በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን FDRE Environment Protection Authority

በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን    FDRE Environment Protection Authority

Share

Ethiopian Environmental Protection Authority is Re-established Under Proclamation No. 1263/2021.

Photos from በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን    FDRE Environment Protection Authority's post 08/06/2026

የስርዓተ-ምህዳር ግልጋሎት (PES) ክፍያ አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት አስፈላጊ መሆኑን ተገለጸ፡፡
አዲስ አበባ
*************************************************************************************************
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እና ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስርዓተ-ምህዳር ግልጋሎት(PES) ክፍያ አዋጅ ቁጥር 1401/2017 በሚመለከት የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄደ፡፡ የዕለቱ ውይይት በዋናነት በአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎች እና ውጤቶቹ እንዲሁም በስርዓተ ምህዳር ግልጋሎት ክፍያ ላይ ያተኮረ ሲሆን መድረኩን ዓለማቀፍ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የምርምር ዩኒቨርስቲዎች፣ ኢምባሲዎች እንዲሁም የፌዴራል ተቋማት ተሳትፈውበታል፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ንጉሥ ለማ መርሃ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት በሀገራችን እየተተገበሩ እንደ አረንጓዴ አሻራያሉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ሀገራችን እና ህዝባችን የሚገጥሟቸው ግዙፍ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ከሚደረጉ ጥረቶች ማሳያ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም የአካባቢ ጥበቃ ተፈጥሮን ከመጠበቅ ባለፈ የምግብ ዋስትናን፣ የኑሮ ሁኔታን፣ የልጆቻችንን ደህንነት፣ ሰላም እና የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስን መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የስርዓተ-ምህዳር ግልጋሎት ክፍያ (PES) አዋጅ ቁጥር 1401/2017፡ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ብርቱ ጥረት እያደረገ መሆኑን እና ለወደፊት ከሌሎች ዘርፍ መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የወርልድ ቪዥን ዳይሬክተር ካርመን ቲል በበኩላቸው ተቋማቸው መሬትን መልሶ ማልማት (restoration) ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ እንደሆነ ገልፀው ይህም ዛፍ መትከል ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ስለ መሬት፣ ውሃ፣ የኑሮ ሁኔታ፣ የአካባቢ ተቋማት፣ እንዲሁም ስለ ህጻናት እና ማህበረሰቦች መጻኢ እድል ጭምር ማሰብ እና መስራት መሆኑን በመድረኩ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በቀጣይ የተሳካ ውጤት እንዲመዘገብ በስርዓተ ምህዳር ግልጋሎት አቅራቢዎች እና ተጠቃሚዎች መካከል ግልፅ የሆነ የአሰራር ስርዓትን በማስፈን ከመስኩ የሚገኘውን ትሩፋት ለማላቅ ከፍተኛ ጥረት መደረግ እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
የዕለቱ መርሀግብር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተፈጽሟል፡፡

08/06/2026

ከብክለት ወደ ውበት!!
ፅዱ ኢትዮጽያን ዕውን እናድርግ!!

07/06/2026
Photos from በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን    FDRE Environment Protection Authority's post 06/06/2026

የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የዓለም የአካባቢ ቀን በአልን በእንጦጦ አዲሱ ፓርክ አካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን በመጎብኘት አከበረ።
‎ግንቦት 29 2018 ዓ ም
‎እንጦጦ ፖርክ
‎፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
‎ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የ2018 የአለም አካባቢ ቀንን ከአዲስ አበባ፣ ከኦሮሚያ ፣ ከተለያዩ አለም አቀፍና ሀገር በቀል ድርጅቶች ፣ ከፌዴራልና ከክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በእንጦጦ ፓርኪ የተሰራውን የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ጉብኝት በማድረግ እና በተለያዩ ኩነቶች በደመቀ ሁኔታ አከበረ።
ክብርት ዶ/ር ለሊሴ ነሜ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት የአካባቢ ሃብት ምትክ የለሽ መሆኑን በመረዳት አካባቢን ሣይንሥ በሆነ መንገድ ለመጠበቅ፣ ለማልማት እና ለመንከባከብ የሚያሥችሉ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን እንዲሁም ዘላቂ የአካባቢ ሃብት አጠቃቀም ሥርዓትን በመዘርጋት በሁሉም ደረጃ ውጤታማ ሥራዎች ለማከናወን ተችሏል።
‎ለዚህም በእንጦጦ ፖርክ መንግሥት በልዩ ትኩረት ከሠራቸው የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በአንድ ሺህ ሰላሣ ሰባት ሔክታር ውስጥ በሀገር በቀል በሆነ እውቀት በኮንሶ ቪሌጅ የተሰራ ሥራ ማሰያ እንደሆነ ገልጸዋሉ።
‎ ‎የእንጦጦ ፖርክ ስራ ዜጎች አብረው በራስ ዕውቀት እና ካፒታል በተቀላጠፈ አፈፃፀም ሌሎች የልማት ትሩፉት ስራዎችን መሥራት እንደሚችሉ ሕያው ማሳያ መሆኑን በመንሳት ‎በዕለቱ ለአካባቢ ጥበቃ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙት የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ስራዎች፣ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠናክረው እንዲሁም በየክልሉ ተሥፉፍተው እንደሚሰሩ በመግለፅ ይህም በክቡር ዶ/ር አቢይ አህመድ አመራር ሰጪነት የሚሰሩ የአረንጓዴ ኢኒሼቲቭ ስራዎች በሀገር ደረጃ ውጤታማ ሥራዎችን መሰራታቸውን አንስተዋሉ፡፡
የዕንጦጦ ፖርክ ስራ ዜጎች አብረው በራስ ዕውቀት እና ካፒታል በተቀላጠፈ አፈፃፀም ሌሎች የልማት ትሩፉት ስራዎችን መሥራት እንደሚችሉ ሕያው ማሳያ መሆኑን በአፅዕኖት ገልፀዋለ።
‎የፕላን እና ልማት ሚኒሥቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በረከት ተሥፋ ፂዎን በበኩላቸው በጉብኝቱ የታየው የፅዱ ኢትዮጵያ ሥራ ውጤት ማሳያ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መሰረት የሚሆኑ መሰል ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የተቀናጁ፣ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የላቀና ለዘመኑ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮት ምላሽ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል።
‎የዓለም የአካባቢ ቀንን አስመልክቶ ዛሬ በተካሔደው የመሥክ ጉብኝት የተሳተፉ የተቋማት ተወካዮች እና ሰራተኞች በጉብኝቱ መደሰታቸውን የገለፁ ሲሆን አካባቢን መጠበቅ እና ማልማት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በተግባር መማራቸውን ገልፀዋል።
‎ከተሳታፊዎቹም መካከል የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ማርጋሬት ኦዱክ በጉብኝቱ መደሠታቸውን ገልፀው በእንጦጦ ደን እና በተፋሰሡ የተፈጥሮን ፀጋ፣ የማህበረሰብ ነባር ዕውቀትን ከዘመኑ ሣይንስ ጋር ተዋሕዶ የተሠራው የአካባቢ ልማት ሥራ እጅግ እንዳስደነቃቸው ተናግረዋል። ሥራው የአካባቢውን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ መሰራቱ ከአካባቢ ጥበቃ መሰረታዊ መርሕ ጋር ስምሙ ያደርገዋል ሲሉ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
‎የዓለም የአካባቢ ቀንን በአልን አስመልክቶ ዛሬ በተካሔደው የመሥክ ጉብኝት የተሳተፉ የተቋማት ተወካዮች እና ሰራተኞች በጉብኝቱ መደሰታቸውን የገለፁ ሲሆን አካባቢን መጠበቅ እና ማልማት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በተግባር መማራቸውን ገልፀዋል።
‎በጉብኝቱ ሐገር በቀል ዛፎች ሥላላቸው ዓይነተ ብዙ ጠቀሜታ፣ ከደን ልማት ጋር ቅይጥ ግብርና በማካሔድ ሥለተገኙ የፍራፍሬና ማር ምርት ውጤቶች፣ እንዲሁም የኤኮ ቱሪዝም ፋይዳን መገንዘብ ተችላል።

‎በዓለም ለ53ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የአካባቢ ቀን "ክላይሜት አክሽን" በሚል መሪ ሃሳብ በቀጣይ የአካባቢ ልማት ውጤቶችን በማሳወቅ እና ማኅበራዊ ተሳትፎን በማነቃቃት ይቀጥላል።በዕለቱ የተካሔደውን ጉብኝት የፌዴራል እና የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ኃላፊ እና ሰራተኞች፣ የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር፣ የፕላን እና ልማት ሚኒሥቴር ሚኒስትር ዲኤታ የከንቲባ ቢሮ ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል ።


‎ፅዱ ኢትዮጽያን ዕውን እናድርግ!!

Photos from በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን    FDRE Environment Protection Authority's post 05/06/2026

የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የ2018 የአለም አካባቢ ቀንን ከባለድርሻ አካላት ጋር አከበረ፡፡
ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
================
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥረልጣን የዓለም አካካበቢ ቀንን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር አካባቢ ጥበቃ ጋር በመተባበር የተለያዩ ባድርሻ አካላት፣ ተማሪዎችና መምህራን እና የተተባባሩ መንግስታት የአካባባ ፕሮግራም(UNEP) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር በደጅአዝማፍ ወንድራድ የመጀመሪያ ደረጃ በተለያ ኪነቶች በደመቀ መልኩ በአሉን አክብራዋል፡፡
በበዓል አከባበር ላይ በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች አካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮሩ ትምህርታዊ መዝሙርና ጭውውት ለታዳሚዎች ቀርበዋል፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ለሊሴ ነሜ በዓሉን በንግግር በከፈቱበት ወቅት የአካባቢ ጥበቃ ስራ ለትውልድ የሚሰራ ስራ መሆኑን በመግለጽ ከግለሰብ ጀምሮ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚያስፈልገው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ በገለጻቸው በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት እየተሰሩ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች፣ የኮሪደር ልማት እንዲሁም የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ተስፋን የሚሰጡና ጽዱ አካባቢን ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች መሆናቸውን በመግለጽ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀምና ወደ ሀብትነት በመቀየር ረገድ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት ብለዋል፡፡
ዛሬ እየተከበረ የሚገኘው የዓለም አካባቢ ቀን በየኣመቱ ዜጎች በአካባቢ ጥበቃ በቂ ትምህርትና ግንዛቤን በተሟላ መልኩ በመጨበጥ ሁሉም ዜጋ የአካባቢ ደህንነት የመጠበቅ ህገመንግስታዊ ግዴታው እንዲወጡ ከማድረግ አንፃር ወሳኝ በአል እንደሆነም ገልፀዋሉ፡፡
የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር ዶ/ር እሸቱ ለማ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደገለጹት የአለም የአካባቢ ቀን በየዓመቱ እ.ኤ.አ June 5 በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር ገልጸው የአካባቢ ጥበቃ ማለት የምንኖርበት አካባቢን መጠበቅ መሆኑን በመግለጽ በዓለማችን ላይ የሚከሰቱ በአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች አገራችን ተጎጂ መሆኗን በመግለጽ ይህንን ተግዳሮት ለመቀልበስ በሀገርአቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች አይነተኛ ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የUNEP ካንትትሪ ዳይሬክተር ዶ/ር ማርጋሬት በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸመች መሆኗን በመግለጽ ይህንን ለማስቀጠል የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲሁም የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የጽዳት ዘመቻ እና በበዓሉ ላይ ያተኮሩ የጥያቄ መልስ ውድድር በተማሪዎች መካከል በማካሄድ ለተማሪዎች ማበረታች ሽልማት በመስጠት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡
የዘንድሮ የአለም አካባቢ ቀን በ154 ሀገራት በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ53 ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ “Climate Action’’ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

03/06/2026

የዓለም የአካባቢ ቀን በሀገራችን ግንቦት 28/2018 በተለያዩ ኩነቶች ይከበራል።
ግንቦት 27/2018
አዲስ አበባ
============
የዓለም የአካባቢ ቀን በየዓመቱ ግንቦት 28 ይከበራል፡፡ የዘንድሮ የዓለም አካባቢ ቀን “Climate Action’’ በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ53ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይከበራል።

የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ሁኔታ እና የበአሉ አስፈላጊነትን በተመለከተም ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት የምታበረክተው አስተዋጽኦ ከ 0.5% በታች ቢሆንም፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለሚከሰቱት ተደጋጋሚ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ የደን መመናመንና የመሬት መራቆት በእጅጉ ተጋላጭ ናት። እነዚህ ተግዳሮቶች በዝናብ ጥገኛ በሆነው ግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በውሃ ሀብታችን እና በገጠሩ ማኅበረሰብ የኑሮ ሁኔታ ላይ ቀጥተኛ ስጋት ደቅነዋል። በመሆኑም “Climate Action’’የሚለው መሪ ቃል ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም ያለው። የአገራችን አየር ንብረት ለውጥ ምላሽ በሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትክረት በማድረግ እየተሰሩ ይገኛሉ፦
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር፦ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋኑን ወደ 23.6% አሳድጋለች።

የ2018 ዓ.ም ትኩረታችን የችግኞችን የመጽደቅ መጠን ማሻሻል፣ ዘላቂ የተፋሰስ ልማት እና የረጅም ጊዜ ሥነ-ምህዳራዊ ጥቅሞችን ማረጋገጥ ላይ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ግብርና እና የውሃ ልማት፦ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወደ አፈር ጥበቃ፣ መስኖ ማስፋፋት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም (climate-smart) አሠራሮች መሸጋገር።
ወደ አረንጓዴ ኢነርጂ/የሐይል ምንጭ ሽግግር፦ ከ95% በላይ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ስኬታችንን መሰረት በማድረግ፣ ንጹህ ኃይልን ወደ ትራንስፖርት እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማስፋፋት።
የከተሞች ጽዳትና ውበት፦ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እና የከተማ አረንጓዴ መሠረተ-ልማትን ማጠናከር እና ከከተሞች የሚወጣውን የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት በመቀነስ።

ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ፋይናንስ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለእውቀት ማሳደግ አጋርነትን ማጠናከር።
የዘንድሮ የዓለም አካባቢ ቀን ሲከበርም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም መላው የህብረተሰብ ክፍል የሚከተሉትን ተግባራት ከግምት ውስጥ በማስገባት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኞችን መትከል እና መንከባከብ።
ዘላቂ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ሥርዓትን መከተል።
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ላይ በንቃት መሳተፍ።
ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ እና የሚበሰብሱ የእቃ መያዣዎችን በመጠቀም፡፡
ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ፋይናንስ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለእውቀት ማሳደግ አጋርነትን ማጠናከር።
የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ግንዛቤዎችን ማስፋፋት፡፡
በወንዝ ዳርቻ ልማት እና በኮሪዶር ማስፋፊያ ስራዎች የተገኙ ውጠየቶችን ለመጠበቅ እና ለማስፋት በሚደረግ ርብርብ ጠንካራ ተሳትፎ ማድረግ፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ጽዱ ኢትዮጵያ ባህል እናደርግ

Photos from በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን    FDRE Environment Protection Authority's post 20/05/2026

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የአደገኛ ኬሚካል ማከሚያ እናማስወገጃ ጣቢያ ዲዛይንና ጥናት ላይ የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።
ግንቦት 2018ዓ.ም
አዲስአበባ
============
አካባቢያዊ ተቀባይነት ያለው የአደገኛ ኬሚካል ማከሚያና ማስወገጃ ጣቢያው የዲዛይንና ጥናት ስራውን የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፖሊሲ ጥናትሰነድ ኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር አዘጋጀ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በባለድርሻ አካላት ውይይቱ ላይ እንደገለፁት ኬሚካል ለኢኮኖሚያዊ ልማት እና እድገት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት በመግለፅ ሆኖም ኬሚካል አካባቢያዊ ተቀባይነት ባለው መንገድ ካልተያዘ በሰውና አካባቢ ጤና ላይ ሊቀለበስ የማይችል ጉዳት እንደሚያደርስ ጠቁመው የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ለተለያዩ የምርት ግብዓቶች ወደ ሀገራችን ገብተው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች የማስወገድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመዋል።
ወ/ሮ ፍሬነሽ በገለፃቸው ሀገራችን በአደገኛ ቆሻሻ የሚከሰተውን ችግር ተቋማዊና ዘላቂነት ባለው መንገድ ለመፍታት እንዲሁም የአካባቢ መብቶች ፣ግቦች እና ዓላማዎች እንዲሁም በህገ መንግስቱ እና የአካባቢ ፖሊሲ ላይ የተቀመጡት መሰረታዊ የአካባቢ ፖሊሲዎች ለመተግበር የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ ከማድረግ በተጨማሪ የአደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ ተቋም በሀገር አቅም ለመገንባት የሚያስችል የጥናትና ዲዛይን ስራ መጠናቀቁን በመግለፅ ለጥናትና ዲዛይን ስራው የተባበሩ አካላትን አመስግነዋል ።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ፍቃዱ ፀጋ በበኩላቸው የአደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ ተቋም የጥናትና ዲዛይን ግንባታ ስራው ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በጥምረት መሰራቱን በመግለፅ ለጥናቱ መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል። የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችን ብሎም የምርምርና አቅም ግንባታ ስራዎችን በዋናነት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ የአደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ ተቋም ግንባታ ጥናትና ዲዛይን ስራው በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ማለትም የአደገኛ ቆሻሻን ከምንጩ ማከም፣የዲዛይን ስራውን መስራት እንዲሁም የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ላይ በማተኮር ሰነዶች የተዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል ።
በመድረኩ ላይ የአደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ ተቋም ጥናትና ዲዛይን ሰነዶቹ ላይ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ተቋማት ሙያዊ አተስያየት የሰጡበት እና ለጥናቱ ተጨማሪ ግብዓቶች ተሰጥተውታል ።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Niger Street
Addis Ababa
12760