ቦሌ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት/Bole Sub City Housing Dev. & Admin Office
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቦሌ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት/Bole Sub City Housing Dev. & Admin Office, Government Organization, Addis Ababa.
እንኳን ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ በደህና መጡ!
ይህ ገፅ በክፍለ ከተማችን የሚከናወኑ የጽ/ቤቱ ተግበሰራት እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተመለከተ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለነዋሪው ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው።
04/04/2026
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷ ደግሞ ብቁ የማድረግ ትልቅ ግብ የሰነቀ ነው። የከተማ አስተዳደሩ "ልማቱ ሰውን ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት" በሚል በያዘው አቋም መሠረት በኮሪደሩ ዳርቻ የፈረሱ የንግድ ቦታዎችን ለመተካት በዘመናዊ መልኩ የተገነቡ ሱቆችን ለተነሺዎች ቅድሚያ በመስጠት የማስተላለፍ ስራ በከፍተኛ ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።የአዲሳ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የተገነቡ በኮሪደር ልማት የለሙ ሱቆችን ለልማት ተነሺዎች በዕጣ የማስተላለፍ መረሃ ግብር አከናዉኗል።
30/03/2026
የዛሬውን ወርቃማው ሰኞ ምክንያት በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች መብቱን እና ግዴታውን አውቆ ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎት መስጠት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የልምድ እና አውቀት ሽግግር ተካሄደ።
ይህ የውይይት መድረክ በዋናነት የመንግስት ሰራተኛውን መብትና ግዴታ በዝርዝር ከመረዳት ባለፈ፣ በጽህፈት ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ለነዋሪው ምቹ ለማድረግ ያለመ ነው።
28/03/2026
የአረንጓዴ አሻራን በዘላቂነት ማጽናት፦ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በወረዳ 12 የእንክብካቤ ስራ አከናዉኗል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎች በ2017 የክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በዛሬው ዕለት በወረዳ 12 አካባቢ በስኬት አከናውነዋል። በንቅናቄው ላይ የጽ/ቤቱ የስራ መሪዎችና መላው ሰራተኞች በነቃ ተሳትፎ የተገኙ ሲሆን። በመድረኩ የተገኙ የስራ ኃላፊዎች እንደተናገሩት፡- ችግኝ መትከል ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የተከልነውን አጽድቆ ለትውልድ ማሳለፍ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብሎዋል። ይህም የከተማዋን ውበት ከመጠበቅ ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ አየር እንዲኖር ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል።
23/03/2026
የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር በየሳምንቱ ሰኞ የሚያካሂደው "ወርቃማ ሰኞ" የውይይት መድረክ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። የዛሬው የውይይት መሪ ቃል "አገልግሎት እና ስነምግባር" የሚል ሲሆን፣ በጽሕፈት ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ ቁልፍ ነጥቦች ላይ የእውቀት ሽግግር ተከናውኗል።
16/03/2026
በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በየሳምንቱ ሰኞ ጠዋት የሚከናወነው የ**"ወርቃማ ሰኞ"** መርሐ-ግብር ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።
የዛሬው የውይይት ትኩረት "የተግባቦት (Communication) ጽንሰ-ሀሳብና አስፈላጊነት" በሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በሥራ አካባቢ ሊኖር ስለሚገባው ጤናማ የመረጃ ልውውጥ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የማዳመጥ ጥበብ፦ የደንበኞችን ፍላጎትና ቅሬታ በትዕግሥት ማዳመጥ ለችግሮች ግማሽ መልስ ነው።
የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በውይይቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፣ የተገኘውን ግንዛቤ ወደ ተግባር በመቀየር ለክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ግልጽነት የተሞላበትና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብሏል።
10/03/2026
በቀን 30/06/2018 ዓ.ም "አመለካከት ለሁሉም ነገር ወሳኝ ነው"፦ በሚል ማሪ ቃል በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር የእውቀት ሽግግርና የውይይት መድረክ ተካሄደ
የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የሰራተኞችን ክህሎት ለማሳደግና ተገልጋይን ማእከል ያደረገ አሰራርን ለማጠናከር ዘዎትር ሰኞ የሚካሄደው "ወርቃማ ሰኞ" “Attitude is Everything” (አመለካከት ለሁሉም ነገር ወሳኝ ነው) በሚል መሪ ቃል ውይይትና የእውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር ተካሄደ። የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ይህንን "ወርቃማ ሰኞ"ን የመማማሪያ መድረክ በማድረግ፣ ሰራተኛው በዕውቀት ብቻ ሳይሆን በስነ-ልቦናም ተዘጋጅቶ ህዝቡን እንዲያገለግል እና መልካም ልምዶቻቸውን በማካፈል የስራ መነቃቃት እና ተነሳሽነት የሚፈጥሩበት ነው፡፡
28/02/2026
የስድስት ወር የግምገማ ግብረመልስን መነሻ በማድረግ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች እና በታዩ ጥንካሬዎች እና መስተካከል በሚገባቸው ጉድለቶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰ እና ውይይቱ የሚያሳየው ካለፉት ስድስት ወራት ክፍተት በመማር፣ ለቀጣዩ ግማሽ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ ተነሳሽነት መኖሩን ነው።
28/11/2025
06/11/2025
02/11/2025
ማስታወቂያ
ከ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ
👇👇👇👇👇👇👇
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 17:30 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |
