13/05/2026
ዓለም አቀፍ የሚድዋይፎች ቀንን በማስመልከት ለወላድ እናቶች ስጦታ ተበረከተላቸው
አዲስ አበባ - ግንቦት 5 - 2018 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)
ዘንድሮው በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ36'ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የሚድዋይፎች ቀን በማስመልከት በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ውስጥ በዕለቱ ለወለዱ እናቶች የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክቶላቸዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም እሸቱ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የእናቶች ጤና ቡድን መሪ አቶ ዳንኤል ናደው ፣ የኢትዮጵያ ሚድዋይፍ ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሜሮን ተሰማ እና ባለሙያዎች ስጦታውን ለወላድ እናቶች አበርክተዋል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
13/05/2026
የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሚድዋይፍሪ ባለሙያዎች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጠ
አዲስ አበባ - ግንቦት 5 - 2018 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)
የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የሚድዋይፎች ቀን አስመልክቶ በሆስፒታሉ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሚድዋይፍሪ ባለሙያዎች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
እውቅና የተሰጣቸው የሚድዋይፍሪ ባለሙያዎች ፦
🔹ከድህረ ወሊድ ክፍል
➪ በፍቃድ አሰፋ
🔹ከማህፀንና ፅንስ ድንገተኛ ክፍል
➪ አጃዒባት መሐመድ
🔹ከክሊኒካል ሚድዋይፍሪ
➪ ሲሳይ ደሳለኝ
🔹ከማዋለጃ ክፍል
➪ ምስጋናው ታረቀኝ
🔹ከማህፀንና ፅንስ ተኝቶ ህክምና
➪ ሽባባው አብጤ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
13/05/2026
ዓለም አቀፍ የሚድዋይፎች ቀን በሆስፒታሉ ውስጥ በድምቀት ተከበረ
አዲስ አበባ - ግንቦት 5 - 2018 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)
"ዓለማችን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ ሚድዋይፎችን ትፈልጋለች!" በሚል መሪ ቃል ፤ 36'ተኛው ዓለም አቀፍ የሚድዋይፎች ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ውስጥ በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
መርሃ-ግብሩ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከኢትዮጲያ ሚድዋይፎች ማህበር ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ ተገልጿል።።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም እሸቱ ሃገራችን ኢትዮጵያ የእናቶችና የጨቅላ ሕፃናት ጤና እንዲሻሻል በትኩረት በመስራቷ የሞት ምጣኔን ከቀነሱ ቀዳሚ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆን ችላለች ብለዋል።
አክለውም የሚድዋይፍሪ ባለሙያዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሳይታክቱ በመስራት በዘርፉ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ላደረጉት የላቀ አስተዋፅኦ ክብርና ምስጋና እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
በቀጣይም በዘርፉ እየተመዘገቡ ያሉ አበረታች ውጤቶችን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል የባለሙያዎችና የአመራሩ ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የሆስፒታሉ ሚድዋይፍሪ ባለሙያዎች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
13/05/2026
He is cured! 🎉
https://bit.ly/4oGnjxl
This case was unique for us not only because it was our published case, but because of the strength and commitment he left on our treating team.
As clinicians, some patients leave a lasting mark on our hearts and minds. This young patient went through ups and downs that no teenager should ever have to face. But in the end, he beat it a truly rare case.
✍️ ID department
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
13/05/2026
ማስታወቂያ
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከዚህ ቀደም ባወጣው የዝውውር ቅጥር ማስታወቂያ አመልካቾች በሊንክ እንዲመዘገቡ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ሆኖም የተከፈተው ሊንክ በመሙላቱ መመዝገብ ያልቻላችሁ አመልካቾች ከዚህ በታች በተገለጸው አዲስ ሊንክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Link 👇
https://forms.gle/kdTaKyCtSTQGNmEBA
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
12/05/2026
Happy international Nurses Day!
"Our Nurses. Our Future. Empowered Nurses Save Lives."
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
11/05/2026
ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ሆስፒታላችን የግል ህክምና አገልግሎት በይፋ መስጠት የሚጀምርበት ቀን ነው።
የግል ህክምና የምትፈልጉ ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ እናበስራለን።
አድራሻ ፦ አዲስ አበባ - ጉለሌ ክፍለ ከተማ - ወረዳ 1 - ከሽሮሜዳ ወደ እንጦጦ በሚወስደው መንገድ ላይ ያገኙናል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
10/05/2026
መልካም የእናቶች ቀን
HAPPY Mother's DAY
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
09/05/2026
ሆስፒታላችን ከግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የግል ህክምና አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
በግል ህክምና የሚሰጡ አገልግሎቶች ፦
🔹የቀዶ ህክምና አገልግሎት በስፔሻሊሰት እና ሰብ-ስፔሻሊሰት ሃኪሞች
🔹የአጥንት ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የጭንቅላት እና ህብረ-ሰረሰር ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የደም ስር (ቫስኩላር) ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የህፃናት ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የፕላስቲክ እና ሪኮንስትራክቲቭ ህክምና አገልግሎት
🔹የውስጥ ደዌ ህክምና አገልግሎት
🔹የልብ ህክምና (ካትላብ)አገልግሎት
🔹የማህፀን እና ፅንስ ክትትል ህክምና አገልግሎት
🔹የስነ-ልቦና እና ማማከር ህክምና አገልግሎት
🔹የጥርስ ህክምና አገልግሎት
🔹ከአንገት በላይ ህክምና አገልግሎት
🔹የቆዳ ህክምና አገልግሎት
🔹የፊዚዮቴራፒ ህክምና አገልግሎት
🔹የራጅ (X-ray) ፣ የአልትራሳውንድ ፣ የሲቲ ስካን (CT-scan) ፣ የኤም.አር.አይ (MRI) ፣ የፓቶሎጂ እና የተለያዩ የላብራቶሪ ምርመራዎች አገልግሎት
የግል ህክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቀናት ፦
🔹ከሰኞ እስከ ሐሙስ
➪ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ
🔹ዓርብ
➪ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ
🔹ቅዳሜ ፣ እሁድና የበዓል ቀናት
➪ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ
የግል ህክምና የምትፈልጉ ሁሉ በተጠቀሱት ቀናት እንዲሁም ሰዓታት ውስጥ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አድራሻ ፦ አዲስ አበባ - ጉለሌ ክፍለ ከተማ - ወረዳ 1 - ከሽሮሜዳ ወደ እንጦጦ በሚወስደው መንገድ ላይ ያገኙናል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
08/05/2026
ማስታወቂያ
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የግል ህክምና አገልግሎት በይፋ መስጠት ይጀምራል።
የግል ህክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቀናት ፦
🔹ከሰኞ እስከ ሐሙስ
➪ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ
🔹ዓርብ
➪ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ
🔹ቅዳሜ ፣ እሁድና የበዓል ቀናት
➪ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ
የግል ህክምና የምትፈልጉ ሁሉ በተጠቀሱት ቀናት እንዲሁም ሰዓታት ውስጥ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን።
አድራሻ ፦ አዲስ አበባ - ጉለሌ ክፍለ ከተማ - ወረዳ 1 - ከሽሮሜዳ ወደ እንጦጦ በሚወስደው መንገድ ላይ ያገኙናል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"
08/05/2026
የዝውውር ማስታወቂያ
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሥራ መደቦች ላይ አመልካች ሠራተኞችን ከአቻ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በዝውውር ተቀብሎ በማወዳደር መድቦ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በተዘረዘሩት የሥራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቶች ከስር በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማስፈንጠሪያ 👇
https://forms.gle/nBmR2r9iemwbbULD7
ማሳሰቢያ ፦
🔹አመልካቾች ስርዝ ድልዝ የሌለበት የትምህርት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
🔹የሙያ ምዝገባ ማረጋገጫ መቅረብ አለበት፡፡
🔹የማመልከቻ ማቅረቢያ ቀናት ፡- ከ1/9 /2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 7/9/2018 ዓ.ም.
🔹ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
🔹የፈተና ቀን በተቋሙ ዌብሳይት ላይ ይገለፃል፡፡
🔹ለፈተና ስትቀርቡ ኦሪጂናል የትምህርት ማስረጃ ይዛችሁ መቅረብ አለባችሁ፡፡
🔹የዝውውር ስምምነት ከምትሰሩበት ተቋም ማቅረብ አለባችሁ፡፡
🔹ፈተናውን ካለፉ ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አድራሻ ፦
አዲስ አበባ - ጉለሌ ክፍለ ከተማ - ወረዳ 1 - ከሽሮሜዳ ወደ እንጦጦ በሚወስደው መንገድ ላይ ያገኙናል።
ለተጨማሪ መረጃ ፦ 011-15-41-746 ላይ ይደውሉ!
✍️ ሆስፒታሉ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"