08/06/2026
ECMA Licenses United Capital Financial Services PLC as Investment Bank
*************************************************************************
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) has granted a Capital Market Service Provider (CMSP) license to United Capital Financial Services PLC, a subsidiary of United Capital Group Nigeria, making it the first foreign investment bank to establish a subsidiary in Ethiopia.
The license authorizes the company to operate under the Investment Banking category. The Authority has also approved the appointment of five Board Directors and licensed four Appointed Representatives within the company.
Issued on Friday, June 5, 2026, the license brings the total number of licensed CMSPs in Ethiopia to 18 and the number of investment banks to 7, reflecting the tangible and continuous development in the operationalization and expansion of the country’s capital market.
At the official licensing ceremony, the Director General Hana Tehelku noted that the entry of a Pan-African institution such as United Capital marks a historic milestone in the development of Ethiopia’s capital market, further indicating that the event demonstrates strong confidence in the credibility of the country’s emerging financial ecosystem and the direction of ongoing reforms.
She noted that such developments reflect growing recognition of Ethiopia’s market potential and institutional progress, and can contribute to strengthening the depth, capacity, and regional integration of the market, while underscoring the importance for licensed service providers to adhere to the highest standards of market conduct, governance, and regulatory compliance.
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ
**************************************************************
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ባለስልጣኑ) የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) ለሆነው ዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ሰጥቷል።
ይህም ተቋሙን በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥላ ኩባንያ በማቋቋም እንዲንቀሳቀስ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ያደርገዋል። የተሰጠው ፈቃድ ድርጅቱ በኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ ስር እንዲሠራ የሚፈቅድ ሲሆን፤ ባለስልጣኑ ከዚህ በተጨማሪ የአምስት (5) የቦርድ ዳይሬክተሮችን ሹመት ያጸደቀ ከመሆኑም በላይ ለአራት (4) ተሿሚ እንደራሴዎችም ፈቃድ ሰጥቷል።
አርብ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተሰጠው ይህ ፈቃድ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ስምንት (18)፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮችን ቁጥር ወደ ሰባት (7) ከፍ አድርጎታል። ይህም የሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ተግባራዊነት እና ልማት እያሳየ ያለውን ተጨባጭና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ያሳያል።
በይፋዊው የፈቃድ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ እንደገለጹት፣ እንደ ዩናይትድ ካፒታል ያለ የፓን-አፍሪካዊ ተቋም ወደ ገበያው መግባቱ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ዕድገት ላይ ታሪካዊ ምዕራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ ሁነቱ እያደገ ባለው የሀገሪቱ የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ተዓማኒነት እና እየተከናወኑ ባሉ የማሻሻያ እርምጃዎች ላይ ጠንካራ እምነት መኖሩን እንደሚያሳይ አመልክተዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም፣ እንዲህ ያሉ ዕድገቶች ለኢትዮጵያ የገበያ አቅም እና ለታየው ተቋማዊ መሻሻል የተሰጡ ትልቅ እውቅናዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የገበያውን ጥልቀት፣ አቅም እና ቀጣናዊ ውህደት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ አመልክተዋል። በተመሳሳይም ፈቃድ የተሰጣቸው አገልግሎት ሰጪዎች ከፍተኛ የገበያ ሥነ-ምግባርን፣ የኮርፖሬት አስተዳደር መርሆዎችን እና የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማክበር እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተው አሳስበዋል::

ECMA remains committed to fostering a fair, transparent, and efficient capital market ecosystem that supports sustainable economic growth and enhances investor confidence.
The Ethiopian Capital Market Authority congratulates United Capital Financial Services PLC and its parent company, United Capital Group, on this milestone and looks forward to their contribution to the ongoing development of Ethiopia’s capital market.
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ
*************************************************
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ባለስልጣኑ) የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) ለሆነው ዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ሰጥቷል።
ይህም ተቋሙን በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥላ ኩባንያ በማቋቋም እንዲንቀሳቀስ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ያደርገዋል። የተሰጠው ፈቃድ ድርጅቱ በኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ ስር እንዲሠራ የሚፈቅድ ሲሆን፤ ባለስልጣኑ ከዚህ በተጨማሪ የአምስት (5) የቦርድ ዳይሬክተሮችን ሹመት ያጸደቀ ከመሆኑም በላይ ለአራት (4) ተሿሚ እንደራሴዎችም ፈቃድ ሰጥቷል።
አርብ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተሰጠው ይህ ፈቃድ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ስምንት (18)፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮችን ቁጥር ወደ ሰባት (7) ከፍ አድርጎታል። ይህም የሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ተግባራዊነት እና ልማት እያሳየ ያለውን ተጨባጭና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ያሳያል።
በይፋዊው የፈቃድ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ እንደገለጹት፣ እንደ ዩናይትድ ካፒታል ያለ የፓን-አፍሪካዊ ተቋም ወደ ገበያው መግባቱ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ዕድገት ላይ ታሪካዊ ምዕራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ ሁነቱ እያደገ ባለው የሀገሪቱ የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ተዓማኒነት እና እየተከናወኑ ባሉ የማሻሻያ እርምጃዎች ላይ ጠንካራ እምነት መኖሩን እንደሚያሳይ አመልክተዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም፣ እንዲህ ያሉ ዕድገቶች ለኢትዮጵያ የገበያ አቅም እና ለታየው ተቋማዊ መሻሻል የተሰጡ ትልቅ እውቅናዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የገበያውን ጥልቀት፣ አቅም እና ቀጣናዊ ውህደት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ አመልክተዋል። በተመሳሳይም ፈቃድ የተሰጣቸው አገልግሎት ሰጪዎች ከፍተኛ የገበያ ሥነ-ምግባርን፣ የኮርፖሬት አስተዳደር መርሆዎችን እና የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማክበር እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተው አሳስበዋል::
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን የሚደግፍ እንዲሁም የኢንቨስተሮችን እምነት የሚያጎለብት ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና ቀልጣፋ የካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር ለመገንባት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል።
ባለስልጣኑ ለዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማ. እና ለእናት ኩባንያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ ለዚህ ስኬት የተሰማውን ደስታ እየገለጸ፣ ተቋማቱ ለኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ቀጣይ ልማት ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
05/06/2026
በካፒታል ገበያ ኢንቨስተር ኤክስፓ ለመሳተፍ እየተዘጋጁ ነው ?
**********************************************
የሀገራችንን የካፒታል ገበያ ገጽታ የሚቀይረው የመጀመሪያው የካፒታል ገበያ ኢንቨስተሮች ቀን አውደ ርዕይ (Expo) እየደረሰ ነው፡፡
በዚህ ልዩ አውደ ርዕይ ላይ በመገኘት ምን ያተርፋሉ ?
✅ ጥያቄዎን በቀጥታ ያቀርባሉ ፦ በካፒታል ገበያው ካሉ የዘርፉ ተዋናዮች ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX)፣ ከኢንቨስትመንት ባንኮች፣ ከአማካሪዎች፣ ከሰነደ ሙዓለ ንዋይ አከናዋኞች ጋር በቀጥታ ጥያቄዎን በማቅረብ ምላሽ ያገኛሉ ።
✅ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፦ የፋይዳ ቁጥርዎን በመጡበት እለት ማግኘት ይችላሉ፤ ወዲያውኑም የኢንቨስትመንት አካውንት የሚከፍቱበት እድል ተመቻችቷል ፡፡
✅ ይጫወታሉ ፣ ይሸለማሉ፦ በኤክስፓው በሚዘጋጁ አዝናኝ ጌሞች ላይ በመሳተፍ የኢንቨስትመንት አካውንትወን በመክፈት አሸናፊ ሲሆኑ ይሸለማሉ፡፡
ቀን፦ ሰኔ 12 እና 13 ቀን 2018 ዓ.ም
ቦታ፦ በአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ግቢ (ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ)
Facebook https://lnkd.in/e5r8YzEh
X https://x.com/CMAEthiopia
You tube https://lnkd.in/euAsnu8b
Website ecma.gov.et
telegram https://t.me/ecma2026
WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029Vb7zYee9WtC6oCBgSk1S
05/06/2026
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) recently hosted a strategic engagement with a delegation from the Intercontinental Investment Bank (iib Group), led by Group CEO Mr. Sohail Sultan.
The discussion covered the current state of Ethiopia's capital market, its emerging investment landscape, and the regulatory and licensing pathways available to institutions seeking to participate in its growth. Having recently received authorization from the National Bank of Ethiopia to establish a Representative Office, iib Group expressed strong interest in deepening its engagement under ECMA's capital market licensing framework.
ECMA remains firmly committed to building a robust, transparent, and world-class regulatory environment. By engaging with diverse international financial institutions and welcoming global expertise, the Authority continues to build an inclusive ecosystem that drives capital formation and supports Ethiopia's overarching economic transformation.
የኢትዮጵያካፒታል ገበያ ባለስልጣን በግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቶ ሶሀይልሱልጣን ከተመራው የኢንተርኮንቲነንታል ኢንቨስትመንት ባንክ (iib Group) ልዑክ ጋር በቅርቡ ስትራቴጂካዊ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱየኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በማደግ ላይ ያለውን የኢንቨስትመንት ምህዳር እንዲሁም በገበያው እድገት ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋማት ያሉትን የቁጥጥር እና የፈቃድ አሰጣጥ መንገዶችን ያካተተ ነበር።
በኢትዮጵያ ተወካይ ቢሮ ለማቋቋም ከኢትዮጵያብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ፈቃድ ያገኘው አይ.አይ.ቢ ግሩፕ ፣ በባለስልጣኑ የካፒታል ገበያ የፈቃድ ማዕቀፍ ስር ያለውን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ገልጿል።
የኢትዮጵያካፒታል ገበያ ባለስልጣን ጠንካራ፣ ግልጽ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቁጥጥር ምህዳር ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል።
ባለስልጣኑ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመገናኘት እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀበል፣ የካፒታል ምስረታን የሚያፋጥን እና የኢትዮጵያን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን የሚደግፍ አካታች ስነ-ምህዳር መገንባቱን ይቀጥላል።
Facebook https://lnkd.in/e5r8YzEh
X https://x.com/CMAEthiopia
You tube https://lnkd.in/euAsnu8b
Website ecma.gov.et
telegram https://t.me/ecma2026
WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029Vb7zYee9WtC6oCBgSk1S
04/06/2026
Public Call for Comments: Collective Investment Schemes (CIS) Draft Directive
***********************************************
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) invites the public and all stakeholders to comment on the latest Collective Investment Schemes (CIS) Draft Directive.
The draft is now officially available for public review. Everyone is welcomed to share their inputs, feedback, and recommendations directly through the FDRE public consultation portal.
🔗 Access the Draft & Submit Comments: https://e-consultation.gov.et/draft/155
Deadline for submission: June 14, 2026
የህዝብ አስተያየት ጥሪ፡ የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ ረቂቅ መመሪያ
*************************************************
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ ረቂቅ መመሪያ የመጨረሻ ረቂቅ ላይ ህዝብ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ይጋብዛል።
ረቂቅ መመሪያው አሁን ላይ ለህዝብ አስተያየት ክፍት ሆኗል። ማንኛውም ፍላጎት ያለው አካል ሃሳብ፣ አስተያየት እና ምክረ-ሀሳቡን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝባዊ ምክረ ሃሳብ መስጫ መድረክ ላይ በቀጥታ ማጋራት ይችላል።
🔗 ረቂቁን ለመመልከት እና አስተያየት ለመስጠት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://e-consultation.gov.et/draft/155
አስተያየት መስጫ ቀን፦ እስከ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም
04/06/2026
ECMA and Expertise France Discuss SME Capital Market Access
***************************************************************
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) held a productive meeting with representatives of Expertise France to discuss developing a strategic roadmap to enhance access to capital markets for Small and Medium-Sized Enterprises (SMEs) in Ethiopia.
The initiative, supported through a project funded by the European Union and Agence Française de Développement (AFD), aims to identify practical measures to strengthen the enabling environment for SME financing and broaden access to market-based sources of capital.
The discussion focused on key priorities for fostering SME participation in Ethiopia’s emerging capital market, including regulatory reforms, capacity-building initiatives, market infrastructure development, and innovative financing mechanisms.
The engagement reflects ECMA’s continued commitment to building an inclusive and dynamic capital market ecosystem that supports entrepreneurship, promotes private sector growth, and contributes to sustainable economic development in Ethiopia.
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከኤክስፐርቲዝ ፍራንስ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሄደ
********************************************************************
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SMEs) የካፒታል ገበያ ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ፍኖተ-ካርታ ለማዘጋጀት ከኤክስፐርቲዝ ፍራንስ (Expertise France) ተወካዮች ጋር የጋራ ውይይት አድርጓል።
ይህ በአውሮፓ ህብረት (EU) እና በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ (AFD) በገንዘብ የሚደገፍ ፕሮጀክት፣ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር እና በገበያ ላይ የተመሰረቱ የካፒታል ምንጮችን ተደራሽነት ለማስፋት የሚያስችሉ ተግባራዊ እርምጃዎችን ለመለየት ያለመ ነው።
በጋራ ምክክሩ ላይ በኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባለው የካፒታል ገበያ ውስጥ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተሳትፎ ማሳደግ በሚቻልባቸው የቁጥጥር ስርአት ማሻሻያዎች፣ የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ የገበያ መሠረተ-ልማት ዝርጋታ እና ኢኖቬቲቭ የፋይናንስ ዘዴዎች ላይ ምክክር ተደርጓል።
ውይይቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ስራ ፈጠራን የሚደግፍ፣ የግል ዘርፉን እድገት የሚያበረታታ እና በሀገሪቱ ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሁሉንም ያካተተ እና ንቁ የካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
Facebook https://lnkd.in/e5r8YzEh
X https://x.com/CMAEthiopia
You tube https://lnkd.in/euAsnu8b
Website ecma.gov.et
telegram https://t.me/ecma2026
WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029Vb7zYee9WtC6oCBgSk1S
02/06/2026
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የመጀመሪያውን የካፒታል ገበያ ኢንቨስተሮች ቀን በድምቀት ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነው ፡፡
የሀገራችንን የካፒታል ገበያ ገጽታ በሚቀይረው የመጀመሪያው የካፒታል ገበያ ኢንቨስተሮች ቀን አውደ ርዕይ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅት ያድርጉ !!
በዚህ ልዩ አውደ ርዕይ ላይ በመገኘት፡
✅ ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX)፣
✅ ከኢንቨስትመንት ባንኮች፣
✅ ከኢንቨስትመንት አማካሪዎች
✅ ከሰነደ ሙዓለ ንዋይ ደላሎች (Brokers) እና አከናዋኞች ጋር በቀጥታ በመገናኘት የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ያመቻቹ!
ቀን፦ ሰኔ 12 እና 13 ቀን 2018 ዓ.ም
ቦታ፦ በአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ግቢ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ
መግቢያ፦ ለሁሉም ፍላጎት ላላቸው ጎብኚዎች በነጻ ክፍት ነው !!
02/06/2026
Strengthening AML/CFT Readiness in Ethiopia’s Capital Market
******************************************************
The Ethiopian Capital Market Authority successfully conducted a training for Capital Market Service Providers on Anti-Money Laundering and Countering the Financing of Terrorism (AML/CFT), with a particular focus on Ethiopia’s ongoing ESAAMLG (East and South Africa Anti Money Laundering Group) Mutual Evaluation.
The training covered key FATF effectiveness requirements, risk-based AML/CFT obligations, Customer Due Diligence (CDD), suspicious transaction reporting, beneficial ownership transparency, and the expectations placed on capital market institutions during the mutual evaluation process.
As Ethiopia advances its capital market development agenda, strengthening AML/CFT compliance remains essential to safeguarding market integrity, enhancing investor confidence, and aligning with international standards.
We appreciate the active participation and commitment of all Capital Market Service Providers in fostering a secure, transparent, and resilient capital market ecosystem.
በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ መከላከል ዝግጁነትን ማጠናከር ያለመ ስልጠና ተሰጠ
****************************************************************
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ መከላከል ዙሪያ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል። ስልጠናው በተለይም በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ባለው የESAAMLG የጋራ ግምገማ ላይ ትኩረት አድርጓል።
በስልጠናው ውስጥ የFATF ውጤታማነት መስፈርቶች፣ በስጋት ላይ የተመሰረቱ የበወንጀል የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ መከላከል ግዴታዎች፣ የደንበኛነ ማወቅ ተገቢ ምርመራ ፣ አጠራጣሪ ግብይቶችን ሪፖርት ማድረግ፣ የተጠቃሚ የሚሆነው ባለቤት ግልጽነት እና በጋራ ግምገማ ሂደቱ ወቅት ከካፒታል ገበያ ተቋማት የሚጠበቁ ኃላፊነቶች በስፋት ተዳሰዋል።
ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን እያለማች ባለችበት ወቅት፣ የበወንጀል የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ መከላከል ተገዢነትን ማጠናከር የገበያውን ታማኝነትና ቅንነት ለመጠበቅ፣ የባለሀብቶችን መተማመን ለማሳደግ እና ከዓለም አቀፍ መስፈርቶች ጋር ለመጣጣም ወሳኝ ነው።
ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ግልጽና እና አስቻይ የካፒታል ገበያ ሥርዓት ለመገንባት በስልጠናው ውስጥ በንቃት ለተሳተፉ እና ቁርጠኝነት ላሳዩ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።
Facebook https://lnkd.in/e5r8YzEh
X https://x.com/CMAEthiopia
You tube https://lnkd.in/euAsnu8b
Website ecma.gov.et
telegram https://t.me/ecma2026
WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029Vb7zYee9WtC6oCBgSk1S
29/05/2026
ECMA and Oromia Sovereign Fund Held Discussions on Capital Market Participation
******************************************************************
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) has held discussions with senior officials of the Oromia Sovereign Fund on the fund’s potential participation in Ethiopia’s emerging capital market.
During the discussion, ECMA Director General Hana Tehelku emphasized that the fund’s broad investment capacity across multiple strategic sectors could play an important role in strengthening the national capital market, while also supporting its own institutional growth.
The discussions focused in particular on how enterprises under the fund could transition into public companies to raise long-term financing for expansion projects through the issuance of shares and corporate bonds.
The discussions also explored how the fund could diversify its income sources by investing its existing assets in credible securities as an institutional investor.
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ሶቨሬን ፈንድ ጋር ተወያየ
*************************************************************
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ሶቨሬን ፈንድ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ፈንዱ በካፒታል ገበያው ስለሚሳተፍበት ሁኔታ ውይይት አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ በውይይቱ እንደገለጹት ፈንዱ በተለያዩ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን አቅም ወደ ካፒታል ገበያው በማምጣት ተቋማዊ ዕድገቱን ከመገንባት ባለፈ ለሀገራዊው ገበያ መጠናከር ወሳኝ ሚና መጫወት እንደሚችል ገልጸዋል።
በተለይም በፈንዱ ሥር የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ወደ ሕዝብ ኩባንያነት በመቀየር አክሲዮኖችን ወይም የዕዳ ሰነዶችን ለገበያ በማውጣት ለፕሮጀክቶቻቸው ማስፈጸሚያ የሚሆን የረጅም ጊዜ ፋይናንስ ማግኘት ስለሚችሉበት፣ እንዲሁም ተቋሙ ያለውን ሀብት በሌሎች አስተማማኝ የሰነደ-ሙዓለ ነዋይ አማራጮች ላይ እንደ ተቋማዊ ኢንቨስተር የገቢ ምንጩን ስለሚያሰፋበት ሁኔታ ውጤታማ ምክክር ተደርጓል።
28/05/2026
ECMA and ESX Soft Launch Ethiopia’s Sustainable Securities Framework
*****************************************************************
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) and the Ethiopian Securities Exchange (ESX), in collaboration with FSD Ethiopia, held soft launch session for Ethiopia’s Sustainable Securities guidelines and listing frameworks, a key initiative aimed at supporting sustainable finance and responsible investment in the country.
The launch program was officially opened by ECMA Director General Hana Tehelku, who highlighted the importance of creating a capital market that supports sustainable economic growth and encourages investments with positive environmental and social impact.
The soft launch introduced the Sustainable Securities Guideline, the Minimum Documentation Pack, and the ESX Guideline on Listed ECMA-Labelled Sustainable Securities. The framework will support the issuance of green, social, sustainability, and sustainability-linked securities in Ethiopia.
The event brought together key market stakeholders, investors, financial institutions, and development partners to engage on the new framework and its role in advancing Ethiopia’s capital market development.