መከኀየ ወ

መከኀየ ወ

Share

ለህብረተሰቡ የእንስሳት ዝሪያን በማሻሸል ፣የተሻሻለ መኖ ል?

Photos from መከኀየ ወ's post 15/10/2022

የስልጤ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ የ2014 ዓ.ም የተግባር አፈፃፀም መነሻ በማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የምሳ ፕሮግራምና አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍል የዱቄት ድጋፍ ማድረጉን ገለፀ፡፡
የመማሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሸምሴ ኑሪ እንደገለፁት በ2014 ዓ ም በነበረው ሃገራዊ ነበራዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በዞኑ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መደረጉን ገልፀው በተለይ በወራቤ ከተማ አስተዳደር የተጀመረውን የቅዳሜ ገበያ በማስፋፋት ረገድ ጥሩ የሚባሉ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል ፡፡ አያይዘውም የንግድ እንቅስቃሴ ለማዘመን የተለያዩ ስራዎች በመስራት ሁሉም መዋቅራችን ከነ ጉድለቱም ቢሆን የonlione አገልግሎት ማደረስ ተችሏል ብለዋል ፡፡
ይህንን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በመገምገም በክልል በቢሮ ደረጃ የሶስተኛ ደረጃ እውቅና በተመሳሳይ በዞን ምክር ቤት በኢኮኖሚ ዘርፍ የሁለተኛ ደረጃ እውቅና ማግኘት ተችሏል በመሆኑ ይህ እውቅና የሚያኩራራ ሳይሆን ተጨማሪ የህዝብ አደራን ስለሚጥል በቀጣይ ተጠናክሮ ጉድለትን በማረም መስራት ይጠበቅብናል በማለት አሳስበዋል ፡፡
ይህንን በማስመልከት መምሪያው በዛሬ ዕለት ከአቅመ ደካሞችና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የምሳ ግብዣ ያደረገ ሲሆን ለ16 አቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣና በአራት ዱቄት ፋብሪካዎች እስፖንሰር ፈድሉ ፣ ሲሃም ፣ አዳዘርና ሀጂ ወርቄ ዱቄት ፋብሪካዎች የሰጡንን ዱቄት ለየ አንዳንዳቸው 25 ኪ.ግ ዱቄት ስጦታ ማድረግ ተችሏል በማለት የገለፁት ኃ
ኃላፊው ከፕሮግራሙ በማያያዝ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በመሆን የወራቤ ከተማ አስተዳደር የቅዳሜ ገበያና በመምሪያ ጊቢ ላይ እለማ ያለ የከተማ ግብር /ምግቤን ከጓሮዬ/ከስራ ገበታዬ/ የጉብኝቱ አካል እንደነበረ ገልፀዋል ፡፡
አያይዘውም በፕሮግራሙ በመገኘት የምሳ ግብዣና ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት በሰጡት አስተያየት ያለነበትን የኑሮ ደረጃ በመረዳት በክብርና በእንክብካቤ የምሳና የዱቄት ድጋፍ ስላደረጋቹልን አላህ ኸይር ጀዛ ይክፈላችሁ በማለት ዱኣ አድርጓል ፡፡
በመጨረሻምፕሮግራም እንዲሳካ ላደረጉ አካላት በሙሉ በመምሪያው ስም ከልብ አመስግነዋል ፡፡
# #መረጃውም ከስልጤ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ

Photos from መከኀየ ወ's post 07/10/2022

የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው የተለያዩ የፋብሪካ ምርቶችን ማስወገዱን ስራውን የሳንኩራ ወረዳ ን/ገ/ል/ጽ/ቤት አስታወቀ።
~
የሳንኩራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በወረዳው የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ያለፈባቸዉ የተለያዩ የፋብሪካ ምርቶችን በመሰብሰብ እንዲወገዱ ማድረጉን ገለፀ።

ጽ/ቤቱ በረ/ማዞሪያ እና በበርጮ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮችና የንግድ ድርጅቶች ላይ ባደረገው የውጭ ኢንስፔክሽን ስራ የህብረተሰቡን ጤናና ደህንነት ሊጎዱ የሚችሉ ጊዜ ያለፈባቸው የፋብሪካ ምርቶችንና የጥራት ደረጃ እውቅና የሌላቸው የተለያዩ የለስላሳ መጠጦችን ፣ የዱቄት ሳሙና ፣ ብስኩቶች፣ የፀጉር ቅባቶች፣ ካሜራ … ወዘተ ምርቶችን አግኝቶ ከወረዳው ህገ–ወጥ ንግድ ተቆጣጣሪ አስተግባሪ ግብረኃይል በጋራ በመሆን ከንግድ ድርጅቶቹ እንዲወገዱ ያደረገ ሲሆን ምርቶቹ የተገኙባቸው የንግድ ድርጅቶችን በቃል የማስጠንቀቅ ስራም መሰራቱን ጽ/ቤቱ አስታወቋል ።

ጽ/ቤቱ በንግድ ድርጅቶቹ ላይ የሚያደርገውን የክትትልና ቁጥጥር ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለፀ ሲሆን ነጋዴዎችና ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍልም የፋብሪካ ምርቶችን ሲገዛ በተለይ የህፃናት አልሚ ምግብና መጠጦችን የምርት ጊዜያቸውን የማረጋገጥ ልምዳቸዉን ሊያዳብሩ እንደሚገባም ተመላክቷል።

06/10/2022

መንግስት በየወቅቱ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ በሸቀጦች እና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል
=======================================

አዲስ አበባ 24/1/2015 (ንቀትሚ) በየትኛውም ሃገር እንደ ስትራቴጂካዊ ምርቶች ከሚቆጠሩ የምርት ዓይነቶች ውስጥ ነዳጅ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ነው፡፡ መንግስትም ይህንን ምርት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ መድቦ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ነዳጅ አምራች ሃገራት እንኳን በማይደፍሩት ዋጋ በሃገራችን ሲሸጥ ነበር፡፡

ታዲያ የዚህ አሰራር ተግባራዊ መደረግ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከመደጎም አንጻር የጎላ ሚና ቢኖረውም በአሁኑ ወቅት መንግስት ከሚያከናውናቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ጋር ተደማምሮ መንግስት ኪሳራ ውስጥ እንዲገባ አስገድዶታል፡፡

ለውጡን ተክተሎ ባለፉት ዓመታት በሃገራችን በርካታ የሪፎርም ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ሪፎርሞች ውስጥም የታለመለት የነዳጅ ድጎማ የሪፎርም ስርዓት አንዱ ነው፡፡ ይህ ሪፍርም በመላ ሃገሪቱ ከሃምሌ 01-2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

የዚህን አሰራር ተግባራዊ መደረግ ተከትሎ አንዳንድ የራሳቸውን ተጠቃሚነት ብቻ ለማረጋገጥ እቅድ ያላቸው ስግብግብ የህብረተሰብ ክፍሎች መሠረታዊ ሸቀጦች እና ምስል ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሃላፊነት የጎደለው ህገ-ወጥ ድርጊት አብዛኛው የሃገሪቱ የህብረተሰብ ክፍላችን በተለይም በዝቅተኛው የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚኖሩ ወገኖቻችን ካሁን ቀደም ከሚያገኙት ዕለታዊ ገቢ በባሰ መልኩ የእለት ፍጆታቸውን መሸፈን ወደ ማይችሉበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እያስገደዳቸው ይገኛል፡፡
ከዚህም በተጓዳኝ ይህ ህገ-ወጥ ድርጊት ትልቅ የኦኮኖሚ አሻጥር በመሆኑ ህዝቡ በሚመራው መንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ ስለሚያደርገው ድርጊቱ በምንም መልኩ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በዚህ የኢኮኖሚ አሻጥር ውስጥ ተሳትፎ የሆኑ አካላት ከዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት መታቀብ ይኖርባቸዋል፡፡

የንግዱን ሴክተር እንዲመራ ሃገራዊ ሃላፊነት የተሰጠው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በህገ-ወጥ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣይም ከሚመለከታቸው የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መሰል እርምጃዎችን የሚወስድ ይሆናል፡፡ ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍልም እንደነዚህ ያሉ ህገ ወጥ አካላትን ሲያስተውል ለሚመለከታቸው የንግድ ቢሮ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡የመረጃው ምንጭ etrade.gov.et

etrade.gov

16/09/2022

"ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው የሲሚንቶ ምርት ለግብይት ይዞ መገኘት አይችልም" የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ማንኛውም የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ የሲሚንቶ ሽያጭ መፈፀም ያለበት ለተፈቀደላቸው አካላት ብቻ ነው ሲል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳስቧል።

የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ በመውሰድ ለየክልልና ከተሞች እንዲያቀርቡ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ ማናቸውም ሰው የሲሚንቶ ምርት ለግብይት ይዞ መገኘት እንደማይችልም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህን ያስታወቀው የሲሚንቶ ስርጭትና ዝውውርን ለመወሰን ባወጣው የሕዝብ ማስታወቂያ ነው።

የማስታወቂያው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የሲሚንቶ ስርጭትና ዝውውርን ለመወሰን የወጣ የሕዝብ ማስታወቂያ !

ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በንግድ ውድድርና ሸማቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 24 (1) እና 46 (2) በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ እያደገ በመጣው የግንባታ ዘርፍ እና በሌሎችም ልዩ ልዩ ምክንያቶች በሲሚንቶ ምርት አቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ በመምጣቱ በገበያ ላይ የሲሚንቶ ምርት እጥረት ተከስቷል፡፡

ስለሆነም ለሕዝብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ሜጋ የግንባታ ፕሮጀክቶች እንዳይጓተቱና የሲሚንቶ ስርጭቱም ፍትሃዊ እንዲሆን ለማድረግ ሲባል ከዚህ በታች የተመለከተው የሕዝብ ማስታወቂያ ወጥቷል፡፡

1. ማንኛውም የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት ለተፈቀደላቸው አካላት ብቻ የሲሚንቶ ሽያጭ መፈፀም አለበት፤

2. በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት በፌደራልም ወይም በክልል ወይም ከተማ አስተዳደር የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ በመውሰድ ለየክልልና ከተሞች እንዲያቀርቡ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ ማናቸውም ሰው የሲሚንቶ ምርት ለግብይት ይዞ መገኘት አይችልም፡፡

3. ለአንድ ጊዜ ለግል ወይም ለቤተሰብ ፍጆታ የተፈቀደ ከፍተኛው የሲሚንቶ ምርት መጠን 15 ኩንታል ነው፤

4. በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲሚንቶ እንዲያከፋፍሉ የተፈቀደላቸው አካላት ወይም በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተፈቀደላቸው ተቋራጮች የገዙትን የሲሚንቶ ምርት ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለሽያጭ ማቅረብ፣ ለመሸጥ መሞከር ወይም ከተፈቀደለት መስመር ውጪ በማንኛውም ማጓጓዣ ጭኖ መገኘት፣ ማጓጓዝ፣ በንግድ መደብር ወይም በማናቸውም ቦታ አከማችቶ መገኘት የተከለከለ ነው፤

5. ማንኛውም ሰው ከዚህ በላይ የተገለጸውን የሕዝብ ማስታወቂያ ተላልፎ ከተገኘ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 43 እና አግባብ ባላቸው ሌሎች ህጎች መሠረት በአስተዳደራዊ እና በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል፤

6. ይህ የህዝብ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሌላ የህዝብ ማስታወቂያ እስከሚሻር ድረስ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼

14/09/2022

ለ3 ወራት የሚቆይ የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ተወሰነ
================================
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4/2015 (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሰኔ/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገውን የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ አፈጻጸም ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በተደረገው ክትትልም ከመመሪያው ውጪ የሚሰሩ ህገ-ወጦች መኖራቸው የተረጋገጠ ሲሆን ይህንን ህገ-ወጥነት ለማስቀረትና የመመሪያውን ተግባራዊነት ለማጠናከር ሲሚንቶ በየፋብሪካዎች የሚሸጥበት ዋጋ ተመን ተወስኗል፡፡
ሲሚንቶ በየፋብሪካዎች እንዲሸጥበት የተወሰነው ዋጋ ለሦስት ወራት የሚቆይ ሲሆን ሚኒስቴር መ/ቤቱ የፋብሪካዎችን የመሸጫ ዋጋ እንዲሁም በተዋረድ ያለውን የግብይት ሰንሰለት በመገምገም የተረጋጋ፣ ፍትሐዊ እና ወጥ የሆነ የግብይት ስርዓት እንዲኖር ለሚያስችሉ ተግባራትን ከዘርፉ ተዋናዮች ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ገልጸዋል፡፡
እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ለማስተካከል ፋብሪካዎች የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተጠይቀው ያወጡት ዋጋ እጅግ የተጋነነ በመሆኑ ነው በዘርፉ ያለውን የምርት ሂደት ጥናት የሚያደርግ ቡድን በማቋቋም አዲስ የዋጋ ተመን ይፋ ያደረገው፡፡
በዚህ መሰረት ሲሚንቶ ከፋብሪካ የሚወጣበት አዲሱ የዋጋ ተመን ዝቅተኛው 510 ብር ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 683 ብር ከ44 ሳንቲም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ አሁን ላይ የሲሚንቶ ምርት እጥረት በመኖሩ ለመንግስታዊ ስራዎች ቅድሚያ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም ማረጋገጫ በማምጣት ከፋብሪካዎች በቀጥታ ምርት የሚገዙበት መንገድ ተመቻችቷል ብለዋል፡፡
የግል ተጠቃሚዎችን በተመለከተም የሁሉም ከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ፍላጎት ምን ያህል እንደሆነ ስለሚታወቅ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና በተደራጁ ማህበራት በኩል እንደሚያገኙ አስረድተዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ይሁንታ ካገኙ አካላት ውጪ ሲሚንቶ ይዞ የሚገኝና በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ግብይቶች ህገወጥ በመሆናቸው ተቋሙ ማስታወቂያ ካስነገረበት ቀን ጀምሮ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።
በከተሞች ላይ የሚኖረው ሽያጭም የትራንስፖርት፣ የጫኝና አውራጅ እንዲሁም የመጋዘን ኪራይን ታሳቢ በማድረግ የሚሸጥ ይሆናል
የመረጃው ምንጭ etrade.gov.et

etrade.gov

26/08/2022

በስኳርና መሰል ምርቶች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ የተቀናጀ እርምጃ በመውሰድ ገበያውን የማረጋጋት ስራ እንደሚሰራ የሳንኩራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
==============
በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በእጅጉ እየተስፋፋ ያለውን የስኳር፣ የፍራፍሬ(ሙዝ በኪ/ግ) እና ሌሎችም መሰል ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪና አሻጥር በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ ስለመሆኑ አስታውቋል።

ተቋሙ በዛሬው እለትም ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ ያሉ የጅምላና ችርቻሮ የንግድ ድርጅቶችን ለመለየት የኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን፣ የሸማቾች ጥበቃ ፣ ንግድና ምዝገባ ባለሙያዎችንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ቲም በረግዲና ማዞሪያ ከተማ ባደረገው ኦፔሬሽን ምርት በማከማቸት አላግባብና ከልክ በላይ የዋጋ ጭማሪ ለሚያደርጉ ነጋዴዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ የተሰራ ሲሆን ችግሮች የተገኙባቸው ህገ ወጥ ነጋዴዎችን በመለየት ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የማስጠንቀቅ ስራ መሰራቱ ተገልጿል።

የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት እንዳስታወቀው በኦፔሬሽኑ ወቅት የአንድ ኪሎ ስኳር ዋጋ ጎን ለጎን ባሉ ሱቆች መካከል ከ10 እስከ 15 ብር ልዩነት ያለው መሆኑ እየታየ ያለው የዋጋ ጭማሪ ምክንያታዊነት እንደሌለው የሚያመላክት እንደሆነና በሁሉም ቁሳቁሶች ላይ አሻጥር በመፍጠር የገበያ አለመረጋጋት እንዲፈጠር አስበው በሚሰሩ ነጋዴዎችና ህገወጥ ደላሎች ላይ ጽ/ቤቱ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳልም ተብሏል።

ጽ/ቤቱ ሃገሪቱ የገባችበትን ችግር ታሳቢ ያደረገ የገበያ ትስስር በመፍጠር ፍትሃዊና ተመጣጣኝ የግብይት አማራጮችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ከስግብግብ ነጋዴዎች መታደግ እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን በህገ ወጥ ግብይትና የዋጋ ጭማሪ ህ/ሰቡን ሊያማርር በሚችልና በሚጎዳ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርቶ በተገኘ ግለሰብም ሆነ ተቋም ላይ ጽ/ቤቱ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል።

Photos from መከኀየ ወ's post 19/08/2022

የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው የተለያዩ የፋብሪካ ምርቶችን የማስወገድ ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን የሳንኩራ ወረዳ ን/ገ/ል/ጽ/ቤት አስታወቀ።
~~~~~
የሳንኩራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ከወረዳው ጤና ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆንበወረዳው የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ያለፈባቸዉ የተለያዩ የፋብሪካ ምርቶችን በመሰብሰብ እንዲወገዱ አድርግያለሁ አለ።

የጽ/ቤቱ የኢንስፔክሽን ቡድን ከወረዳው ጤና ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በረ/ማዞሪያ እና በበርጮ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮችና የንግድ ድርጅቶች ላይ ባደረገው የውጭ ኢንስፔክሽን ስራ የህብረተሰቡን ጤናና ደህንነት ሊጎዱ የሚችሉ ጊዜ ያለፈባቸው የፋብሪካ ምርቶችንና የጥራት ደረጃ እውቅና የሌላቸው የተለያዩ የለስላሳ መጠጦችን ፣ የማንጎ ጁሶች ፣ የተለያየ ዓይነት ቺኘሶች፣ ማስቲካና ከረሜላ … ወዘተ ምርቶችን አግኝቶ ከወረዳው ህገ–ወጥ ንግድ ተቆጣጣሪ አስተግባሪ ግብረኃይል በጋራ በመሆን ከንግድ ድርጅቶቹ እንዲወገዱ ያደረገ ሲሆን ምርቶቹ የተገኙባቸው የንግድ ድርጅቶችን በቃል የማስጠንቀቅ ስራም መሰራቱን ጽ/ቤቱ አስታወቋል ።

ጽ/ቤቱ በንግድ ድርጅቶቹ ላይ የሚያደርገውን የክትትልና ቁጥጥር ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለፀ ሲሆን ነጋዴዎችና ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍልም የፋብሪካ ምርቶችን ሲገዛ በተለይ የህፃናት አልሚ ምግብና መጠጦችን የምርት ጊዜያቸውን የማረጋገጥ ልምዳቸዉን ሊያዳብሩ እንደሚገባም ተመላክቷል።

Photos from መከኀየ ወ's post 08/07/2022

#በሳንኩራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የ2015 የንግድ ፈቃድ እድሳት እና የ2014 ዓ/ም የገቢ አሰባሰብ ተግባር በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ስሆን ኃለፊዎች፣ የዞንና የወረዳው ባለድርሻ ሴክታር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ለተገልጋዩ አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ ኮሚትመንተቻው የሚበረታታ ነውና ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

Photos from መከኀየ ወ's post 07/07/2022

#የ2014 ዓ/ም የገቢ አሰባሰብ እና የ2015 የንግድ ፈቃድ እድሳት ተግባር በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ተግባራዊ መሆን እንደምገበ የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳደር ገለፁ።

///////////////////////////////////////////////////////

#የንቅናቄ መድረኩንም የተሟላ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው መሰከት የተቸለ ስሆን በንቅናቄ መድረኩም የሳንኩራ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት
ቤት፤ የ2014 የግብር አሰባሰብ እና የ2015 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ ዕድሳት የዝግጅትና ትግበራ ስራዎች ማስፈፀሚያ ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ መሆኑም በወረዳ ዋና አስተዳደር ተገልጿል ።
///////////////////////////////////////////////////////
#በመድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት አስፈላጊውን የግንዛቤ ስራ በጠራና በተደራጀ መልኩ መስራት ከተቻለ የግብር አሰባሰብና የንግድ ፈቃድ ዕድሳት ስራውን በተያዘለት ጊዜ ቀድሞ መጨረስ እንደሚቻል ከተሳታፊ አካላትም መግባባት ተችሏል ።
#ግብር ከፋዮች የንግድ ፍቃድ እደሳቸውን በተቀላጠፈ መንገድ እንዲያደርጉ ከወዲሁ የጠራ መረጃ በማደራጀት አገልግሎቱን በተደራጀ መልኩ ተደራሽ መሆን እንዲችል ቅንጅታዊ ስራዎችን በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ የሁለቱም ተቋም ኃላፍዎች ተደምጠዋል ።
#እንደ ወረዳ አሁን የለነበትን የአረፋ በዓል ዋዜማን ከግምት በማስገባት የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮችና ንግድ ፍቃድ የሚያድሱ ነገዴዎች በነገው እለት ሀምሌ 1 በጧቱ ክፍላ ጊዜ በሁለቱም ቦታ በርጮና ራግዲና ማዞሪያ ማዕከል ተጠናቆ ሊከፈል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
///////////////////////////////////////////////////////
#በተጨማሪም የ2015 ዓ.ም የንግድ ስራ ፍቃድ እድሳት በወቅቱ ሊደረግ እንደሚገባ እና ግብር ከፋዮ የማህበረሰብ ክፍል በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ግብሩን ከፍሎ እንዲጨርስ ያመላከቱት አቶ ታማም ፍጣሞ ነገዴው ህብረተሳብ ከአላስፈላጊ ወለድና ቅጣት ተጠብቀውር የገቢ አሰባሰብና የንግድ ፍቃድ እደሳ ተግባር በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በመፈፀም የንግዱ ማህበረሰብ ከእንግልት በጸዳ አገልሎቱን ማግኘት እንዲችል ማድረግ ይገባል ስሉ በአጽንኦት ገልፀዋል ።

30/06/2022

ከሀምሌ 1 ጀምሮ ሁሉም ክልሎች ወደ ኦንላይን ትግበራ እንዲገቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
=====================================

አዲስ አበባ ሰኔ 22/2014(ንቀትሚ) ከፊታችን ሀምሌ 1 ጀምሮ ሁሉም ክልሎች ወደ ኦንላይን ትግበራ እንዲገቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ጅራታ ነመራ ገለፁ።

በክልል ደረጃ እስከ ወረዳ ድረስ ይህንን የኦላይን ትግበራ ከህዝቡ ጋር ለማላመድ ወደ አንድ አመት ጊዜ መፍጀቱን ገልፀዋል ።

ምን ያህሉ የህብረተሰብ ክፍል ነው ይህንን የኦንላይን ፕላትፎርም ተጠቅሞ ንግድ ፍቃድ ማውጣት ወይም ማሳደስ የሚችሉት ጊዜ ገደብም ወደ አንድ አመት ጊዜ መፍጀቱን አንስተዋል ።

ይህን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ከተጠቃሚው ብቻ ሳይሆን ከአገልግሎት ሰጪውም ጭምር ችግሮች ነበሩ ያሉት ዳይሬክተሩ ፣የነበረው አሰራር ለሙስና የተጋለጠ ስለነበር ብዙዎች እንዲቀየር ፍላጎት እንዳልነበራቸውም አስረድተዋል።

ብዙ ቁጥር ያለው የንግዱ ማህበረሰብ አነስ ያለ የትምህርት ደረጃ ላይ ነው ያለው ያሉት አቶ ጂራታ ፣ በመሆኑም ይሻላል የምንለውን ቀላል አሰራር አዘጋጅተናል ብለዋል ።
በፌደራል ደረጃ መቶ በመቶ ወደ ኦንላይን ትግበራ ከተገባ ከዓመት በላይ እንደሆነዉም ተናግረዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Wednesday 00:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00