ዕለት እና ድህረ ምርጫም በስኬት እንዲጠናቀቁ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የዋናው ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ አስታውቀዋል።
የጸጥታ ስራችን ለህብረተሰቡ ደህንነትን ያረጋገጠ ለጸረ-ሠላም ኃይሎች ጫናን የሚያሳድር መሆን እንዳለበት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ባደረጉት ንግግር ገልጸው በተለይ ፀጉረ-ልውጦችን ለመቆጣጠረ በሸገር ከተማ ስር ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ ቅድመ ምርጫ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ተገምግሟል።
ምርጫው ያለ ምንም የፀጥታ እንከን እንዲከናወን ህብረተሰቡ ማንኛውም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪ ተላልፏል።
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
30/05/2026
አዲስ አበባ የሚገኘው የጣልያን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚ/ር ሉካ ካርፔንትዬሪ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በመገኘት በጋራ ስለሚከናወኑ ተግባራት መክረዋል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ የጣልያንን ምክትል አምባሳደር ሚ/ር ሉካ ካርፔንትዬሪን በቢሮአቸው ተቀብለው ትውውቅ በማድረግ በቀጣይ በጋራ ስለሚከናወኑ ተግባራትም መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያና ጣልያን ረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት እንዳላቸው ያወሱት ምክትል አምባሳደሩ የከተማዋ ፖሊስ እያከናወናቸው ያለውን የፀጥታና የህግ ማስከበር ስራዎች አድንቀዋል፡፡ ኤምባሲያቸው ከዚህ ቀደም ለትራፊክ ሞተረኞች የተለያዩ ስልጠናዎችን ሰጥቶ እንደነበር ያስታወሱት ሚ/ር ሉካ በቀጣይም ከተቋሙ በሚቀርብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ማንኛውንም ዓይነት ትብብር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ በበኩላቸው ከተማዋ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች መገኛ መሆኗን በማንሳት የመዲናዋን ሠላምና ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ ከተለያዩ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር ዋና ጠቅላይ መምሪያው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ምክትል አምባሳደሩ በዋና ጠቅላይ መምሪያው በመገኘታቸው አመስግነው በቀጣይም ከኤምባሲው ጋር በሚያግባቡ ጉዳዮች ላይ በተለይም በጸጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩም ሌ/ጀነራል አስራት ገልፀዋል፡፡
*
ዘገባ፡- ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
29/05/2026
ተቀጥራ ከምሰራበት መኖሪያ ቤት ከ1ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ ንብረቶችን የሰረቀች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተከሳሽ ዓለም ሲሳይ የተባለች የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በልዩ ስሙ አትሌቶች መንደር ነው።
በግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ያለ ምንም ተያዥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የአሰሪዎቿን እንቅስቃሴ በሚገባ ስታጠና የቆየችው ተጠርጣሪዋ በተቀጠረች በ9ኛ ቀኗ የተለያዩ አልባሳት እና መዋቢያ ጌጣጌጦችን፣ የአሜሪካን ዶላር 500፣ የቻይና ሀገር ዩዋን 400፣ የህንድ ሩፒ 600 የCCtv ካሜራ ዳይመንድ የጣት ቀለበት በአጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው አንድ ሚሊየን አራት መቶ ሃያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ብር (1,423,192.00) የሚያወጡ የተለያዩ ንብረቶችን ሰርቃ ከአካባቢው መሰወሯን የግል ተበዳይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ጎሮ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው አመልክተዋል፡፡
የጎሮ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ ባደረገው ክትትል ተከሳሿን ከነሙሉ ኤግዚቢቱ ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጥቷት የተወሰኑ ኤግዚቢቶችን በመሸሸግ የተባበራትን ተጠርጣሪ ከሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3B-95611 አ/አ ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን ጭምር የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ለክፍሉ አቃቤ ህግ በማቅረብ ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል፡፡
ህብረተሰቡ ማንኛውንም ዓይነት ቅጥር ሲፈፅም ህጋዊነትን በተከተለ መልኩ ቢሆን የተሻለ መሆኑን ያስገነዘበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላትም ከወንጀል ፈፃሚዎች ጋር በጥቅም ተሳስረው የወንጀል ተጠያቂ ላለመሆን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
*
ዘገባ ፦ ዋና ሣጅን አዳነ ደስታ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
29/05/2026
የመኪና እቃ ስርቆት ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ።
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተከሳሽ አቡበከር ሰይፈ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አካባቢ ነው።
የግል ተበዳይ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ -2C-77538 አ/አ የሆነ BYD የኤሌክትሪክ መኪና በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ አቁመው በሄዱበት አጋጣሚ ተከሳሽ 130 ሺህ ብር የሚገመት የቻርጅ ማድረጊያ ክዳንና 41 ሺህ ብር የሚያወጣ የግራ ስፖኪዮ በአጠቃላይ 171 ሺህ ብር ግምት ያለው ንብረት ከተሽከርካሪው ላይ ገንጥሎ ለማምለጥ ሲሞክር ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላትና በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፈንጅ መያዙን በክፍለ ከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ የአለም ባንክ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል።
በተከሳሽ አቡበከር ላይ አስፈላጊውን ምርመራ ሲያጣራ የቆየው የአለም ባንክ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መዝገቡን ለዐ/ህግ በማቅረብ ክስ እንዲመሰረትበትም አድርጓል፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ የወንጀል ችሎት ተጣርቶ የቀረበለትን መዝገብ በማጤን ተከሳሽ ጥፋተኝነቱን በሰው ማስረጃዎች ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሹን ያስተምራል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል ሲል በ4 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ እንዳስተላለፈበት ገልጿል።
የተሽከርካሪ ባለ ንብረቶች መኪና አቁመው በሚሄዱበት ወቅት ለወንጀል ፈፃሚዎች ምቹ ሁኔታን በማይፈጥር መልኩና በቂ ጥበቃ ባለበት ቦታ አቁመው መሄድ እንዳለባቸው ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ከተፈፀመም በአፋጣኝ ለአቅራቢያ ፖሊስ ጣቢያ በማመልከት ወንጀል ፈፃሚዎች ተይዘው በህግ አግባብ እንዲቀጡ ማድረግ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል።
*
ዘገባ ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዘላለም አበበ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
29/05/2026
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ አዲስ የተሾሙትን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፎች አስተባባሪና ልዑካቸውን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፎች አስተባባሪ ተደርገው የተሾሙትን ናይጄሪያዊውን ኦዞኒያ ኦጂሎንና ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
አስተባባሪው በትውውቃቸው ወቅት እንዳነሱት የአዲስ አበባ ከተማ ዕድገት ከዕለት ወደ ዕለት የመላው አፍሪካውያንን ቀልብ እየሳበ መሆኑን ገልጸው በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከዋና ጠቅላይ መምሪያው ጋር አንድ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረው ኢትዮጵያ በቀጣይ በ2027 ለምታካሂደው 32ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እያደረገች ያለችውን ቅድመ ዝግጅት አደንቃለሁ ብለዋል፡፡
በአሁን ወቅት እየተሰሩ ያሉ ተቋማዊ አዳዲስ ተግባራት መጀመራቸውን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀኔራል አስራት ደኔሮ ከተማዋን የሚመጥን የወንጀል መከላከልና የፀጥታ ማስጠበቅ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2027 32ኛውን የተ.መ.ድ. /UN/ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንድታካሂድ መመረጧ የሚታወስ ነው።
*
ዘገባ፡- ም/ሳጅን መልካሙ ዜና
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”