Federal Civil Service Commission

Federal Civil Service Commission

Share

We aspire to see a Public Service Which Effectively and Ethically Achieves its Mission by 2020 E.C.

Photos from Federal Civil Service Commission's post 28/05/2026

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ትግበራ ላይ የተካሄደው ድጋፋዊ የክትትል ሪፖርት ተገመገመ፡፡
*********************
አዲስ አበባ ግንቦት 20/2018 ዓ.ም ፣ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፤
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ያደራጀው የሱፕርቪዥን ቡድን በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ሲያካሄድ የነበረውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ክትትልና ድጋፍ ስራ ሪፖርት በማጠናቀቅ አፈጻፀሙ የሚገመገምበትን መድረክ አዘጋጅቷል።

በየክልሉ ተሰማርተው የነበሩ የሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት አሁን ባለቡበት ቦታ ሆነው በቀላሉ መሳተፍ እንዲችሉ መድረኩ በበይነ-መረብ (ኦንላይን) የተከናወነ ሲሆን፣ በመድረኩ የተገኙትና ውይይቱን የመሩት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ሲሆኑ የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ክብርት ወ/ሮ አልማዝ መሰለም በውይይቱ ላይ ተገኝተው ከክትትልና ሱፐርቪዥን ቡድኑ የተጠናቀረውን ጥቅልና ጭምቅ ሪፖርት አቅርበዋል።

ይህ ሰፊ የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ሥራ የተከናወነው በመጀመሪያው ዙር (Wave 1) የዝግጅት ምዕራፍ ሥራቸውን በስኬት አጠናቀው ወደ ትግበራ የተሸጋገሩ አራት የፌዴራል ተቋማት ሪፎርሙን ወደ ክልልና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች የማውረድ ሥራ መጀመራቸውን ተከትሎ ነው።

በዚህም መሠረት ከፌዴራልና ከክልል የተውጣጡ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎችን ያቀፉ 12 የክትትል ቡድኖች በ11 ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ስር በሚገኙ አራት ቁልፍ ቢሮዎች ማለትም በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት፣ በሥራና ክህሎት፣ በጤና እንዲሁም በፋይናንስ ቢሮዎች ላይ የተዘጋጀውን የመገምገሚያ መስፈርት መሠረት በማድረግ ድጋፋዊ ምልከታና ክትትል ያደረጉ ሲሆን የክትትሉ ዋና ዓላማ የሪፎርም ሥራው ወደ ክልል ሴክተር ቢሮዎች የወረደበትን ደረጃ መፈተሽ፣ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን መለየት፣ እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በቦታው ላይ በሚደረግ ድጋፍ መሙላትና መልካም ተሞክሮዎችን መቅሰም እንደነበር ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ በቀረበው ዝርዝር ሪፖርት መሠረት በእያንዳንዱ ተቋም የታዩ የሪፎርም አፈጻጸሞች፣ የተደረጉ የተሞክሮ ልውውጦች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች ላይ ከክልል ም/ቢሮ ኃላፊዎችና ከጠቅላላው የቡድኑ አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ከተሳታፊዎች የተነሱ አንዳንድ ጠቃሚ የማስተካከያ ሐሳቦችን በማካተት የተጠናቀረው ይህ የሪፎርም አፈጻጸም ሪፖርት፣ በቀጣይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለሚመራው ሀገራዊ የሪፎርም ኮሚቴ ቀርቦ ውሳኔና አቅጣጫ የሚሰጥበት እንደሚሆን ተገልጿል።
# የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ

Photos from Federal Civil Service Commission's post 28/05/2026

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፖሊሲ በተግባር፦ አካታችነትና እና ብዝሃነት
*********************
አዲስ አበባ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፖሊሲ አንዱ አምድ አካታችነትና እና ብዝሃነትን (Inclusivity and Diversity) ማረጋገጥ ነው። ይህ ፖሊሲ የመንግስት ተቋማት እያንዳንዱን ዜጋ በእኩልነት፣ በክብርና ያለ አድልዎ ማገልገል እንዳለባቸው ይደነግጋል።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) በጋራ በመሆን “FUTURE SMART: Transforming the Public Sector for Improved Service Delivery” የተሰኘውን ታሪካዊ የሙከራ ፕሮጀክት በስኬት በማጠናቀቅ ይህንን የሪፎርም ፖሊሲ በተግባር ምን እንደሚመስል አሳይተዋል።

ይህ ለ15 ወራት የቆየው የሙከራ ፕሮጀክት በከፍተኛ ደረጃ የተቀመጡ የፖሊሲ ግቦችን ወደ ተጨባጭ የአካባቢ ለውጦች ቀይሯል። ፕሮጀክቱ ትኩረቱን ያደረገው የአካባቢው የመንግስት አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ዲጂታል፣ ቀልጣፋ እና ሁሉንም ያካተቱ በማድረግ ላይ ያደረገ ሲሆን፤ የአካል ጉዳተኞች (PwDs) እና ሴቶች በክብር እንዲስተናገዱ የሚያደርጉ ሰፊ ድጋፎችንም አካቶ የያዘ ነበር።

የአካታችነትና እና ብዝሃነት ፖሊሲ አምድ ተግባራዊነት ሙከራ በተደረገባቸው አካባቢዎች በተግባር የተፈተሸው እንደሚከተለው ነው፦
📍 ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7 (አዲስ አበባ) — ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት (PADet) ጋር በመተባበር
• እናቶችንና ቤተሰቦችን መደገፍ፦ እናቶች ልጆቻቸውን በንጽህና እና በሰላም የሚያጠቡበት እንዲሁም ዳይፐር የሚቀይሩበት ልዩና ራሱን የቻለ ክፍል ተገንብቷል።
• ተደራሽነትን ማሳደግ፦ ለአካል ጉዳተኞች ያለ ምንም እንቅፋት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ ምቹ የእግር ጉዞ መንገዶች እና ልዩ መጸዳጃ ቤቶች ተገንብተዋል።
• የአቅም ግንባታ፦ ለ30 የወረዳው ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች ዜጎችን በክብር እና ሁሉን ባካተተ መልኩ ማስተናገድ እንዲችሉ የስራ ደረጃ ስልጠና ተሰጥቷል።
📍 ከርፌ ቀበሌ፣ አደዓ ወረዳ (ኦሮሚያ) — ከሲቄ የሴቶች ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር
• እናቶችንና ቤተሰቦችን መደገፍ፦ ማዘጋጃ ቤቱን ለሚጎበኙ እናቶች የሚሆን ልዩና ምቹ የጡት ማጥቢያና የዳይፐር መቀየሪያ ክፍል ተዘጋጅቷል።

• ተደራሽነትን ማሳደግ፦ የማዘጋጃ ቤቱ ህንፃዎች በዊልቸር ለመግባት እንዲያመቹ ተደርገው በሮችና መወጣጫዎች የተስተካከሉ ሲሆን፣ 35 አጋዥ መሣሪያዎች (ዊልቸሮች፣ ክራንቾችና ምርኩዞች) አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሰዎች ተሰራጭተዋል።

• የዲጂታል ሽግግር፦ የቢሮ አሰራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረግ፣ 73 ሰራተኞች የአካባቢውን አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች በቀላሉ መዝግበው መደገፍ እንዲችሉ ስልጠና ተሰጥቷል።

የ“FUTURE SMART” ፕሮጀክት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቅ ሁለቱን የሙከራ ቦታዎች ከማዘመን ባለፈ፣ የሪፎርም ፖሊሲውን የአካቶነት ቁርጠኝነት በመላ ሀገሪቱ እንዴት መተግበር እንደሚቻል ማሳያ የሆነ ትልቅ አርአያ ጥሎ አልፏል። ይህ ተግባር ደግሞ ማንም ዜጋ ወደኋላ የማይቀርበት ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ለመገንባት በቁርጠኝነት እየተጓዝን መሆኑን ማሳያ ነው፡፡
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ

Public Service and Administration Reform Policy in Action: Inclusivity & Diversity
**********************
A cornerstone of the Public Service and Administration Reform Policy is the Inclusivity and Diversity pillar. This policy mandates that our public institutions evolve to welcome, respect, and serve every single citizen equitably.
The Federal Civil Service Commission and UNDP Ethiopia have just demonstrated exactly what operationalizing this policy looks like by successfully concluding their milestone pilot project: "FUTURE SMART: Transforming the Public Sector for Improved Service Delivery."
This 15-month initiative translated high-level policy goals into tangible, local-level changes. It focused on making government hubs digital, efficient, and deeply inclusive—expanding support to ensure that both persons with disabilities (PwDs) and women are accommodated with dignity.
Here is how the Inclusivity and Diversity pillar came to life in the pilot locations:
📍 Bole Sub-City, Woreda 7 (Addis Ababa) — In partnership with CSO PADet
• Supporting Mothers & Families: Built specialized, dedicated spaces for women, providing a clean, private room to safely nurse their children and change diapers.
• Enhancing Accessibility: Constructed accessible pavements and specialized restrooms to guarantee barrier-free physical access to public services.
• Capacity Building: Delivered service-standard training to 30 municipal staff members to ensure dignified, inclusive citizen engagement.
📍 Karfe Kebele, Adea Woreda (Oromia) — In partnership with Siiqqee Women's Development
• Supporting Mothers & Families: Integrated private, dedicated nursing and diaper-changing spaces for mothers visiting the municipal hub.
• Enhancing Accessibility: Modified municipal infrastructure with wheelchair-accessible doors and ramps, and distributed 35 assistive devices (wheelchairs, canes, crutches) directly to the community.
• Digital Transformation: Digitized office operations and trained staff to seamlessly register and support 73 local residents with disabilities.
The successful finalization of the "FUTURE SMART" initiative does more than upgrade two offices—it provides a proven, scalable blueprint that shows exactly how to implement the Reform Policy's commitment to inclusion across the entire nation. From accessible ramps to private nursing rooms, we are moving closer to a modernized public service that truly leaves no citizen behind!
Relations and Communication Executive

26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሰዎ! ዒድ ሙባረክ!!
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን #🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Photos from Federal Civil Service Commission's post 24/05/2026

ለፌዴራል ተቋማትና ለዩኒቨርሲቲዎች የኢስሚስ ሥርዓት አጠቃቀም የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ::
*************
አዲስ አበባ | ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና የዲጂታል ሪፎርሙን ለማፋጠን ሲያከናውን የቆየው ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ አንድ ምዕራፍ መሻገሩም ተጠቁሟል።

የሰራተኞችን መረጃ ወደ ስማርት የሰው ሀብት አስተዳደር አስሚስ አጠቃቀም እና መረጃ ሥርዓት ለማስገባት በአዳማ ከተማ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።

በዚህ ስልጠና ላይ ከተለያዩ የፌዴራል መንግሥት ተቋማት እና ከሀገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) የተውጣጡ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) እና የሰው ሀብት (HR) ልማት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ የሰጡት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሽብሩ አባዲማ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ የጀመረችው ሁለንተናዊ የዲጂታል ሪፎርም ዋና ዓላማ የህዝብን እንግልት መቀነስ ነው ብለዋል።

ም/ኮሚሽነሩ የሪፎርሙ ዋና ግብ የመንግሥት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ምቹ ማድረግ መሆኑን ገልፀው የባለሙያዎች ኃላፊነት ሰልጣኞች ወደየ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ የተማሩትን ቲዎሪ ብቻ ሳይሆን በተግባር በመተርጎም የለውጥ መሪ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ባህላዊ አሰራርን ማስቀረት በሰው ሀብት መረጃ አያያዝ ዙሪያ የሚታዩ ሰነዶችን የማጥፋት፣ የማጭበርበር እና የቢሮክራሲ መዘግየቶችን በቴክኖሎጂው ሙሉ በሙሉ ማስቀረት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም አሁን ከዚህ የወሰዳችሁትን ስልጠና ወደ ተቋማችሁ ስትመለሱ በተግባር ማሳየት ይኖርባችኋል በማለት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በመዘርጋት በአገልግሎት አሰጣጥ እንግልት የሚደርስበትን ህዝባችንን ልንታደገው እንደሚገባ አሳስበዋል::

በተጨማሪም በፌዴራል ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የኢስሚስ ሥርዓት የመንግሥት ሠራተኞችን መረጃ ከቅጥር እስከ ጡረታ ባለው ሂደት በዲጂታል መንገድ ለመቆጣጠርና ለማደራጀት የተዘረጋ ሲሆን የሚሰጠው ፋይዳ የደመወዝ፣ የበጀትና የሠራተኛ ስምሪት መረጃዎችን ትክክለኛነት ያረጋግጣል እንዲሁም መንግሥት ስለ ሲቪል ሰርቪሱ አጠቃላይ ቁጥርና አቅም ትክክለኛ መረጃ አግኝቶ ፈጣን ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ይረዳል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ስልጠናቸውን ያጠናቀቁት የአይሲቲ እና የሰው ሀብት ባለሙያዎች በቀጣይነት በየተቋማቸው የሚገኙ የሠራተኞችን ዝርዝር መረጃ (Profile) ወደ ሲስተሙ የማስገባት ሥራን በቀጥታ ስራ እንደምጀምሩ ተገልፆዋል::

በመጨረሻም ም/ ኮሚሽነሩ በየመስሪያ ቤቶቻቸው ላሉ ሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ያገኙትን እውቀት በማካፈል የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የስርዓቱን ትግበራ ሂደት በቅርበት ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግበት ታውቋል።
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ

Photos from Federal Civil Service Commission's post 24/05/2026

በሴት ሰራተኞች የአመራርነት ሚና፣ ያላቸው ተሳትፎ እና በሚያጋጥሟቸው ዋና ዋና ተግዳሮቶች ዙሪያ የተዘጋጀ የጥናት ሰነድ ላይ ያተኮረ የማረጋገጫ (Validation) ወርክሾፕ ተካሄደ።
*************
አዲስ አበባ | ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም | ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

በሴት ሰራተኞች የአመራርነት ሚና፣ ያላቸው ተሳትፎ እና በሚያጋጥሟቸው ዋና ዋና ተግዳሮቶች ዙሪያ የተዘጋጀ የጥናት ሰነድ ላይ ያተኮረ የማረጋገጫ አውደ ጥናት ተካሄደ። ጥናቱን ያዘጋጁት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚና እስታስትክስ ፖሊሲና ጥናት ምርምር መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሥራ ክፍሎች ናቸው።

የጥናቱ ዋና ዓላማ እና አስፈላጊነት በአውደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሽብሩ አባዲማ እንደገለጹት፣ የዚህ ጥናት ዋነኛ ግብ ሴት ሰራተኞች ወደ አመራርነት ቦታዎች እንዳይመጡ ወይም በነበራቸው ተሳትፎ ላይ እንቅፋት የሆኑባቸውን ስር የሰደዱ ችግሮችና ተግዳሮቶች በሳይንሳዊ መንገድ መለየት ነው ብለዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም ችግሮችን በግልጽ መለየት ሴቶች በአመራርነት ቦታዎች ላይ ያላቸውን ዝቅተኛ ተሳትፎ በጥናት በተደገፈ መረጃ በትክክል ለማወቅ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ከሪፎርሙ ጋር ማስተሳሰር ከጥናቱ የተገኙትን ውጤቶች (ግኝቶች) በአገሪቱ እየተካሄደ ካለው የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም (የማሻሻያ ስራዎች) ጋር ማጣጣም እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል::

የሴቶችን አቅም ማጎልበት ሴቶች ወደ ፊት መጥተው የራሳቸውን የአመራርነት እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና እንዲወጡ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንድንችል የሚያግዙ ሆኖ እንዳገኙት ገልፀው በጥናቱ በተገኙ ግኝቶች ዙሪያ ወደፊት የሚሰሩ ስራዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ይህንን ጥናት መነሻ በማድረግ የሴቶችን ተሳትፎና አመራር ሰጪነት ወደ ፊት በማምጣት የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የሚያግዙ ስራዎች በስፋት ይሰራሉ ብለዋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አልማዝ መሰለ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፣ ሴቶች በርካታ እና ውስብስብ የሆኑ ችግሮች እንዳሉባቸው አብራርተው እነዚህ ተግዳሮቶች በጊዜ ሂደት እየተፈቱ እና መሻሻሎች እየታዩ መሆናቸውን በተስፋ ሰጪነት ቢመለከቱም፣ ገና ሙሉ በሙሉ ያልተቀረፉ እና ሰፊ ትኩረት የሚሹ ብዙ የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል።

እነዚህ በጥናቱ የተለዩት ችግሮች በዘላቂነት ምላሽ ማግኘት እንዳለባቸው እና ተቋማዊ ድጋፍ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላካች መሆኑን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ አልማዝ መሰለ አክለው ገልፀዋል።

ይህ አውደ ጥናት በሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ውስጥ የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ እና የሴቶችን የአመራር ብቃት ለመጠቀም ትልቅ መደላድል ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል።

በወርክ ሾፑ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ዲጂታላይዜሽን ለሥርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጪነት በሚል ርዕሰ ጉዳይ በአቶ ተሾመ መገርሳ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የኢስሚስ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ቀርቦ ውይይት ተደርጓበታል።

በወርክ ሾፑ በርካታ ሀሳብ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ከመድረኩም ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ

Photos from Federal Civil Service Commission's post 21/05/2026

የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎትን ጎበኙ፡፡
*******************
ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ አዲስ አበባ
በተከበሩ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀላፊ የተመራው የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስራ ሀላፊዎች ቡድን በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን በፌዴራል በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፤ የመሶብ አገልግሎት በተመለከተ በፌዴራል መሶብ አገልግሎት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ከኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም ምክክር አካሂደዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የደረሰበት ደረጃ በክቡር ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌና በክብርት ወ/ሮ አልማዝ መሰለ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ማብራሪያዎች ቀርበዋል፡፡

ሪፎርሙ አሁን የደረሰበት ደረጃ ከቀረበ በኋላ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱን የመሩት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌና የተከበሩ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና ኢ.ኮ.ቴ. ዘርፍ ሀላፊ ናቸው፡፡ የኮሚሽኑ የካውንስል አባላትም በውይይቱ ላይ ታድመዋል፡፡

በመድረኩ ላይ በአሁኑ ወቅት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርሙን ሊመሩና ሊሸከሙ የሚችሉ የተሟሉ የህግ ማእቀፎችና፣ ማስፈጸሚያ ሰትራቴጂዎች የተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባላትም የተሰራውን ስራ አድንቀው በውይይቱ የተነሱና በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት እንደሚቻል ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ

Photos from Federal Civil Service Commission's post 15/05/2026

በሥራ ቦታ ወሲባዊ ብዝበዛና ጥቃትን ለመከላከል በሚያስችለው ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት ተደረገ::
*********************
አዲስ አበባ | ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም
በሥራ ቦታ የሚፈጸሙ ወሲባዊ ብዝበዛና ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችለው ረቂቅ ደንብ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

መድረኩን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፆታዊ ብዝበዛና ጥቃት መከላከል (UN/PSEA) ኔትወርክ በጋራ በመሆን ነው ያዘጋጁት።

የዚህ ረቂቅ ደንብ መዘጋጀት ዋና ዓላማ በሥራ ቦታ ማንኛውም ዓይነት የፆታዊ ብዝበዛና ጥቃት እንዳይፈጸም አስቀድሞ መከላከል ሲሆን፤ ከማንኛውም ዓይነት ትንኮሳ ነፃ የሆነ፣ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ አካባቢን መፍጠር መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

የመድረኩ አዘጋጆች እንደጠቆሙት፤ ይህ ረቂቅ ደንብ በተቋማት ውስጥ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣትና ፆታዊ ጥቃቶችን ለመግታት እንደ ትልቅ መሣሪያ ያገለግላል። በውይይቱም የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡

• የመከላከያ ማዕቀፎችን መዘርጋት፦ ፆታዊ ጥቃቶችና ብዝበዛዎች ሳይከሰቱ አስቀድሞ ለመለየትና ለመከላከል የሚያስችሉ ጠንካራ አሰራሮችንና ሥርዓቶችን በደንቡ ላይ ማካተት።

• ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ አካባቢ መፍጠር፦ ሠራተኞች ያለ ምንም ስጋትና ፍርሃት፣ ክብራቸው ተጠብቆ ሥራቸውን በነፃነት የሚያከናውኑበትን ሙያዊ ባህልና ሥነ-ምግባር ማሳደግ።

• የሥነ-ምግባር ደንቡን ደረጃውን የጠበቀ ማድረግ፦ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ የሥነ-ምግባር መመሪያዎችን ከዓለም አቀፍ የPSEA ስታንዳርዶች ጋር በማጣጣም ወጥ የሆነ ጥበቃ እንዲኖር ማድረግ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተወካዮች በበኩላቸው፤ ውጤታማ የሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት ከጥቃት ነፃ የሆነ የሥራ አካባቢ መኖር ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ይህ ረቂቅ ደንብ ሕጋዊ አስፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ፣ ሥነ-ምግባር የተላበሰና በዜጎች ላይ ያተኮረ የመንግሥት አገልግሎት ለመገንባት የሚደረግ መሠረታዊ እርምጃ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ረቂቅ ደንቡን በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችሉ መመሪያዎችን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዚህም እያንዳንዱ የመንግሥት ሠራተኛ በደንቡ የተካተቱ መብትና ግዴታዎችን ተረድቶ ለተግባራዊነቱ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበት በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ተመላክቷል፡፡
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ

Joint Workshop Strengthens Civil Service Code of Conduct to Ensure Safe Work Environments.
********************
ADDIS ABABA, May 2026 – The Ministry of Women and Social Affairs (MoWSA), the Federal Civil Service Commission (FCSC), and the UN/PSEA Network have concluded a joint workshop in Addis Ababa focused on the development of a specialized draft regulation concerning sexual misconduct.

The primary objective of drafting this new regulation is to proactively prevent all forms of sexual exploitation and abuse within the workplace. By establishing clear legal and ethical boundaries, the initiative aims to create a work environment that is entirely free from harassment and misconduct, ensuring the safety and dignity of all public servants.

During the sessions, organizers emphasized that the draft regulation serves as a critical tool for institutional reform. The discussions centered on several key areas:

• Preventative Frameworks: Implementing robust measures to identify and mitigate risks of sexual misconduct before they occur.

• Creating a Safe Environment: Establishing a professional culture where employees feel secure, respected, and empowered to perform their duties without fear of exploitation.

• Standardizing the Code of Conduct: Aligning the Federal Civil Service guidelines with international PSEA standards to provide a unified approach to workplace safety.

Advancing Institutional Integrity Representatives from MoWSA and the FCSC highlighted that a misconduct-free workplace is a prerequisite for effective public service. They noted that this draft regulation is not merely a legal requirement but a fundamental step toward building a modern, ethical, and citizen-centered government.

The workshop participants agreed on a framework to finalize the draft, which will include comprehensive training and awareness programs across government institutions to ensure every employee understands the protections and responsibilities outlined in the new regulation.

# External Relations and Communication Executive

11/05/2026

የመንግስት ሠራተኞች የባህርያዊ ብቃት ማዕቀፍ በዲጂታል አማራጭ ቀርቦላችኋል፡፡ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ማስፈንጠያውን /ሊንኩን/ ይጫኑ 👇
https://heyzine.com/flip-book/6c70ee2f72.html

Photos from Federal Civil Service Commission's post 04/05/2026

በመንግስት መሥሪያ ቤቶች እየተካሄደ ባለው የሪፎርም እና የብቃት ምዘና ሂደት መሠረት፣ ከደረጃ 1 (Level 1) በታች ያሉ የመንግስት ሰራተኞችን አቅም ለመገንባት የሚያስችል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።
+++++++++++++++++++++++++++++++++
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፡
በመንግስት መሥሪያ ቤቶች እየተካሄደ ባለው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የብቃት ምዘና ሂደት መሠረት ወደ ምዘና ከመግባታቸው በፊት ቅድመ ስልጠና፣ በዌቭ አንድ ወደ ሪፎርሙ ለገቡ ተቋማት ከደረጃ 1 በታች ያሉ የመንግስት ሰራተኞችን አቅም ለመገንባት የሚያስችል የቴክኒክና ሙያ ማሻሻያ ስልጠና አዲስ አበባ በሚገኙ 10 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ገብተው የብቃት ስልጠና የሚያገኙበት መንገድ መመቻቸቱ ተገለጸ፡፡

ይህ ስልጠና የሚሰጠው በአራት ዙር ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የፌዴራል ቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት፣ ጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ፣ አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ጎፋ ኢንዱስትሪያል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ምስራቅ ፖሊ ቴኪኒክ ኮሌጅና ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ለሰራተኞቹ ስልጠናውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ከሁለት እስከ ሶስት ወር በሚቆየው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በፌዴራል ተቋማት የሚገኙ ከ30 በላይ ከሚሆኑ የመንግስት ተቋማት የተውጣጡ በተለያዩ ሙያዎች ላይ እያገለገሉ የሚገኙና ከደረጃ አንድ በታች የሆኑ ሰራተኞች ተለይተው እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጾዋል፡፡

ስልጠናውም በተለያዩ ብቃቶች ዙሪያ የተዘጋጀ ሲሆን ከስልጠናው በኋላ በሚደረገው ምዘና ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ለሰልጣኞች ሰርተፍኬት ይበረከትላቸዋል፡፡

ይህ መሰል ስልጠና መዘጋጀቱ መንግስት የሰራተኛውን አቅም ከማጎልበትና ለብቃት ምዘናው ዝግጁ ከማድረግ አንጻር የተሰራና ከፍተኛ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ቢሮ

Photos from Federal Civil Service Commission's post 01/05/2026

ዓለም አቀፍ የላብአደሮች ቀን በኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ እየተከበረ ነው: 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
+++++
አዲስ አበባ ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (May 1, 2026) የላብአደሮች ቀን ወይም ዓለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

የዕለቱ ታሪክ የሚጀምረው በፈረንጆቹ 1886 በአሜሪካ ቺካጎ ከተማ በወቅቱ ሰራተኞች በቀን እስከ 16 ሰዓት ያለ ዕረፍት እንዲሠሩ በሚገደዱበት ወቅት ነበር።

ይህንንም ግፍ የተቃወሙ የቺካጎ ሰራተኞች "8 ሰዓት ለሥራ፣ 8 ሰዓት ለዕረፍት፣ 8 ሰዓት ለራሳችን" በሚል መሪ ቃል በሄይማርኬት አደባባይ ተቃውሟቸውን በማሰማታቸው ዓለምን የሚቀይር አዲስ የሥራ ሕግ እንዲረቀቅ መሠረት ጣሉ።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ የሰራተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበር ጀመር።

በኢትዮጵያ ላለፉት 51 ዓመታት በየዓመቱ ሚያዚያ 23 (በፈረንጆቹ ግንቦት 1) የኢትዮጵያ ሰራተኞች የሀገር ግንባታ ምሰሶ መሆናቸውን በማስታወስ፣ የሰራተኛ ማኅበራት መብታቸውን የሚያስከብሩበትና ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ታላቅ ዕለት በማድረግ በዓሉ ሲከበር ቆይቷል።

ዛሬ ላይ ይህንን ዕለት ስናከብር ከታሪክ ባለፈ የነገውን ተስፋ እያለምን ነው።
#የውጭ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Bole Road, Kirkos S. City Woreda 09 Around Flamingo Restaurant
Addis Ababa
1082

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 02:30 - 17:30
Wednesday 02:30 - 17:30
Thursday 02:30 - 17:30
Friday 02:30 - 17:30