TMA/Traffic Management Authority

Call Directions Website Contact the organization

TMA/Traffic Management Authority A governmental organization under Addis Ababa city Administration responsible for traffic management

07/09/2026
07/09/2026
ባለስልጣን መ/ቤቱ ዿጉሜን 2 "የማንሰራራት ቀን" በፓናል ውይይት አከበረ*********************(ት/ማ/ባ/ዿጉሜን 2/2018 ዓ.ም)፡- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን...
07/09/2026

ባለስልጣን መ/ቤቱ ዿጉሜን 2 "የማንሰራራት ቀን" በፓናል ውይይት አከበረ
*********************
(ት/ማ/ባ/ዿጉሜን 2/2018 ዓ.ም)፡- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ዿጉሜን 2 "የማንሰራራት ቀን" በሚል ስያሜ ኢትዮጵያ ከአዝጋሚ እድገት ወደ ሁለንተናዊ ከፍታ መሸጋገር የጀመረችበት ቀን መሆኑን ያመላከተ ውይይት በዋናው መ/ቤት ተካሂዷል፡፡

የውይይቱን መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የፓርኪንግ ጥናት እና መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር አቶ ቢንያም ጌታቸው ሲሆኑ ሀገሪቱ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ አልፋ ያስመዘገበቻቸውን አዳዲስ የኢኮኖሚና መዋቅራዊ ስኬቶች እንዲሁም መጪውን አዲስ ተስፋ ለማብሰር እና ወደ ላቀ የከፍታና የልማት ምዕራፍ መሸጋገሯን አመላክተዋል፡፡

እንዲሁም እለቱም ለሕዝብና ለአለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማብሰር ያለመ ቀን መሆኑንን እና ሀገሪቱ ከተለያዩ የዓለም ሃገራት ተሞክሮዎችን በመውሰድ እና ወደ ተግባር በመቀየር በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ አንዲሁም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሰፊ ሃገራዊ ለውጥ የመጣበት እና የማንሰራራት ጊዜ መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል፡፡

የአዲስ ዓመት መዳረሻ የሆነውን ጳጉሜን 2 የ"ማንሰራራት ቀን" በተለይ በሀገራዊ ምርታማነት፣ በግብርና፣ በቴክኖሎጂ እና በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች የተመዘገቡ ስኬቶችን የምናይበት ጊዜ እንደሆነም አቶ ቢኒያም ጠቁመዋል፡፡

በቀረበው ሰነድ ላይም ሰራተኛው በጥሞና በመከታተል የተወያየ ሲሆን በመጨረሻም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ጳጉሜን ቀናት አሮጌውን ዓመት ሸኝተን አዲሱን የምንቀበልባት ልዩ ሳምንት በመሆኗ "የማንሰራራት ቀን" እያንዳንዱ ሰሪተኛ ለግል ሕይወቱ ስኬት ለተቋሙ ብሎም ለሀገሩ ሁለንተናዊ ብልጽግና አዲስ ዕቅድና ሙሉ የሥራ ተነሳሽነት የሚሰንቅበት ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሰራተኛው ለእራሱ፣ ለተቋሙ እና ለከተማው እድገት በአዲስ መንፈስ ተነሳስቶ ለበለጠ ውጤት እንዲዘጋጅ አሳስበዋል፡፡

በኢምፒርያል እና ጎላጎል አካባቢዎች የመንገድ ደህንነት ማሻሻያ ተግባራት እየተከናወኑ ነወ*******************(ት/ማ/ባ  ጿጉሜ 2/2018) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥል...
07/09/2026

በኢምፒርያል እና ጎላጎል አካባቢዎች የመንገድ ደህንነት ማሻሻያ ተግባራት እየተከናወኑ ነወ
*******************
(ት/ማ/ባ ጿጉሜ 2/2018) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥና የከተማዋን የትራፍክ እንቅስቃሴ ለማሻሻል 24/7 እየሰራ ይገኛል።

በዚህ መሠረት፣ በImperial Overpass እና ጎላጉል አካባቢ የመንገድ አካፋይ ጠርዝና የትራፊክ አቅጣጫ በግልጽ እንዲታይ እያደረገ ነዉ።

በተለይም አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የመንገድ ክፍልን ለማመላከት እና አሽከርካሪዎች ከተወሰነው የጉዞ መስመር እንዳይወጡ ለመርዳት Flexible Plastic Delineator Posts ተገጥመዋል።

ይህ የመንገድ ደህንነት መሳሪያ ደልነተሮች በተለይ የOverpass መግቢያ አካባቢን በግልጽ እንዲለዩ በማድረግ አሽከርካሪዎች በተፈቀደው የትራፊክ አቅጣጫ እንዲጓዙ እና በተከለከለ ቦታ እንዳይዞሩ ያግዛሉ።

በተለይም በሌሊትና በዝቅተኛ የእይታ ሁኔታ ወቅት በግልጽ የመንገድን መስመር በማመላከት ፣ ተገቢ ያልሆነ ቅስቃሴን እና ያልተፈቀደ የመንገድ መሻገርን በመከላከል በአከባቢ የትራፍክ አደጋን ለመቀነስና ተገቢ የሆነ የትራፍክ ፍሰት እንዲኖር የጐላ ሚና ይኖረዋል።

እንደ ማሳሰቢያ
ለአሽከርካሪዎችና ለመንገድ ተጠቃሚዎች በሙሉ፦
1. የመንገድ ምልክቶችንና የትራፊክ መመሪያዎችን በማክበር የተፈቀደውን የጉዞ አቅጣጫ ብቻ ይከተሉ።

2. U-Turn ማድረግ ሲያስፈልግ ከOverpass ስር በTraffic Signal የሚመራውን የተፈቀደ የመዞሪያ ቦታ ብቻ ይጠቀሙ።

3. ያልተገባ እንቅስቃሴ በማድረግ በተተከለዉ መሰረት ልማት ላይ ጉዳት የሚያደርሱት ላይ አኣባቢዉ ባሉ ካሜራዎች 📹 በመታገዝ ተገቢዉ የእርምት እርምጃ ይወሰዳል።
ነፃ የስልክ መስመር 696ን ይጠቀሙ!

አሮጌውን ዓመት ሸኝተን፤ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ እገኛለን፡፡ አዲሱን ዓመት በደስታ እና በፍቅር ለመቀበል ሁላችንም የመንገድ ደህንነት ደንቦችና ህጎችን በማክበር ከትራፊክ አደጋ እንጠበቅ፡፡...
07/09/2026

አሮጌውን ዓመት ሸኝተን፤ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ እገኛለን፡፡ አዲሱን ዓመት በደስታ እና በፍቅር ለመቀበል ሁላችንም የመንገድ ደህንነት ደንቦችና ህጎችን በማክበር ከትራፊክ አደጋ እንጠበቅ፡፡ 🙏
ውብ ዋዜማ ብሩህ ወርሃ ጳጉሜ!💥
መልካም የማንሰራራት ዘመን ይሁንልን!😇

የአዲስ አበባ ትፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን!

Address

Equatorial Guinea Road, (22 Mazoria
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TMA/Traffic Management Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to TMA/Traffic Management Authority:

Shortcuts

Share