Ethiopian Agricultural Transformation Agency

Call Directions Website Contact the organization

Ethiopian Agricultural Transformation Agency Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Agricultural Transformation Agency, Public & Government Service, Addis Ababa.

The ATI was established in 2010 to drive agricultural transformation by supporting governmental, non-governmental, and private sector partners to effect change.

🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼
10/09/2026

🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼

Call for Scientific Paper!
10/09/2026

Call for Scientific Paper!

09/09/2026

#ፋና #ኢትዮጵያ

09/09/2026

#ፋና #ኢትዮጵያ

09/09/2026

#ፋና #ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ግ.ት.ኢ) ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ለሶማሌ ክልል  ብሔራዊ የግጦሽ መሬት ጤና ክትትል ሲስተምን (NRMS)  ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በ...
06/09/2026

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ግ.ት.ኢ) ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ለሶማሌ ክልል ብሔራዊ የግጦሽ መሬት ጤና ክትትል ሲስተምን (NRMS) ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በጅግጅጋ ከተማ በይፋ አስጀምሯል። በ ግ.ት.ኢ የላይቭስቶክ ኮሜርሻላይዜሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ዮሴፍ መካሻ እንደገለጹት፣ ሲስተሙ በሳይንሳዊና ወቅታዊ የመረጃ አቅርቦት ላይ ተመስርቶ ዘላቂ የግጦሽ መሬትና የእንስሳት ሀብት አስተዳደርን ለመደገፍ እንዲሁም የአየር ንብረት ተጽዕኖን የመቋቋም አቅምን ለማጠናከር ያስችላል። በተጨማሪም ATI እና አጋሮቹ ሲስተሙን በተለያዩ አካባቢዎች በማስፋፋት ረገድ ያስመዘገቡትን እመርታ ጠቅሰው፣ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን፣ በአፋር ክልል እና በድሬዳዋ አስተዳደር ዲዛይኑ ተጠናቅቆ፣ በይፋ መጀመሩን ገልጸዋል።

የሶማሌ የእንስሳትና ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ሸሪፍ በበኩላቸው፣ አስተማማኝ የግጦሽ መሬት መረጃ መኖሩ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የመሬት መራቆትና ወራሪ አረሞች በግጦሽ መሬቶች ላይ እያሳደሩት ያለውን ተጽዕኖዎች በማንሳት ይህ ሲስተም እነዚህን ችግሮች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመካላከል ወሳኝ ነው ብለዋል። የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታን የወከሉት ወ/ሮ ጸጌረዳ ፈቃዱም በብሔራዊ ደረጃ የተቀናጀና በሳይንሳዊ መሠረት የተደገፈ የክትትል ሥርዓት አስፈላጊነትን አስገንዝበዋል።

የግ.ት.ኢ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር ፍሬው ተገኘ ፣ በበኩላቸው፣ ዛሬ ይፋ የሆነው የግጦሽ መሬት አያያዝና አጠባበቅ ሲስተም በተቀናጀ አስተዳደር፣ ቀጣይነት ባለው የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና በጠንካራ ትብብር ላይ በመመሥረት ዘላቂ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ገልጸው ሁሉም አካላት ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት የአርብቶ አደሩን ማኅበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል በጋራ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሃ ግብሩ የሲስተሙን ዲዛይንና ልማት በማካሄድ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች ገለጻዎች አቅርበዋል። በመጨረሻም በኢትዮጵያ የእንስሳት እርባታ ማህበር ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዳንኤል ተመስገን እና በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ጸሐዬ የተመራ አጠቃላይ ውይይት ተካሂዷል።

📌Website: https://ati.gov.et/
📌Facebook: Ethiopian Agricultural Transformation Agency
📌Twitter or X:
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/posts/ethiopianata
📌YouTube: www.youtube.com/

በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ፍሬው ተገኘ  የተመራ የልዑካን ቡድን፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ውስጥ በተፈናቃዮች...
04/09/2026

በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ፍሬው ተገኘ የተመራ የልዑካን ቡድን፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ውስጥ በተፈናቃዮች እና በአካባቢው ማህበረሰቦች ላይ በኦሮሚያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ማዕከል አማካኝነት እየተተገበሩ ያሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ–ልማት–ሰላም (HDP Nexus) ተግባራትን ጎብኝቷል።

በጃለሌና ገመቺስ ቀበሌ የሚኖሩ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ ተፈናቃዮች፣ ከምግብ ዕርዳታ ጥገኝነት ወደ ራስን መቻልና ምርታማነት እንዲሸጋገሩ ላደረገው ድጋፍ ኤቲአይንና አጋሮቹን አመስግነዋል። ተጠቃሚዎቹ በማሽላና በሐብሐብ ምርት እንዲሁም በፍየል ማድለብ ሥራዎች በመሰማራት ኑሯቸውን እያሻሻሉ ይገኛሉ።

በጉብኝቱ ወቅት ፕሮፌሰር ፍሬው በሰጡት አስተያየት፣ የHDP Nexus አቀራረብ ተፈናቃዮችና አስተናጋጅ ማህበረሰቦች ዘላቂ የኑሮ መሠረት እንዲገነቡ፣ ራሳቸውን በምግብ እንዲችሉና ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲሰሩ እያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል። የተገኘው ውጤት በተጠቃሚዎች፣ በአጋር አካላትና በአካባቢው አስተዳደር ትብብር የተገኘ በመሆኑ ተጨማሪ ትብብር እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።

ልዑኩ በተጨማሪም በቆላጂ አካባቢ የሶማሌ ልማት ማህበር በመተግበር ላይ ያለውን ፕሮጀክት ጎብኝቷል። በዚህም ተፈናቃዮች በካፍቴሪያ አገልግሎት በመሰማራት ገቢ እያገኙ ከመሆናቸውም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ፕሮፌሰር ፍሬው የፕሮግራሙን ድጋፍ ላደረገው ለዴንማርክ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (DANIDA) ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

📌Website: https://ati.gov.et/
📌Facebook: Ethiopian Agricultural Transformation Agency
📌Twitter or X:
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/posts/ethiopianata
📌YouTube: www.youtube.com/

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት  ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴና የኦሮሚያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ሲኒየር ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ዱጉማ ከዞኑ የመንግሥት አ...
25/08/2026

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴና የኦሮሚያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ሲኒየር ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ዱጉማ ከዞኑ የመንግሥት አመራሮች ጋር በመሆን የኢንስቲትዩቱ የማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባር አካል የሆነውን የመዋዕለ ሕፃናት ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ ያቤሎ ወረዳ፣ አረሪ ቀበሌ አስቀምጠዋል።

በመርሀግብሩ ወቅት ዶ/ር ማንደፍሮ እንደገለጹት፣ ኢንስቲትዩት ትኩረቱን በግብርና ትራንስፎርሜሽን ላይ ብቻ ሳይወስን የገጠሩን ብሎም የአርብቶ አደር ማኅበረሰቦችን አቅም በማጎልበትና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ መሰረተ-ልማት በመስራት ትራንስፎረሜሽኑን ሊያስቀጥሉ የሚችሉ ብቃት ያላቸውን ትውልድ ለመፍጠር ተግቶ ይሰራል። ትምህርት ቤቶችንና መሰረተ ልማቶችን መገንባት የነገዋን ኢትዮጵያ የሚገነባ የሰው ኃይል ለማፍራት ወሳኝ መሠረት መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ግንባታው ከ2019 የትምህርት ዘመን በፊት ተጠናቆ፣ ሙሉ በሙሉ በቁሳቁስ ተሟልቶ ሕፃናትን ለመቀበል ዝግጁ እንዲሆን ታቅዷል። ዶ/ር ማንደፍሮ ፕሮጀክቱ በወቅቱ እንዲጠናቀቅ የአካባቢው አስተዳደርና ማኅበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በተጨማሪም 160 ለሚሆኑ የአካባቢው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። በተያያዘም ከያቤሎ ከተማ ለተመረጡ ወጣቶች በአዎንታዊ አስተሳሰብና በአመራር ክህሎት ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተካሂዷል።

📌Website: https://ati.gov.et/
📌Facebook: Ethiopian Agricultural Transformation Agency
📌Twitter or X:
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/posts/ethiopianata
📌YouTube: www.youtube.com/

እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
24/08/2026

እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251115570678

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Agricultural Transformation Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Agricultural Transformation Agency:

Shortcuts

Share