Ministry of Planning and Development - Ethiopia

Ministry of Planning and Development - Ethiopia

Share

This page provide information about activity's that took place at FDRE Ministry of Planning and Dev't

Photos from Office of the Prime Minister-Ethiopia's post 05/06/2026

ጋዜጣዊ መግለጫ
ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም
‎አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ


05/06/2026

የአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ የወንዝ ዳርቻዎችን ከማስዋብ ያለፈ ፋይዳን የያዘ ፕሮጀክት ነው!

05/06/2026

በማያቋርጥ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ለሁሉም የምትሆን ዘመናዊና የበለፀገች ኢትዮጵያን መገንባታችንን እንቀጥላለን!

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 03/06/2026
02/06/2026

''በአፍሪካ ቀዳሚውን እድገት እውን ለማድረግ በትጋት እየሰራን ነው። ህዝባችንና ሀገራችን ብርታትና ስራ ይፈልጋል'' ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

02/06/2026

ማየት ማመን ነው - መጥታችሁ እዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 02/06/2026

‎ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ስራ አስጀምረናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

02/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

28/05/2026

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያን የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ

አዲስ አበባ — የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፥ ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ አንዱ መሆኑ ታውቋል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ፣ አስፈላጊ ግብዓቶችን በማከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

የረቂቅ አዋጁ ዋና ዋና ዓላማዎች፡

የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጁ በዋናነት የሀገሪቱን የልማትና የአካባቢ ጥበቃ ግቦች ለማሳካት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፥ የሚከተሉትን ቁልፍ ነጥቦች ያጠቃልላል፡

የስትራቴጂ ትግበራና አረንጓዴ ኢንቨስትመንት፡ የኢትዮጵያን የካርበን ገበያ ስትራቴጂ ወደ ተግባር ለመለወጥ እና ለአረንጓዴ ኢንቨስትመንት እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ምቹ ሁኔታን መፍጠር፤

ግልጽ አሰራር፡ የካርበን ግብይት አሰራሮችን እና ሂደቶችን በግልፅ መደንገግ፤

የማኅበረሰብና አካባቢ ጥበቃ፡

በካርቦን ፕሮጀክቶች ሳቢያ በአካባቢው ማህበረሰብና ስነ-ምህዳር ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስ መከላከያ አሰራሮችን መዘርጋት፤

ፍትሐዊ የገቢ ክፍፍል፡ ከካርበን ንግድ የሚገኘው ገቢ በመንግስት፣ በአልሚዎች፣ በአካባቢው ማህበረሰብ እና በባለድርሻ አካላት መካከል በፍትሃዊነት የሚከፋፈልበትን ስርዓት መዘርጋት፤

ዓለም አቀፍ ግዴታዎችን መወጣት፡

ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ውሎችና የገባቻቸውን የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ቅነሳ ቃል ኪዳኖች ከሌሎች አጋሮች ጋር በትብብር እንድትወጣ የህግ ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል ማድረግ።

ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታይቶ እንደሚጸድቅና ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል።

27/05/2026

የቦረና ብሔራዊ ፓርክ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Addis Ababa