የውስጤን በግጥም-ሚኪ

የውስጤን በግጥም-ሚኪ

Share

ስለፍቅር ብዙ ብዙ ይባላል, እስኪ እኛም ስለ ፍቅር ያለንን ሀሳብ በስንኝ እንግለፅ.ፍቅር ሀያል ነው, በምንም ነገር የማይረታ ከእግዚአብሄር የተሰጠ ልዩ ፀጋ

04/10/2016

★★★ ኤሎሄ ኤሎሄ ★★★
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የሀገሬ ችግር የወገኖቸ ሞት
እያደር ቢጨምር፣
ባንዱ ባንዱ ምክንያት ግፉ ቢጠነክር፣
ያሳለፍነው አመት ያደረሰብንን
ያፈሰሰውን ደም፣
ጦሱን ይዞ እንድያልፍ በአድሱ አመትም
ዳግም እንዳይደግም፣
ፈጣሪን ተማፅነን ባንድነት ለምነን፣
እጅ ለእጅ ተያይዘን ሰላምን ለማብሰር
ምለን ተማምለን፣
አድሱን አመትም ገና እንደጀመርነው፣
ወርሃ መስከረምን በፍቅር እንደጀመርን
ገና ሳንጨርሰው፣
ልብን የሚሰብር ሀዘን ሰማን ምነው?፣
ክቡሩ የሰው ልጅ በዚች በኛ ምድር
ምነው ረከሰ?፣
የዜጎች ንፁህ ደም እንደ ክረምት ውሃ
በከንቱ ፈሰሰ፣
በሀዘኑ ምሬት ውስጤን እጅግ ከፋው
አይኔም አለቀሰ፣
መከራው ሲጨምር በወገኖቸ ሞት
ሆደ ተላወሰ፣
አምናና ታች አምና በደረሰው ሀዘን
ልቤ ሳያገግም፣
ያም አልበቃ ብሎ ዛሬ ላይ ሲደገም፣
ምነው አላለቅስ ልቤ እንደት አያዝን?፣
ሲደራረብብኝ ከሀዘን ላይ ሀዘን፣
ቅስሜ እጅግ ቢሰበር ሀዘኔ ባይወጣ፣
እጅጉን ቢጨምር የመከራው ቁጣ፣
ኤሎሄ ኤሎሄ ልበል ለፈጣሪ
ለእውነተኛው ዳኛ፣
ፍፁም ይቅርታውን ፍቅሩን ምህረቱን
እንድሰጠን ለኛ፣
እባክህ አምለኬ ስማኝ ልለምንህ፣
የሞቱትን ምረህ ያሉትን ጠብቀህ፣
እምባችን ታብሶ ደስታ ተተክቶ
ፍቅር እንድመጣ፣
ምህረት ርህራሄ ፍቅር የሞላበት
አድስ ዘመን አምጣ፣
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
(ለሞቱት ወገኖቻችን ነፍሳቸውን በገነት እንድያኖርልን እየተማፀንን ለወዳች ዘመዶቻቸውም መፅናናትን እንመኛለን)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሚኪያስ መሰለ
24/01/09 ዓ·ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

Photos 26/09/2016

★★★ መስቀል ★★★
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
እዮሃ አበባየ
መስከረም ጠባየ
ብለን ከተቀበልን አዲሱን አመት፣
እነሆ አሳለፍን ሁለት ሳምንታት፣
ለመስቀል ዋዜማ ደመር ደመራ፣
ችቦውን እንለኩስ ህይወታችን ይብራ፣
መጭው ዘመናችን እንድባረክልን፣
በጨለማው ምትክ ብርሃን ይሁንልን፣
ሀገር ሰላም ይሁን ኸይር ይሁን ቀያችን፣
አዝመራው ይትረፍረፍ ይሙላ ጎተራችን፣
በስደት ያላችሁ እህት ወንድሞቸ፣
ሀገር ውስጥም ያለን ወገን ዘመጆቸ፣
ሁላችን ባንድ ላይ እንኳን አደረሰን፣
እንድህ እንዳሁን በሰላም እንዳለን፣
ደስታ በኛ ነግሶ ፍቅርን ተላብሰን፣
ደሞ ለመጭ አመት በሰላም ያድርሰን፣፣
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
(ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
Ⓜሚኪያስ መሰለ
16/01/09 ዓ·ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

21/09/2016

**እማማ እናቴ እወድሻለሁኝ**
~~~~~~~~~~~~~~~~~
አዎ እማማ እናቴ እወድሻለሁኝ፣
ካጠገብሽ ሳለሁ ከቤት ከደጃፍሽ
እጅጉን እወድሻለሁኝ፣
እማ
ካገር ከቀዬው ስሰደድማ
ያንን ወደርና አምሳያ የሌለው
ጠረንሽን ተርቤዋለሁኝ፣
እናቴ እወድሻለሀኝ፣
ታድያ ምን ያደርጋል....
አንቺ እኔን ወልደሽ አሳድገሽ፣
የወላድ መካን አደረኩሽ፣
አንቺ ብትመርቂኝ፣
ጓደኞችሽ ሲረግሙኝ፣
እኔማ እናቴ እወድሻለሁኝ፣
እንዴት እንዳትይኝ፣
ጸጉሬን እየዳበስሽ እንዳትመረምሪኝ፣
እኔም መልስ የለኝ ግን እወድሻለሁኝ፣
እኔን ለማሳደግ ውሀ ብትሸጭ፣
እሰዎች ኩሽናም ብትርመጠመጭ፣
አስፋልት ጎዳና ላይ ልመና ብትወጭ፣
ክብርሽን ስለኔው ለሰዎች ብትሰጭ፣
አይ እማ እወድሻለሁኝ፣
አንቺ ዝቅ ብለሽ እኔ ከፍ አልኩና፣
ቴክኖሎጅ ካሉት ከስህተት ጎዳና፣
ማንም ሳይገራኝ ከች አልኩልሽና፣
በሀገር በእድር በባእልም ሳይቀር፣
አብረውሽ የኖሩትን የተከበሩትን
እነኛ ጓደኞችሽን፣
ዘር እና አይማኖት እንዲሁም ንብረት
ሳይለዩ የሚያከብሩሽ የሚወዱሽን፣
ሁሉንም እኮ ነው የሰደብኳቸው፣
እናትሽ እናትህ አፈር ትብላ እያልኩ፣
እንደው በዘመኑስ ምንም አልተመረኩ፣
አንቺን እናቴን ግን እወድሻለሁኝ
አይ እማ በቃ ብዙ አትመርምሪኝ
ግን ደሞ አትቀየሚኝ
በሀዘኑ አይኖችሽ እንዲህ አትመርምሪኝ፣
ያስተማኩት ሁሉ ወዴት ነው አትበይኝ፣
አንቺ አስተምረሻል አደራም ብለሻል፣
አክብሩ ተከባበሩ እያልሽ አጉርሰሻል፣
ታድያ ምን ያደርጋል በዘመኑ እውቀት፣
አንቺን የማይሰድብ ወሬ አልጣፈጠለት፣
እናቴ እወድሻለሁ፣
እያልኩ የምልሽ እንደማታውቂያቸው ዛሬ ግን እኔ በግድ ባህል ካላወረችሁ እያልኩ የተጣበቅዋቸው እንደ ነጫጮቹ ነው፣ እንዳንቺማ ቢሆን እንደ መከራሽ፣
ይህን ሁሉ ጉድ ዛሬ ላይ ባልሰማሽ፣
የነሱኮ ፍቅር እጅጉን ያስቃል፣
ጠዋት በማለዳ የወረወሯቸው፣
ከመኝታው በቀር ጭራሽ አያዩቸው፣
ታድያ የሚደንቅሽ አቤት ልጆቹ ሲያከብሯቸው፣
እንደአንቺማ ሆነው ቢያሳድጓቸው፣
ማንም ባልተጣላ ባልተራረዱላቸው፣
ያለ ባእልሽ mam s DAY እያልኩኝ፣
እማማ እናቴ እወድሻለሁኝ፣፣
-------------------------------
ሚኪ
11/01/09 ዓ•ም

17/09/2016

*** ትዝታ ***
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ጥርት ባለው ሰማይ ከዋክብት ሲደምቁ፣
በጨረቃ ብርሃን አምረው ሲመርቁ፣
ቁልቁል ወደ መሬት ብርሃንን ሲረጩ፣
የፍቅርን ዝማሬ ሲያዜሙ ሲያፏጩ፣
ውሃ ለቅዳ ብለሽ ስትመጭ ወደ ምንጩ፣
አጠብቅሽ ነበር ከወንዝ ዳር ቆሜ፣
በናፍቆት በስስት በፍቅርሽ ታምሜ፣
በቀዝቃዛው አየር ፍቅርን ስንቋደስ፣
በሳቅ በጨዋታ የልባችን ሲደርስ፣
ያን የፍቅር ጊዜ ዞሬ ሳስታውሰው ፣
አልቅስ አልቅስ አለኝ ሆደንም ሆድ ባሰው፣
ፍፁም አልጠፋ አለኝ ከውስጤ ትዝታው፣
ሰአቱን ጠብቆ ይመጣል በማታው፣
ቀን ለማታው ለቆ ጊዜውን ሲረከብ፣
ያኔ ያደመቁን ጨረቃና ኮከብ፣
ፀባይ መልካቸውን ምንም ሳይለውጡ፣
ሰዓቱን ጠበቀው በድምቀት ሲወጡ፣
እኔና አንች ብቻ ዛሬ ተራራቅን፣
የፍቅርን ካባ ከላያችን አወለቅን፣
ከቶ አንለያይም ዘላለም አንድ ነን፣
ላልከዳህ ላልከዳሽ እንዳልተባባልን፣
ያ ሁሉ ቃል ኪዳን ቀርቶ መሃ‘ላችን፣
ይሄው ተለያይን ፈረሰ ፍቅራችን፣
ይብላኝ እንጅ ላንች እኔስ ለምጃለሁ፣
ትዝታሽን ብቻ በልቤ ይዣለሁ፣
_______________________________
ሚኪያስ መሰለ
07/01/09 ዓ•ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

11/09/2016

*** ራሄል ወዴት አለሽ? ***
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አምላክ ከአርያም ጩኸትሽን የሰማሽ፣
ሀዘን እንጉርጉሮ ለቅሶና ዋይታሽ፣
እንደ ብርቱ ፅናት እንደ ጥንካሬሽ፣
አምላክ ከባርነት በነፃ ያወጣሽ፣
ታማኝ ወዳጁንም ሙሴንም የሰጠሽ፣
"እግዚአብሄር ታላቅ ነው!" ብሎ ያዘመረሽ፣
ወከባ ግርግር የጠላቶች አዲማ፣
ምንም ሳያግደው ድምፅሽ የተሰማ፣
ዘራ አድምጭኝማ ብሶቴን ልንገርሽ፣
ብዙ ጉድ አለብኝ ቁጭ በይ ላካግልሽ፣
አንች ያምላክ ባሪያ ራሄል ወደት አለሽ?፣
በቀደም ለት አንዱ ምን አለኝ መሰለሽ፣
"ብሄርህ ምንድነው ከየት ነው የመጣህ?፣
አማራ ነህ ትግሬ ወይስ ጉራጌ ነህ?፣
አፋር ነህ ጋምቤላ ኦሮሞ ሲዳማ፣
ከየት ነው ብሄርህ ድምፅህን አሰማ፣
ብሄር ሀይማኖትክን በልንጂ ንገረኝ፣"
ብሎ ቢጠይቀኝ፣
ከፀጉሬ ጀምሮ እስከ እግሬ ወረረኝ፣
እኔም መለስኩለት፣
"መነሻውም አዳም፣
መጨረሻው አዳም፣
ታድያ ከየት መጣ ይህ ዘር መለቃቀም?፣"
ስለው ተገረመ አዘነ መልሶ፣
እሱም ጋ አለና የክፍፍል ከቅሶ፣
ራሄል ሰማሽኝ ተረዳሽ ችግሬን፣
በዘር በሀይማኖት እጅግ መማረሬን?፣
ይህንን ብሶቴን ላምላክ ንገሪልኝ፣
ጩኸትን ተረድተሽ ፀሎት አድርሽልኝ፣
⤵ከላይ የተሰጠን ጠፍቶ አንድነታችን፣
በዘር በሀይማኖት መከፋፈላችን፣
ለኮንትራት ኑሮ ለዚች ጠፊ አለም፣
በጎጥ በቀበሌ በጎሳ በቀለም፣
ፈጣሪ ባምሳሉ አንድ አድርጎ ፈጥሮን፣
እኛ እርስ በርሳችን እየተከፋፈልን፣
ስንት አመት አለፈ ስንት ዘመን ኖርን?፣
አሁን ግን መረረኝ እባካችሁ ይብቃን፣
👉🏻እስኪ ራሳችንን ላፍታ እንጠይቀው፣
ማንነታችንን ጠልቀን እንወቀው፣
ነገ የሚባል ቀን ከቶ የለምና፣
ከዛሬ ጀምረን ባንድነት እንፅና፣
💞~~~~~~~~~~~~~~~~💞
√"መልካም አዲስ አመት ይሁንልን። አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የብልፅግና ይሁንልን!!!"
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሚኪያስ መሰለ
01/01/09 ዓ•ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

Photos 10/09/2016

✔✔ እንቁጣጣሽ ✔✔
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በጊዜ አቆጣጠር ቀን በቀን ሲለካ፣
አሮጌውን አመት ባድሱ ስንተካ፣
አዲስ ልብስ ለብሰን
አዲስ ጫማ ተጫምተን
አዲሱን አመት ለመቀበል ተዘጋጅተን፣
ወዳጅ ዘመድ አዝማድ ጓደኛ ጎረቤት፣
ህፃናት አዋቂ ሽማግሌ አዛውንት፣
ዶክተር ፐሮፌሰር ምሁራን ሊቃውንት፣
ሁላችን ባንድ ላይ አብረን ተሰብስበን፣
ያለፈውን አመት በሰላም ሸኝተን፣
እንቁጣጣሽ ስንል እጅግ ተደስተን፣
ከንጀራው ከወጡ ተጎራርሰን በልተን፣
ጠላው ና ዳቦው ሁሉንም አሟልተን፣
ሳቅ ደስታችን ሲያምር ጨዋታው ሲደራ፣
አንድ ነገር ብቻ እንዳንረሳ አደራ፣
↘ ባገር ውስጥም ሆነ ባህር ማዶ ያለን፣
ልክ እንደ አሮጌው ልብስ በጣልነው አውልቀን፣
መንፈሳችንንም መቀየር አለብን፣
እርስ በርስ ጥላቻ መቃቃርን ትተን፣
ያለፈን ቂም በቀል ይቅር ተባብለን፣
በአዲስ አስተሳሰብ ባዲስ ብሩህ ተስፋ፣
ጥላቻን አጥፍተን ፍቅርን እናስፋ፣
🌷🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌷
ሚኪያስ መሰለ
05/13/08 ዓ•ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

05/09/2016

**** እጠብቅሻለሁ****
ክረምቱ ሲነጋ ሰማዩ ሲያጠራ፣
ፍክት ድምቅ ስትይ እንደ ንጋት ጮራ፣
ፈገግታሽን ለምዶ መላ ሰውነቴ፣
ስንሰፈሰፍልሽ እንደ እምየ እናቴ፣
ስትስቂ እየሳኩኝ ሳጣሽ እየከፋኝ፣
ልክ እንደ ህፃን ልጅ ፍቅርሽ ጅል ሲያደርገኝ፣
ስንት ክረምት አልፎ ስንት በጋ መጣ፣
ሌላውን ሲያመላልስ አንችን ሳያመጣ፣
አሁንስ ጨነቀኝ መላው ጠፍቶብኛል፣
ትዝታን መቋቋም እጅግ አቅቶኛል፣
ጧት ማታ መናፈቅ ስስቱ ገድሎኛል፣
በወርሃ መስከረም በአመቱ መግቢያ፣
ፍልቅልቅ እያልሽ እንደ ክረምት አጥቢያ፣
ዘንድሮም እንዳምናው እጠብቅሻለሁ፣
ነይልኝ የኔ አለም እጎዳብሻለሁ፣
----------------------------
ሚኪያስ መሰለ
30/12/08 ዓ•ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

30/08/2016

**** የመጀመሪያየ ****
ያኔ በልጅነት በለጋው እድሜየ፣
በደምብ ሳልበስል ሳይፀና አእምሮየ፣
ፍቅርን ይስተማርሽኝ የመጀመሪያየ፣
የት ይሆን ያለሽው ድምፅሽ እራቀብኝ፣
መዓዛን ያስለመደኝ ጠረንሽ ጠፋብኝ፣
እንጆሪ ከንፈርሽ ድሮ የሳምኳቸው፣
ለስላሳ ጉንጮችሽ የደባበስኳቸው፣
አይጠፉም ከውስጤ መቸም አልረሳቸው፣
ስርቅር አይኖችሽ እልም ስልም ሲሉ፣
ልብን አሸፍተው ሰላም ይነሳሉ፣
የተስተካከለው የልጅነት ገላሽ፣
መላ ሰውነትሽ ውብ ተክለ ቁመናሽ፣
ሌት ቀን በትዝታ እየቀሰቀሱኝ፣
በሀሳብ ወደሁዋላ እያገሰገሱኝ፣
የዛሬ ሀይወቴን ኑሮየን አስረሱኝ፣
የፍቅር አቡጊዳን ቆጥረሽ ያስተማርሽኝ፣
የሀይወቴን ምእራፍ መኖር ያስጀመርሽኝ፣
የመጀመሪያየ ፍቅሬ ሆይ ናፈቅሽኝ፣
የደስታየ ቅኔ የልቤ መቅደስ ነሽ፣
ዘላለም በውስጤ ነግሰሽ ትኖሪያለሽ!፣
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ከሚኪያስ መሰለ
24/12/08 ዓ•ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

24/08/2016

***** ይቅርታ *****
------------------------------
አዝነሽብኝ አንች ከምኖር በፀፀት፣
ሁሌም ከምትሰጭኝ ፈገግታን በምፀት፣
ከልብሽ ያልሆነን ሰላምታን የውሸት፣
እውነት ነው የምልሽ ከልብ አዝኛለሁ፣
ይሄን ካንች ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ፣
አውቃለሁ አልክድም ....
ካንድም ሁለት ሶስቴ አስቀይሜሻለሁ፣
አውቄም ሳላቅም ጥፋት አጥፍቻለሁ፣
ግን እኮ ፍቅሬ ሆይ ...
ያጠፋሁት ጥፋት ታየሽ‘ንጅ ጎልቶ፣
ገዝፎ እንደ ተራራ እንደ አሸዋ በዝቶ፣
ጥሩም ጎኖች አሉኝ ለጊዜው ያልታዩሽ፣
ጥፋት ከልሏቸው ያልተገለፁልሽ፣

አሁን ግን አለሜ ጥፋቴን አምኘ፣
በበደልኩሽ በደል ከውስጤ አዝኘ፣
ነፍሴ ተጨንቃ ከደጅሽ ቁማለች፣
ከልብ የመነጨ ይቅርታን ትሻለች፣
ትንሽ ጊዜም ቢሆን ባሳለፍነው ፍቅር፣
ይቅር በይኝና ሁሉም ነገር ይቅር፣
አብረን ባንሆን እንኳን ፍቅራችን ባይቀጥል፣
ይቅርታ አድርጊና ነፍሴ አረፍ ትበል!፣
---------------------------
ሚኪያስ መሰለ
18/12/08 ዓ•ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

15/08/2016

**** ዝም ብየ አላይም****
-----------------------------
የፍቅርሽን ቅኔ በክራር ተቀኝተሽ፣
በከበሮ አጃቢ በዜማ አገናኝተሽ፣
ላይላዩን ጥሩ ሰው አሳቢ በመምሰል፣
ለኔ ተቆርቋሪ አዛኝ በማስመሰል፣
የውሸት ፈገግታ እየሳቅሽ ለይምሰል፣
በመላ አካላቴ መርስሽን ረጭተሽ፣
ልክ እንደ ክራርሽ እኔንም ከርክረሽ፣
ባሰኘሽ አቅጣጫ እኔን አሽከርክረሽ፣
ደሜን ስትመጭኝ 30 ዓመት ሞላሽ፣

በዶሮ ማልያ አሞራ እያጫወትሽ፣
በዳይም ፈራጅም ዳኛም አንች ሁነሽ፣
ስንቱን ምሁር ጀግና በግፍ አሰቃየሽ፣
ያለርህራሄ ስንቱን ገድለሽ ቀበርሽ፣
ስንቱንስ በድብቅ አፍነሽ አስቀረሽ፣
ስንቶቹን ሊቃውንት ከሀገር አባረርሽ፣
.........
ሆድ ይፍጀው ነው እንጅ ሁሉን ላምላክ ሰ‘ቶ፣
ያንች በደልማ አያልቅም ተወርቶ፣

ከቀን ቀን በደልሽ ይገባሻል ብየ፣
ጆሮየ እየሰማ አይኔ ብዙ እያየ፣
ብዙ አመት ታገስኩኝ መከራየን ችየ፣
አሁን ግን አልቻልኩም በቃኝ ቆርጫለሁ፣
በደልሽን ካላቆምሽ እፋለምሻለሁ፣
አንችን ለመዋጋት ተዘጋጅቻለሁ፣
አጥንቴን ከስክሸ ደሜን አፈሳለሁ፣
ጨርቄን ማቄን ሳልል ታጥቄ እነሳለሁ፣
ለብዙ ዘመናት ከወራሪ ሀገር፣
ጀግኖች አስጠብቀው ያቆዩዋትን ምድር፣
ዝም ብየ አላይም ባንች ስትወረር!!፣
(ማስታወሻነቱ ለጎንደር ጀግኖች)
--------------------------------
ሚኪያስ መሰለ
04/12/08 ዓ•ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

24/07/2016

**** የፍቅር ሻማ ****
-----------------------------
አምላክ አንችን መርጦ ለኔ ስለሰጠኝ፣
ለመኖሬ ትርጉም በፍቅር ያስቀመጠኝ፣
የዘላለም ህልሜ የልቤ ፍላጎት፣
ሁሌም ፍቅር ደስታ የተሞላ ህይወት፣
እንደ ፀሃይ ብሩህ ብርሃን የዘራበት፣
ውበት ግርማ ሞገስ ፀዳል የሞላበት፣
ውብና ማራኪ አንፀባራቂ ፊት፣
ይህ ነው ፍላጎቴ ይህን ካንች ማየት፣፣
------------------------------
ሰላምና ደስታን ባንች ላይ ለመፍጠር፣
ተራራውን ልውጣ ገደሉን ልቆፍር፣
ፀሃይ ብርዱ ቁሩ ይፈራረቁብኝ፣
ምንም ነገር የለም ካንች ‘ሚበለጥብኝ፣
ክንዴን ሳልንተራስ አፈር ሳይጫነኝ፣
አንችን ለማስደሰት የለም የሚሳነኝ፣
ህይወት እስትንፋሴ ማንነቴ አንች ነሽ፣
በማንም በምንም ሁሌ ‘ማልቀይርሽ፣
ህመምሽ ህመሜ ደስታሽ ደስታየ፣
ፀዳልሽ ውበቴ ሳቅሽ ፈገግታየ፣
እስትንፋስ ነፍሴ ነሽ ብርታት አለኝታየ፣
አንችን ለማስደሰት ምንም ነገር ልሁን፣
ነፍስሽ ተደስታ የኔ ብቻ ትሁን፣
እድሜየን በሙሉ ላንች ልኑርልሽ፣
ሁልጊዜም እንዳየው ውብ ሆኖ ፀዳልሽ፣
የፍቅር ሻማሽ ሁኘ እየቀለጥኩልሽ፣
ብርሃንን ፈንጥቄ ለፍቅሬ ላብራልሽ፣።
------------------------------
ሚኪያስ መሰለ
17/11/08 ዓም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

15/07/2016

***** ጨምርላት *****
---------------------------
ዛሬም እንደጥንቱ ከእንቅልፌ ስነቃ፣
በመንፈስ ተውጨ ተይዤ በሲቃ፣
ካልጋየ ወርጀ ስሮጥ ተንደርድሬ፣
ከመስኮት ፊት ለፊት ቆሜ ተገትሮ፣
በፍቅር ሃይል ስበት ግፊት ተገፍትሬ፣
ግጥሜን ከመቅፅበት ድንገት ገጣጥሜ፣
በዜማ አዋህጄ በቅኔ አጣጥሜ፣
የጠዋት ፀሎቴን ላደርስ በዜማ፣
ድምጼን ከፍ አድርጌ ላምላኬ ላሰማ፣
ስላንች የውስጤን የልብ ልመኛየን፣
የዘላለም ምኞት ፍላጎት መሻቴን፣
የፍቅር ርሃብ የፍቅር ጥማቴን፣
ላምላኬ ልነግረው ላደርስ ፀሎቴን፣
ዛሬም ፊቱ ቆሜ እንዳመሰግነው፣
ክብሩን እንፍናገር ምስጋና እንዳደርሰው፣
ላደረገኝ ጌታ ከሁሊ አስቀድሜ፣
ምስጋናየን ላድርስ ከፊቱ ላይ ቆሜ፣
-------------------
አምላኬ በልዩ በድንቅ ችሎታህ፣
በህያው እስትንፋስ በልዩ ጥበብህ፣
የፈጠርካት እንስት በገፀ አምሳልህ፣
እናትም እህትም ሚስትም ሁና እንድትኖር፣
ላዳም ዘር በሙሉ ፍቅርን እንድትዘምር፣
አንድ ነገር ለሷ ልለምንህ ጌታ፣
ለፀሎቴ ውጤት ለፍቅርህ ውለታ፣
አስውበህ አሳምረህ ጥንቱን ብትፈጥራት፣
ምንም ባይጎላትም ሁሉም ቢሟላላት፣
ብዙ አመት እንዲትኖር ቀኗ እንዲረዝምላት፣
ከኔ እድሜ ቀንሰህ ለሷ ጨምርላት፣
----------------------------
ሚኪያስ መሰለ
08/11/08 ዓም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
251