በት/ቤታችን በሚኖር የመምህራን ስልጠና ምክንያት የዛሬ መጋቢት 26 ፣ 2016 ዓ.ም ሳምንታዊ መርሐ-ግብር እንደማይኖር ለማስታወቅ እንወዳለን።
አፍሪ ክለብ 2016 - Afri Club 2024
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አፍሪ ክለብ 2016 - Afri Club 2024, Social service, Addis Ababa.
29/03/2024
5ኛው የአፍሪ ሰብ ሳምንታዊ መሰናዶ ተካሄደ!
ሐሙስ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም 5ኛው አፍሪ ክለብ 2016 ሳምንታዊ መሰናዶ ሲከናወን ለአፍሪ ክለብ 2016 ተማሪ አባላት የሙያ ተሞክሮውን ያቀረበው የቀድሞ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የነበረው እና በተለይ በተወዳጁ የወንዶች ጉዳይ ፊልም ላይ ጠጆ በሚለው የትወና ስሙ የምናውቀው መስፍን ኃይለእየሱስ ነው። መስፍኔ ከ50 ያላነሱ ፊልሞች ላይ በትወና ተጫውቷል። ሁለት ፊልሞችንም ፅፏል። በተለያዩ ፊልሞች ላይም በአዘጋጅነት እና በረዳት አዘጋጅነት ሰርቷል። "ምን ልታዘዝ" የተሰኘው የቴሌቪዥን ድራማ እምቅ ችሎታውን ካወጣባቸው ስራዎቹ የሚጠቀስ ነው።
መስፍኔ የአፍሪካ አንድነት ት/ቤት ትውስታውን ፣ የፊልምና የቴሌቪዥን ድራማ ተሞክሮውን በማካፈል ከተማሪዎች ጋር ውይይት አድርጓል ጥያቄዎችንም መልሷል። ፈገግታን በተላበሰ አቀራረቡ ተማሪዎችን ዘና አድርጓቸዋል። የመጀመሪያው ፊልሙ ገፀ-ባሕርይ ስም 'ጠጆ' ቢያሰኘውም በግሉ ግን ጠጅ እንደማይወድ እያስፈገገ አጫውቶናል።
በዚህ አጋጣሚ አሁን ያሉትን ተማሪዎች እንደየተሰጧቸው ምንም ነገር በሌለበት እየደገፈ ያለውን ለኪነጥበብ ቅርብና ፣ ትጉህ ሰው መምህር አየሁ ሞላ ልናበረታታው እና ልናመሰግነው እንወዳለን። መስፍኔም ጥሪያችንን አክብረህ ከተማሪዎቹ ጋር ቆይታ ለማድረግ ስለተገኘህ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
6ኛው ሳምንት መርሐ-ግብር ሐሙስ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:45 እስከ 11:00 ሰዓት በት/ቤቱ አዳራሽ ይካሄዳል።
የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ በመርሐ-ግብሩ ላይ እንድትታደሙ ተጋብዛችኋል።
23/03/2024
4ኛው የአፍሪ ሰብ ሳምንታዊ መሰናዶ ተካሄደ !
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት በማዕረግ ተመራቂ እና የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ በአሁኑ ሰዓት በዚያው ት/ቤት በመምህርነት እያገለገለ የሚገኘው ፤ እንደ ረመጥ ፣ ዋዜማ እና ለሌሎች አያሌ ፊልሞች በሰራቸው የማጀብያ ሙዚቃዎች የ2015 ዓ.ም የጉማ የፊልም ሽልማት በዘርፉ ተሸላሚ ፤ ተመሳሳይ ሽልማቶችንም በአሜሪካን እና እንግሊዝ ሃገር በተደረጉ ውድድሮች ያሸነፈው ፤ ብዙዎቻችን በፋና ላምሮት የድምፃዊያን ውድድር ዳኝነት የምናውቀው የሙዚቃ ባለሙያው ብሩክ አሰፋ ከአፍሪ ክለብ 2016 ተማሪ አባለት ጋር ሐሙስ መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከ10:00 እስከ 11:00 ሰዓት የሙያ ተሞክሮውን በማቅረብ ጣፋጭ ቆይታ አድርገናል።
በመርሐ-ግብሩ ማገባደጃም ለተማሪዎቹ የአንድ ቀን የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ጉብኝት እንዲያደርጉ ቃል ተገብቶላቸዋል።
በዕለቱ ከቀድሞ ተማሪዎች መኻከል ሰምሐል አድሀኖሞ እና አርቲስት ዓለምፀሐይ አረጋዊም ተገኝተዋል።
5ኛው ሳምንት መርሐ-ግብር ሐሙስ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከ9:45 እስከ 11:00 ሰዓት በት/ቤቱ አዳራሽ ይካሄዳል። የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ በወንዶች ጉዳይ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ፊልሞች ላይ በተዋናይነት የምናውቀው የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ተማሪ አርቲስት መስፍን ሀይለየሱስ ነው።
የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ በመርሐ-ግብሩ እንድትታደሙ ተጋብዛችኋል።
18/03/2024
3ኛው የአፍሪ ክለብ 2016 ሳምንታዊ የአፍሪ ሰብ መሰናዶ ሐሙስ መጋቢት 5 ቀን ፣ 2016 ዓ.ም በአፍሪካ አንድነት ቁ1 ት/ቤት አዳራሽ ተካሂዷል። በዕለቱ 'ትመጭ እንደሁ' ፣ 'ቁልፉን ስጪኝ' ፣ 'ተከፍሏል' ፣ 'አሜን' ፣ 'አስርቱ ቀናት' እና 'ጊዜ ለኩሉ' የተሰኙትን ጨምሮ ከሰላሳ በላይ ፊልሞችን በደራሲነት / Writer ፣ በአዘጋጅነት/Director እና በ'ፕሮዲውሰር'ነት ያበረከተልን ውዱ የትምህርት ቤታችን ፈርጥ ሳሙዔል ካሳሁን የቀድሞ የት/ቤት ትዝታውን ፣ የዛሬ የሙያና ማህበራዊ ሕይወት ተሞክሮውን ለተማሪዎች ፣ መምህራን እና ተጋባዥ እንግዶች አካፍሏል። ለቀረቡላትም ጥያቄዎች ምላሹን ሰጥቷል።
በወር አንዴ ለተማሪዎቹ በገባነው ቃል መሰረት 4ኛው መሰናዶ የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 12 ቀን ፣ 2016 ዓ.ም ከትምህርት ቤቱ ውጭ በምንጋብዛቸው አንቱ የተባሉ ባለሙያዎች ይከናወናል።
ተሞክሯችሁን ማካፈል የምትፈልጉ የቀድሞ ተማሪዎች ኘሮግራም ቀድማችሁ አስይዙን። መጥታችሁ የዝግጅቱ አካል በመሆን እንድሳተፉም የምትወዱት ትምህርት ቤታችሁ ይጋብዛችኋል።
08/03/2024
ጥቂት ስለ ደራሲ ፣ ገጣሚ እና ጋዜጠኛ የምወድሽ በቀለ
በአፍሪካ አንድነት ቁ.1 የህዝብ ት/ቤት ከ1ኛ እስከ ከ6ኛ ክፍል የተማረች
ሙያ:
ደራሲ ፣ ገጣሚ እና ጋዜጠኛ
ያገለገለችባቸው መስሪያ ቤቶች:
በፖሊስ እና ርምጃው ጋዜጣ ከዘጋቢነት እስከ ዋና አዘጋጅነት
አሃዱ ራድዮ እና ቴሌቪዥን
አሻም ቴሌቪዥን
ህትመቶች
የባከነ ጊዜ እና ዋቢኖስ የተሰኙትን ጨምሮ 3 የግጥም መድብሎች
ፍቅር የጠማቸው ሰዎች እና የጀርባ ሃቆች የተሰኙትን ጨምሮ 6 ለብቻ የታተሙ የአጫጭር እና ረዥም ልብወለድ ስብስቦች
ነገን በተስፋ እጠብቃለሁ ፣ አዙሪት ፣ ያልተናበቡ ልቦች ፣ የዋርካ ስር ጉባዔ እና እጣ የተሰኙትን ጨምሮ 10 ከሌሎች ደራስያን ጋር በጋራ የታተሙ የአጫጭር ልብወለድ ስብስቦች
እውነታዎች
በፖሊስ እና ርምጃው ጋዜጣ ከደራሲ ማሞ ውድነህ በመቀጠል ብቸኛ የፖሊስ አባል ያልሆነች ዋና አዘጋጅ
የሴት ደራስያን ማህበርን በፕሬዘዳንትነት ያገለገለች
ሴቶች ይችላሉ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መስራች
የባከነ ጊዜ የተሰኘው የግጥም መድብል ጀማል ሱለይማን እና የዝና ሙሉ በጋራ ካሳተሙት በመቀጠል ለብቻ የታተመ የመጀመሪያው ሙሉ የግጥም መድብል ነው።
በአማርኛ ተጽፎ ወደ እንግሊዝኛ እና ኦሮምኛ የተተረጎመ መጽሃፍ ባለቤት
ነች ውዷ የህዝብ ልጅ የአፍሪካ አንድነት ቁ.1 የህዝብ ት/ቤት ትሩፋት የሆነችው እማዋይሽ በቀለ።
08/03/2024
2ኛው የአፍሪ ክለብ 2016 ሳምንታዊ የአፍሪ ሰብ መሰናዶ ሐሙስ የካቲት 28 2016 ዓ.ም በአፍሪካ አንድነት ቁ1 ት/ቤት ቤተ-መፃህፍት ተካሄደ። በዕለቱ ደራሲና ጋዜጠኛ የምወድሽ በቀለ የቀድሞ የት/ቤት ትዝታዋን ፣ የዛሬ የሙያና ማህበራዊ ሕይወት ተሞክሮዋን አካፍላለች። ለቀረቡላትም ጥያቄዎች ምላሿን ሰጥታለች።
3ኛው መሰናዶ መጋቢት 5 ቀን 2016 ይቀጥላል።
ተሞክሯችሁን ማካፈል የምትፈልጉ የቀድሞ ተማሪዎች ኘሮግራም ቀድማችሁ አሲዙን።
02/03/2024
ሰላም ውድ የአፍሪ ክለብ 2016 አባላት
ያለፈው ሐሙስ የካቲት 21 ፣ 2016 ዓ.ም 'አፍሪ ሰብ' ብለን የሰየምነውን እና ሳምንታዊውን ቀድሞ በት/ቤቱ የተማሩ ስኬታማ የትምህርት ፣ የንግድ ፣ የሚድያ ፣ የኪነ-ጥበብ እና ሌሎችንም ሰዎችን ጋብዘን ልምዳቸውን እና የህይወት ተሞክሯቸውን አሁን በት/ቤቱ ለሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች የሚያካፍሉበትን የመጀመርያ መርሐ-ግብር በስኬት አከናውነናል።
ክበቡ የዚህ ሳምንት ተጋባዥ እንግዶች የነበራችሁትን
1. መ/ር ጌታቸው እሸቱ
2. ፋሪስ ሁሴን
3. ሚልዮን ታደሰ
4. ካሳሁን ፍሰሐ (ማንዴላ) እና
5. ኢንጅነር ተዘራ ፍቅሩ
ለተማሪዎች ልምዳችሁን እና የህይወት ተሞክሯችሁን በማካፈል እንዲሁም ቀጣዩን ትውልድ ለማነቃቃት ፣ ህልም ፣ ትልም እና ፍላጎታቸውን ጠንቀቀው እንዲያውቁ በጎ ተጽዕኖ በማሳደር ላደረጋችሁት አይተኬ ተሳትፎ ክለብ አፍሪ 2016 እጅግ አድርጎ ያመሰግናችኋል።
ይህንን አላማ ጊዜአችሁን በመሰዋት ፣ በሃሳብ ፣ በቁሳቁስ ፣ በገንዘብ እንዲሁም በሙያ መደገፍ ከሁላችንም ይጠበቃል እና በምትችሉት ሁሉ ከጎናችሁ አለን በሉን።
በመጨረሻ የፊታችን ሐሙስ የካቲት 28 ፣ 2016 10:00 ሰዓት ላይ ሳምንታዊው 'አፍሪ ሰብ' በት/ቤታችን ሴት ፈርጦች ደምቆ ይከናወናል። በዚህ አጋጣሚ ሁላችሁንም ተገኝታችሁ እንድትታደሙ እና እንድትደግፉ አፍሪ ክለብ 2016 በአክብሮት ይጋብዛችኋል።
ለትውልድ እድገት በህብረት እንትጋ
የአፍሪ ክለብ 2016 አደራጅ እና ጊዜአዊ አስተባባሪ ኮሚቴ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
