Arada subcity worada 8 communication

Arada subcity worada 8 communication

Share

ኢትዮጵያዊነት we serve the government of Ethiopia PR for the purpose of Addise Abeba press secretary

Photos from Arada subcity worada 8 communication's post 06/06/2026

ከአምራች ወደ ሸማች በቀጥታ – ለሸማቹ ማህበረሰብ ጠቀሜታ!"

ግንቦት 29/2018 ወረዳ 8 ኮሚኒኬሽን

የአራዳ ወረዳ 8 አስተዳደር የቅዳሜና ዕሁድ ገበያ አማራጭ በማመቻቸት የሸማቹ ማህበረሰብ የኑሮ ጫና ማቃለያ ሆኖ ቀጥሏል

የወረዳው ንግድ ጽ/ቤት ከህብረት ስራ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመተባበር በሴቶች አደባባይ የጅምላ አምራቾች ከ ሸማች በቀጥታ የሚገበያዩበት
የቅዳሜና ዕሁድ ገበያ በማመቻቸት ለነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በማቅረብ የኑሮ ጫናን ለማቃለል እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑ ተገለጸ።

በገበያው ላይ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ : ሌሎች የፍጆታ እና የኢንድስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑ ተጠቁሟል።

በሳምንቱ መጨረሻ በሚዘጋጀው ይህ ገበያ ምርቶቻቸውን ለሸማቹ በቀጥታ በማድረስ ኑሮ በማረጋጋት እና ከአላስፈላጊ ወጪ እያዳነ ያለ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሸማቹ ማህበረሰብ ተናግረዋል።

ገበያው ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት እና የምርት ተደራሽነት ከማሳደግ ባለፈ ለሸማቾች የዋጋ ንረትን የሚቋቋም ስለሆነ ጠቃሚ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተጠቁሟል።

06/06/2026
Photos from Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን's post 05/06/2026
Photos from Arada subcity worada 8 communication's post 05/06/2026

የዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ዘመናዊ የፎረንሲክ (ዲ ኤን ኤ) እና የሥነ ምረዛ ምርመራ ልሕቀት ማዕከል ምረቃ ሥነ ሥርዓት በምስል

05/06/2026

ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማለዳ ላይ፤ የመጀመሪያው የወገግታ ጭላንጭል በከፍታማዎቹ የኢትዮጵያ ተራሮች ላይ ፈንጥቆ ጨለማውን ሳይቀድ በፊት ኢትዮጵያውያን ረጃጅም ሰልፍ ተሰልፈዋል። በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ፣ በባሕር ዳር እንዲሁም ስማቸው በዓለም አቀፍ የዜና ጋዜጣዎች ላይ ፈጽሞ ሊወጣ በማይችሉ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች፤ ወሳኝ ተግባር ለመፈጸም በሰልፍ ቆሙ። ድምፅ ሰጡ! ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሃምሳ አራት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበው ነበር። ይህ ቁጥር ከአንዳንድ ሀገሮች አጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር በላይ ነው። ይህ ምርጫ እውነተኛ ስለመሆኑ ጥያቄ ለሚያነሣ ለማንኛውም አካል ግልጽ እና የማያሻማ ምላሽ ሰጥቷል!

‎የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት
‎የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ52,000 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል ከ50,188 በላይ የሚሆኑት በሰዓቱ ተከፍተው ቀኑን ሙሉ መራጮችን ሲያስተናግዱ እንደነበር አረጋግጧል። ከ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ ከ10,438 በላይ ዕጩዎች እና 80 የግል እጩዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ለማሸነፍ ተወዳድረዋል። ይህ በማንኛውም ሊለካ በሚችል መሥፈርት በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ እና በውሳኔ አሰጣጥም ሆነ በአስተዳደራዊ ረገድ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረገ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ የታየበት ኩነት ነበር።

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫውን “ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በሰፊው በሚደግፍ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ ውስጥ የተካሄደ” ሲል ገምግሞታል። በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ክብርት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት፥ በታዘቡባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የምርጫ ሳጥኖች በትክክል የታሸጉ መሆናቸውን፣ የፓርቲ ወኪሎች በሂደቱ በሙሉ መገኘታቸውን እንዲሁም ምርጫው አስደናቂ ተቋማዊ፣ አስተዳደራዊና የቴክኖሎጂ ዕድገትን ያሳየ መሆኑን አረጋግጧል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ይሄንን ምርጫ «የበርካታ አዳዲስ ምዕራፎች ምርጫ» ሲል ሰይሞታል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በድምፅ መስጠት ሂደት ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳልተመለከተ አረጋግጧል። የሲቪክ ማኅበረሰብ ታዛቢዎች ጥምረት በምርጫ ቦርድ እውቅና ከተሰጣቸው 55 ድርጅቶች 65,299 የታዛቢዎችን በመላ ሀገሪቱ ያሠማራ ሲሆን፥ 99 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያለምንም ዕንቅፋት የመታዘብ ዕድል ማግኘቱን አረጋግጧል። እነዚህ ተዓማኒነት ያላቸው ሀገራዊ እና አኅጉራዊ ተቋማት ያደረጓቸው ግምገማዎችና የሰጧቸው እውነተኛ ፍርዶች ናቸው። እነዚህ ለአፍሪካ ጥላቻ ካላቸው ወይም የአፍሪካን ዴሞክራሲ በውጫዊ መሥፈርቶች ከሚለኩ ተቋማት የተደመጡ ድምፆች አይደሉም።

‎አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተንታኞች ይሄንን ምርጫ እንደ ንግሥና በዓል አድርገው ያቆሸሹት ሲሆን ውጤቱም አስቀድሞ የተወሰነ ድራማ እንደነበር አድርገው ሊያቀርቡት ሞክረዋል። እነዚህን መግለጫዎች ከእውነታው ፈጽሞ የራቁ፣ በጥናትና ትንተና ላይ ያልተመሰረቱ እንዲሁም ነፃና የታሰበበት ዴሞክራሲያዊ ምርጫቸውን በኩራት ላደረጉ በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ክብር የማይሰጡ በመሆናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሙሉ በሙሉ የማይቀበላቸው መሆኑን ያረጋግጣል። አስቀድሞ የተወሰነ ውጤት ቢኖር ኖሮ፤ ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ገለልተኛ ታዛቢዎችን፣

Photos from Arada subcity worada 8 communication's post 05/06/2026

አዲስ አበባን የአፍሪካ የከተሞች ልማት ተምሳሌት ያደረገው የ24/7 የመፈጸም አቅም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም "የዛሬ አምስት ዓመት አዲስ አበባ በአፍሪካ ውስጥ እጅግ ውብ ከሚባሉ ከተሞች አንዷ ትሆናለች" በማለት አቅጣጫ ያስቀመጡት ከተማዋ ስሟን የምትመጥን እንድትሆን በማሰብ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ዛሬ በከተማዋ ተግባራዊ በሆኑት መዋቅራዊ እና ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች አማካኝነት በተጨባጭ እውን እየሆነ ይገኛል።

ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ወደ መሬት አውርዶ በተግባር ለመተርጎም ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሳየው የአፈጻጸም ብቃት ሁነኛ ሚና ተጫውቷል።

በከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራው የከተማዋ አመራር ቁርጠኝነት የለውጡ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሞተር ሆኖ አዲስ አበባን እንደ ስሟ የፈካች አበባ አድርጓታል።

አስተዳደሩ ያሰፈነው የ24/7 (ቀን ከሌሊት) የሥራ ባህል ቀደም ሲል ለዘመናት ስር ሰድዶ የነበረውን ዝግተኛ የመንግሥት ቢሮክራሲ በመስበር፣ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ እና በከፍተኛ ጥራት የማጠናቀቅ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል።

ይህ የሥራ ባህል ለውጥ ከተማዋን የማዘመን ተግባር ብቻ ሳይሆን፣ የከተማዋን ኢኮኖሚ ሌት ተቀን በማንቀሳቀስ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ የልማት ኃይል ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

የአመራሩ በቢሮ ከመቀመጥ ይልቅ በምሽት የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ በአካል በመገኘት እና በመከታተል፣ በበዓላት ቀናት ከኮሪደር ልማት ሠራተኞች ጋር ማዕድ በመጋራት፣ እንዲሁም ሠራተኛውን በቅርበት በማበረታታት መሪነትን በተግባር አሳይተዋል።

ይህ ዓይነቱ ያልተቋረጠ የአመራር ክትትል እና አብሮነት የሥራ ባህልን በመቀየር ረገድ ትልቅ ሥነ-ልቦናዊ ለውጥ አምጥቷል።

የአስተዳደሩ ትጋት ከተማዋ ላይ ያመጣቸው ተጨባጭ ለውጦች ያፈሩት ፍሬ ዛሬ በገሃድ ይታያል፤ በርካቶችንም ተጠቃሚ አድርገዋል።

የከተማዋን ገጽታ ሙሉ ለሙሉ የቀየሩት ሰፋፊ የኮሪደር ልማቶች፣ ግዙፉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር፣ የወንዝ ዳር ልማቶች፣ ማራኪ የሆኑት የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎች እና ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ ልማቶች የአዲስ አበባን ትክክለኛ ውበት አጉልተው አውጥተውታል።

አዲስ አበባን የኪነ ጥበብ እና ፍልስፍና ማዕከል ለማድረግም ዘመናዊ የሲኒማ ኮምፕሌክሶች እና አምፊ ቴአትሮች በስፋት ተሠርተው ለአገልግሎት በቅተዋል።

አዲስ አበባ መጪውን ጊዜ ስታስብ ትላንቷንም ሳትረሳ ኢትዮጵያን ላገለገሉት ልጆቿ መታሰቢያ በማቆም ለቅርሶቿ ጥበቃ አድርጋለች።

የወንዝ ዳር ልማት፣ ትላንት የበሽታ እና የወንጀል ምንጮች የነበሩ ወንዞችን በማደስ ለከተማዋ አዲስ አስትንፋስ ሰጥቷል።

እነዚህ ተከታታይ ስኬቶች አዲስ አበባ ስሟን የሚመጥን ከተማ እንድትሆን ከማድረጋቸውም ባሻገር፣ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫነቷን እና የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በሚመጥን መልኩ የዓለምን ቀልብ በከፍተኛ ሁኔታ እንድትስብ አድርጓታል።

ዛሬ ላይ ቱሪስቶችም ሆኑ ዓለም አቀፍ ልዑካን በከተማዋ ንጽህና እና ፈጣን ዕድገት መገረማቸውን በተደጋጋሚ ከመግለጽ አልፈው በአካል መጥተው ለዓለም አረጋግጠዋል።

መዲናችንን የጎበኙ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችም ከተማዋ ከየትኛውም የዓለማችን ከተማ ጋር የምትወዳደር ውብ ከተማ እንደሆነች አረጋግጠዋል።

ከዚህም በላይ የከተማ አስተዳደሩ የጀመረው የኮሪደር ልማት እና የመልሶ ማልማት ሥራ፣ ማንንም ወደ ኋላ የማይተው ሰው-ተኮር መርሕን የተከተለ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስመዘገበው ይህ

Photos from Arada subcity worada 8 communication's post 05/06/2026

የልማት ስራዎች የአንድ ወቅት ብቻ አይደሉም፥ ዘመን ተሻጋሪ እንጂ!

በተለያዩ የልማት ስራዎች ፈር ቀዳጅ የሆነችው አዲስ አበባ፣ ከ7ኛው ሀገራዊ መርጫ ማግስት በተለያዩ የልማት ስራዎች መገለጥዋን ቀጥላለች፡፡

የልማት ስራዎች የአንድ ወቅት ብቻ አለመሆናቸውን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከዚህ ቀደም በእንግልት እና በኃላ ቀር አሰራር ህዝብ ሲማረርባቸው የነበሩ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይስተዋል የነበረውን ችግር በማስቀረት፣ በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ቀልጣፋና የተቀናጀ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ዘመናዊ ተቋማት እየተገነቡ ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

ከዚህም የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዘንድ ለዓመታት የቆየውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ታላቅ ስራ ሲሆን፤ በተለይም በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተደራሽ መሆኑ ነዋሪዎች ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚያገኟቸውን አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተቀናጅና በተናበበ እንዲሁም በሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲያገኙ አድርጓል።

ቀደም ሲል ቀናትና ሳምንታት ይወስዱ የነበሩ ጉዳዮች፥ ዛሬ በመሶብ የአንድ ማዕከል በደቂቃዎች ውስጥ እልባት ማግኘት ችለዋል፡፡ ከሁሉም በላይ አገልግሎቱ ወደ ነዋሪዎች መቅረቡ ነዋሪዎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ባሉበት ቦታ በተንቀሳቃሽ መሶብ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።

እነዚህ ማዕከላት በውስጣቸው ከንግድ ፈቃድ ምዝገባ ጀምሮ እስከ መታወቂያና የውልና ማስረጃ አገልግሎቶች ድረስ እጅግ በርካታ ፋይዳ ያላቸውን ዘርፎች አካትተዋል። በተለይም ለአገልግሎት ፈላጊዎች ምቹ የሆኑ የጥበቃ ስፍራዎች፣ ዲጂታል የሰልፍ መቆጣጠሪያዎች፣ የህፃና ማቆያና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ መሰረት ልማቶችን በመያዛቸው ተገልጋዩ የጊዜ ብክነት እና እንግልት እንዳይገጥመው ታድገዋል፡፡

በአዲስ አበባ የተጀመረውና በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ የሆነው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቁጥሩን ወደ ስምንት ከፍ በማድረግ እንዲሁም በተንቀሳቃሽ አውቶብስ አገልግሎቱን በማስፉት ነዋሪው እፎይታን እንዲያገኘ ማድረግ ተቸሏል።

የልማት ስራዎች የአንድ ወቅት ብቻ አይደሉም፥ ዘመን ተሻጋሪ እንጂ፥ ይቀጥላል!

05/06/2026

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማግስት መደበኛ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በከፍተኛ ተነሳሽነት እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡

አራዳ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 28/2018 ዓ.ም

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከምርጫ ማግስት ጀምሮ ሙሉ ትኩረቱን በልማት ስራዎች ላይ በማድረግ፣ አገልግሎት አሰጣን በማሻሻልና መልካም አስተዳደርን በማስፈን እንዲሁም እየተከናወኑ ያሉ ካፒታል ፕሮጀክቶችን በፍጥነት አጠናቆ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በከፍተኛ ተነሳሽነት እየሰራ ይገኛል፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ ዑመር እንደገለፁት ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ አስታውሰው የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ለመመለስ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ ነው በማለት የተከናወኑ ካፒታል ፕሮጀክቶችንም በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ተዘጋጅቷል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ነዋሪው ከክፍለ ከተማው ተቋማት የሚያገኘው አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ግልፅና እርካታውን ባረጋገጠ መልኩ እንዲተገበር በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለው ነዋሪዎች በልማት ስራዎችና በሰላምና ፀጥታው ዘርፍ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ ለክፍለ ከተማው ትልቅ አቅም በመሆኑ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

የአስተዳደሩ ተቋማት ከምርጫው ማግስት ጀምሮ ያሳዩትን የስራ ተነሳሽነት በመቀጠል ውጤታማ ስራ መስራታቸውን ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

https://linktr.ee/Arada_communication

Photos from Arada subcity worada 8 communication's post 05/06/2026

በጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት 3 የመሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከላት ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናሉ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በይፋ የመረቁት የመሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከል ነዋሪዎችን ለዓመታት ሲያማርር ከኖረው የአገልግሎት አሰጣጥ እንግልትና ከብልሹ አሠራር የሚታደግ መሆኑን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች በማዕከሉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የኮልፌ ነዋሪዎችን ከአገልግሎት አሰጣጥ እንግልትና ከሙስና የሚታደገው የመሶብ ዲጂታል ማዕከል በይፋ ሥራ መጀመሩን አብስረዋል።

ይህ ዘመናዊ የዲጂታል ማዕከል ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ፣ የረጅም ጊዜ የሀገር ግንባታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተገነባ መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባዋ፤ ነዋሪዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚደርስባቸውን ውጣ ውረድ በማስቀረት፣ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ሳያባክኑ የፈለጉትን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።

በከተማዋ በርካታ የልማት ሥራዎች ቢሠሩም፣ አሁንም ድረስ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚታዩትን እንደ ፈጣን አገልግሎት አለመስጠት፣ እንግልት እና የእጅ መንሻ (ጉቦ) ጥያቄዎችን ከመዋቅሩ ውስጥ መንጭቆ ለማውጣት ማዕከሉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ነዋሪዎች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ያለምንም ጉቦ ማግኘት የሚችሉበትን አስተማማኝ ሥርዓት ይፈጥራል ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የተጀመረው ይህ የዲጂታላይዜሽን ንቅናቄ በዚህ ብቻ እንደማያበቃ የገለጹት ከንቲባ አዳነች ፣ ሦስት ተመሳሳይ የዲጂታል ማዕከላት የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት፣ ተጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።

ሕዝቡ በምርጫው ወቅት ያሳየው ታላቅ ፅናትና ፍላጎት፤ ሰላም፣ ልማት እና አጠቃላይ ሀገራዊ አካሄዶች በሕጋዊ መንገድ ብቻ እንዲጓዙ መሻቱን በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የዚህን ፅኑ ሕዝብ ጥያቄዎችና ፍላጎቶች በሚመጥን መልኩ ምላሽ መስጠት፣ ሥልጣን ከሚይዘው አካል የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ያለምንም የውጭ ተፅዕኖ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በራሷ ሕዝቦች፣ በሰላማዊና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ማካሄዷ እና በምርጫው ማግስትም እንደነዚህ ያሉ ተጨባጭ ፍሬዎችን ማስመዝገቧ፣ የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ ወደ ከፍታ እንደሚመራ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ማሳያ መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Addis Ababa