03/06/2026
አካዳሚው በሁሉም ስፖርት አይነቶች በሀገሪቱ ስፖርት ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የቻሉ በርካታ ተተኪ ስፖርተኞችን እያፈራ ነው፦
አቶ አምበሳው እንየው የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር
ግንቦት 26/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ የሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ከቡሩንዲ ጋር አድርጎ በድምር ውጤት 4ለ2 በማሸነፍ ከዛምቢያ ጋር ለመጨረሻ የደርሶመልስ ጨዋታ የሚያደርግ ሲሆን ከብሄራዊ ቡድኑ አባላት መካከል ከአካዳሚው ሁለቱ ካምፓሶች 10 ተጨዋችችና አንድ የአካል ብቃት አሰልጣኝ የሚገኙበት ሲሆን በድል ለተመለሱት የቡድኑ አባላት አካዳሚው ዛሬ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም በቅጥር ግቢው ደማቅ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የዕውቅና ፕሮግራም አከናውኗል።
ብሄራዊ ቡድኑ በማጣሪያ አራት ጨዋታዎችን አድርጎ 12 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን ከተቆጠሩት ጎሎች ውስጥ 10 ጎሎችን የአካዳሚው ሰልጣኞች አስቆጥረዋል።
በመድረኩ የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ አምበሳው እንየው ባስተላለፉት መልዕክት አካዳሚው በሁሉም ስፖርት አይነቶች በሀገሪቱ ስፖርት ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የቻሉ በርካታ ተተኪ ስፖርተኞችን እያፈራ መሆኑን በመግለፅ በዚህ ብሄራዊ ቡድን ከአካዳሚው ሁለቱም ካምፓሶች ተመርጣችው እየተጫወታችሁ ያላችሁ ሰልጣኞች ሀገርን በትልቅ ደረጃ ሊያስጠራ የሚችል ታሪክ ለመስራት በመመረጣችሁ በጣም እድለኞች ናችሁ። በቀጣይም የሚቀራችሁን የደርሶመል ጨዋታ በማሸነፍ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን ለአለም ዋንጫ እንደምታሳልፉ አካዳሚው ሙሉ እምነት አለው ብለዋል አያይዘውም ሰልጣኞቹን ከመላው ሀገሪቱ መልምላችሁ እና አሰልጥናችሁ ለዚህ ያበቃችሁ አሰልጣኞችና መላው ሰራተኞች ፍሬያችሁን ስላያችሁ ልትኮሩ እና ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ አሰልጣኞች እስካሁን በተገኘው ውጤት የተሰማቸውን ደስታ እና መልካም ምኞታቸውን የተናገሩ ሲሆን ሰልጣኞቹም በበኩላቸው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና ዕውቅና ፕርግራም አካዳሚውን በማመስገን በቀጣይ ጠንክረን በመስራት ሀገርን እና አካዳሚውን የሚያኮራ ስራ እንሰራለን ብለዋል።
በመጨረሻም አካዳሚው በብሄራዊ ቡድኑ ለተሳተፉ 10 ሰልጣኞችና አንድ የአካል ብቃት አሰልጣኝ ለእያንዳዳቸው ግምታዊ ዋጋው 25000(ሃያ አምስት ሺ ብር) የሚያወጣ የስፖርት ትጥቅ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።
በፕሮግራሙ የአካዳሚው ከፍተኛ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣የማኔጅመንት አባላት፣ ሰልጣኞችና ሰራተኞች ታድመዋል።
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064708597717&mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም https://t.me/+0K6_bE7YFzU5YmY0
ድህረ ገፅ http://www.esacademy.gov.et/
ቲክቶክ www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy" rel="ugc" target="_blank">https://www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy
"ወርቃማ የትውልድ ቅብብሎሽን እናረጋግጣለን"
”We Ensure the Golden Generational Continuity”
02/06/2026
የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ሲጠናቀቅ የአካዳሚው 3 ነባር ሰልጣኞች በተለያየ ዘርፍ ኮኮብ በመሆን አጠናቀቁ
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከታህሳስ 4/9/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን 3 የአካዳሚው ነባር ሰልጣኞች በተለያየ ዘርፍ ኮኮብ ተጨዋች በመሆን አጠናቀቁ።
በወንዶች ወላይታ ዲቻ ሻምፒዮን የሆነ ሲሆን ፌዴሬሽኑ በመዝጊያ ስነስርአቱ ላይ ባዘጋጀው ሽልማት ላይ የአካዳሚውን የአራት አመት ስልጠና በማጠናቀቅ ክለብ ከተቀላቀሉት ውስጥ በወጣት ዘርፍ የመቻሉ ቃልአብ እንዳለ እና የሙገሩ ሱልጣን ሀጂከድር በኮከብ ተጨዋችነት የተመረጡ ሲሆን በአዋቂዎች ምድብ ደግሞ የመቻሉ ሉል ሮድ ኮከብ ብሎከር በመባል ተመርጧል።
አካዳሚው በቮሊቦል ስፖርት ከመላው ሀገሪቱ ታዳጊዎችን መልምሎ በማሰልጠን እና ለክለቦች በማሸጋገር በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064708597717&mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም https://t.me/+0K6_bE7YFzU5YmY0
ድህረ ገፅ http://www.esacademy.gov.et/
ቲክቶክ www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy" rel="ugc" target="_blank">https://www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy
"ወርቃማ የትውልድ ቅብብሎሽን እናረጋግጣለን"
”We Ensure the Golden Generational Continuity”
30/05/2026
#10 የአካዳሚውን ሰልጣኞች የያዘው የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የደርሶመልስ ጨዋታውን አሸነፈ
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ የሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከቡሩንዲ ጋር አድርጎ በድምር ውጤት 4ለ2 በማሸነፍ ወደቀጣዮ ዙር ማለፍ የቻለ ሲሆን ከቡድን አባላቱ ውስጥ ከአካዳሚው 10 ተጨዋችችና አንድ የአካል ብቃት አሰልጣኝ ይገኙበታል።
ብሄራዊ ቡድኑ በደርሶ መልስ ያስቆጠራቸውን አራቱንም ጎሎች የአካዳሚው የሁለቱ ካምፓስ የአራተኛ አመት ሰልጣኞች ምኅረት አየለ(1 ጎል) እና ሊዲያ ኢያሱ (3 ጎሎችን) አስቆጥረዋል።
በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ካሉ 18 ተጫዋቾች ውስጥ በአካዳሚው በመሰልጠን ላይ ካሉና የአራት አመት ስልጠና አጠናቀው ክለብ ከተቀላቀሉት ውስጥ መድሀኒት አለሙ፣ ማንጠግቦሽ አድማሱ፣ ሊዲያ እያሱ፣ ምህረት አየለ፣ያንጓ ሜኔ፣ መቲ ረታ፣አጅሉ ኡዶንግ፣ሊያን ዳንኤል፣ ኮኮቤ ደጀኔ እና ሊዲያ ሰለሞን በድምሩ 10 ተጨዋቾች እና የአካል ብቃት አሰልጣኙ አስናቀ ገደፍ ይገኙበታል።
ለአንድ ብሄራዊ ቡድን 10 ተተኪ ተጫዋቾችን አካዳሚው ማስመረጡ የተተኪዎች መፍለቂያነቱ ማሳያ ነው።
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064708597717&mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም https://t.me/+0K6_bE7YFzU5YmY0
ድህረ ገፅ http://www.esacademy.gov.et/
ቲክቶክ www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy" rel="ugc" target="_blank">https://www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy
"ወርቃማ የትውልድ ቅብብሎሽን እናረጋግጣለን"
”We Ensure the Golden Generational Continuity”
27/05/2026
አካዳሚው በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ ከነማን 3ለ1 አሸነፈ
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ምድብ "ለ" ሀዋሳ ላይ የተደለደለው የአካዳሚው ከ20 አመት በታች የወንዶች እግርኳስ ሰልጣኞች ቡድን የሊጉን 2ኛ ዙር የ21ኛ ሳምንት ጨዋታውን ትናንት ግንቦት 18/ 2018 ዓ.ም 8:00 ሰአት ላይ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር አድርጎ 3ለ1 በማሸነፍ በዙሩ የመጀመሪያውን ድል አስመዝግቧል።
የአካዳሚውን የማሸነፊያ ጎሎች ታረቀኝ ቀጀላ ( 23' )፣ ነብዩ ባህረዲን (45+1') እና ዳዊት ጋጋ (47' ) አስቆጥረዋል።
በሊጉ መደበኛ ስልጠናቸውን ለመገምገምና ሰልጣኞች በክለቦች እንዲታዩ ዕድሉን ለመፍጠር እየተጫወተ የሚገኘው አካዳሚው በሊጉ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል።
አካዳሚው በቀጣይ የሊጉን የ22ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታውን በመጪው ቅዳሜ ግንቦት 22/ 2018 ዓ.ም ከፋሲል ከነማ ጋር 8:00 ሰአት ላይ በሀዋሳ ሎጊታ አርቴፊሻል ሜዳ እንደሚያደርግ ፌዴሬሽኑ ያወጣው መርሃግብር ያመለክታል።
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064708597717&mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም https://t.me/+0K6_bE7YFzU5YmY0
ድህረ ገፅ http://www.esacademy.gov.et/
ቲክቶክ www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy" rel="ugc" target="_blank">https://www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy
"ወርቃማ የትውልድ ቅብብሎሽን እናረጋግጣለን"
”We Ensure the Golden Generational Continuity”
26/05/2026
አካዳሚው የተሳተፈበት 19ኛው የፌደራል መስሪያ ቤቶች የስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል ተጠናቀቀ
ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከየካቲት 26/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የ2018 ዓ.ም 19ኛው የፌደራል መስሪያ ቤቶች የስፖርት ለሁሉም ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን አካዳሚው በአምስት ስፖርት አይነቶች በሁለቱም ፆታ ሰራተኞቹን በማሳተፍ የዋንጫ እና የሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን የፌስቲቫሉ ድምቀት መሆን ችሏል።
በውድድሩ አካዳሚው በእግርኳስ(በወንዶች)፣በቼስ (በወንዶች)፣ በቮሊቦል፣ በዳርት፣ እና ጠረጴዛ ቴኒስ ሰፖርት አይነቶች በሁለቱም ፆታ በንቃት በመሳተፍ በአንደኛ ዲቪዚዮን የወንዶች እግርኳስ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን በሴቶች ቮሊቦል የነሀስ ሜዳሊያ፣ በዳርት ድብልቅ ነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆን ችሏል።
ዛሬ በመዝጊያ ስነስርአቱ ላይ በተደረገ አዝናኝ የሴቶች ጆንያ ውድድር ላይ አካዳሚው የብርና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
በፌስቲቫሉ አካዳሚው ከአዲስ አበባ እና አሰላ ካምፓስ ሰራተኞቹ በሁለቱም ፆታ 71 ሰራተኞችን አሳትፏል።
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064708597717&mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም https://t.me/+0K6_bE7YFzU5YmY0
ድህረ ገፅ http://www.esacademy.gov.et/
ቲክቶክ www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy" rel="ugc" target="_blank">https://www.tiktokcom@ethiopiansportsacademy
"ወርቃማ የትውልድ ቅብብሎሽን እናረጋግጣለን"
”We Ensure the Golden Generational Continuity”
24/05/2026
አካዳሚው እና ሜዳሊያ በማሸነፍ ሻምፒዮናን አጠናቀቀ
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከግንቦት 12-15/2018 ዓ.ም በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሲካሄያድ የቆየው የ3ኛው ዙር የኢትዮጵያ ቦክስ ክለቦች ሻምፒዮና ትናንት ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን አካዳሚው በሁለቱም ፆታ በመሳተፍ እና ሜዳሊያ በማሸነፍ ሻምፒዮናን አጠናቀቀ።
በሻምፒዮናው አካዳሚው 6 ወንድ እና 4 ሴት በድምሩ 10 ቦክስ ሰልጣኞችን በማሳተፍ በእምነት ዮሐንስ በ50 ኪ.ግ ብር ሜዳልያ ፣ እስከዳር አባተ በ48 ኪ.ግ የብር ሜዳልያ፣ታሪኩ መለስ በ51 ኪ.ግ ብር እና ረሂማ ቦንሳ በ50ኪ.ግ ነሀስ ሜዳሊያ በማሸነፍ ሻምፒዮናውን አጠናቀዋል።
በሻምፒዮናው አካዳሚውን ጨምሮ 11 ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ለብሄራዊ ቡድን ምርጫ እና በኢንተርናሽናል ውድድሮች የመሳተፍ ዕድል እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።