አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .

አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .

Share

ይጎብኙን አብረን ለለውጥ እንስራ የመረጃ ምንጮች ነን ።

Photos from አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .'s post 02/06/2026

‎ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ስራ አስጀምረናል።

‎ይህ ትልቅ ተነሳሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል።

‎በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፤ የማይቆራረጥ የልማት ስራችን ህያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሃገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)

Photos from አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .'s post 02/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የድምፅ መስጫ ሂደቱ እስከ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ሲከናወን ቆይቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ግንቦት 24 ቀንም ሆነ ሌሊት ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙ ተገልጿል።

ድምጽ የመስጠት ስርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ መራጩ ህዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ መላው የጸጥታ አካላት ኮማንድ ፖስቱ ምስጋናውን አቅርቧል።

ድምጽ ቆጠራው ቀጥሏል።

ድህረ ምርጫ ያለው ሂደት በተመሳሳይ በስኬት እንዲከናወን ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት ጥሪውን አቅርቧል።

02/06/2026

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡

ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 01/06/2026
Photos from አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .'s post 01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
አዲስ አበባ እየመረጠች ነው!

የከተማችን ነዋሪዎች ድምፅ የመስጠት፥ ዴሞክራሲን የማፅናት ቁርጠኝነት፣ የዜግነት ድርሻ ለመወጣት ትጋት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች እየታየ ነው።

ከማለዳ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ 7ኛውን ህገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት አሁንም በአዲስ አበባ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ቀጥሏል፡፡

01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር)

Photos from አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .'s post 01/06/2026

በምሽት ተሰልፈው ለሚገኙ መራጮች ወ/ሮ መሪማ ታደሰ በነፃ ምግብና ውኃ እያቀረቡ ነው

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መሪማ ታደሰ፤ የምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ማራዘሙን ተከትሎ በምሽት ተሰልፈው ድምፃቸውን ለመስጠት እየተጠባበቁ ላሉ ነዋሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ምግብና ውኃ በነፃ እያቀረቡ ነው፡፡

ወ/ሮ መሪማ መራጩ ሕዝብ ሳይሰለችና ሳይደክም የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ለማበረታታት ቆሎ፣ ውኃ፣ ዳቦ እና ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ወቅትም በክፍለ ከተማው የምርጫ ክልል 28 ሥር በሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎች በርካታ መራጮች አሁንም ድረስ ተሰልፈው ተራቸውን እየተጠባበቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡

Photos from አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .'s post 01/06/2026

"'ዲሞክራሲ አይገባህም፤ እኛ እናውቅልሃለን' በሚሉ ተጽዕኖዎች፣ ጉትጎታዎችንና ማስፈራሪያዎችን ሲያስተናግድ የቆየዉ ሕዝባችን፣ ዛሬ በቃል ከሚገለፀዉ በላይ ታላቅ ጽናቱን እና ለሀገሩ ያለዉን ፍቅር በተግባር አስመስክሯል።

በምርጫው ሂደት ከሌሊቱ አንስቶ በየምርጫ ጣቢያው የታየው አስደማሚ ረጅጅም ሰልፍ፣ እነሆ ምሽቱን ጭምር ተጠናክሮ በጽናት ቀጥሏል።

በዚህ ታሪካዊ የታማኝነት እና ዲምክራሲን የማፅናት ጉዞ በሕዝብ ተመርጦ የመንግሥትን በትረ ሥልጣን የሚረከብ ማንኛውም አካል፣ ይህንን ታላቅ የሕዝብ አደራ ፣ የዓላማ ጽናትና የዲሞክራሲ እምነት ከግንዛቤ በማስገባት፣ ከባድ አገራዊ ኃላፊነትን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እንደሚቀበል እምነቴ ነው።

#ኢትዮዽያእየመረጠችነው
#ዲምክራሲ #የሕዝብሉዓላዊነት

ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .'s post 01/06/2026

ድምፃችንን ሳንሰጥ ወደ ቤት አንገባም - የመዲናዋ ነዋሪዎች

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ረጅም ሰልፎችን ይዘው ተራቸውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ መራጮች፣ የዜግነት ግዴታቸውን ተወጥተው ድምፃቸውን ሳይሰጡ ወደ ቤታቸው እንደማይመለሱ ገለጹ።

ኤ ኤም ኤን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የምርጫ ክልል ተገኝቶ ያነጋገራቸው መራጮች ፤ አቶ ሲሳይ ዘይኑ፣ አቶ ዘነበ ግዛቸው፣ ወ/ት ሰላማዊት ግርማ፣ አቶ ስዩም ዘለቀ እና አቶ ሙባረክ ሙዘይን፤ በሰጡት አስተያየት ድምፃችን ለሀገራችን ትልቅ ዋጋ አለው ብለዋል።

መራጮቹ አክለውም፣ የምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ማራዘሙን ተከትሎ ቀኑ ቢመሽም የያዙትን የመራጭነት ካርድ እንደማያባክኑና በጽናት ተሰልፈው ይበጀናል ለሚሉት ፓርቲ ድምፅ ሳይሰጡ ወደ ቤት እንደማይሄዱ በቆራጥነት ተናግረዋል።

Photos from አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .'s post 01/06/2026

ኢትዮዽያ እየመረጠች ነው!

7ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ከሌሊት ጀምሮ በመውጣት ሲመርጡ ለነበሩ የከተማችን ነዋሪዎች፥ በተፈጠረው የምርጫ ሂደት መዘግየት ምክንያት፣ የድምፅ መስጠት ሂደት ባልተጠናቀቅባቸው የምርጫ ጣቢያዎች እስከ ምሽት 6 ሰዓት ማራዘሙን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ይህን ተከትሎ፥ መላው የከተማችን ነዋሪዎች በማለዳ በነበረው ከፍተኛ መነሳሳት የሚስተካከል፣ በታላቅ ሃላፊነት እና ትዕግስት አሁንም በዚህ ሰዓት በየድምፅ መስጫ ጣብያዎች ተሰልፎ ድምፅ እየሰጠ ይገኛል። ለዚህም ላቅ ያለ አድናቆት ይገባዋል።

!

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa