Addis Ababa City Roads Authority /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

Addis Ababa City Roads Authority  /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች  ባለሥልጣን

Share

This is Addis Ababa City Roads Authority's official face book page. Respected followers of the page,please get verified information here.

We appreciate if you could invite others to like our page.

Photos from Addis Ababa City Roads Authority  /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች  ባለሥልጣን's post 06/06/2026

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ ከባለስልጠኑ ሥራ መሪዎች እና ባለድርሻዎች ጋር በመሆን የመንገድ ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታ እያደረጉ ይገኛል፡፡

የአውቶቡስ ተራ መሳለሚያ -18 ማዞሪያ መንገድ ፕሮጀክት ምልከታ በምስል፡-

Photos from Addis Ababa City Roads Authority  /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች  ባለሥልጣን's post 06/06/2026

ወደ ሰሜን የሀገራችን ክፍል ዋነኛ መውጫ መንገድ የከባድ ጥገና ሥራ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ወደ ሰሜን የሀገራችን ክፍል ዋነኛ መውጫ መንገድ ከባድ ጥገና ስራ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡
የጥገና ስራው የተከናወነው ከሰሜን መዘጋጃ - በአዲሱ ገበያ - በሸገር ኤፍ.ኤም ራዲዮ አድርጎ እስከ ሱሉልታ መውጫ ኬላ በሚዘልቀው መስመር ላይ ነው። ይህ መንገድ በቀን ውስጥ በርካታ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠቱ ምክንያት አስፋልቱ ተቦርቡሮ ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ለይቶ በማንሳት 17 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና በአማካይ ከ20 እስከ 30 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ከባድ የጥገና ስራ ተከናውኗል።

የመንገዱ መታደስ በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ከመቅረፉም በላይ፣ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ቀልጣፋ፣ ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የያደርገው ይሆናል።

06/06/2026

የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

በአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራን በተግባራዊ ፖሊሲዎች ለመደገፍ ያለመ አህጉራዊ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኔ 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ያዘጋጀው ይህ ጉባኤ በአካዳሚክ ምርምሮች እና በፖሊሲ አፈጻጸሞች መካከል ያለውን ክፍተት መሙላትን ታሳቢ ያደረገ ነው።

የአፍሪካ ልማትና የተግባራዊ መፍትሄዎች መድረክ (ADIF 2026) የሚል ስያሜ ያለው ጉባኤ “በአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ የሚረዱ ምርጥ ተሞክሮዎችና የፈጠራ መፍትሔዎች” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ነው።

ጉባኤው በአፍሪካ በፍጥነት እያደገ የሚገኘውን የወጣት ማኅበረሰብ፣ በዓመት ከ15 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድል በመፍጠር አህጉራዊው ፍላጎትን ለመመለስ ከተያዘው ውጥን ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው።

ይህ አዲስ መድረክ ከተለመዱ አህጉራዊ ስብሰባዎች በተለየ፤ የፖሊሲ አፈጻጸምን በማፋጠን በዘርፉ ያለውን የፖሊሲ እና የአሰራር ሂደት ለማቀለጣፈ ያለመ መሆኑን ኢዜአ ከኢሲኤ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህም መሠረት የኢኮኖሚክ ኮሚሽኑ በገንዘብ እጥረት ምክንያት መሬት ያልወረዱ ጥናታዊ ምርምሮችን ወደ ተግባር ለመለወጥ፣ በጥቂት አካባቢዎች ተሞክረው ስኬታማ የሆኑ አነስተኛ የሙከራ ፕሮጀክቶችን ለማስፋት እንዲሁም አህጉር በቀል ምርጥ ተሞክሮዎችን በአገራት አጠቃላይ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ውስጥ በቀጥታ ለማካተት አቅዷል።

አሠራሩ በልማት ላይ የሚፈሱ የአህጉሪቱ ኢንቨስትመንቶች አስተማማኝና ዘላቂ ውጤት እንዲያመጡ ለማድረግ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ተብሏል።

የፎረሙን ውጤታማነትና ተጠያቂነት በተረጋገጠ መልኩ ለመከታተልም፣ ከጉባኤው በፊት፣ በጉባኤው ወቅትና ከጉባኤው በኋላ የሚተገበር የአሠራር ሥርዓት ተዘርግቷል።

የመድረኩን ቀጣይነትና ትስስር አስተማማኝ ለማድረግ፣ የየዓመቱ መሪ ሀሳቦችን አንዱ ከሌላው ጋር በማስተሳሰር እና ተመጋጋቢ በማድረግ እንደሚዘጋጁ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በቀጣይ የሚካሄዱት ፎረሞች፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ትግበራን ከአህጉራዊ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂዎች ጋር ማስተሳሰር ጨምሮ ሌሎች የልማት የትኩረት መስኮችን ታሳቢ በማድረግ እንደሚካሄድ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

Photos from Addis Ababa City Roads Authority  /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች  ባለሥልጣን's post 05/06/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ።

ለካቢኔው በዛሬው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሰረት፡-
1ኛ. የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስተዳደር ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ተፈፃሚ እንዲሆን አፅድቋል።

2ኛ. የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

3ኛ. በግል ዘርፍ ለህክምና ተቋማት ግንባታ እና ማስፉፍያ የሚውል መሬት ለማስተላለፍ የቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ፣ ተፈፃሚ እንዲሆን አድፅድቋል።

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 05/06/2026
Photos from Addis Ababa City Roads Authority  /አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች  ባለሥልጣን's post 05/06/2026

አዲስ አበባን የአፍሪካ የከተሞች ልማት ተምሳሌት ያደረገው የ24/7 የመፈጸም አቅም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም "የዛሬ አምስት ዓመት አዲስ አበባ በአፍሪካ ውስጥ እጅግ ውብ ከሚባሉ ከተሞች አንዷ ትሆናለች" በማለት አቅጣጫ ያስቀመጡት ከተማዋ ስሟን የምትመጥን እንድትሆን በማሰብ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ዛሬ በከተማዋ ተግባራዊ በሆኑት መዋቅራዊ እና ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች አማካኝነት በተጨባጭ እውን እየሆነ ይገኛል።

ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ወደ መሬት አውርዶ በተግባር ለመተርጎም ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሳየው የአፈጻጸም ብቃት ሁነኛ ሚና ተጫውቷል።

በከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራው የከተማዋ አመራር ቁርጠኝነት የለውጡ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሞተር ሆኖ አዲስ አበባን እንደ ስሟ የፈካች አበባ አድርጓታል።

አስተዳደሩ ያሰፈነው የ24/7 (ቀን ከሌሊት) የሥራ ባህል ቀደም ሲል ለዘመናት ስር ሰድዶ የነበረውን ዝግተኛ የመንግሥት ቢሮክራሲ በመስበር፣ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ እና በከፍተኛ ጥራት የማጠናቀቅ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል።

ይህ የሥራ ባህል ለውጥ ከተማዋን የማዘመን ተግባር ብቻ ሳይሆን፣ የከተማዋን ኢኮኖሚ ሌት ተቀን በማንቀሳቀስ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ የልማት ኃይል ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

የአመራሩ በቢሮ ከመቀመጥ ይልቅ በምሽት የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ በአካል በመገኘት እና በመከታተል፣ በበዓላት ቀናት ከኮሪደር ልማት ሠራተኞች ጋር ማዕድ በመጋራት፣ እንዲሁም ሠራተኛውን በቅርበት በማበረታታት መሪነትን በተግባር አሳይተዋል።

ይህ ዓይነቱ ያልተቋረጠ የአመራር ክትትል እና አብሮነት የሥራ ባህልን በመቀየር ረገድ ትልቅ ሥነ-ልቦናዊ ለውጥ አምጥቷል።

የአስተዳደሩ ትጋት ከተማዋ ላይ ያመጣቸው ተጨባጭ ለውጦች ያፈሩት ፍሬ ዛሬ በገሃድ ይታያል፤ በርካቶችንም ተጠቃሚ አድርገዋል።

የከተማዋን ገጽታ ሙሉ ለሙሉ የቀየሩት ሰፋፊ የኮሪደር ልማቶች፣ ግዙፉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር፣ የወንዝ ዳር ልማቶች፣ ማራኪ የሆኑት የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎች እና ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ ልማቶች የአዲስ አበባን ትክክለኛ ውበት አጉልተው አውጥተውታል።

አዲስ አበባን የኪነ ጥበብ እና ፍልስፍና ማዕከል ለማድረግም ዘመናዊ የሲኒማ ኮምፕሌክሶች እና አምፊ ቴአትሮች በስፋት ተሠርተው ለአገልግሎት በቅተዋል።

አዲስ አበባ መጪውን ጊዜ ስታስብ ትላንቷንም ሳትረሳ ኢትዮጵያን ላገለገሉት ልጆቿ መታሰቢያ በማቆም ለቅርሶቿ ጥበቃ አድርጋለች።

የወንዝ ዳር ልማት፣ ትላንት የበሽታ እና የወንጀል ምንጮች የነበሩ ወንዞችን በማደስ ለከተማዋ አዲስ አስትንፋስ ሰጥቷል።

እነዚህ ተከታታይ ስኬቶች አዲስ አበባ ስሟን የሚመጥን ከተማ እንድትሆን ከማድረጋቸውም ባሻገር፣ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫነቷን እና የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በሚመጥን መልኩ የዓለምን ቀልብ በከፍተኛ ሁኔታ እንድትስብ አድርጓታል።

ዛሬ ላይ ቱሪስቶችም ሆኑ ዓለም አቀፍ ልዑካን በከተማዋ ንጽህና እና ፈጣን ዕድገት መገረማቸውን በተደጋጋሚ ከመግለጽ አልፈው በአካል መጥተው ለዓለም አረጋግጠዋል።

መዲናችንን የጎበኙ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችም ከተማዋ ከየትኛውም የዓለማችን ከተማ ጋር የምትወዳደር ውብ ከተማ እንደሆነች አረጋግጠዋል።

ከዚህም በላይ የከተማ አስተዳደሩ የጀመረው የኮሪደር ልማት እና የመልሶ ማልማት ሥራ፣ ማንንም ወደ ኋላ የማይተው ሰው-ተኮር መርሕን የተከተለ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስመዘገበው ይህ አስደናቂ የመፈጸም አቅም እና የልማት አርአያነት በዋና ከተማዋ ብቻ ተወስኖ አልቀረም።

ከተማ አስተዳደሩ ይህን ተጨባጭ ለውጥ ወደ ክልል ከተሞችም በተሳካ ሁኔታ እንዲሰርጽ አድርጓል።

ባለሙያዎችን በመመደብ እና የቴክኒክ ድጋፎችን በማቅረብ ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የጀመረችውን የኮሪደር ልማት በፍጥነት እና በጥራት እንድታከናውን ትልቅ አሻራውን አሳርፏል።

በተመሳሳይ መልኩ የሐይቆች ከተማ የሆነችውን ቢሾፍቱ ከተማን የኮሪደር ልማት እና የቱሪስት መዳረሻነት ለማጠናከር የተደረጉት የልምድ ልውውጦች፣ የአመራሩን አጋርነት እና ሀገራዊ ቁርጠኝነት በተግባር ያሳዩ ናቸው።

በአዲስ አበባ የታየው ይህ አስደናቂ ለውጥ በምኞት የመጣ ሳይሆን፣ በጠንካራ መዋቅራዊ ዕቅድ፣ ቀን ከሌሊት በሚተጋ ቁርጠኛ አመራር፣ በተለወጠ የሥራ ባህል እና ከሕዝብ ጋር በተመሠረተ ጠንካራ ትሥሥር የመጣ ውጤት ነው።

ይህ ስኬት "የጀመርነውን እናጠናቅቃለን" የሚለውን የይቻላል መንፈስ በዜጎች ልቦና ውስጥ ያሰረጸ እና መላው ኢትዮጵያውያን በመዲናቸው እንዲኮሩ ያደረገ ብሩህ ተስፋ ነው።

አዲስ አበባ ዛሬ በአፍሪካ እጅግ ተወዳዳሪ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ለሌሎች ከተሞች ታላቅ የልማት ትምህርት ቤት ሆና በኩራት ቆማለች።

EBC

05/06/2026

የቦሌ ኤድናሞል - 22 ጎላጎል የመንገድ ፕሮጀክት አስፋልት የማንጠፍ ስራ እየተፋጠነ ነው

05/06/2026

24/7 በላቀ ፍጥነት
የአየርጤና-ወለቴ የመንገድ ፕሮጀክት ተደራቢ አስፋልት የማንጠፍ ሥራ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Sar Bet
Addis Ababa
9206