26/02/2022
ALERT Center አለርት ማዕከል
This is the official Facebook account of All Africa Leprosy TB Rehabilitation and Training Center (ALERT Center). ALERT HOSPITAL
ALERT CENTER was established in 1932 by philanthropist for treatment of leprosy. After a period of time due to the case of leprosy emperor Haile Selassie I make it a treatment center for leprosy disease in 1934 and was named princess Zenebework Memorial Hospital
As a result of due attention to leprosy in Ethiopia and other African countries many non governmental organization starts participating o
26/02/2022
03/02/2022
01/02/2022
በኢትዮጵያ ለ23ኛ በዓለም ለ68ኛ ጊዜ የሚከበረው አለማቀፍ የስጋ ደዌ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡
ዓለማቀፍ የስጋ ደዌ ቀን World Leprosy (Hansen’s Disease) Day የስጋ ደዌ በሽታን አንዘንጋው /Don’t forget Leprosy/ በሚል መሪ ቃል ጥር 21 እና 22/2014 ዓ.ም በፓናል ውይይትና የተሰሩ ስራዎችን ጉብኝት በማድረግ ተከብሮ ውሏል፡፡
ለዚህም የኢትዮጵያ ሥጋ ደዌ ተጠቂዎች ብሄራዊ ማህበር አካል ጉዳተኞች ማህበርን በመተባበር ከሌሎች አጋር አካላት ጋር የሥጋ ደዌ ቀን በዋዜማ በአለርት ሆስፒታል ስለ ሥጋ ደዌ ታካሚዎች በሆስፒታሉ እየተሰሩያሉትን ሥራዎች በ4 ቡድን በመከፋፈል በሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ ማምረቻ በመኝታ ክፍሎች ፣በሆስፒታሉ ለታካሚዎችና ለሰራተኞች ምቹ የማረፊያና የመገልገያ ቦታዎችን ሌሎች ስራዎችን ከየክልሉ በመጡና ከአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞችና ከይታወቅልን የአካል ጉዳተኞች ማህበር እንዲሁም ከሌሎች ብሄራዊ ማህበሮች ተገኙ ሃላፊዎች በሆስፒታሉ ተገኝተው አለርት ሆስፒታል ስለ ህክምናውና ለአካል ጉዳተኞች ድጋፉ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የሥጋ ደዌ ተጎጅዎች ብሔራዊ አካል ጉዳተኞች ማህበር የገቢ ማስገኛ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ1 ጀሞ1ውስጥ የሚገኘውን ባለ 5 ወለል ህንፃ ለመጎብኘት ጉዞ ባደረጉበት ወቅት መንፈስን የሚያረካ፣ አዕምሮን የሚያጠናክር ሥራ ተሰርቶ ከዓመት ዓመት ለውጥ አምጥቶ በመገኜቱ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የማህበራትና የተቋማት የስራ ሃላፊዎች ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በፓናል ውይይቱ ላይ መወያያ ፁሁፎች ቀርበው የስጋ ደዌ በሽታ መዘንጋት እንደሌለበትና የስጋ ደዌ ተጠቂዎችን በተለያዩ ስልጠናዎች የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራትና በሃገር ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥ ሃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ የውይይቱ ዋና ዋና ሃሳቦች ነበሩ፡፡
14/01/2022
አለርት ሆስፒታል በ2014 በጀት ዓመት በስድስት ወራት በተከናወኑ ክንውኖች እና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ከጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ፡፡
ጥር 06/2014 ዓ.ም በስድስት ወራት በተከናወኑ ክንውኖች በተደረገው ውይይት ላይ ተገልጋዩ ማህበረሰብና ሰራተኛው የሚያነሳቸውን ችግሮች በመለየት የበላይ አመራሩ መፍትሄ ለመስጠት ግብዓት የሚያገኝበትና መልካም ጎኖችን በማጠናከር በየጊዜው ከሰራተኛው ጋር የግንኙነት መድረኮችን በማዘጋጀት የህክምና አገልግሎቱን ለማዘመን የጤና ባለሙያው ብቻ ሳይሆን ድጋፍ ሰጭ ሰራተኛውም በትኩረት የሚሰራበት እንደሚሆን የማዕከሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አብራርተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ አለርት ሆስፒታል በቅርብ ጊዜ እያሳየ ያለው ለተገልጋይና ለሰራተኛው የህክምና ቦታዎችን ምቹ፣ፅዱና ውብ በማድረግ የህክምና አገልግሎትን ለማዘመን የበላይ አመራሩ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚደነቅና በተለይ የበታች ሰራተኞችን ትኩረት በመስጠት በተቋሙ ብዙ ለውጦችን በማየትና ከዚህ በፊት ያልተለመደ ለዝቅተኛው ሰራተኛ የበዓል ስጦታዎች መደረጋቸውን የሆስፒታሉ ሰራተኞች አመስግነዋል፡፡
በመጨረሻም በሆስፒታሉ የሚታዩ የሰራተኛ የመድሃኒት እጥረቶችን፣የህፃናት ማቆያ ቦታዎችን፣የጥቅማጥቅም አቅርቦትን እና ሌሎችንም ከተገልጋዩና ከሰራተኛው የሚነሱ ጥያቄዎችን በቀጣይ የሚፈቱ መሆናቸውን ማብራሪያ ተሰጦባቸዋል፡፡
በፌስ ቡክ ገፃችን ይከታተሉን!
11/01/2022
Advanced Leprosy TOT training For International Trainees began in ALERT center, which includes 6 trainees from Somalia, 1 from Uganda and 1 from Ethiopia. The training lasts for 12 days, starting from January 03/2022. It is organized by GLRA in collaboration with ALERT CPD Center
Dr. Nurhusen kedir Quality and innovation Development General Director .His speech saying that first the trainees "welcome to your home” then he briefly introduce about ALERT , ALERT General Specialized Hospital is the only institute that has Leprosy trained trainees from Africa and other countries for many years. This training facility is accredited by the World Health Organization.
The institute is currently working to grow into a college, but it continues to focus on preventing the spread of infectious diseases that have been known for years. He further said, "I hope you will put this knowledge, skills and experience into practice."
28/12/2021
E-shining hope የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአለርት ሆስፒታል ሲታከሙ ለነበሩ እና ተደራራቢ የአካል ጉዳት ላለባቸው ሶስት(3) ተገልጋዮችን መልሶ ለማቋቋም ለእያንዳንዳቸው የዊልቸርና የ7500 ብር የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በተጨማሪም ለ19 ችግርተኛ ታካሚዎች ለምግብ፣ለመድሃኒት፣ለምርመራና ለትራንስፖርት ወጭ መሸፈኛ የሚሆን የ36,000 (የሰላሳ ስድስት ሺ) ብር በሆስፒታሉ የሶሻል ኬዝ ቲም መሪ በኩል ለታካሚዎች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የተለያዩ የጤና መረጃዎችን እና ሌሎች ክንውኖችን ለማግኘት አዲስ የተከፈተውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!
08/03/2021
በአለርት የስልጠና ማእከል የሚሰጡ ስልጠናወችን ለማየትና ለመመዝገብ ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ ማግኘት ይችላሉ፡
facebook
https://m.facebook.com/ALERT-CPD-Center-105138368143159/
Telegram
t.me/alertcpd
website
alertethiopia.org/training-center
Alert Center | Home HomeWELCOME TO ALERT CPD CENTERThe All African Leprosy Rehabilitation and Training Center (ALERT) was established in 1934 to serve as a specialized clinical research and training center for Ethiopia, Africa and beyond on Leprosy, TB and other relevant infectious diseases. ALERT comprises of two big....
23/02/2021
የአለርት ሆስፒታል ከጤና ሚ/ር ክሊኒካል ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የቆዳ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በሃገሪቱ በተመረጡ ከ20 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የቆዳ ህክምና አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያስችል ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ማዕከሉ ባለው ልዩና ከፍተኛ ሙያ በስጋ ደዌ፣ በቆዳ ህክምና፣ በፕላስቲክ ሰርጀሪ፣የቲቢ በሽታ፣ ኤች.አይ.ቪ./ኤ.ዲ.ስ፣በእናቶችና ህፃናት ጤና፤ የድንገተኛ አደጋዎች ህክምና እና ሌሎች ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ በማተኮር ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካና ለሌሎች አገሮች የህክምና፣ የምርምርና የስልጠና አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ሚና ሲጫወት የነበረ ተቋም ነው፡፡
በዚህም ሆስፒታሉ ግንባር ቀደም የህክምና ተቋም ስለሆነ የህክምና አገልግሎቱን በሃገሪቱ ባሉ ሆስቲታሎች ተደራሽ ለማድረግ ከተመረጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል በቆዳ ህክምና ላይ ከተለያዩ የሃገሪቱ ሆስፒታሎች የተውጣጡ ሃኪሞችን ስልጠና መስጠት ተጀምሯል፡፡
ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የአለርት ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን እንደገለፁት ‹በቆዳ ህክምና አገልግሎት ተገልጋዮች ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተው ወደ ህክምና በሚመጡበት ጊዜ ከአካል ጉዳት በተጨማሪ ለሞትም የሚያደርስ ጉዳት እየደረሰባቸው በመሆኑ ይህንን የህክምና አገልግሎት በሁሉም ሆስፒታሎች ተደራሽ ከማድረግ አኳያም የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሰው ኃይልን ከማሰልጠንና በክፍተቶች አሸጋሽጎ ለመጠቀም ከጤና ሚ/ር ክሊኒካል ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የተለያዩ ድጋፎችን ለሆስፒታሎች ድጋፍ ለማድረግና ለማገዝ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡
በዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፉ ሃኪሞችም በሚገባ ስራ እንዲሰሩ የሚደረግና ሰልጥነው ካጠናቀቁ በኋላ በቆዳ ህክምና ላይ ችግር የሚገጥማቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች በሚገባ እንዲረዱ ይደረጋል፤ ለዚህም የቆዳ ህክምና አገልግሎት በሆስፒታሉ ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በየተቋሙ አገልግሎቱ ጥራቱን ጠብቆ የተሳለጠ አገልግሎት እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
በማዕከሉም የሚሰጡ ተጨማሪ አገልግሎቶችን በቆይታ ጊዜያችሁ ጉብኝት በማድረግ ተጨማሪ እውቀቶችን የምታገኙበት ነው›፤በዚህም ለአንድ ወር የሚቆየውን ስልጠና አስጀምረው መልካም የስልጠና ጊዜ ይሁንላችሁ› ሲሉ የማዕከሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ‹በስልጠናው ቆይታ በምታደርጉበት ጊዜ ክሊኒካል ሰርቢሱ ላይ በተግባር የምታዩበትና ሪፈር ከማድረጋችሁ በፊት እንዴት ማየት አለብን የሚለውን ማወቅ ወሳኝ ነገር ነው› በማለት የማእከሉ የቆዳና አባለዘር ህክምና ሃላፊው ዶ/ር ሽመልስ ንጉሴ አብራርተዋል፡፡
15/02/2021
አለርት ሆስፒታል ከጤና ሚ/ር ጋር በመተባበር መሰረታዊ የዓይን ህክምና አገልግሎት ባልጀመሩ ሃያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የዓይን ህክምና አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችል ስልጠና በይፋ ተጀምሯል፡፡
ስልጠናውን ያስጀመሩት የአለርት ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን እንደገለፁት ‹ሆስፒታሉ ወደ ኮሌጅ እያደገ በመሆኑ ተቋሙ ከያዛቸው ዋና ዋና ስራዎች አንዱ የዓይን ህክምና አገልግሎት ነው፤ይህንን የህክምና አገልግሎት በክልል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እንዲሰጥ ለማድረግ የማሰልጠኛ ማንዋሎችን በማዘጋጀት ስልጠናውን አስጀምረናል፤በዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፉ ሃኪሞችም በሚገባ ስራ እንዲሰሩ የሚደረግና ሰልጥነው ካጠናቀቁ በኋላ የድንገተኛ ዓይን ችግር የሚገጥማቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች በሚገባ እንዲረዱ ይደረጋል፤በዚህም ለአንድ ወር የሚቆየውን ስልጠና አስጀምረው መልካም የስልጠና ጊዜ ይሁንላችሁ› ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ጤና ሚ/ር የህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ከነዚህም መካከል ዋነኛው የስፔሻሊቲና ሰብስፔሻሊቲ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ከማሻሻል አንፃር ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡
ለዚህም የመሰረታዊ የዓይን ህክምና አገልግሎት ተደራሽ ከማድረግ አኳያም የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሰው ኃይልን ከማሰልጠንና በክፍተቶች አሸጋሽጎ ለመጠቀምና ጤና ሚ/ር የተለያዩ ድጋፎችን ለሆስፒታሎች ድጋፍ ለማድረግና ለማገዝ የተዘጋጀ እና ስልጠናው በየደረጃው ቀጣይነት ያለው መሆኑን የሚ/ር መስሪያቤቱ የክሊኒካል ዳይሬክቶሬት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ማርቆስ ፃውሎስ አብራርተዋል፡፡
15/02/2021
በአለርት ሆስፒታል የካችመንት ትስስርን ለማጠናከር ከክፍለ ከተማ ሃላፊዎች፣ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ከጤና ጣቢያ ሃላፊዎችና ከአካባቢው ፖሊስ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የማዕከሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን በዕለቱ ከተገኙት እንግዶች ጋር ትውውቅ በማድረግ የካችመንት ትስስሩን ለማጠናከርና ከዚህ በፊት የነበረውን የግንኙነት ስርዓት ለማሳለጥ በትኩረት ተወያይተዋል፡፡
በዚህም ከተለያዩ ተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን በቀጣይ መፍትሄ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራና ለወደፊት በሚደረጉ የውይይት መድረኮች ላይ ከጤና ጣቢያዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ መፍትሄዎችን በመስጠት መቀጠል አለብን ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
29/01/2021
የ22ኛውን የስጋደዌ ቀን አከባበር አስመልክቶ በአለርት ሆስፒታል የስጋ ደዌ ታካሚዎች የሚያነሱትን ችግሮች ለመቅረፍ ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
በቅድሚያ ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን እራሳቸውን ለህብረተሰቡ ካስተዋወቅ በኃላ በመክፈቻ ንግግራቸው ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የዕለቱን ፕሮግራም በይፋ አስጀምረው እንዲሁም ማዕከሉ ከስጋ ደዌ ሕክምና ባሻገር በዓይን ሕክምና"በቆዳ ሕክምና "በፕላስቲክ ሰርጀሪ "ድንገተኛ አዳጋ ህክምና እንዲሁም የፊዚዮ ቴራፒና ራስን የማገዝ -ኦክፔሽናል ቴራፒ እነዚህ በይበልጥ ጎልተው በአገር አቀፍ ደረጃ እንደ ሞዴል ማስተማሪያ እንዲሆኑና እንዲቀጥሉ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም እስካውን ድረስ ለህክምናው የበኩላቸውን አስተዋፆ ሲያበረክቱ ለቆዩት የማዕከሉ የጤና ባለሙያዎች ፣ለማህበራት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረውን የስጋ ደዌ ቀን ለመዘከር ‹‹ሥጋ ደዌን እንግታ ፤መገለልን እናቁም "ለስጋ ደዌ ተጠቂዎች ስነልቦናዊ ጤንነት እንቁም››በሚሉ ሐሳቦች ዙሪያ የ2013ዓ.ም የስጋ ደዌ ቀን ከሚመለከታቸው የስጋ ደዌ ማህበራት፣ከታካሚዎች እና ከተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች ጋር በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡
የአለርት ማዕከል የሆስፒታል አገልግሎት እየሰፋ የመጣው እንዱም በአገር አቀፍ ደረጃም ሆነ እንደ አህጉራችን አፍሪካ ያለውን አስተዋፅኦ እንዲወጣ እና የአገልግሎት ጥራትን ለማምጣት በከፍተኛ ደረጃ የአጋር ድርጅቶችን ድጋፍ እንደሚሻ እና በተጠናከረ ሁኔታ ለመስራት እንደሚረዳ የአለርት ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን ገልፀዋል፡፡
በዚህም ሆስፒታሉ ከሥጋ ደዌ ክህምና አንፃር ታካሚዎች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ለማድርግ እና ከበሽታው አንጋፋነት አንፃር እንዲሁም በሽታው በባክቴሪያ እምደሚመጣ የታወቀው የዛሬ አንድ መቶ አምሳ ዓመት ገደማ እንደሆነ ፤እንደ እ.ኤ.አ 1940 የበሽታው መድኀኒት እንደተገኘና እንደ እ.ኤ.አ1950 የሥጋደዌ ቀን መከበር እንደተጀመረ እንዲሁም ሆስፒታሉ ከስጋደዌ ታካሚዎች ሕክምና ጋር የህክምና አገልግሎቱን እኩል ተደራሽ ለማድርግ ተጨማሪ አገልግሎቶችን በላብራቶሪ ፓቶሎጂ ምርመራ "በአጥንት ሕክምና ተጨማሪ ህክምና ለመስጠት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ የማዕከሉ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ዶ/ር ሽመልስ ንጉሴ ዕለቱን በተመለከተ ባቀረቡት ጽሑፍ አብራርተዋል፡፡
በዕለቱም በማዕከል ደረጃ ሥጋ ደዌን ለመግታት የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ እያከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀረቡት ዶ/ር መንግስቱ ጉርሙ ስጋ ደዌ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ ህመም ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ትኩረት እያጣና በሽታውን ወደ መቆጣጠር ደረጃ እየቀነሰ እየመጣ እንደሆነ ገልፀው በከፍተኛ ደረጃ በህብረተሰቡና ህክምናውን በሚሰጡ ባለሙያዎች ለህክምናው ተነሳሽነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም እለቱን አስመልክተው ከሥጋ ደዌ ተጠቂዎች ማህበራት ፣ከአጋር አካላት እና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ሆስፒታሉ ስላለው ግንኙነትና በሥጋ ደዌ ህክምና አሰጣጥ ላይ በተነሱ ውይይቶችና አስተያይቶች በሚመለከታቸው ሃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
25/01/2021
ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን ሃሰን በአለርት ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተመድበዋል፡፡
ዶ/ር እስማኤል በሙያቸው ኢንተርኒስት እና ኢንቴንስቪስት ናቸው፡፡
ከዚህ በፊት ለ18 አመታት ያህል በተለያዩ የህክምና ተቋማት በመምህርነት ያገለገሉ ሲሆኑ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የክሊኒካል ገቨርናንስና ኳሊቲ ዳይሬክተር በመሆን፣ በአቤት ሆስፒታል በዋና ስራ አስኪያጅነት፤ እንዲሁም በቅርቡ የኮቪድ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ በሚገኜው ሚሊኒየም አዳራሽ ኮቪድ ሴንተር አደራጅና ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሰርተዋል፡፡
ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን አለርት ማዕከልን ታካሚና ባለሙያ ተኮር ተቋም አድርገው ለመገንባት በእቅድ እንደሚሰሩ ገልፀው ፤ በዚህም በዋናነት ሆስፒታሉ የሁሉንም ታካሚዎች ፍላጎት ያለዕንግልት በተቀናጀ ሁኔታ ሊያሟላ የሚችል ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም የአለርት ሰራተኞችና አመራሮች ለረጅም ጊዜ ከማህበረሰቡ ጋር ሲያከናውኑ የነበሩትን ስራዎች ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ገልፀዋል፤ለዚህም የአለርት ማዕከል ሰራተኞችና አመራሮች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa, Ethiopia Kolfe Keraniyo Zenebework Area
Addis Ababa
P.O.BOX165
