04/06/2026
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
ግንቦት 27/2018 ዓ.ም(የሰላም ሚኒስቴር)፤ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በውጭ ግንኙነት መምሪያ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒ ሴቭሪዩክ የተመራውን የልዑካን ቡድን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በሁለቱ ሀገራት፣ ህዝቦች እና አብያተ ክርስቲያናት መካከል ዘመናትን ያስቆጠረ እንዲሁም ልዩ የሆነ ሰላማዊ አብሮነትን ያጎላ ለዓለም ምሳሌ የሆነ
የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ይህም በትብብር ለመስራት የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑን በአፅንኦት ገልፀዋል።
የቮሎኮላምስክ ሜትሮፖሊታን እና የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሞስኮ ፓትርያርክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሊቀ መንበር የሆኑት ብፁዕ አንቶኒ ሴቭሪዩክ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በተደጋጋሚ ወደ ተጠቀሰችው ታሪካዊት ሀገር ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በመምጣታቸው ጥልቅ የሆነ ደስታ እና ክብር እንደተሰማቸው ገልጸው በሩሲያ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን አመላክተው፤ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም በሀገራቱ መካከል ለሚኖረው ታላቅ የወደፊት ተስፋ ማረጋገጫ መሆኑን ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ /ር ከይሬዲን ተዘራ፣ በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ከፍተኛ አማካሪ አቶ አሌክሴ ቼስኖኮቭ፣ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት መምሪያ የክርስቲያናዊ ግንኙነት ጉዳዮች ጸሐፊ ሂሮሞንክ ስቴፋን፣ የብፁዕ አቡነ አንቶኒ የግል ረዳት ቄስ አሌክሳንደር ኤርሾቭ፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሊቃውንት ጉባዔ አባል እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌስር ቀሲስ መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ተገኝተዋል።
Honorable Mr. Mohammed Idris, the Minister of the Ministry of Peace, received the delegation of the Russian Orthodox Church at his office and had discussions.
June 4/2026 (Ministry of Peace): The Minister of Peace, Honorable Mr. Mohammed Idris, received in his office the delegation led by the Chairman of the Department of External Church Relations of the Moscow Patriarchate of the Russian Orthodox Church, His Holiness Mr. Anton Sevryuk.
During their meeting, Honorable Mr. Mohammed Idris emphasized that the two countries, people, and churches have a close relationship that has been going on for centuries and that emphasizes a unique peaceful coexistence that is an example to the world, and that this is of great importance for working together.
The Metropolitan of Volokolamsk and the Chairman of the Department of External Church Relations of the Moscow Patriarchate of the Russian Orthodox Church, his Holiness Anton Sevryuk, expressed his deep joy and honor in coming to the historical country of Ethiopia, which is frequently mentioned in the scriptures, for the first time. His Holiness pointed out that the relationship between the Russian and Ethiopian Orthodox Churches has been going on for a long time and said it is proof of the great future between the two churches and countries.
State Minister for Peace Building and National Consunsus at the Ministry of Peace, Dr. Keiredin Tezera; Senior Counselor of the Russian Embassy in Ethiopia, Mr. Aleksei Chesnokov; Secretary for Inter-Christian Relations of the Department of Foreign Relations of the Russian Orthodox Church, Hiromonk Stefan; Personal Assistant of the Chairman of Metropolitan Anthony, Priest Aleksandr Ershov; President of Holy Trinity Theological University and Archbishop of South Omo and Ari Zone Diocese, His Holiness Abune philipos as well as the member of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church and the teacher and researcher of the Holy Trinity Spiritual University, Assistant Professor Daniel Seife Michael, were present at the discussion.

04/06/2026
03/06/2026
02/06/2026
02/06/2026