18/03/2023
መግለጫውን በአጭሩ ለመግለጽ ያህል
ኢትዮጵያ ሀገራችን ወደ ታላቅ ምእራፍ በምትሻገርበት ድልድይ ላይ ትገኛለች፡፡
1. ከድልድዩ ወደኋላ ሊመልሷት ይታገላሉ፡፡
2, ሌሎቹ ድልድዩን ሰብረው ገደል ሊከቷት
ይለፋሉ፡፡
3, ታጋይ ልጆቿ ደግሞ በድልድዩ ላይ ብዙ
ሳትቆይ ወደፊት እንድትራመድ ለማድረግ
ይታገላሉ፡፡
ብልጽግና ደግሞ ይህን መርጧል፡፡
👉ድልድይ ያለፈውን መንገድ ያህል ጠንካራ አይሆንም፡፡
👉ገደሉን ለመሻገር ግን የግድ ነው፡፡ ረዥም ጊዜ በድልድዩ ላይ መቆየትም አደጋ አለው፡፡
👉በቶሎ መሻገርና ወደጸናው መሬት መድረስ አስፈላጊ ነው፡፡
👉ያለንበት የሽግግር ጊዜም የሚነግረን ይሄንን ነው፡፡
👉የሽግግሩ ወቅት ዓላማው በዚያው መቆየት ሳይሆን ወደ በለጸገች ኢትዮጵያ መሸጋገሪያ ነው፡፡
👆እየገጠሙን ያሉትም የሽግግር ጊዜ ፈተናዎች ናቸው፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ
👉ኢትዮጵያ ካለፈው መንገድ የመጣችበትን፣ ወደ ብልጽግና ለመሻገር በድልድዩ ላይ የቆየችበትን፣ በድልድዩ ላይ በቆየችባቸው ወቅቶች የገጠሟትን ፈተናዎች፤ ከድልድዩ ወደኋላ ለመመለስ የሚታገሏትን ኃይሎች፣ ድልድዩን ተሻግራ ወደ ብልጽግና እንዳትሸጋገር ያጋጠሟትን አምስት ተግዳሮቶች በዝርዝር መርምሯል፡፡
1ኛ, ታሪክ ካሸከመን ዕዳችን ነው።
መፍትሄው፦ ለዕድሉም ለዕዳውም ተገቢውን ዕውቅና መስጠት ነው ብሏል።
2ኛ, ነፃነትን ለማስተዳደር አለመቻል ነው።
መፍትሄው ፦ ነፃነት ከኃላፊነት ጋር ሚዛናዊነቱን ጠብቆ እንዲሄድ ሂሉም ተቋማት የሚጠበቅበትን መስራት ነው።
3ኛ, ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን የሚፈታትኑ ሁኔታዎች እየገነገኑ መምጣታቸው ነው።
መፍትሄው ፦ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያለፉ ቁስሎችን ከሚቀሰቅሱ ጥላቻ ከሚያነገሱ እና መሰሎችን ከድርጊታቸውና ንግግሮች መቆጠብ አለባቸው።
4ኛ, የኑሮ ውድነት ነው።
መፍትሄው ፦ ምርትን በተገቢ መጠን ማምረትና ወደ ገበያ ማድረስ ችግሮችን ማረም ስራ ዕድል መፍጠር የቤት ስራችን ነው።
5ኛ, ሌብነት ነው።
የሌብነት እንደ መግለጫው መሠረት ዓይነቶች በ4 አከባቢዎች ይከፈላሉ!
1, በመንግስት ውስጥ ያሉ ሌቦች
2, በባለሀብቱ አከባቢ ያሉ ሌቦች
3, በብሔሮ አከባቢ ያሉ ሌቦች
5, በሚዲያ አከባቢ ያሉ ሌቦች ናቸው።
መፍትሄው፦ የጀመርነውን ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠል። ከራሳችን ጀምረን እጃችን ንጹህ በማድረግ ትግሉን መምራት ነው።
👉እኛም እንደ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወጣቶች ሊግ ያሉን ችግሮችን ተረድተን በሙሉ አቅም ለመስራት ቁርጠኛ መሆናችን እናረጋግጣለን።
መጋቢት 8/2015ዓ.ም
አቃቂ ቃሊቲ
02/02/2023
"ለኢትዮጵያ እና ለአፍረካዊ ብልጽግና የሚተካ ወጣት" በሚል መሪ ቃል የተደረገው ጉባኤ ውሳኔዎች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
ቀን 25/05/2015ዓ.ም(አቃቂ ቃሊቲ)
*********************************************** የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች ዙሪያ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከ12 ወረዳዎች የተወጣጡ የሊግ አመራሮችና አባላት የሀገራችን ወጣቶች ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎን በተመለከተ 6 ዋና ዋና የጉባኤ ውሳኔዎችን እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች አስቀምጧል።
በውይይቱ ወቅት የሊጉ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የክ/ከተማው የመንግስ ህንፃ በመሆኑምአስተዳደር ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ቢሊሴ አብሼ እና የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደቻሳ አየለ ተገኝተዋል። የጉባኤው ውሳኔዎችንና የቀጣይ የትኩረት ላይ የክፍለ ከተማችን ወጣቶች ጋር ውይይት ጊዜ ወጣቶች ተቋሙን ያጠናክራል ያሉትን ሀሳቦችና የወጣቶች ኢኮኖሚ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ ሀሳብና አስተያየት አንስተው በመድረኩ ላይ ተቋሙን በማጠናከር ፣ ከህዋሳት ጀምሮ በመታገል ብልሹ አሰራሮችን እንዲስተካከሉ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
01/02/2023
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች ዙሪያ ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ በክፍለ ከተማችን ወጣቶች ጋር ውይይት ይካሄዳል።
"ለኢትዮጵያ እና ለአፍረካዊ ብልጽግና የሚተካ ወጣት" በሚል መሪ ቃል የተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ የሀገራችን ወጣቶች ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎን በተመለከተ 6 ዋና ዋና ውሳኔዎችን እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች አስቀምጧል።
በመሆኑም የጉባኤው ውሳኔዎችንና የቀጣይ የትኩረት ላይ የክፍለ ከተማችን ወጣቶች ጋር ሐሙስ 25/05/2015ዓ.ም በክ/ከተማ ደረጃ ውይይት የሚካሄድ ሲሆን ቀጣይ በወረዳ ደረጃ ከመላ ወጣቶች ጋር ውይይት ይካሄዳል።
ስለሆነም የክ/ከተማችን ወጣቶች ውይይት መድረኩ ስኬታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አሳልፋለሁ።
ደቻሳ አየለ
የአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ
21/12/2022
በወጣቶች ማብቃትና ተሳትፎ ዙሪያ ወጣቶችን ያማከለ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በማከናወን ወጣቶች ዕምቅ አቅምና ችሎታቸውን አውጥተው በመጠቀም በሁሉም መስኮች ተሳታፊ፣ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ በትኩረት ይሰራል፡፡
ሴቶችንና ወጣቶችን በአመራርና በውሳኔ ሰጪነት ፍትሃዊ ተሳትፎና እና ውክልና እንዲሰፋ ለማድረግ፣የሴቶችና የወጣቶች የውሳኔ ሰጪነት ሚና በህግ አውጪና በህግ ተርጓሚ የሚኖራቸው ስፍራ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል፡፡
አገር አቀፍ የወጣቶች ካውንስል የሚቋቋምበትን ሁኔታ በማመቻቸት ወጣቶች ውክልና እንዲኖራቸው ብልጽግና ፓርቲ ይሰራል፡፡የወጣቶች የግንኙነትና የመረጃ ማዕከል ዩዝ ኮኔክት ፕሮግራም በመተግበር ወጣቶች ከአፍሪካና አለም አቀፍ አቻዎቻቸው ጋር ትስስር የሚፈጥሩበት ዕድል ያመቻቻል፡፡ወጣቶች ከሱስ የሚያገግሙበት የወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ማዕከላትን እንዲስፋፉ ይደረጋል፡፡
የልማት ፈንድ በማቋቋም ስራ ፈጣሪ ሴቶች በተለያዩ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ፈንዶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥና የማስተሳሰር ሚና የሚከናወን ሲሆን ሴቶች በብድር፣በህብረት ስራ ማህበራት፣በገጠር መሬት ባለቤትነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት ብልጽግና ይሰራል፡፡
19/12/2022
"የብልፅግና ዋና መርህ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ነው። ይህ መርህ እርስ በእርሳችን እንድንተሳሰብ እንድንደጋገፍ ይረዳል። እንደ ሀገር የሚገጥሙንን ችግሮች ልናልፋቸው የምንችለው በዚህ እሳቤ ስንመራ እና የአንዳችን ቁስል የአንዳችን ህመም መሆኑን ስንገነዘብ ብቻ ነው!!"
- አቶ አደም ፋራህ
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት