05/06/2026
ጋዜጣዊ መግለጫ
The Institute of Ethiopian Standards has appointed a National Standard Agent for FDRE.
• Develop Ethiopian standards for products and services through stakeholder engagement
• Develop standards for indigenous products and make them competent internationally.
• Engaged in technical assistance, consultation and training on management system and product standards to facilitate the implementation of standard by various manufacturing and service providing organizations.
05/06/2026
ጋዜጣዊ መግለጫ
05/06/2026
ሰፊ ተቀባይነት ያለው Grant Thornton በግንቦት ወር በኢትዮጵያ ከተከናወኑ አበይት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ካላቸው ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ያስጀመረው የደረጃ ምልክት መለያ ማረጋገጫ (IES verifier) ስለመሆኑ መረጃውን በሊንክዲን ገጹ አጋርቷል።
ዝርዝር መረጃው ከታች ሊንኩን ተጭነው ያገኙታል 👇
May 2026 - Monthly Regulations Update - Grant Thornton | Grant Thornton Advisory Ethiopia May 2026 | Monthly Regulations Update Our monthly publication equips you with the right insights you need to stay ahead of evolving regulations and industry shifts. Review and share with your team to ensure everyone is aligned. Click here - https://bit.ly/4opImVR to subscribe and join our mailing li...
03/06/2026
የጥራት ስራ አመራርን በተገቢው በመተግበር የተቋሙን ከፍታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ፤
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ISO9001:2015 የጥራት ስራ አመራር ስርዓት አተገባበር ላይ እንዲሁም በግዢ አዋጅና መመሪያዎች ላይ ለተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ።
ግንቦት 26/2018ዓ/ም - ኢ.ደ.ኢ.
በስልጠና መርሃ-ግብሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ በሀገሪቷ ለሚገኙ የመንግስት ተቋማት፣ ለአምራች ድርጅቶች፣ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ለሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ስልጠናና ቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጥ በመሆኑ የተቋሙ ሰራተኞችም በዘርፉ በቂ እውቀት ከመጨበጥ ባለፈ ስርዓቱን በተግባር ላይ ማዋል አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የመንግስት የግዢ አዋጅንም በተመለከተ ከእያንዳንዱ ስራችን ጋር ተያያዥነት ያለው መሆኑን በመገንዘብ ስለ አዋጁ በቂ እውቀት በመጨበጥና ስራዎቻችንን በማዘመን የተቋሙን ከፍታ ማረጋገጥ አለብን ሲሉ ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱ የጥራት ሥራ አስኪያጅ (Quality Manager) አቶ አለማየሁ ሰጠኝ የደረጃ ምንነትን በተመለከተና የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት (QMS - ISO9001:2015 ) ጠቀሜታና አተገባበር ላይ ለሰራተኛው የሚጠቅም ሰፊ ስልጠና ተሰጥተዋል።
በመቀጠልም ግዢና ፋይናንስ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ተስፋዬ የግዢ አዋጅ ቁጥር 1333/2016 እና መመሪያ ቁጥር 1073/2017ን በተመለከተ የኢጂፒ ሲስተም የግዢ አፈፃፀም እና መሰል ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ መስጫ ገለፀ አድርገዋል።
28/05/2026
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና ከጃራ ሆልዲንግስ ጋር የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ።
ግንቦት 20/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና ከጃራ ሆልዲንግስ አ.ማ ጋር በአለም አቀፉ - የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት (QMS - ISO 9001:2015) ትግበራን ለማስፈጸም የሚያስችለውን የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ አሰፋ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ ተቋሙ የሚገኝበት የጥራት መንደር አምስት የጥራት መሰረተ-ልማት ተቋማትን በውስጡ የያዘ ነው ያሉ ሲሆን እነዚህ ተቋማት የሀገሪቱን የጥራት ደረጃ ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ በቅንጅትና በተሟላ ሁኔታ እንደሚሰሩም አስገንዝበዋል።
ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ ብቸኛው የደረጃ አዘጋጅ ተቋም መሆኑንም የገለጹ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ ከ12 ሺህ በላይ ደረጃዎችን አዘጋጅቷል። ከእነዚህ መካከልም 500 የሚደርሱት አስገዳጅ ደረጃዎች መሆናቸውን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
የወጡ ደረጃዎችን በተግባር ላይ ማዋል እንዲቻል ለባለድርሻ አካላትና ለአስፈጻሚዎች አቅምን የሚገነቡ ስልጠናዎችን፣ የማማከር አገልግሎትና የቴክኒክ ድጋፎችን በስፋት ይሰጣል ብለዋል።
የኢንዱስትሪዎችንና የምርቶችን የደረጃ አተገባበር ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የደረጃ ምልክቶችን የማስተዳደር ስራዎችን በኃላፊነት ያከናውናል በማለት አቶ ወንድማገኝ ተናግረዋል።
በደረጃዎች አወጣጥና በጥራት ማረጋገጫ ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲሁም ዘመኑን የዋጁ አሰራሮችን ለመዘርጋት የሚያስችሉ ምርምሮችን ያካሂዳል ሲሉም ነው የጠቆሙት።
ሀገሪቱ የጀመረችውን ጽዱና አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ጥረት ለመደገፍ፣ ተቋማት የአካባቢ ብክለትን የሚቀንስ አሰራር እንዲከተሉ የሚያስችል የ"ክሊነር ፕሮዳክሽን" (Cleaner Production) የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ስራዎችን ያከናውናል በማለት ተናግረዋል።
የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት (ISO 9001:2015) የአሰራር ስርዓትን በማዘመን፣ ተቋማት በአለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል በማለት የተናገሩት አቶ ወንድማገኝ ይህንን የአመራር ስርዓት በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር ከፍተኛ ቁርጠኝነት፣ ስርዓቱን አጠናክሮ ማስቀጠልና ዘላቂነቱን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነቱን የተፈራረሙት የሁለቱ ተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው፤ የጥራት አመራር ስርዓት የውስጥ አሰራርን ለማሻሻልና ውጤታማ ተወዳዳሪነትን ለመፍጠር ያለውን ፋይዳ በከፍተኛ ደረጃ እንደተገነዘቡት ገልጸዋል። ይህንን አለም አቀፋዊ አሰራር በላቀ ደረጃ ለመተግበርና ዘላቂነቱን ለማስቀጠልም የተቋማቱ አመራር ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳለው አረጋግጠዋል።
26/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲቲዩት እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሐ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም የአረፋ በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
25/05/2026
የኢትዮጵያየደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከ UNIDO ጋር በመተባበር በማር ምርትና ማምረቻ ላይ የተዘጋጁ ደረጃዎችን የማስተዋወቂያና በደረጃዎች ላይ ይግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ እየተከናወነ ይገኛል።
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም - ኢ.ደ.ኢ.
በምክክር መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ የደረጃ ዝግጅት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ይልማ መንግስቱ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከዩኒዶ ጋር በመተባበርና የባለድርሻ አካላትን የነቃ ተሳትፎ በማረጋገጥ 3 ደረጃዎች ተዘጋጅተው በአሰራሩ መሰረት መጽደቃቸውን አስታውሰው እነዚህ ጀረጃዎች ለሀገራችን ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸውና የሀገራችንን የማር ምርት ተወዳዳሪነትና የዘርፉን እድገት የሚያሳልጡ ይሆናሉ ብለዋል።
ቀደም ባለው ጊዜ የማር ጥራትን በተመለከት ከ14 በላይ የተለያዩና ወጥነት የሌላቸው አስተሳሰቦች ነበሩ ያሉት መሪ ሥራ አስፈጻሚው በተደረገ ሰፊና ቀጣይነት ባለው ምክክር እንደ ሀገር ወጥ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ደረጃዎች መጽደቃቸውን ገልጸዋል።
የUNIDO ተወካይና የማርና የማር ውጤቶች ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ሰለሞን መንገሻ በበኩላቸው
UNIDO መንግስት በሚሰራቸው ስራዎችና ጉድለት ባለባቸው ቦታዎች በመግባት የማገዝና በትብብር ስራዎችን የመስራት አካሄድን ይከተላል ያሉ ሲሆን ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋርም በማር ዘርፍ በትብብር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም የማር ምርትን ማዘመን የሚያስችል በተለይ ዘመናዊ የንብ ቀፎ ፣ የፓኬጂንግ ስራዎችና የማነቢያ መሳሪያዎች ደረጃዎች እንዲዘጋጁ በማገዝ ለውጤት በቅቷል ያሉት አቶ ሰለሞን በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ ወጥነት ያለው የቀፎ አጠቃቀም እንዲኖር አስገዳጅ የቀፎ ደረጃ መጽደቁ ለዘርፉ ትልቅ እድል ነው ብለዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረኩ ለቀጣይ ሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ሲሆን የክልሎች የንብ ዘርፍ ባለሙያዎች፣ ተቆጣጣሪ አካላት ፣ የንብ አንቢዎች እና ማህበራት ተሳታፊ ሆነዋል።
የምክክር መድረኩ ደረጃዎቹ በተገቢው ግንዛቤ ተይዞባቸው በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚተገበሩበት እድልን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
25/05/2026
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ኢዲሱ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ (ጥራት አዳራሽ) በምስል፤
24/05/2026
ዶ/ር መሰረት በቀለ - የኢትዮጵያየደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በኢንስቲትዩቱ የዲጅታላይዜሽንና የሪኖቬሽን ስራዎች ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ በተቋማዊ የለውጥ ስራዎች በትጋት ላገለገሉ እንዲሁም መላ ሰራተኞችን ያበረታቱ ሲሆን ምስጋናም አቅርበዋል።
ተቋሙ የተጣለበትን ትልቅ ሀገራዊ ሀላፊነት በብቃት እንዲወጣ የጀመርነውን ውጤታማ ስራ አጠናክረን እንቀጥል ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች አዲስ የተሰሩ የዲጅታላይዜሽንና የሪኖቬሽን ስራዎችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
24/05/2026
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩ አዲሱ ደረጃውን የጠበቀ ሬስቶራንት በምስል፤
23/05/2026
ንዑስ ኮሚቴዎች እስካሁን ያከናወኗቸው የሪፎርም ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ፤
ግንቦት 15/2018 ዓ.ም ኢ.ደ.ኢ.
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ዘርፍ ሪፎርም ዐቢይ ኮሚቴ፣ በሪፎርሙ ንዑስ ኮሚቴዎች የተከናወኑ የሥራ አፈጻጸሞችን በዛሬው ዕለት ገምግሟል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በግምገማ መድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የንግድ ዘርፍ ሪፎርሙ የሕግና የመመሪያ ማሻሻያዎችን ከማድረግ ባሻገር፣ ንግድን በማሳለጥ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት አሠራሩን በቴክኖሎጂ እና በግልጽነት ላይ እንዲመሠረት በማድረግ፣ ጠንካራ ተቋማትንና ትውልድ ተሻጋሪ ሥርዓትን የመገንባት ሂደት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በግምገማውም፣ ንዑስ ኮሚቴዎች እስካሁን ያከናወኗቸው ሥራዎች አበረታች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ዐቢይ ኮሚቴው ጥብቅ አቅጣጫ አስቀምጧል።
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 17:30 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |